የፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ትምህክት ተረገጥ! /ክፍል አራት/

እንኳን ደህና መጣችሁልኝ
ምርመራ።
ክፍል አራት።
„እግዚአብሄር ፍርድን በማድረግ የታወቀ ነው።“
መዝሙር ፱ ቁጥር፲፮

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02.04.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።

እንዴት ናችሁ ከንጹሁ ልቤ የማከብራችሁ ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬም በባጀው በፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ንግግር ላይ ቆይታ ማድረግን ፈለግሁኝ። አብዛኞቻችን አንዱን ይዘን ሌላውን እዬጣልን ከጎረፈው ጋር ጎርፈን፤ ከወጀበው ጋር ወጅበን፤ ከነፈሰው ጋር ነፍስን አቅማችን አባክነናልን፤ ይቅርታውም ምኑም አሁን ላይ ሳዬው በውስጥነት የሰከነበት ተፈጥሮ እንደሌለ ነው እኔ የሚገባኝ። የልብን እያደረሱ ይቅርታ ማባጨል ይለዋል ጎንደሬው ... ባተደሞው የዕድምታ ባለሟል። 

ስለሆነም አላምጠን እንውጥ ዘንድ እያንዳንዱን ሂደት ሰብን በማመን ብቻ መተው ተፈላጊ አለመሆኑ ልብ ልንለው ይገባል። የሰሞናቱ የዛ መከረኛ የጋዜጠኛ አስክድር ከመጋቢት ልደታ ጀምሮ ያለው ጫና እና ወጀብ ሁሉ ሳስበው፤ ሳስተውለው በዝግታ እንራመድ ዘንድ መልክት ልኮልኛል። መፎካከር በማይገባው ጊዜና ሁኔታ ሲሆን እጅግ ይከረፋል። የሚሊዮን ግርማ ሞገስ ተሸከመህ ይህን ያህል ከብዕር ገበሬ ጋር እሰጣ እገባ ሁለመናውን ለመዝጋት መታታተር ስልጣን አለኝ ብለህ በፍጹም በምንም መስፈርት ከዚህ ተፈረጅ የሚባል አይደለም። 

ሁሉ ነገር አይጠቅምም ሁሉነገር አይጎዳም። ጎጂና ጠቃሚውን ለመለዬት ደግሞ ከሥር እዬጀመሩ ጉዳዮችን በምልሰት አጥሞ ማጥናት ይጠይቃል። ቀጣዩ ትውልድ ፍዳን ተሸካሚ እንዳይሆን የመንፈስ ውላችን እውነትን ወግኖ ከመቆም ጋር መሆን እንዳለበት በጽኑ አምናለሁኝ። 

ዘመን ተቀበልን ዘመንን ስንሸኝ እንደ ጥንቸል መንፈሳችን፤ ሥነ - ልቦናች መሞከሪያ ሆኖ የደከመው ሲሸኝ ሌላ ባለ አቅም ደግሞ እስኪበቃው የሚለነቅጠንን ስንፈቅድ ቅንነት ተሞርኩዘን ቢሆንም መታመናችን ፋይዳ ቢስ ከሆነ አደብ ገዝቶ፤ አስተውሎ አቅምን በቅጡ ማስተዳደር የሚገባ ይመስለኛል። እንደ ኩታራ በዬጊዜው አረቂ ከረሚላችን ለቀመጥ እያደረገን ውሃ ወቀጣው መቆም አለበት ብዬ አስባለሁኝ። 

ረጅም ዓላማ እና ትልም ላላው መንፈስ ቀበቶ ማስፈታት ዋነኛ ስትራቴጅ እና ትልሙ ነው። ሙቀቱ ቀዝቀዝ አድርጎ ሌላውን ይከውናል። ለዚህ ነው ከሰሞናቱ የ አዲስ አባባ ካድሬዎች በ አዲስ ኦሮማማ ስልጠና ስብሰባ የተጠራው? እስከዛሬ የት ነበሩ? 

አሁን ወደ ተነሳሁበት ጭብጥ ... በዘንካታ ትህትና አብረን ብያለሁኝ ... 
  • ·         መነሻ ምንጭ።

መረጃ ሳይኖረን የማንንም ስም አላጠፋንም፦ ትርጉም በአብርሃም ዓለሙ (/)

Filed under: ነፃ አስተያየቶች | -ሐበሻ


ይህ ከፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ የተወሰደ ነው....

„….ሌላው የፖለቲካ ጥያቄ ሊመለስ የሚችለው መጀመሪያ ህዝቡ እንደ ሰው ተፈጥሯዊና ሰብአዊ መብቱ ተጠብቆ መኖር ሲችል ነው፡፡ በሰንሰለትና ገመድ ታስሮ እያለ ሌሎች ጥያቄዎች ሊመለሱለት አይችልም፤ ሊመለሱለት አይችሉም ብቻ ሳይሆን ሊጠይቅም አይችልም፡፡ ከእስር እራስን መፍታት፣ ከእስር ሰዎችን መፍታት ተቀዳሚው ተግባር ነው፡፡ ይህም የህዝባችንና የሁላችን ጥያቄ ነው የነበረው፡፡ በዚህም ምክንያት ዛሬ ከኦሮሚያ ጀምሮ እስከ ፌደራል ባሉ እስር ቤቶች ኦሮሞ በቻ ሳይሆን ሌሎችንም ሞት እንኳን የተፈረደባቸውን ሳይቀር ከሞት አተረፍናቸው፡፡ ሰዎችን ከሞት ለማትረፍ፣ ነፍስ የእግዝአብሄር ናት፤ እግዝአብሄር እኛን ተጠቅሞ ሰዎችን ከሞት አትርፎ ይሆናል ለማለት ነው እንጂ፣ እኛ ሰዎችን አተረፍን ማለት አንችልም፡፡ ይሁን እንጂ ከሞት እንኳን ብዙ ሰዎችን ማትረፍ ተችሏል፡፡"

በባጀው በፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ንግግር ላይ ቆይታ ማድረግ እጅግ ወሳኝ ነው። የ100 ሚሊዮን ህዝብ ዕጣ ፈንታ ነውና። የ100 ሚሊዮን ዕጣ ፈንታ ባህሉ፤ ወጉ፤ ልማዱ፤ ቋንቋው ዕምነቱ ሁሉ በዚህ የመስፋፋት የመጫን፤ የመዋጥ አያያዝ እጅግ አደገኛ ሁኔታ ሊያስከትል የሚችል ውጥን ስለሆነ ከልብ ሆኖ፤ ከራስ ጋር ሆኖ ራሰን ላለማጥፍት መፈቀድን በልኩ ማድረግ ይገባል። 

እኛ አዳኝ ነን ነው የሚሉት ፕሬዚዳንቱ። ራሳቸውን በቤንዚን አንድደው ያቀጠሉት እነ ሰማዕት የኔሰው ገብሬ፤ ያቺ ቀንበጥ ሰማዕት ሺብሬ ደሳለኝ፤ ስንቱ ይጠቀስ? አካሉ የጎደለ፤ የዘር ፍሬው የተነቀለ፤ ጥፍሩ ከ አካሉ የተነጠለ፤ አፍር የገባው ሁሉ ምንም ነው በሳቸው ገለጻ። ያ መስዋዕትነት እነሱ ከነበሩበት ካቴና ማስለቀቁ ተዘንግቷል። በዚህ አይዲኦሎጂ ነው እነዛ አገር ያፈራቸው ሊቀናት ወገኖች በተሰበሰቡት ይህ የሚነገረው። 

ይህን ነው የሚያስጠኗው ለልጆቻቸው ለዚህም ነው ጣሪያ በነካ ሥነ - ልቦና ባልተመጣጠነ የራስ መተማምን መታበይ አገር በስጋት እዬታረሰች ያለችው። „ገድሎ መስቀል ሲያንስ ነው? ገድሎ ማቃጠልም ሲያንስ ነው ምን እዬተባለ እዬተነገረ እንደሆን እያስተዋልን ነው። በአማራኛ ቋንቋ የሚነገረው ሌላ ነው በ ኦሮምኛ ሌላ ነው ... የ አንቀጽ 17 የውጫሌ ውል ነገር ነው የሆነው።  

በዚህ ንግራቸው ላይ እኔ ያስተዋልኩት እነሱ ብቻ ታግለው ለውጡን እንዳመጡት እንጂ ሌላው ያደረገው መስዋትነት፤ ሰማዕትነት ልሙጥ ነው በሳቸው አገላለጽ። ቀድመን ጀምረናል የሚለው ፈሊጥም የመጣው ከዚህ አንጻር ነው።

„ትግሉ ውሎ አድሯል፤ ቆይቷል፡ መጀመሪያ የኦሮሞ ደም መፍሰስ የጀመረ እለት ነው ትግላችን የጀመረው እንጂ፣ በቀደም እለት እዚህ አዳራሽ ውስጥ በአስራሰባቱ ቀናት አንዳችን የሌላችንን ራስ ያሳመምን ጊዜ የተጀመረ አይደለም፡፡ ማን ነው ወንበር አመቻችቶ ኑና ውሰዱ ያለንአሳምረውልን ነው የጠበቁን ወይስ እሳት ለኩሰውበት ነው የሰጡን?“

እሳቸው ሰብሰበው የሚመሩትን ህዝብ ሲያነጋግሩ ማሰተማር ይገባቸው የነበረው መሰረታዊ ነገር የኢትዮጵያ ህዝብ ያደረገውን ሁለገብ ቀደምት ተጋድሎ፤ የከፈለውን መስዋዕትነት አብሶ የጎንደር ጎጃም የአማራ ተጋድሎ ጋር ተያይዞ የጠፋው ነፍስ፤ ከ20ሺህ በላይ ወጣቶች ለካቴና መዳረጋቸው እና የብአዴን ያደረገው ተጋድሎ በሚገባ ሊገለጽ ሊብራራ ይገባ ነበር። ሌላው ቢቀር ማለት ነው እንጂ ስንት ስንት ተጋድሎ ተደርጎበታል። 

የሌሎች መስዋዕትነት ጭምር የመጣ ለውጥ የትሩፋቱም ባለቤት፤ የገድሉም ባለቤት ራሳቸውን አድርገው ቁጭ ብለዋል። ያማል በጣም። እንዲያውም ለሌላውም መትረፋቸውን ነየሚነግሩን።  

"በዚህም ምክንያት ዛሬ ከኦሮሚያ ጀምሮ እስከ ፌደራል ባሉ እስር ቤቶች ኦሮሞ በቻ ሳይሆን ሌሎችንም ሞት እንኳን የተፈረደባቸውን ሳይቀር ከሞት አተረፍናቸው፡፡"

ለዚህ ነው የአማራ የህልውና ተጋድሎ ውሹን ያነሳ ውሹን አድርገው የውሽማ ሞት ሆኖ እንዲቀር ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከተመረጡበት ዕለት ጀምሮ ሲያዳፍኑት የኖሩት። ዋና ኢላማቸው ነበር የዚህ ተጋድሎ ሥረ መሰረት ከንቱ ሆኖ ከታሪክ ውጭ እንዲሆንም ምክር ተደርጎበታል ማለት ነው ይህን ገለጣ ሳዳምጠው። እነሱን ብቻ አዳኝ አድርገው ነው ያቀረቡት። ይህ ሌላው የታሪክ ሽሚያ እና ክህደትም ነው።

በውነቱ ይሄ ስስታምነትም ነው። በፍጹም ሁኔታ ራስ ወዳድነትም ነው። በዚህ ንግግር ውስጥ አንድም ቦታ … „ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው“ የለም። ለጅሎቹ ነው „ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው፡" እንደ አሞሌ ጨው የሚታደለን በወረፋ። ለማሞ ቂሎቹ። አንዲትም ቦታ የኦሮሞማራ ጥምረት ብሎ ነገር የለም። 

እነሱ ብቻቸውን ታግለው ያን አስፈሪ የማይደፈር ስርዓት እንደገረሰሱት እና በዛው ልክ ህዝባቸውን የለውጡ ተጠቃሚ ለማድርግ ጥረት ላይ እንዳሉ ነው የሚገልጸው። የታሪክ ፍርፋሪ ለዛ ገድለኛ ለአማራ የማንነት የህልውና ተጋድሎ አልተሰጠም። ለ ኢትዮጵያ ህዝብም፤ በጸሎት የተጋው፤ ሰንቅ ለማቀበል የባከነው። 

ኪዘህ አንጻር የአማራ ተጋድሎ ጥያቄውም መፍትሄ ያገኛል ብዬ አላስብም። ለዚህም ነው የትግራይ እና የአማራ ጦርነት በፆም በፀሎት እዬታሰበ ያለው። ሁለቱ ከገባቸው ይህን በጥበብ መያዝ ይኖርባቸዋል። ልብ ካላቸው። በዚህ ግብግብ አትራፊው ኦሮማማ ስለመሆኑ ልብ ሊሉትም ይገባል። „የስሜኘኞች ኢጎ“ ሌላ ፍች የለውም። 

ወደ ተጋድሎ የራስ ጥረት ብቻ አድርጎ መውሰድ ይህ እኮ ታሪክንም ማፋለስም ነው፤ ትውፊትንም በተናጠል ለራስ ኢጎ መገንባት ነው። በሌላ በኩል ይህ ተጋድሎ በቅጡ የጋራ እና የወል አለመሆኑ በአጽህኖት አለመገለጹ ነው በዬቦታው ያለው የመገፍት መከራ አና ያለው። ህዝቡ የተስተካካለ መረጃ ማግኘት አልቻለም፤ አልተሰጠውም። ይህ በምን ያህል ኪሎ ሊያስጠይቅ እንደሚችል አላውቅም። እኔ አንድም ቀን ነጥዬ ሠርቼ አላውቅም፤ እንሱ ግን የሴራ ድራቸው ጥልቀቱ እንዲህ በዋዛ የሚደረሰብት አይደለም። \/

"ይህ ደግሞ የ18ቀኑ ስብሰባ ሳይሆን እኛ ቀድመን ጀምረናል" ነው የሚሉት ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ፤ በዚህ ውስጥ የብአዴን አቅም ለመፈታተን የተገለጸ ነው፤ የድል አጥቢያ አርበኛ አትሁኑ አይነት … ለእኔ የገባኝ እንደዚህ ነው …

የሆነ ሆኖ አንድ የትግል ምዕራፍ ተጠናቋል በማባጨል ሆነ በብልጠት ፖለቲካ። ቀጣዩ ምዕራፍ ግን በብቻ ጥረት ብቻ የትም አይደረስም? ቀድሞ ነገር ም/ጠ/ሚር አቶ ደመቀ መኮነን እራሳቸውን ከእጩ ጠ/ሚር ባያገሉ ይህን ያህል መሆን ይቻል ነበር ወይም? ብሎ ለማሰብም ህሊናቸው የት ላይ እንደተቀመጠ እዮር ይጠይቃቸው። ያ ኦሮማራ ለጊዚያዊ የሥልጣን መወጣጫ ስትራቴጂ ብአዴን ባይፈቅድ ይቻል ነበርን? ለዚህ ጉባኤ ይህ ሃቅ ያልተነገረ መቼ ሊነገር ይሆን?

በሌላ በኩል መከላከያን አንስተዋል በአዲስ በማደራጃታቸው የትናንቱ  ዛሬ ላይ እንደሌለ። ይህን ደግሞ ሌላውም ህዝብ በሚገባ አስተውሎታል። መከላከያ ኢትዮጵያዊ እንዲሆን እንጂ ኦሮማይዝድ እንዲሆን አልነበረም ምኞታችን። ትናንት የህውሃት ዛሬ ደግሞ የኦዴፓ። ይህን ድላቸውን ነው ለህዝባቸው ያበሰረቱ ፕ/ ለማ መገርሳ  እንዲህ በማለትም ነው … በኩራት …

„ተመልከቱ፤ በሀገር መከላከያ ውስጥ የዛሬ ዓመት፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት እያልኳችሁ አይደለም፣ የዛሬ ዓመት የኦሮሚያ ክልል መንግስትና የሀገር መከላከያ ሲካሰሱ ነበር፤ አይደል? እኔም ፕሬዚዳንት ነበርኩ፤ ወደ መድረክ ወጥቼ ምንም ሳልፈራ፣ እኔውርጅሙሰውዬ፣እነዚህ ናቸው ህዝባችንን እየጨረሱ ያሉት፤ብዬ ተናገርኩ፡፡ ህዝባችንን እያስቸገረ ያለው፣ ህዝባችንን እጃችን ላይ እየጨረሰብን ያለው ከሩቅ የመጣ ጠላት ሳይሆን፣ ይኸው መከላከያ ሰራዊት ነው፤ እያልን አልነበር ስንከስ የነበርነው? ሌላ ማንንም አልከሰስንም እኛ፡፡ ያኔ እንዴት ነበር የምንፈላለገው? ጠመንጃዎቻችንን አቀባብለን እየተፈላለግን ነበር፡፡ እኛ እንኳን አልነበረንም፤ የነበራቸው ግን አቀባብለው እየፈለጉን ነበር፡፡“
„ዛሬስ ትልቁ ጉልበታችን ማን ነው?“ ብለው ይጠይቃሉ ፕሬዚዳንቱ …  እራሳቸው ደግሞ ይመልሱታል „ይሄ መከላከያ ሀይል ነው፡፡ ዛሬንና የዛሬን ዓመት ጎን ለጎን አስቀምጣችሁ ተመልከቱ፡፡“

ይህን ጠ/ሚር አብይ አህመድ ፕሮፌሺናል ምደባ ነው የተካሄደ ሲሉ አሰተባብለውታል።

ለዚህ ማገናዘቢያ ይሆን ዘንድ ... ከሳተናው የወሰድኩትን ሊንኩን ብቻ ከምለጥፍ ምንጩ ሳተናው እንደሆነ በአጽህኖት ገልጬ ዝርዝሩን በጥሞና ማዬት የሚገባ ይመስለኛል ... ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከሰሞናቱ ሲገልጡ ፕሮፌሽናል ምደባ ነው ያካሄድነው ሲሉ 27 ዓመት ሙሉ ለአብይ ሌጋሲ የመጠነ አንድ አማራ መኮንን ብቻ ነበር ማለት ነው? ይህም ለብአዴን ሞቱ ይመሰለኛል። ለነገሩ የመከላከያ 7ኛ ዓመት ክብረ ባዕል ላይም ባይታዋር ነበር ብአዴን ማለት ይቻላል ... 

„ብአዴን(አዴፓ) ለሌላ ዙር መከራ አሳልፎ እየሰጠን ነው፡፡አዲሶቹ ተረኞች በሁለት እግራቸው ሳይቆሙ በፊት መላ ሊባል ይገባል“
„በመከላከያ ውስጥ ብሔርን ለማመጣጠን ታስቦ በተካሄደው አዲሱ ወታደራዊ ሪፎርም የተገኙ ውጤቶቹ በአጭሩ ሲዳሰሱ።“
የመከላከያ አራቱ ዕዞች:-

1. ሰሜን ዕዝ:-

አዛዥ—- / ጌታቸው ጉዲና (ኦሮሞ)
ምክትል—- / አማረ ደብሩ (አማራ)
ሎጅስቲክ—– / ከድር አራርሳ (ኦሮሞ)
አስተዳደር—— / /እግዚአብሔር በየነ (ትግራይ)

2. ምዕራብ ዕዝ:-
አዛዥ- / አስራት ዲኔሮ (ደቡብ)
ምክትል- / አሰፋ ቸኮል (አገው)
ሎጅስቲክ—– / ወዲ ሙሉ (ቅፅል ስም ነው) (ትግራይ)
አስተዳደር—— እንዳልካቸው /ሚካኤል (ኦሮሞ)

3. ምስራቅ ዕዝ:-

አዛዥ- / ዘውዱ በላይ (አገው)
ምክትል- ተስፋዬ /ማርያም (ደቡብ)
ሎጅስቲክ—– / መሰለ ሸለሞ (ደቡብ)
አስተዳደር—— / ዱባለ (ኦሮሞ)

4. ደቡብ ዕዝ:-

አዛዥ- / ምዑዝ መኮንን (ትግራይ)
ምክትል- / ሰለሞን ኢቴፋ (ኦሮሞ)
ሎጅስቲክ—– / ኩመራ ነገሬ (ኦሮሞ)
አስተዳደር—— /ሕይወት ሱስንዮስ (ትግራይ)

ዕዝ ላይ ብሔር ማሰባጠሪያው ቀመር:-
ስድስት ኦሮሞ፣ አራት ትግራይ፣ ሦስት ደቡብ፣ ሁለት አገው እና አንድ አማራ።
በኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ታሪክ፤ በምክትል ኤታማዦር ሹምነት እና በኦፕሬሽናል ኃላፊነት ወንበር ስር ከፍተኛው ስልጣን የጠቀለሉት ሰው:-

ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ (ኦሮሞ)

በስራቸው የታቀፉት ተቋማት:-

ዘመቻ መምሪያ፣ መረጃ መምሪያ፣ መሀንዲስ መምሪያ እና መገናኛ መምሪያ።

የጄኔራል ብርሃኑ ጁላ /ቤት ኃላፊ——— ኮሎኔል ተስፋዬ (ኦሮሞ)

**************

ሌላኛው ቁልፍ ሹመት:-

የአየር ኃይል አዛዥነት- / ይልማ መርዳሳ (ኦሮሞ)

(አዛዡ ቁልቁል የሚያዟቸው መኮንኖች ሲኒየር እና በማዕረግ የሚበልጧቸው ናቸው)

****************

የሪፎርሙ ቀማሪ:-

የጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር——- / ተሾመ ታደሰ (ኦሮሞ)

****************** የመከላከያ የሰው ሃብት አስተዳደር——— / ሀጫሉ ሸለሙ (ኦሮሞ)

የመከላከያ የሎጂስቲክ መምሪያ ኃላፊ——– / ኩምሳ (ኦሮሞ)

የሪፐብሊካን ጋርድ አዛዥ——— / ብርሃኑ በቀለ (ኦሮሞ)

*******************

(ምንጭ: ፍትሕ መፅሔት አንደኛ
ዓመት ቁጥር 18 መጋቢት 2011 ..)

የአዲስ አበባ መገናኛ ብዙሃን አዲሱ መዋቅር የሹመት ዝርዝር:-
የሚኒስትሮች ሹመት – ሳይድበሰበስ! (ዮፍታሔ)
የአዲስ አበባ መገናኛ ብዙሃን አዲሱ መዋቅር የሹመት ዝርዝር:- በጥቂቱ
ይህስ ምን እንበለው ይሆን? ይሉኝታ የሚባል አልሰራላቸውም።  

1. እናትአለም መለስ ዋና ዳይሬክተር (ኦሮሞ)
2. ነጻነት አለሙ…………/ዳይሬክተር (ኦሮሞ)
3. ሳሙኤል ከበደ ……../ዳይሬክተር (ኦሮሞ)
4. ዮሚ ተመሰገን…….……../ዳይሬክተር (ኦሮሞ)
5. ካሳ /ሰንበት…….. አማካሪ (ኦሮሞ)
6. ውብሸት ወልዱ……..ልዩ ረዳት (ኦሮሞ)

ኦሮሞ ሊያስተውለው የሚገባው ነገር፣ እየተካሄደ ያለው ነገር ቀላል አይደለም፤ እየተሰራ ያለው ነገር ቀላል አይደለም፡፡“ ፕሪዚዳንት ለማ መገርሳ። ከዚህች አቋማቸው ፈቅ ይላሉ ተብሎ አይታሰብም። የብአዴን የእንቅልፍ ዘመን በዚህ መልኩ ነው እንግዲህ ከውስጡ መፈተሽ የሚኖርበት። ይቀጥላል ... 

መረጃ ሳይኖረን የማንንም ስም አላጠፋንም፦ ትርጉም በአብርሃም ዓለሙ (/)

Filed under: ነፃ አስተያየቶች | -ሐበሻ

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።