ልጥፎች

(ለመንግስትና ለብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች)

ከአቶ ጀንበሩ አረጋ ፔጅ ነው ያገኜሁት። አላነበብኩትም። እንዳያመልጠኝ ነው ፖስት ያደረግኩት። ይድረስ ለመሪዎቻችን !! (ለመንግስትና ለብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች) ስለአገሬ ሰላምና ደህንነት አሁንም እጮሀለሁ !! በጀምበሩ አረጋ (ረ/ፕሮፌሰር) ጎንደር ዩኒቨርስቲ ስነ-ትምህርት ኮሌጅ ሀ) ታሳቢዎች (Assumptions) አገሬ ኢትዮጵያ አሁን ከገጠማት ውስጣዊ ፈተና በፍጥነት ትወጣ ዘንድ ይህንን የአጭር ጊዜ የመፍትሔ ሀሳብ በራሴ ተነሳሽነት ሳቀርብ የሚከተሉትን ጉዳዮች ታሳቢ አድርጌ ነው፡፡  የአገሬና ሕዝቧ ሰላምና ደህንነት እንደሚያስጨንቀው አንድ ተራ ዜጋ ለሰላምና ደህንነት መረጋገጥ ያለኝን ከመወርወርና ከቅንንነት በስተቀር ምንም አይነት ሌላ ፖለቲካል ፍላጎት (Other Political Interest) የሌለኝ መሆኑን ትረዱኛላችሁ በሚል  የመንግስትና የገዢው ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ከተስተካከለ የአገራችን ችግር በወሳኝ መልኩ መፍታት እንችላለን የሚል ጠንካራ ዕምነት ስላለኝ  ከመንግስትና ከገዢው ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች መካከልየችግሩ አሳሳቢነት የሚያስጨንቃቸው አንዳንድ አመራሮች ይኖራሉና ለመፍትሔውም ይተጋሉ የሚል ግምት ስላለኝ  ከታሪካችን እንደምንረዳው መላ የአገራችን ሕዝብ መንግስት የሚለውን በቀላሉ የሚያምንና በጠንካራ መንግስት አስፋላጊነት የሚያምን እንደሆነ ስለምረዳ  መሰሪ ፖለቲከኞቻችን በየመድረኩ እንደሚያስጮሁት የጨቋኝ-ተጨቋኝ ትርክት ሳይሆን አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ አብሮነትን የሚፈልግ ነው የሚል ጠንካራ እምነት ስላለኝ ነው፡: ለሕዝብ እብሮነትና የጋራ ተጠቃሚነት የሚተጉ ቅንና ቆራጥ መሪዎችን ወደፊት ካመጣናቸው የሕዝቧ ሰላምና ደህንነት የተረጋገጠማት ውጫዊ ጠላቶቻችን በርቀት የሚያከብሯትና በቀላሉ የማትደፈር ጠንካራ ኢትዮጵያን በ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽኑ መንግሥት በተደጋጋሚ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ለሚፈጸምበት የኦሮሚያ ክልል ትኩረት እንዲሰጥም ጠይቋል በኦሮሚያ ክልል የዜጎች ደህንነት የከፋ ደረጃ ላይ መድረሱን ኢሰመኮ ገለጸ።

  ·        የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽኑ መንግሥት በተደጋጋሚ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ለሚፈጸምበት የኦሮሚያ ክልል ትኩረት እንዲሰጥም ጠይቋል በኦሮሚያ ክልል የዜጎች ደህንነት የከፋ ደረጃ ላይ መድረሱን ኢሰመኮ ገለጸ። ·        የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ( ኢሰመኮ ) በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ወለጋ ዞን ጎቡ ሰዮ ወረዳ አኖ ከተማ በሚኖሩ ተፈናቃዮች ላይ አሰቃቂ ግድያ መፈጸሙን አስታውቋል። ·        ኮሚሽኑ በጥር 25 ቀን 2015 ዓ . ም የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ኢላማ በማድረግ በተፈጸመ ጥቃት በሰው ሕይወት፣ አካል እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን በምርመራዬ አረጋግጫለሁ ብሏል። ·        በተጠቀሰው ዕለት ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በርካታ ቁጥር ያላቸው የወታደር ልብስ የለበሱ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ( በተለምዶ ኦነግ ሸኔ ) መሆናቸው በነዋሪዎች የተገለጹ ታጣቂዎች በሦስት አቅጣጫ ወደ አኖ ከተማ ገብተው በሲቪል ሰዎች ላይ ግድያና የአካል ጉዳት፣ የንብረት ዘረፋ እና ውድመት አድርሰዋል ነው ያለው ኮሚሽኑ በመግለጫው።   ·        በጥቃቱ ዋና ኢላማ የተደረጉት ከጎቡ ሰዮ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች ተፈናቅለው በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች የተጠለሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መሆናቸውንም ኢሰመኮ በምርመራው ማረጋገጡን ገልጿል። ·        በከተማዋ ውስጥ ከ 2014 ዓ . ም . ጀምሮ በአካባቢው በተከሰቱ ግጭቶች ምክንያት ከ 13 ቀበሌዎች ተፈናቅለው በአኖ ከተማ በመጠለያ ውስጥ እ