የቤተ ሲዖሎች ገመና!

የቤተ ሲዖሎች ገመና!
ከሥርጉተ ሥላሴ 26.06.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ)
„ጥበብ ክርስት ጋር መልካም ነው፤ ፀሐይንም ሊሚዩ ሰዎች ትርፍ ይሰጣል“
            (መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፯ ቁጥር ፲፩ ቁጥር)



  • ·        መነሻ።

የቃሊቲ ሴት እስረኞች ለዶር አብይ መልእክ አስተላለፉ

  • ·       ፍጥረት እሾኽዎች።

ምን ሊባሉ እንደሚቻሉ አይታወቀም? ይሄ ናቸው ብሎ ለመናገርም አይቻለም። ህፃናትም አብረው ከወላጆቻቸው ጋር ታስራወል። ድንግል ማርያምም አብራቸው ታስራለች። አድህኖ ስዕሏን ማዬት ይቻላል። ቤተ ሲኦሎች እንዲህ ናቸው። ከሰው ስለመፈጣራቸው፤ እንደ ሰው ስለማሰባቸው ሰው ነኝ ለማለት መድፈራቸው እራሱ ይግርማል፤


በአንድ ወቅት የአማሪካ ራዲዮ ዋና ዘጋቢ ልዕልት ጽዮን ግርማ ሴት እስረኞችን እነ አርበኛ ጫልቲሻ እና ንግሥት ይርጋ ከቃሊት ከእሥር እንደ ተለቀቁ ቃለ ምልልስ ስታደርግ ስቃዩን፤ መከራውን፤ ፍዳውን፤ ሰቆቃውን ሲገልጹላት በጥርጣሬ ነበር ስትመለከተው የነበረው፤ ዛሬ አቻዋ ጋዜጠኛ መቼስ ሰላም ካሳደሩት ይገርመኛል እዛው እቦታ ሄዶ ያለውን ሁኔታ ሲዘገብ ነበር …

የዛ አካባቢ ተወላጆች መቼም መሬት ተክፈታ ብትውጣቸው ይሻላቸዋል። የሚገለማ የሚከረፋ ድርጊትን እንደ ክብር ጀብጅብው ስለመያዛቸው መሬት ተከፍተሽ ዋጪኝ ማለት ነበረባቸው ነገር ግን በዬቦታው የሚታዬው ደረትን ገልብጦ ማጣጣል እና ማናናቅ ስለነገ መራራነት እለታያቸውም … ይህ ሁሉ የተከፋ መንፈስ እኮ ፍንጅ መሆኑን ልብ ሊሉት አልተቻላቸውም። መሬት እዬከዳቻቸው ስለመሆኑ እንኳን ሊያገናዝቡት አልተቻላቸውም …

እነኝህ ሲኦሎች በምን ሁኔታ የኢትዮጵያን መከራ ሲመገቡ፤ በኢትዮጵያ ዕንባ ሲዘፍኑ፤ በኢትዮጵያ ሰቆቃ ሲሳለቁ እንደነበሩ ይሄው ምስክሩ። ግን አሁን ይህ ሁሉ መከራ ነገ እንዲያው ነገረ ልጅ ሊያወጣ ይችል ይሆን? እንዲያው ቀኑም ሌቱም ኢትዮጵያ ላይ ወጥ የሆነ የጨለማ ወቅት አለመሆኑ የፈጣሪ ቸርነት ነው።

አሁን ይሄን ምን ይሉታል? ማን እንበለው? ይህ እንግዲህ በአደባባይ በሚታወቀው እስር ቤት ነው ከነክንፈ ማስልጠኛ፤ ከነ ባዶ 6፤ በዬቤቱ ባላው እስር ቤትማ ምን ዓይነት የሰው ልጅ ማሰቃያ ሁኔታ እንደ ተፈጸመ ህሊና ይዳኛው። ይሄ ሁሉ ገመናቸው ተይዞ ደግሞ እኮ የበለዳችሁትም፤ ደም የጠጣችሁትም፤ የዘረፋችሁትም፤ ዘመንን መርሳት ባይቻልም ስለፍቅር ስቢባል ይቅርታ እናድርግላችሁ ሲባሉ ነው ደግሞ ስውሩ መንግሥት አዲስ አባባ ላይ ሞት ጠምዶ ድጋሚ ደም ለማፈስስ ነበር የተጋው።




ሥውሩ መንግሥት ይፋዊ መንግሥትን ውጊያ እኮ ነው የገጠመው። አሁን እኮ ጦርንቱ የስውሩ መንግሥት እና የይፋዊ መንግሥት ጦርነት ነው መሃል አዲስ አባባ ላይ የተካሄደው፤፡ ይህን እንዲቀጥል ነው ዶር አብይ አህመድን ማይክ የያዘ፤ ብእር የጨበጠ ሁሉ ሲቀጠቅጥ የከረመው። ሲያወግዝ የባጀው። ጥርጣሬ ሰፍኖ ለውጡ ድጋፍ እንዳያገኝ ሌት ተቀን ሲተጋ የተኖረው …

ገመናችን ከገመና በላይ ነው። ይህንስ ከቶ ማን እንበለው በ አዲሱ ለውጥ ላይ ሲወናጨፍ የከረመውን ሁሉ። ወያኔ ሃርነት ትግራይስ ሰውሩ መንግሥት እንበለው ደግነትን፤ ፍቅርን፤ ርህርህና፤ ቸርንትን፤ ምህረትን፤ ፍቅርን ሲዋጋ የባጀውንስ ማን ይባል? ግራጫው መንግሥት ከቶ ብለን እንጥራውን?

አላዛሯ ኢትዮጵያ በግራ ቀኝ እሾኽ እንሆ 43 ዓመት ሙሉ ታመሰች፤ መቅኖ አጣች፤ ተበላች፤ ተጋጣች፤ ተበጠበጠች፤ አሁን ያ አደጋ ለዚያ ብቻ መስቀል አደበባይ ለተገኘው ብቻ የተቃጣ የነበር የሚለስለው ይኖራል። 

አዲስ አባባ ቀጠናን እሳት ለኩሶ ሌላ የተደባለቀ መንግሥት አልባ የሚያደርግ የመፈንቅለ መንግሥት ሂደት ነበር። ሙሴውን ከነካቢኔው ከዛው ላይ አመድ አድርጎ ተሰላፊውን በመፈንጅ ቀቅሎ የሚሊዮንች ሬሳን መስቀል አደባባይ መናህሪያው እንዲሆን፤ የሚሊዮኖች አካል ጉዳተኝነት አዲስ አባባ ላይ ፈጥሮ አደስ አባባ ላይ ልጄን ትዳሬን እያለ የሚወጣውን ሁሉ እርምት አድርጎ አመድ እና ለቅሶ ለማፈስ የተቃጣ ነው።

በዛ ቀውጢ ወቅት ቢቀጥል አዲስ አባባ አንድም ቤት፤ አንድም ሰው መትረፍ አይችልም ነበር። አንድም የማለድርጅት ንብርት አይተርፍም ነበር። ሞት ያለ የነበረ ወደፊትም ሊኖር የሚችል ነው። ታስቦ የነበረው ግን አዲስ አበባን የማፍለስ አደጋ ነበር።

ዘራፊዎች ሁሉ ተደራጅተው ጠብቃዋል ብዬ አስባለሁኝ። በውስጥ ለውስጥ ትእዛዝ በተጠንቀቅ የ እጅ መሳሪያ የታጠቁ ሆሉ እንደነበሩ ይሰማኛል። መመሪያ የተሰጣቸው በቀጥታ በህዝብ ላይ ሊያነጣጥሩ ያሰቡ እኩዮች እንደነበሩ ይሰማኛል። ለዚህ ነበር እኔ የድጋፍ ሰልፉ የሰከነ እርምጃም አይደለም፤ በቂ ዝግጅትም የለውም፤ ወቅታዊም አይደለም፤ አደብ የጎደለው ነው የድግፉን ሰልፍ ድባብ በማህብራዊ ሚሲያ የወል ዕድምታ፤ በሚዲያ የወል ድምቀት ብናከብረው ይሻላል ብዬ አሳስቤ የነበርኩት።



ቅንጅት አዲስ አባባን ተረከቦ ቢሆን ኖሮ የአዲስ አባባን ጥበቃ ክፍት አድርጎ ይህን መሰል የምጥ አድማ ታድሞ ነበር ብዬ አስባለሁኝ። ቅዳሜ የሆነው ከታሳበው እፍታው ቅንጣቢው ነው … ስላለፈ ብቻ ነው እንጂ የታሰበው እቅድ ሰፊ ነበር። አሁንም ቀጣይ ነው … አዲስ አባባ መከራዋ አለላቀም። በዝምታ ውስጥ አገር እንዲረጋጋ እዮባዊነት በ እጅጉ ያስፍለጋል። የቆጡን አውርድ ብላ የብብቷን ጣለች እንዳይሆን፤ በብዕር ሲአውግዝ የነበረው መንፈስ ነው ተገልብጦ የድጋፍ ሰልፍ አስተባባሪ የሆነው … መጀመሪያ ራሰን መግራት ይቅደም …

እስቲ ይታሰብ አውሬ እና ሰው እኮ ነው 27 ዓምት አብረው መንደር መሥርተው የተቀመጡት። ይህ አውሬ መቼውንም ይሁን መቼም ለጥፋታዊ ተልዕኮ ያርፋል ብሎ ማሰብ ከጅልንት በላይ ነው።


አሁን ጉዳቱ የ100ዎች ስለሆነ ነው እንጂ እቅዱ እኮ አዲስ አባባ ለእኛ ካልሆነች ትንድደድ ነበር ዓላማው። ወደፊትም የሚሆነው በአፋጣኝ ካልሆነ በዬጓዳው ያለው ፈንጅ የሚፈነዳው ከእንግዲህ ሌላ ቦታ ሳይሆን እምቁ የማህበረ ደራጎን ሴራ የሚፈነዳው አዲስ አባባ ላይ ነው። ስለዚህም መላ ይፈልግለት እንናላን ትቢያ ላይ ያለቸው ባለብራና ሥርጉትሻ።

እኔ እንደማድመጥው ስሜቴ አዲስ አባባ በዚህ መልክ በአጣቃላይ በወያኔ ሃርነት ቁጥጥር ስር እንድትወጣ እርምጃ እስካልተወሰሰደ ድረስ ፈንጁም ቦንቡም ቀጣይ ነው … ለማን ያዝናሉ እንዚህ፤ ለማንስ ግድ ይላቸዋል፤ አሁን ከዚህ ቃለ ምልልስ የሚያደርገው ሳጅን እስኪ እዩት ትክ ብላችሁ ደም ሲጠጣ መኖሩን ይክዳል፤ ልክ እንደ ጋዜጠኞቻቸው … ግን መሬት እሾኽን ስተባቅል ምን አለ እንብኝ አሻም ብትል።

ሌላው ቅዳሜው የሰኔ 16ቱ ጉዳይ በታቀደ ሁኔታ መፈናቀል መንግሥት ለማድረግ ታስቦ ነው የተከወነው።
በተጨማሪም ማካሄጃ ድልድዩ ደግሞ ደቡብ ላይ የነበረው ማፈናቀል ነው። ይህ እያለ ነው አዲስ አባባ ላይ የድጋፍ ስልፍ የተሰናዳው።

ተፈናቃዮችም ሰለባ ናቸው ለዚህ ለመፈንቅለ መንግሥቱ ሙከራ የመጀመሪያው ገፍት ቀማሾች ናቸው። ገዲዮ ዞን ያው ህዝብ በዚህ መልክ እግዚኦ ይላል።
ይህን ሁሉ መከራ ተሸከምን እኛ የሠርግ ቤት ሽርሽር ያምረናል፤ እኛ የሚዚ ልብስ መረጣ ያሻናል፤ እኛ በዚህኛው ሥማችን ላይ ይሄኛው ይታከልበት እንላላን ግን እኛ ምኖች ነን?

አቅማችን አጎልብተን ሁመናችን፤ መንፈሳችን በአውሬው ላይ አድርገን ተስፋን ያያዘውን እሸት መንፈስ ከመደገፍ ጓሮ ለጓሮ ያሰኘናል የራሳችን የመወደስ ክብር ያነሳናል ይጥለናል።

 … እነኝህ ህፃናት፤ እነኝህ ታዳጊዎች ወጣቶች እስር ቤትም እነሱው፤ በመፈናቀሉም እነሱ በክርመት ፈሰዋል ሜዳ ላይ ይብቃኝ …


አቤቱ አንተ ሁሉ ይቻልሃል እና የማህበረ ፈርንን ትልም ገስጽልን!

የኔወቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።