ፀረ ኢትዮጵያው አቶ ሌንጮ ይምሩኝ ስትል ኮንቬንሽናል ሴንተር …… አርባጉጉን እርሳው አዲስ #አበባ አራባ ጉጉ ሆኖልኃል ……ብቻ ተውበህ ተገኝለት ለሞነር ዬቁም ተዝካር።
ፀረ ኢትዮጵያው አቶ ሌንጮ ይምሩኝ ስትል ኮንቬንሽናል ሴንተር …… አርባጉጉን እርሳው አዲስ #አበባ አራባ ጉጉ ሆኖልኃል ……ብቻ ተውበህ ተገኝለት ለሞነር ዬቁም ተዝካር።
ይህ ሠርግና መልስህ ከሆነ በዕለተ ሃሙስ ኮንቬንሽናል ሴንተር ቤተኛ መሆን ነው።
ኮንቬንሽናል ሴንተር ሃሙስ ቀጠሮ ተይዟል አገር አልባ ላደረገህ መቅሰፍታዊ ዘመን ወረፋ ይዘህ ተሰልፈህ ተገኝ እና ስለሞትህ ማረጋገጫ ፊርማ ስጥበት¡¡¡¿¿¿¿ ማህበረ ጲላጦስ ጋር ማህበርተኛም ሁን። ያምርብኃልና¡¡¡¡
"ዬቤትህ ቅናት በላኝ"
አትገኙ ዬሚል ቅስቀሳ አለ ተብሏል። አቶ ወንድም አቤ ቱኩቻው ነው ይህን ሲል ዬሰማሁት። ይህ ዬተገባ አይደለም። የሚቃወም እንደአለ ሁሉ ዬሚደግፍ መኖሩ ተፈጥሯዊ ነው። ለዴሞክራሲ እንታገላለን ከሆነ ዬማይማቹትን ሃሳብ ሁሉ ማስተናገድ ይገባል። ሌላውን መጫን ዲስክርምኔሽን ነው። ሞልቶ የፈሰሰ ሃቅ ስላለን እሱን አቅርበን እንሞግታለን። ዬሚሞገተው ሰውኛ ለሆነ ተፈጥሮ ብቻ ነው።
ከዚህም በተጨማሪ ማን እንደተገኜ ማወቅም ይጠቅማል። ዬተወሰነ ኃይል ተገኝቶ ለታሪክ በሚያመች መልኩ ሂደቱን ዘግቦ መያዝ ለሰባዕዊነት፤ ለተፈጥሯዊነት፤ ለፓን አፍሪካ ሙቭመት እጅግ ጠቃሚ ነው። ለዚህ ግብረ ኃይል አደራጅቶ መሰነድ ይገባል። በተለይ #ዬአማራ ማህበር በአሜሪካ ታሪኩን መያዝ ይገበዋል።
አሁን ዬሚሰጠው ፊርማ 360 ቀናት አሜሪካ ነጩ ቤተ መንግሥት አስፓልት ላይ ካለ እህል ውኃ ቢቀመጡ ከቶውንም መመከት ዬማይቻል ይሆናል። ገዳ መስፋፋቱን፤ ገዳ በመጠነ ሰፊ የማጥፋት ወረራውን፤ አስምሌሽኑን፤ ዲስክርምኔሽኑን፤ ጆኖሳይድን እንዲቀጥል መሸለም ነው። #እንድንጠፋ ስጦታ ማበርከት ነው።
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የሌሉበት የፕሮጀክት ዓይነት ዬለም። ከዚህ ውስጥ ህዝብ መቀነስ አንዱ ነው። ሌላም፤ ሌላም። ልንሰማቸው የማንፈቅዳቸው ዓለምን እዬፈተነ ያለ ግድፈት ሁሉ ኢትዮጵያ እንደ ጥንቸል መሞከሪያ ጣቢያ እያደረጓት ነው። ያልተወጠነ፤ ያልተጀመረ ስውር ነገር ዬለም። ነገ ይገለጣል። ልቅነት በስፋት ይሰራበታል። ዬሰው ግብርነትም። ለዚህ ሁሉ መከራን ላዘለ አመራር አቅም ማዋጣት መርዝ ማብቀል ነው። ለትውልድም ዲዲቲ።
#ለሞትህ ማረጋገጫ ኮንቤንሽናል ሴንተር ይሁን ቀጠሮህ ከማህበረ ጲላጦስ ጋራ¡¡¡¡
1) እርሰ መዲናህን ለማጣት ፊርማህን አሜሪካ ላይ አስቀምጥ¡
2) ለውድመትህ፤ አመድ ለማፈስህ ምስክርነት ወፊቱ ሳትቀድምህ የሚጠዬፋትን ማህበረ ኦነግ አብዝቶ ዬሚጠዬፈውን፤ ዬአቶ ሌንጮ ለታን፤ የአቶ ሌንጮ ባቲን፤ ዬዶክተር ዲማ ነግዖን፤ የአቶ ዳውድ ኢብሳን አረመኔ መንፈስ ለማስቀጠል አብዝተው የሚጠዬፋትን ሰንደቅ ዓላማ ለብሰህ ሰንደቅ ዓላማህን ለብሰህ አሸሼ ነዋ¡
3) ለአዲስ አበባ ጽዳት አትመጥንም ተብለህ ደብረ ብርሃን፤ ከዛ አርሲ፤ ከዛ አዋሽ #ዶሮ ኩስ ካዝና መከዘንህን እንደ ሠርግህ መቀበልህን ፈርምላቸው ዕብን ሆይ ………
4)18 + 10= 28 ዬደንቪደሎ ተማሪወችን እገታ ፌስታህ ስለሆኑ ማተሚያውን ኮንቤክሽናል ሴንተር ተገኝተህ ሙሽሮቼን ድብዛቸውን ስላጠፋህ ክብር ለአንተ በላ¡ ያንጊዜ የጫካው ሳይሆን የዲስው አጋች አንተ መሆንህ ይታወቃል።
5)አምስት ዓመት ሙሉ አዲስ አበባ አትገባም ተብለህ በዓራቱም ማዕዘን መንገድ እዬተዘገ መታገድህ፤ መረሸንህ፤ ድብዛህ መጥፋትህ፤ መስተጓጎልህ የጫጉላ ጊዜዬ ነው ብለህ ለመቀበልህ ውሳኔህ ይሆናል።
5)በአጣዬ፤ በሻሸመኔ፤ በደራ፤ በሽዋ ሮቤት፤ በአርሲ ነገሌ፤ በዝዋይ፤ እሬሳህ ልጆችህ እያዩ ለጅብ መሰጠቱ፤ ተቋማትህ በአንድ ቀን ወድመው አቧራ ለብሰህ የጎዳና ተዳዳሪ መሆንህ ክብሬ¡ ኩራቴ¡ ነው ብለህ መቀበልህን ዕውቅና መስጫው ይሆናል።
6)አምስት ዓመት ሙሉ በዘር ሃረግህ በዬሄድክበን ከቤተ እግዚአብሔር እንደገባ ውሻ እዬታደንክ ተነጥለህ መታሰርህ፤ መሪወችህ በርዕሰ መዲናህ በባህርዳር መረሸናቸውን፤ መሪወችህ መገፋታቸው፤ ድሎቴ ነው ቀጥቅጠኝ ብለህ ዕውቅና መስጠትህ ይሆናል።
7) በዬትኛውም ዬኢትዮጵያ ክልል ያኮረፈ ሁሉ ዬቁጫን መወጣጫ ሆነህ ከቤት ንብረትህ ስትፈናቀል፤ መውደቂያ አጥተህ ስትንከራተት ጅንካ፤ አማሮ ሳይቀር ሲያባርርህ ሐሴቴ¡ ነው ብለህ ለገዳ ስለገዳ ፈርምበት። አቶ አዲሱ አረጋ ነገ በዳብል አቅም ያስመነጥሩኃል። ምን ይጨንቃል ፈቅደህ ዬለ።
ያ ማሰብ ዬተሳነው ልቅ ድጋፍ ኖቤል አሸለመ። ለሬሳው ጥላምአሸለመ። ለምን እንደ ተኛህ ስለሆነ አሁንም ኮንቬንሽናል ሴንተር ተገኝ እና ያ ዬሚረገጥ፤ እንደ ማበሻ ጨርቅ ዬሚጠቀጥቁትን ሰንደቅህን እዛው አሜሪካን አገር ለብሰህ ተንከላወስ።
9)ሰርክ በእገታ፤ አብራክ ሳይቀር ቋንጣ በሆነበን መተከል የማረጃ መቀዬሪያ ካንፕ አሰናድቶ መኖርህን ላብጠለጠለ ዬትናንቱ ሳይቆጭህ፤ ዬትናንቱ ሳያንገበግብህ፤ ዬትናንቱ ሳያነድህ አብረህ በደም ጋን ዬደም የወል ጽዋህን አንሳ። ጅል፤ ጅላጅል፤ ጅልአንፎብሎኃል እኮ ማህበረ ገዳ ሞደሬተር። አከናቦኃል። ተመችቶኛል ብለህ በኮንቤክሽናል ሴንተር አታሞኽን ደልቅ።
10) በኦሮምያ፤ በወለጋ፤ በሁሩጉድሩ፤ በቄለም፤ በቶሌ ምን አላት በቀን 1300 ለስምንት ተከታታይ ሰዓት ባሩድ ዬዘነበበት ወገን ለዓንተ ሰው አይደለም። ዬአውደዓመት አውራ ዶሮ ነው። እልልልል ………¡¡¡¡¿¿¿¿ ብለህ አንግሥለት፤ አቅስለት። ጨካኝነት ከጨካኞች ጋር ማዕደኛ መሆን አይደለም በአንተ ቤት ………ልሙጥ።
11) "ወላሂ ከእንግዲህ ወዲያ አማራ አልሆንም" ያለች የስድስት ዓመት የተበሳሰከ በጥይት ገላ ለዓንተ ኮንሰርት ነውና በኮንቬክሽናል ሴንተር ተገኝተህ አጨብጭብለት ………
12) ሰርክ ጫካ ለጫካ፤ ዳዋ ለዳዋ ዬሚንከራተተው ገላ ዬአንተ አይደለም። ባለ መኖር ውስጥ ስላለህ የደም ንክሩ ፌስታ በኮንቤክሽናል ሴንተር ነውና ሠርጉን ጨፍርበት፤ ዳንስበት፤ አሽካካበት።
13) በሰበሩን ቦታ ሠብረን ጥሩ ማስያዥ ነው፤ አባይን ተሻግረንም ጥሩ ወጌሻ ነው፤ አዲስ አበባ ኦሮሞን ዬሚጠሉ አሉም መልካም ቴራፒ ነው ይደላል አይደል ለቤተ መንግሥት ፊርንበኛ፤ እናማ ገዳይህን፤ አራጅህን እጅ ለመንካት፤ እርግማን ለመቀራመት ተሰናዳ፤ እና በውል ጭካኔ ዘውድ ለደፋባት ኢትዮጵያ የሙት ቀኗን ተዝካር አብረህ አውጣ።
14) 12993 ዬአማራ ተማሪ ከፈተና ውጪ ሁኖ ኮሽ ዬለም፤ ይመቻል¡ ዬገዳ ሳውና የአማራን ትውልድ የመቅበር ስትራቴጂያዊ ትልም ፦፦፦ ዬአማራ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህር ቤት እንዳይልኩ መቅሰፍት።
15) ከ 4500 - 12000 የሚደርስ ደሙን ገብሮ አገር ለመጠበቅ ዬተሰናዳ ዬተፈጥሮ ቀይ መስቀልህ ፋኖ ተሰውሮ፤ ተገድሎ፤ ስልጠናው ተስተጓጉሎ፤ ኦነግ ግን በአደባባይ ዘመናይ መኪና አደራጅቶ፤ ዘመናይ ድንኳን ጥሎ ያስመርቃል። ይወራል። ያፈናቅላል። ያርዳል፤ ያሻውን ያደርጋል። ይህ የዘበጠ ሥርዓት እንዲቀጥል በሽሚያ ሄደህ ኮንቤንሽናል ሴንተር ጃኬትህን አስመርቅበን፤ ኮፍያህን አሳይበት፤ እስካርፕህን ናኝበት¡¡¡ ምድራዊውን ተወው ዬላይኛው ያያል ………
16) ከታሠሩት ውስጥ 700 በአፋር በርኃ በምን ሁኔታ እንደሚገኙ አይታወቅም። ይህ ተስፋህ ሆኖ ኮንቬክሽናል ሴንተር ተገኝተህ አድምቀው በደም ቀለም አንተም ማህበርተኝነትህን ጨልጥበት። ያ ዘመን አልፎ እኛ በዛ ዬበረዶ ተራራ ኮፐን ሃገን ስንሰበሰብ ያልነበሩ ተጋሩወች ዛሬ በዲሲ ላይ ተገኝተዋል። ምስክሩ አባይ ሚዲያ ኢትዮጵያ ላይ አለ ጠይቁት እንዴት እንደ ነበር፤ ምን እንደከወንበት አውሮፓ የምንገኝ ኢትዮጵውያን በታህሳስ 18 -22 በ2018 ……… እኔም ሂጃለሁኝ። 100 እንጀራ ተሸክሜ ለፆመኞች ሰሊጥ እና ተልባ አሰናድቼ ከ300 ያላነሰ በራሪ ፁሁፍ እና ፖስተር አዘጋጅቸ። ያ ሁሉ ድካም ለአቶ ሌንጮ ለታ ፍሰኃ፤ ለዶር ዲማ ነግኦ ሰናይ???? ማሰብ ያስፈልጋል። መጠሞን ያስፈልጋል። በተለይ ዬአማራ ልጅ። አቅምህ የወንዝ ዳር አሽዋ ነው። ከንቱ።
17) አንድ ቀን አይዞህ ያላለህ፤ አንድም ቀን በወደመ በተቃጠለ በነደደ በአዘኑ ተስፋ ባጡ
18) የኦነግ ግዙፋ ፕሮጀክት ዬአማራን ህዝብ ሙሉ ለሙሉ ዬማደህዬትም ነው። ያወድማሉ፤ ወይ ያስወድማሉ ያ ዬሚቋቋመው በነፍስ ወከፍ ውጪጪ ነው። ደግሞ ደጋግሞ ይወድማል። ታጥቦ ጭቃ። ይህ ረቂቁ ጆንሳይድ ነው። ለዚህም ነው አሳቻው መሪ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ጆኖሳይድን አዘምነውታል ዬምለው።
19) ህዝብ ዬመቀነስ ግሎባል ፕሮጀክት ነው። ኢትዮጵያ ላይ እንዲቀነስ ዬሚፈለገው ዬአማራ ህዝብ ነው። ወሎ ዬበቃኝ አብዮትን ፋና ወጊ ሆነ። በዝምታ ውስጥ ህወሃት ድቅቅ እንዲያደርገው አደረጉ። ህወሃት ባልደረሰበት ቅኔው ጎጃም ጦርነት አውጀው ያልመነጠሩት ዕውነት ዬለም። ሽዋ፤ መተከል፤ ወለጋ ደቡብ የጫካው ኦነጋቸው ይመነጥራል። አዲስ አበባ እራሳቸው ኦፕሬሽን ሰርተው ይመነጥሩታል። በእስር፤ በመሰወር፤ በማገት፤ ከሥራ በማፈናቀል፤ በዲሞሽን።
12) የለውጡ ውጤት ዬሰናፍጭ ታክል ለአማራ ህዝብ ዬፈዬደው ዬለም። ከውጪ ሄዶ የተሾመ እንዲኖር ዬተፈቀደለት፤ በግብረ ሰናይ ድርጅቶች ዶላር ዬሚዘባነን ዬአማራ ልጅ ዬለም። ማህበረ ገዳ ግን ተፍነሸነሹበት። ባይገርማችሁ ቢኦኤ፤ ዶቼቬሌም፤ ዬወረራው ጠበለ ጣዲቀኛ ናቸው። ቪኦኤ ላይ በኦሮምኛም ይሠራሉ፤ በአማርኛም። ዳብል ማክዳ። አወቁበት። ለዚህ ነው ኮንቬንሽናል ሴንተር ተገኝተህ ብራቦ እንድትል ዬተጋበዝከው። ለዝልኝ መንፈስ ሁሉ መንገዱን ጨርቅ ያድርግለት።
13) ደም ከፍለህ ያመጣኽው "የወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ" ሌላ ያደም ጥሪ ተደግሶልህ። ሁለመናህን ገብረህ፤ ቅራቅር ላይ ተዋድቀህ ከህወሃትጋር፤ ማይካድራን ጭናን፤ ሙሉ ወሎን፤ ከፊል ስሜን እና ደቡብ ጎንደርን ገብረህ፤ ሁሉን አጥተህ አሁን ደግሞ ለአዲስ የደም ሙሽራ ግብዣ ለድርድር ሳትበቃ እንደ ማበሻ ጨርቅ ስትወረወር #ግጥግጤ ነው ብለህ ሆ ብለህ ኮንቤንሽናል ሴንተር ተገኝተህ ድሪና ድኮት ሁንለት ለቀውሰኛው የኦነግ ሥርዕወ መንግሥት። ኪሳራ¡ ሠርግ እና መልስህ ከሆነ ዘንዳ ……ውርዴት መባህ ከሆነ……
13) ዬቅድስት ተዋህዶ ልጆችም በመረገጣችን፤ በመጨፍለቃችን፤ በመንገዋለላችን፤ ሰማዕታት ስለተገበሩልን፤ ቅድስት ዓውደ ምህረታችን ስለተደፈረች፤ ጉባኤ አዲስ አበባ ላይ አታደርጉም፤ ስለመስቀሉም አትሮጡም በመባላችን፤ ንዋዬ ቅድሳት ስለነደዱልን፤ አትቀበሩም ስለመባላችን፤ ገዳማትን ስለረገጡልን አመስግኖ ለገዳወኦዳ ተንበርክኮ ሰግዶ በኮንቤንሽን ሴንተር ተገኝቶ መደርመሳችን ማፅደቅ ነዋ¡¡¡¡
14) ዬመስቃ ኩትኩት በዓይነት ኮምኩመሃል፤ ዬት እንደነበሩ የማይታወቁ ሁሉ በዬሚዲያው እዬወጡ ሲፎገሉ አያለሁኝ፤ እራሳቸው ላፈሰሱት መገበር አልሻም እንጂ አንዲን ቀንጣ ዬሚር መሥሪያ ቤት ተጠሞናችሁ ተብሎ ይደለቃል። ኧረ አለቆቻችሁ እነ ማህበረ ሌንጮ የ30 ሳንቲም ፌስታል ይዘው ሲንከራተቱ ለአውሮፓ ህብረት ፕሮቶኮል ማን እንደ አበቃ ይታወቃል። ዕውነት ነውና። ለምን በህወሃት ላይ ፊት ተዞረ ሥራ ተሠርቶ ነው። የአማራ ልጆች ልባም ተግባር ከውነን ነበር ፍንቅልቅሉን ያወጣነው።
ይህም ሆኖ አያፍሬ "ዬኢትዮጵያ ችግር ሳይፈታ የሚፈታ የሠፈር ችግር ዬለም" ሲሉ አሽሙርልከውልናል። አንደፍድፎ እስራኤል ምን ወሰዳችሁ? አንደፍድፎ የአውሮፓ ህብረትን ምን አስጋበዛችሁ? በምን አጣብቂኝ ምክንያት። የሠራነውን እናውቀዋለን። ዬሆኖ ሆኖ ለሲዳም እራስ ገዝነት፤ ለምዕራብ ኢትዮጵያ ምስረታ ይህ ጥያቄ አልቀረበም። ለአንተ ነው ጅል፤ ጅላጅል ጅልአንፎ ላለህ አጃቢነት ቅርሻ ነው። አትንተከተክም ምርኮኛ ……… ስለሆንክ።
ዲሲ ሆይ ትናንት አልይህ አልስማህ ያልካቸው አቶ ሬድዋን ሁሴንም ተገኝተውልኃል። ሂደቱንሪከርድ አድርጌው ነበር። በዛው በዘለበ ጃኬት ትርትሩን ብአዴን ለሻጋታው ጨረታ መሰለፍ ነዋ ………
10000000000000 ፈተና ይጠብቅኃል በዘመነ ገዳወኦዳ። ጠብቀው።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
15/12/2022
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ