ልጥፎች

የኤርትራን ልኡካን ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ተቀበሏቸው።

ምስል
የቤተሰባዊው የመንትዮሹ  ዕሴት በምን እና  በምን ቀልመው ባጁ? ልግመኛው ጥላቻ  ዛሬ ተቀጣ! ከሥርጉተ © ሥላሴ። 26.2018  (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ) „ምህረትና እውነት ከ አንተ አይራቁ፣ በአንገትህ      እሰራቸው፤  በልብህ ጽላት እሰራቸው።“     (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፫) የሰው ልጅ ላካ ከማያውቀውም ስሜት ጋር ነው አብሮ የሚኖረው ማለት ነውን? ከእኔ ቁጥጥር ውጭ ከሆነ ስሜት ጋር መኖሬን ዛሬ አረጋገጥኩኝ። በፍጹም ሁኔታ ፈጽሞም ያልጠበቅኩት ነገር ነው አሁን የገጠመኝ። የኔወቹ ግን ልታምኑኝ ትፈቅዳለችሁን? እባካችሁ እመኑኝ። ዛሬ የኤርትራ የልዑክ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በፍጹም ሁኔታ ጭራሽም ያልጠበቅኩት ነገር ነው የገጠመኝ። እያዬሁኝ ከእኔ ቁጥጥር ውጬ በሆነ ሁኔታ የገፄ መስኮቶች ለካናስ ዝናቡን ከፈቃዴ ውጪ ለቀውታል። ምን ነካኝ ብዬ ራሴን እስክታዘብ ድረስ። ለካንስ እንዲህ እኛ ሳናውቀው ውስጣችን የተጎዳበት መለዬትን ያለመፍቀድ ሰቆቃ ነበረብን። ለካንስ ይህን ያህል ውስጤ አዝኗል። ዘጋቢው 18 ዓመት ይላል ዘመን አይለካውም፤ በመሃል የነበረውን የታሪክ ስንጥቅጥ። ግን ለምን ሆነ? እኮ ስለምን? ለዚህ መራር የሀዘን ስሜት ፈቀደንለት? ክፉነት ግን እንዴት ክፉ ነው። ክፉነት እሱ ከፍቶበት እኛንም አስከፋን። እኛንም ክፉነቱን ለክፉነት አዋረሰን። ወንድሞቻችን የገበርንበት የመከራ ዘመን ይህን መሰል የውስጥ እረመጥ ተሸክመን እንድንኖር ተገደድንበት። መለዬት ለካንስ ሰው ከሰው ብቻ ሳይሆን የአገር ሆኖ ሲሆን ደግሞ እንዲህ ግዙፍ ነው። እንደ ገና ደግሞ በምልሰት መለዬት በቃኝ ብሎ ወደ እኛ ሲመጣ የሚሰማው ስሜት ምን ይግለጸው? ለካ ሥርጉተ // ሥርጉተን ሳታውቃት ነው አብረ

ዜሮም እያለፈለት ነው ...

ዜሮም እያለፈለት ነው በአላዛሯ ኢትዮጵያ።  ከሥርጉተ   ሥላሴ  10.12.2014 / ሲወዘርላንድ  –  ዙሪክ / „እግዚአብሄርም የቀደመ ወገኖች የቃዬንን ልጆች፤ ስለ ኃጢአታቸው በጥፋት ው ባኃጣፋቸው ጊዜ ምድርን በማዬ አይህ አጠመቃት፤ ከቃዬል ልጆችም ኃጢያት ሁሉ አነፃት።“ (መጽሐፈ መቀብያን ምእራፍ  ፲፬ ቁጥር ፩)   ·         እፍታ። የኔዎቹ ቅኖቹ ይህ ጹሑፍ ቅኑ ዘሃበሻ ልጥፎልኝ የነበረ ነው በ10.12.2104። ልብ ላለው ህሊና ለላው ዛሬ አለዛሯ ኢትዮጵያ ያላችበት ሁኔታ ከቃዬል ልጆችም ሃጢያት ሁሉ ነፃ ለመሆን ተጋድሎ እያደረገች ያለችበ ጊዜ ነው። አንድ የአገር መሪ በዬሄደበት ቦታ ሁሉ እንደ አረኖ በትር ለምልም የሆነ የወገን የምሥራች ይዞ የሚመለስበት፤ ስደተኛ እስረኛ ህሊናዎቹን አስፈትቶ እንደ እናት እቅፍ አድርጎ ሰብስቦ፤ የታመሙትን ተመጓቶ ከነካሳቸው በክብር ተቀበሎ፤ ወደ መሬታቸው በግርማ አስገብቶ፤ ከተመለሱም በሆዋላ ሄዶ ጠይቆ፤ የተጎዱትን በዬሆስፒታሉ ተንከራቶ ጠይቆ፤ ሰዎች በጎ እንዲያስቡ፤ ሃላፈነት እንዲሰማቸው፤ ወገኖቻቸውን ሄደው የተከፉትን እንዲያዩ፤ እንዲያጽናኑ የሚያደርግ። የተማሙትን ደውሎ የሚያጽናን፤  አይዞህን የማይሰስት፤  ደሙን የሚለግስ፤ የሟች ሰምዕትን ቤተሰብን ስልክ ደውሎ የሚያጽናና፤ ስጋቶችን የጎረቤት አገሮችን በፍቅር ቀርቦ  ፍርሃትን የሚመነጥር የፍቅር ጌታ፤ የመሆን ልኡል፤ የፈርሃ እግዚአብሄር እጬጌ፤ የ አላዛሯ ኢትዮጵያ የንስሃ አባት። ግን እሱን ለመቀበል ዳገት ነበር ዳጥ፤ ተው እያልን እንኳን አድማጭ አልነበረነም። አሁን እሱን ለማሳጣት እሱን አካሉን ለማጉደል በአደባባይ እንዲህ ሞት ሲታወጅበት እንዴት ህሊናችን እንቅልፍ አግኝቶ ልንተኛ እንደምንችል ሁሉ ሳስበው የተከረመው ክ