ልጥፎች

ዕውን ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ዬኢትዮጵያኒዝም አንከር ናቸውን? መረቅ ጥያቄ ለአቶ ግዛው ለገሰ።

ምስል
    ዕውን ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ዬኢትዮጵያኒዝም አንከር ናቸውን ? መረቅ ጥያቄ ለአቶ ግዛው ለገሰ። " ዬቤትህ ቅናት በላኝ። " ዘለግ ያለ ሙግት ነው ከአቶ ግዛው ለገሰ ጋር።     # መግቢያ ። አቶ ግዛው ብቻ አይደለም ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን ኢትዮጵያኒዝም ዬሚዪደርገው። አሳቻ ስለሆኑ ለረጅም ጊዜ አቶ ኤርምያስ ለገሰም ይህን አመክንዮ ይሞግትበት ነበር። አንድ ዓመቴ ነው አቶ ኤርምያስ ለገሰን አዳምጬው ከማላውቅ አሁን ያለው አቋሙን አላውቅም። ሌላ በቅርቡ ዶር አብይ አህመድ በ 15/11/ 2022 በፓርላማ ቆይታቸውም ባደረጉት ገለጣ ተመስጠው ዬአደባባይ ሚዲያ መሥራች ቀሲስም በኢትዮጵያዊነታቸው እንደ ተደመሙ በአጽህኖት ሲገልጡ ሰምቻለሁኝ። ይቅናችሁ ……… # ዕፍታ ። በስሜን አሜሪካ ስፖርት ፌስቲባል ላይ ደረሰብኝ ላልከው መጎዳት እጅግ አዝኜ ጽፌበታለሁኝ። ትናንትም ያ ተደግሟል። ትክክል ነው ብዬ አላምንም። ሥርዓት ይለዋወጣል። ትውልድ ይቀጥላል። አክሰሱ ላላቸው ልጆች ጥሩ ምልክት አይደለም። ከአምስት ዓመት በፊት ለማይታወቅ ሰብዕና አብራችሁ እምትኖሩት መገፋፋት ዬተገባ አይደለም። ከሁሉም ልጆች ይጎዳሉ። በቅንጅት፤ በግንቦት 7 ዬተፈጠረው መለያዬት በቂ ነው። በዛ መስመር መጓዝ አይገባም። ለእኔ ከአቶ ሚስጢረ ኃይለሥላሴ፤ ከማክዲ በላይ ዬሚቀርብ እህት ወንድም አልነበረም። ግን መርዛሙ ፖለቲካ በተነን። ያ ልንማርበት ሲገባ ዛሬም መቀጠሉ ያቆስላል። # መቅድም ። 1) ጥቂት ፎቶወ