የኤርትራን ልኡካን ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ተቀበሏቸው።

የቤተሰባዊው የመንትዮሹ 
ዕሴት በምን እና 
በምን ቀልመው ባጁ?
ልግመኛው ጥላቻ 
ዛሬ ተቀጣ!

ከሥርጉተ©ሥላሴ። 26.2018 
(ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ)
„ምህረትና እውነት ከ አንተ አይራቁ፣ በአንገትህ 
    እሰራቸው፤ በልብህ ጽላት እሰራቸው።“ 
   (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፫)



የሰው ልጅ ላካ ከማያውቀውም ስሜት ጋር ነው አብሮ የሚኖረው ማለት ነውን? ከእኔ ቁጥጥር ውጭ ከሆነ ስሜት ጋር መኖሬን ዛሬ አረጋገጥኩኝ። በፍጹም ሁኔታ ፈጽሞም ያልጠበቅኩት ነገር ነው አሁን የገጠመኝ።

የኔወቹ ግን ልታምኑኝ ትፈቅዳለችሁን? እባካችሁ እመኑኝ። ዛሬ የኤርትራ የልዑክ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በፍጹም ሁኔታ ጭራሽም ያልጠበቅኩት ነገር ነው የገጠመኝ። እያዬሁኝ ከእኔ ቁጥጥር ውጬ በሆነ ሁኔታ የገፄ መስኮቶች ለካናስ ዝናቡን ከፈቃዴ ውጪ ለቀውታል። ምን ነካኝ ብዬ ራሴን እስክታዘብ ድረስ።

ለካንስ እንዲህ እኛ ሳናውቀው ውስጣችን የተጎዳበት መለዬትን ያለመፍቀድ ሰቆቃ ነበረብን። ለካንስ ይህን ያህል ውስጤ አዝኗል። ዘጋቢው 18 ዓመት ይላል ዘመን አይለካውም፤ በመሃል የነበረውን የታሪክ ስንጥቅጥ። ግን ለምን ሆነ? እኮ ስለምን? ለዚህ መራር የሀዘን ስሜት ፈቀደንለት?

ክፉነት ግን እንዴት ክፉ ነው። ክፉነት እሱ ከፍቶበት እኛንም አስከፋን። እኛንም ክፉነቱን ለክፉነት አዋረሰን። ወንድሞቻችን የገበርንበት የመከራ ዘመን ይህን መሰል የውስጥ እረመጥ ተሸክመን እንድንኖር ተገደድንበት። መለዬት ለካንስ ሰው ከሰው ብቻ ሳይሆን የአገር ሆኖ ሲሆን ደግሞ እንዲህ ግዙፍ ነው። እንደ ገና ደግሞ በምልሰት መለዬት በቃኝ ብሎ ወደ እኛ ሲመጣ የሚሰማው ስሜት ምን ይግለጸው? ለካ ሥርጉተ // ሥርጉተን ሳታውቃት ነው አብረው የኖሩት? እስተዚህ ድረስ ወስጤ ያመረቀዘ መከራት ነበረበትን? ዋ! መለዬት ምንኛ ጨካኝ ነህ? ዋ! መገናኘት ደግሞ ምንኛ ሩህሩህ ነህ?

ዘጋቢው „ቁርሾ ትተው“ ይላል፤ በዚህ ዘመን ቁርሾ ለሳጥናኤለዊ መናፍስት ይሁንላቸው። ለማህበረ ዳራጎን ይሸሉሙ። አሁንም በዛው ላይ ለሚዳክሩት፤ ላልታደሉት ክፉዎች።

አንድ ሰው ከወገብ በላይ ከወገብ በታች ተለያይቶ ሰው መሆን ይችላልን? ብቻ እኔ አንዲህ እሁናለሁኝ ብዬ በፍጽም አላሰብኩትም ነበር። እኔስ ለቀጣይነቱ ምንም አልጠራጠረም። ስለምን? ሁሉም የሆነው በፈጣሪ ጥበብ ሰለሆነ። በሰው ሰውኛማ ይህን ያህል ውስጣችን እስዛሬዋ ዕለት ድረስ ስለመጎዳቱ እንኳን አላወቅነውም ነበር።

ሰውኛው ተፈጥሮኛው ጉዳይ ተከድቶ የሆነውን ሁሉ በዕድሚያችን አስተናገድን። ታሪክ ለእውቀት ጥሩ ነው ግን ታሪክ ተፈጥሮን ከሁለት ለመግመስ፤ ለመሰንጠቅ ከሆነ ዕብንነት ነው።

ቁስ አምላኪዎች ስለተሆነ እንጂ በላጩ ነገር መንፈስ ነው። ዛሬ የተሰማኝ መንፈሳዊ ሁኔታ ሥም የለሽ ነው። እኔ እራሴ ይህን ያህል በዚህ ጉዳይ እንዲህ እሆናለሁኝ ብዬ አንድም ቀን አስቤው አላውቅም። ምን አልባት ስደት ላይ ስለሆንኩኝ ይሆን? አላውቅም። 

ብቻ ዛሬ ሥርጉተን ፈተና ገጥሟታል። ሥርጉትሻ ጠንካራ ነበረች። ዛሬ ግን ተረታች። ዋጥ አድርጋ የመያዝ አቅሟ ሙሉ ነበር። ዛሬ ግን አልሆነም። እንደ እኔ የሆኑም ዜጎች ሊኖሩ ይችላሉ።

አቀባበሉ ከተጎዳው መንፈስ ጋር ሳዳምረው የሚክስ ነበር። ጉዳቱ ታምቆ፤ ተከድኖ የተያዘ፤ ግን በእልህ እና በቁጭት ማህል የተኖረ። ግን ዕውነታዊ የቤተሰብ ፍቅራዊ ዕሴት ለምን ቀን ጎደለው ብሎ ጥልቅ በሆነ ሀዘን ጥቁርን ተላብሶ የባጀበት መንፈስ ነበር ተሸክመን የኖርነው።

ላይ ላዩን ሳይሆን ዛሬ በዚህች ቅጽበት እኔን በተሰማኝ ስሜት ለመተርጎም እውነት ለመናገር አቅም አነሰኝ።

  • መንትዮሹ!

Ethiopia: የኤርትራን ልኡካን / አብይ በደማቁ ሲቀበሏቸው

·       የባድመ ዕይታ በሥርጉተ ዕይታ።


ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
እጬጌው የመኖር ነፍስ ፍቅር ሆይ እስኪ እንዲህ ይመርብህ፤ ሙሴ፤  የአሮን በትር በመዳፍህ አለ፤ ለምልም፤ ብቅል፤ ጽደቅ፤ አፈራ!
ፈጣሪ ሆይ! ይህን መልካምነት ፍቅር ለፈቀዱ ሁሉ ብለው ይቀበሉት ዘንድ ልቦናቸውን ወደ ፍቅር ጎዳና አቃና!“አሜን!“
ሙሴ አሜኑም ይቅናህ! ኑርልንም!

የኔዎቹ ደጎቹ እና መልካሞቹ የአገሬ ናፍቆቶች ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።