ልጥፎች

የአቶ ለማ መገርሳ ለህዝባቸው ሥነ - ልቦና ያላቸው ጥንቃቄ ሲሰፈር ሲከነዳ?

ምስል
 እንኳን ደህና መጣችሁልኝ  ምርመራ። ክፍል አምስት። „እግዚአብሄር ፍርድን በማድረግ የታወቀ ነው።“ መዝሙር ፱ ቁጥር፲፮ የሥነ - ልቦና ጉዳቱ                     ከቶ መለኪያ            ይኖረዋልን? ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 02.04.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። ·        በ ሥነ ልቦና ጉዳት እና ጥገና … „ከእስር ቤት የተፈታው ሰው ብዛት ሶስት ሺህም ይሁን አስር ሺህ፣ ዋናው ቁምነገር እሱ አይደለም፡፡ እስር ቤት ያለን ኦሮሞ ከእስር ቤት ማውጣት ማለት፣ ውጭ ያለን ኦሮሞ ከእስር መፍታት ማለት ነው፤ ወኔ እንዲያገኝ፣ ሞራል እንዲያገኝ ማስቻል ማለት ነው፡፡“ ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ። መረጃ ሳይኖረን የማንንም ስም አላጠፋንም፦ ትርጉም በአብርሃም ዓለሙ ( ዶ / ር ) April 1, 2019 |  Filed under:  ነፃ አስተያየቶች  |  Posted by:  ዘ - ሐበሻ https://www.zehabesha.com/amharic/archives/94532#respond የሥነ - ልቦና ጉዳይ እጅግ በተመሰጠ ሁኔታ ገልጸውታል። ከመሰከረም ጀምሮ የአዲስ አበባ ህዝብ ልቡ ተንጠልጥላ ጭንቅ ላይ መኖሩስ በምን ሚዛን ሊታይ ይሆን? ነፍሰ ጡር እናት ምጥ ውስጥ ሆና ነው ዛሬ አዲስ አባባ ላይ እያማጠች በዬሰከንዱ የምትኖረው ዘጠኝ ሙሉ ወሩን ስለሆኑስ?   ዜጋው የመኖር ዋስትና የለውም። የመኖር ዋስትና ከሌላ ደግሞ ማሰብ፤ መመራመር አይቻልም። ስሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሥነ - ልቦና ጉዳትስ ማነው ተጠያቂው? የአዲስ አባባ ህዝብ ነጋ ጠባ በሽብር የሚናጥበትን በሚመለከት

የፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ትምህክት ተረገጥ! /ክፍል አራት/

ምስል
 እንኳን ደህና መጣችሁልኝ  ምርመራ። ክፍል አራት። „እግዚአብሄር ፍርድን በማድረግ የታወቀ ነው።“ መዝሙር ፱ ቁጥር፲፮ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 02.04.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። እንዴት ናችሁ ከንጹሁ ልቤ የማከብራችሁ ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬም በባጀው በፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ንግግር ላይ ቆይታ ማድረግን ፈለግሁኝ። አብዛኞቻችን አንዱን ይዘን ሌላውን እዬጣልን ከጎረፈው ጋር ጎርፈን፤ ከወጀበው ጋር ወጅበን፤ ከነፈሰው ጋር ነፍስን አቅማችን አባክነናልን፤ ይቅርታውም ምኑም አሁን ላይ ሳዬው በውስጥነት የሰከነበት ተፈጥሮ እንደሌለ ነው እኔ የሚገባኝ። የልብን እያደረሱ ይቅርታ ማባጨል ይለዋል ጎንደሬው ... ባተደሞው የዕድምታ ባለሟል።  ስለሆነም አላምጠን እንውጥ ዘንድ እያንዳንዱን ሂደት ሰብን በማመን ብቻ መተው ተፈላጊ አለመሆኑ ልብ ልንለው ይገባል። የሰሞናቱ የዛ መከረኛ የጋዜጠኛ አስክድር ከመጋቢት ልደታ ጀምሮ ያለው ጫና እና ወጀብ ሁሉ ሳስበው፤ ሳስተውለው በዝግታ እንራመድ ዘንድ መልክት ልኮልኛል። መፎካከር በማይገባው ጊዜና ሁኔታ ሲሆን እጅግ ይከረፋል። የሚሊዮን ግርማ ሞገስ ተሸከመህ ይህን ያህል ከብዕር ገበሬ ጋር እሰጣ እገባ ሁለመናውን ለመዝጋት መታታተር ስልጣን አለኝ ብለህ በፍጹም በምንም መስፈርት ከዚህ ተፈረጅ የሚባል አይደለም።  ሁሉ ነገር አይጠቅምም ሁሉነገር አይጎዳም። ጎጂና ጠቃሚውን ለመለዬት ደግሞ ከሥር እዬጀመሩ ጉዳዮችን በምልሰት አጥሞ ማጥናት ይጠይቃል ። ቀጣዩ ትውልድ ፍዳን ተሸካሚ እንዳይሆን የመንፈስ ውላችን እውነትን ወግኖ ከመቆም ጋር መሆን እንዳለበት በጽኑ አምናለሁኝ።  ዘመን ተቀበልን ዘመንን ስንሸኝ እንደ ጥንቸል መንፈሳችን፤ ሥነ - ልቦናች መሞከ