ልጥፎች

ደስ ይበልህ ጐጃም።

ምስል
        ደስ ይበልህ ጐጃም።                                           ከሥርጉተ ‚ ሥላሴ 09.06.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።                                    „ብርና ወርቅ አገር ያጸናሉ፤ ከሁለቱ ምክር በ ጐ ምክር ደስ ታሰኛለች።“                                                 (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፵ ቁጥር ፳፭)  የሁነኛ ማተብ የመሆን አብነት የልብ አድርስ ኑሮ፤ የህሊና ባዕት የቁርጥ ቀን ግማድ የመሠረት ጽናት፤ ደስ ይበልህ ጎጃም የኪዳን ጉልላት! ጐ ትንግርተኛው የሰማይ ቅስቱ የአማራ ምስባኩ የናፍቆት ስስቱ ዕውቅናው ፈለቀ በገዱ በእትብቱ። የደምመላሽ አንቱ የአድባራት ቅኝቱ፣ የበካፋ ህይወት የአድም ሰገድ ጥሪኙ የጥንት የጥዋቱ የንግሥ ቱሩፋቱ፤ ዘመኑን አጎላው በውስጥ ሽልማቱ። እስኪ ልጠይቅህ „ጣና ሆይ!“ ሚስጢርህ ምንድነው? እስኪ ልጠይቅህ „ግዮን ሆይ!“ ሚስጢርህ የቱ ነው? የተመሰጠርከው በህብሬ ደማሙ ፈቅደህ የሰጠኸው፤ በጨለመበት ለት፣ ሁሉ ፊት ሲነሳው፣ በደቦ ሲገፋው ደረስክለት አንተ - ፊት ለፊት ተማግደህ - ሩቅ ራይ የሆንከው። እስቲ ልጠይቅህ ጐጃም ሆይ! አንተኑ? ፍቅረኛ የሆንከው፤ የደሙ ግብረኛ የሆንክልን ባይኑ። ጐጃም ሆይ! ስለኛ ምን ያልሆነከው አለህ? የደመር ዕድምተኛ የስቃይ፣ የዕንባ፣ የአይዞህ ማበርተኛ! ቀራንዮ ሆነህ  …. …. ጎለጎታ ሆነህ ዳንኤል ሆነህ …. …  አናንያ ሆነህ  አዛርያ ሆነህ … ….  ሚሳዬልን ሆነህ  በዝምታኽ ሆነህ…  አባታጣቅ ሆነህ … ... በበላይም ዘልቀህ ገልሞን ተወዳጅተህ ..