ዕውን ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ዬኢትዮጵያኒዝም አንከር ናቸውን? መረቅ ጥያቄ ለአቶ ግዛው ለገሰ።

 

 

ዕውን ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ዬኢትዮጵያኒዝም አንከር ናቸውን? መረቅ ጥያቄ ለአቶ ግዛው ለገሰ።

"ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"

ዘለግ ያለ ሙግት ነው ከአቶ ግዛው ለገሰ ጋር።

 


 

#መግቢያ

አቶ ግዛው ብቻ አይደለም ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን ኢትዮጵያኒዝም ዬሚዪደርገው። አሳቻ ስለሆኑ ለረጅም ጊዜ አቶ ኤርምያስ ለገሰም ይህን አመክንዮ ይሞግትበት ነበር። አንድ ዓመቴ ነው አቶ ኤርምያስ ለገሰን አዳምጬው ከማላውቅ አሁን ያለው አቋሙን አላውቅም። ሌላ በቅርቡ ዶር አብይ አህመድ 15/11/ 2022 በፓርላማ ቆይታቸውም ባደረጉት ገለጣ ተመስጠው ዬአደባባይ ሚዲያ መሥራች ቀሲስም በኢትዮጵያዊነታቸው እንደ ተደመሙ በአጽህኖት ሲገልጡ ሰምቻለሁኝ። ይቅናችሁ ………

#ዕፍታ

በስሜን አሜሪካ ስፖርት ፌስቲባል ላይ ደረሰብኝ ላልከው መጎዳት እጅግ አዝኜ ጽፌበታለሁኝ። ትናንትም ተደግሟል። ትክክል ነው ብዬ አላምንም። ሥርዓት ይለዋወጣል። ትውልድ ይቀጥላል። አክሰሱ ላላቸው ልጆች ጥሩ ምልክት አይደለም። ከአምስት ዓመት በፊት ለማይታወቅ ሰብዕና አብራችሁ እምትኖሩት መገፋፋት ዬተገባ አይደለም። ከሁሉም ልጆች ይጎዳሉ። በቅንጅት፤ በግንቦት 7 ዬተፈጠረው መለያዬት በቂ ነው። በዛ መስመር መጓዝ አይገባም። ለእኔ ከአቶ ሚስጢረ ኃይለሥላሴ፤ ከማክዲ በላይ ዬሚቀርብ እህት ወንድም አልነበረም። ግን መርዛሙ ፖለቲካ በተነን። ልንማርበት ሲገባ ዛሬም መቀጠሉ ያቆስላል።

#መቅድም

1)ጥቂት ፎቶወችን ለጥፊያለሁ። ታያቸው ዘንድ በትህትና እጋብዝኃለሁኝ። በዛ ውስጥ ኢትዮጵያ በግርማ ሞገስ ስለመኖሯ ይሞግታል እና።

2) በጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ በተገኙበት ጉባኤ መገኜትህ አይሻክረኝም። ለአንተ ዬፖለቲካ ውሳኔ አንተ እንጂ ሌላ መሪ ስሌለ።

3) እዬራቀን በሄደን ዴሞክራሲም መርሁ ያልተመቸን ሃሳብ ችሎ ማስተናገድ ነውና ደጋፊወቻቸው መደገፍ ሙሉ መብታቸው ነው። ጉዟቸውን ዬምንሞግተውም ሙሉ መብታችን ነው። ሃሳቦች ይታገሉ፤ ሃሳቦች ይፋለሙ ሰብዕናችን ግን በተፈጥሯችን ልክ መቀጠል ይኖርበታል። ኢትዮጵያ ዬተፈጥሯዊነት ካስማ ናትና።

#ውስጠት

1) ጊዜ ውሰድ እና የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን ሎጎወች በሙሉ አጥናቸው። የቤት ሥራ ነው። በሎጋቸው ውስጥ ኢትዮጵያ ካለች። ግን ፒኮክ ዬኢትዮጵያ መለያ ነውን?

2) ስለምን ይሆን ሚኒሊካዊ ጋዜጠኞች የሚሳደዱት፤ ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ተሰዟል። ጉድ እንዳይዘረግፍ ምልጃ ላይ እንደሚገኝ አገዛዙ ይገባኛል።

ለአንተ ባልነግርህም በለገዳዲ ራዲዮ ጣቢያ፤ በትንሳኤ ራዲዮ ጣቢያ አውቀዋለሁኝ። ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ወይሳ ከእኔ ይልቅ በቅርበት አንተም ታውቀዋለህ ስለምን በመንግሥት ሚዲያ ሽፋን ተነፈገው? ፈታኝ ጥያቄ ነው እማቀርብልህ። ቀብሮ ከቀብሩ ጉድጓድ የከበደ እጅግ በረዶ ነበር። ለምን የኢትዮጵያኒዝም ሚስጢር ስለነበር ጋዜጠኛ ስለነበር።

3) ዬኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በግልጽም በስውርም ተሳዳጅ ናት። ሰይፍ ላይ ተቀምጣለች። ለምን? ዬኢትዮጵያዊነት ክፍለዘመን ስለሆነች።

4) አዲስ አበባ የሉሲ መዲና ከመስከረም 5/2011 ጀምሮ ለኦሮምያ ተሰጥታለች ብዬ አምናለሁኝ። በድፍረት አሉታዊ ዴሞግራፊ ተከውኖባታል። አሉታዊ ዴሞግራፊ 2ኛው የዓለም ጦርነትን ዬፈጠረ በውድመት እና በውድቀት የተከወነ ነው። ይህን መርሁ ያደረገ አገዛዝ እና ሙሴው ኢትዮጵያኒዝም ጠረኑ አለበት ብሎ እንደምን ይታመናል። ከተማዋ ውስጥ 6 ሺህ፤ በዙሪያው ግማሽ ሚሊዮን ኦሮምያ ቋንቋ አስፍሮ ኡርባን ፖለቲክስ ከተማን በውዞ ለዘለቄታ ማቀድ፤ መከወን እኮ ዬዘመኑን ዬፖለቲካ ባህሬ ገልጦ ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ከዚህ መነሳት ስለአቃታችሁ ነው ሙት መሬት ላይ ዛሬ ቅሬታ በማቅረብ ላይ ዬምትገኙት።

ሁሉንም ክልል አነጋግረዋል 100 ቀናት። አዲስ አበባ ተነጥላ ቀርታለች። ጋዜጠኛ ቴወድሮስ ፀጋዬ ስሜን አሜሪካ በመጡ ጊዜ ጥያቄ ሲቀርብም። አልመለሱትም። ለምን ዘለሉት? ህወሃትን ከኦሮምያ እንብርት አባረናል ሲሉ አዲስ አበባ ዬኢትዮጵያ እንብርት ወይንስ የኦሮምያ? አዲስ አበባ የአፍሪካውያን ዕንብርት ወይንስ የኦሮምያ? አዲስ አበባ የሽዋ እንብርት ወይንስ ዬኦሮምያ? ይህም ብቻ አይደለም ሰሞኑን በአዋሳው ንግግራቸው አዋሳ ዬኢትዮጵውያን ከተማ፤ ቦንጋ የኢትዮጵውያን ከተማ፤ ጅማ ዬኢትዮጵውያን ከተማ፤ መቀሌ ዬኢትዮጵውያን ከተማ እያሉ ሁሉንም ገለፁ፤ ናዝሬት እና አዲስ አበባ ግን ተዘለሉ? በዚህ ውስጥ የኢትዮጵያን መዲና አልባነት ቁልጭ ብሎ ይታያል። ይህን መንፈስ ነው ስለ ትውልድ፤ ስለ ኢትዮጵውያዊነት ራዕይ አላቸው ብለህ የፈሰሰን እፈሱልኝ ዬምትለን።

4) በአንደበታቸው "አዲስ አበባ ውስጥ ዬኦሮሞ ጥላቻ አለ፤ እኛ ኦሮሞወች ዝሆን ነን፤ እንበላለን፤ እንሰብራለን፤ እኛን ዓለም አውቆናል፤ ከህወሃት ጋር በኢንሳ እዬሰራሁ ለማህበረ ጃራ ሚስጢር እሰጥ ነበር ያሉን። ያውም ለጃራ????? ይህም ብቻ አይደለም "ሥልጣናችን ከተነካ በቀን 100 ሺህ ሰው እናርዳለን ያሉት።" የሰው እርድ፤ ሰውን ሰው መብላት፤ አረማዊነት ኢትዮጵያኒዝም ከሆነ ትነግረኛለህ።

ኢትዮጵያዊነት ፍፁም ደግነት። የሰው ስጋ ሃራም ነው። ጥቁር ቀን ዬሚያርድ ነው። ታማኝነት መለያ ነው። በኢትዮጵያ መሃያ ለአልሲሲ መንፈስ ሚስጢር በነፃ ይታደል ነበር። ለመሆኑ አኖሌ ሃውልቱ ዬማን ፕሮጀክት ይሆን?

#ድፍረት

ድፈር እና ከሉዑኩ ጋር ኦሮምያ ክልል እኩል ከፌድራሉ ጋር የተወከሉበትን ምክንያት ጠይቅ? ከሁሉምክልሎች ተለይቶ ኦሮምያ ከሉዑኩ ስለመን ታደመ? አቶ አዲሱ አረጋ ምን ባይ ናቸው????? እራሱ ጠቅላይ ሚኒስተሩ፤ ዬፍትህ ሚኒስተሩ የኦሮምያ ክልል ውክል አይደሉምን? ስለምን ልዩ ኤክስትራ ውክልና ለኦሮምያ ተሰጠ??????

#ሚዛን

በመኖር ውስጥ ሚዛን ይኖራል። መርህ ግን አይሰፈርም። ዕውነትም አይመተርም። ፋክት አይከነዳም። ኢትዮጵያ ርህርህና ናት። አይዟችሁ ማለትን ዬማይደፍር መሪ ኢትዮጵያኒዝም ያቀረው ብቻ ነው። አይከፈልበትም። ዳገት ቁልቁለት ዬለበትም። ለምን ስለምን አይዟችሁን ሸሹት ጠቅላይ ሚኒስተርህ?

በዝዋይ፤ በሻሸመኔ፤ በአጣዬ፤ በሽዋ ሮቢት፤ በጭና፤ በማይካድራ፤ በወረባቡ፤ በሃይቅ፤ በደሴ፤ በኮንቦልቻ፤ በንፋስመውጫ፤ በወልደያ፤ በዋግ ህምራ፤ በመተከል፤ በደብረብርሃን፤ በማርቆስ፤ በወለጋ፤ ይህ ሁሉ ህዝብ ሲፈናቀል፤ ስቃይ ሲቆላው ዬትኛው የምንዱባን ካንፕ ተገኙ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ።

#አዳዲስ ማንነቶችን መቅረጽ።

ደቡብን ሸንሽነውታል። አሁን በቅርቡ ወልቃይት የሚል ማንነት ቀርፀዋል። ጭልጋ ወረድ ብለው ጫቆ ማንነት፤ ዳዋ ማንነት፤ አዳኝ አገር ማንነት፤ ጮንጮቅ ማንነት፤ ገለድባ ማንነት እያሉ ደግሞ ያስነኩታል። ይህ ኢትዮጵያዊነትን የመሸብሸብ፤ ኢትዮጵያዊነትን የማራቆት፤ ኢትዮጵያዊነትን የመሰልሰል ጉዞ ነው። ይህ በአደባባይ የሚታይ ነው ስውሩን ፈጣሪ ያውቀዋል። አርቲፊሻል ውኃ ሰርተው አዲስ አበባ ምን እንደ ሠሩ ይታወቃል። መስቀል አደባባይ ቀረመት ላይ ነው። ብዙ እጅግ ትብትብ ሰንሰለታማ መከራ ኢትዮጵያ ይጠብቃታል። ይህን የሚመክት ተቋም ቀርቶ ሃሳብ ዬለም። ቢኖርም አሰባሳቢ አያገኝም። ሁሉም ሞክ ብሎ መክኖ ማይክ ብቻ ነው ያለው። ለዚህ ነው እሳቸው ልባቸውን ሞልተው ለአቅመ አዳም የደረሰ ሃሳብ ሲኖራችሁ ብቅ በሉ ያሉት አዋሳ ላይ።

1) መሪነት ደስታን ብቻ ሳይሆን ዕንባንም ታድሞ መምራት ነበር።

2) ብሄራዊ ሰንደቄ ነደደ ብለው ሲበሳጩ ሰምተህ ታውቃለህ?

3) ሚሊዮኖች ተፈናቀሉ ዬመጠለያ ፕሮጀክት አቅደው ሰምተህ ታውቃለህ?

4)አንድ ቀን ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ ሲውለበለብ አይተህ ታውቃለህ?

5) አንድ ቀን በህሊና ፀሎት ጉባኤ ሲጀምሩ አስተውለህ ታውቃለህ?

6)አንድ ቀን የሃዘን ብሄራዊ ቀን ታውጆ አድምጠኃልን?

7)አንድ ቀን ዬአደባባይ ብሄራዊ በዓላት ካለ ህውከት፤ ካለ ወከባ ተከናውኖ ያውቃልን?

8)አንድ ቀን የአደባባይ ዬቅድስት ተዋህዶ በዓላት ተከብሮ ያውቃልን? ስለምን ለመስቀሉ እሮጣለሁ ታገደ? መልስአለህን?

9)ለፕሮቴስታንት ሃይማኖት የሄሰኑን የጀርመን የሰላም ሽልማት 50 ሺህ ኢሮ ሲሸልሙ ምን ዳብል ሮል እንደነበረው አስተውለኃልን?

10) ዬሞት ዘመቻው የህዝብ መቀነስ አካል ስለመሆኑስ አስበህው ታውቃለህን?

11)የብልፅግና ዓርማ እዬው እስኪ በዛ ውስጥ ኢትዮጵያዊነት ልቅላቂው ካለ ትነግረኛለህ።

12) ስለ ትውልድ ግንባታም አንስተኃል የቁቤን ትውልድ ኢትዮጵያኒዝም ለማድረግ ቅንጣት ፕሮጀክት አላቸውን? ዬመንፈስ ነቀላ እና ተከላቸው አዲስ አበባ እና አማራ ክልል፤ ውጠት ደቡብ ክልል ነው። ህሊና ከሰራ። ለሰከንድ እሳቸውን ደግፎ መቆም በራስ ተፈጥሮ ላይ ስቅላት መበዬን ነው ከሀምሌ 19/2010 . ጀምሮ ዬአባይ ግድብ አናት ከተረሸኑ በኋላ። ቀን ነበር በቃን አምጦ መውለድ ይገባ ዬነበረው።

13) ዬአዲስ አበባ አምስት ነዋሪወች በአደባባይ መረሸን ርችት ነበር ዬኦነግ ኢትዮጵያን በመፈንቀል ዬመያዝ ዕለት። ሲጠዬቁ ምን እንደመለሱ ታውቃለህ። ገና ሲቢክስ እያለ ነበር ባልደራስ ላይ ጦርነት እከፍታለሁ ብለው ያወጁት። ለምን ቅምጥ ፍላጎታቸውን ስለሚንደው። ቅምጥ ፍላጎት አላቸው ኦነግን፤ ገዳን፤ ኦዳን አዘምነው ሞደሬት ዬማድረግ።

ኢትዮጵያ እዬተነቀለች ነው። በአካልም በመንፈስም። ለዚህ ደግሞ ብቁ ናቸው። አንተን መሰል ሙሉ አቅሙን የሚለግሥ ቸር ሌላ አማራጭ ዬለም ብሎ እንዲያስብ ሽብር ታቅዶ ይከወናል። የሞገድ ጋዜጣን ካገኜህ አንብበው። 10 ሚሊዮን የሚያወጣ ወንጀል ሠርቶ ሞገድ ጋዜጣ ዜናውን ሲሰራው 20 ሚሊዮን ይሸጠዋል። እንደ ጥንቸል ቤተ ሙከራዋ ኢትዮጵያ አምስት ዓመት ሙሉ ይህ ተፈጽሞባታል። ፈቃጆቹ ደግሞ የመንፈስ ስንቅ አንተን መሰሎቹ ናችሁ። ፀፀቱ እንደ ቋያ ዬሚቀቅልበት ጊዜ ይመጣል። ጠብቀው።

ተረኝነት ዬሚሉ አሉ። ይህ ደረጃውን ያልጠበቀ የፖለቲካ ግንዛቤ ነው። የዘመኑ የፖለቲካ ባህሬ የገዳ ወረራ፤ ዬገዳ መስፋፋት፤ ዬገዳ አስምሌሽን፤ ዬገዳ ዲስክርምኔሽን ነው። አሉታዊ ዲሞግራፊም ፋሺዝም ነው። ይህን የሚተረጉም፤ የሚያመሳጥር ቀርቶ በቁሙ ዬሚያነብ የፖለቲካ አቅም አላዬሁም። ይህን ደግሞ 2019 ጽፌበት በደጉ ሳተናው ወደ 400 ዬሚጠጋ ሼር ነበረው። ለአፍሪካም ያሰጋል ብዬ ነበር ዬፃፍኩት።

- https://sergute.blogspot.com/2019/12/blog-post.html

ዛሬ ያለው ነገርፈረቃም፤ ተረኝነትምአይደለም።

#ምን ይደረግ።

እኔ ለኢትዮጵያ ተፈጥሮ የፖለቲካ ድርጅት ያስፈልጋታል ብዬ አላምንም። ተፈጥሯዊ ሰውነት ያላቸው ከዬትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ጋር ያልተለካኩ የደግነት ግብረ ኃይል ኢትዮጵያን እንዲመራ እሻለሁኝ። ሁሉም የፖለቲካ ድርጅት ወደ ሰባዕዊነት እንዲቀዬር።

መርህ አልባነት፤ አናርኪዝም፤ ዬዕውነት ሽሽት፤ ጭካኔ ነው እኔ ዬማዬው። ከማሌ ፍልስፍናም፤ ከሴራም ፖለቲካ ዬዳነ የፖለቲካ ድርጅት፤ ሰበነክ ድርጅት አላዬሁም። ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ዬምትሆነው ዬፖለቲካ ድርጅትን በህግ ስታግድ። ክፍላተ አገራትን በቀደመው ምልሰት ስታደርግ። ሁሉም ኢትዮጵያን ይወክልልኛል ዬሚለውን ሰንደቅ ለመያዝ ነፃነት ሲኖረው ብቻ ይሆናል። ካለ ህገ መንግሥትም የሚኖሩ አገሮች አሉ። በቡድን የሚመሩ አገሮች አሉ። ሲዊዝ ጠቅላይ ሚር ሆነ ፕሬዚዳንት ዬላትም። ለምን? ሥልጣኔው የህሊና ስለሆነ።

#ማጠቃለያ

ዶር አብይ አህመድ የወጣላቸው ተናጋሪ ናቸው። አማላይ መንፈስ አላቸው። መንፈሱ ከጥቁር አረንጓዴ ብርኃን ይመነጫል። አሳቻም ናቸው። መተርጎም አይቻለም። እኔ ቋሚ ዬሚያምኑበት ሃይማኖት፤ ቋሚ ዬሚያምኑት የልብ ወዳጅ ዘላቂ ይኖራቸዋል ብዬ አላምንም። የደህንነት ሰውነታቸው ለግሎባልም አስቸጋሪ ሊሆኑ ይችላሉ። ሙልጭልጭ ባህሪያቸው የውስጣቸው ድፍንነትን ያሳያል። ለዚህ ነው ዬሚያስቆመን ኃይል ዬለም ዬሚሉት። የላይኛውግን አለ። ለቀኑ ቀን ሲሰጠው መፍትሄ ይገኛል። ጥያቄዬ ሁሉንም ስለመዘንኩት ከዚያስ ለሚለው ጭንቀት ይቀናልኛል።

ሰውን ሳናውቀው እንደግፋለን። ሰውን ሳናውቀው እንማገዳለን። አገር ገደል ለገደል። ለሥር ነቀል ሥርዓት ለውጥ እንትጋ። ዬግለሰብ ሰብዕና ግንባታ ላይ አቅም አይባክን።

አቶ ግዛው ለገሰ ሙግት ካሰኜው ብቅ ይበል። በቴክስት ቻት ማድረግ እንችላለን። ስልክ ግጥሜ ስላልሆነ። አቶ ግዛው ለገሰ ትግረኛ እና ኦሮምኛ ቋንቋ መቻሉን አደንቅለታለሁኝ። የጠቅላዩ ስብሰባ ቤተኛ ሆነህ መገኜትህ በጀ። ውስጤ ስለ አንተ ዬሚለኝን እንሆ ገለጽኩኝ። የኢትዮጵያን ዘመን ጠገብ የባህል፤ የታሪክ፤ የትውፊት ካስማ ኦነግ እንዲመራው ማድረጋቸው ብቻ ሚስጢር ይገለጥልህ ዘንድ ፈጣሪን ለምነው። ቱሪዝምም ………??? ሟጋቿ ዶር መስከረም ለቺሳ እያሉ ………

ክብሮቼ ደህና ዋሉልኝ። አሜን።

እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

16/12/2023

ሲዊዘርላንድ ቪንተርቱር ከተማ።

ትዕግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል፤ ፍቅርም ሲያልቅ ትዕግሥት ይሰደዳል።

ኢትዮጵያ ፍልስፍና፤ ሳይንስ፤ ዩንቨር፤ ህግም ናት።

ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

ዕውነት ሠራዊት ዬለውም።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።