ዜሮም እያለፈለት ነው ...

ዜሮም እያለፈለት ነው በአላዛሯ ኢትዮጵያ። 

ከሥርጉተ ሥላሴ 10.12.2014 /ሲወዘርላንድ – ዙሪክ/
„እግዚአብሄርም የቀደመ ወገኖች የቃዬንን ልጆች፤ ስለ ኃጢአታቸው በጥፋት ው ባኃጣፋቸው ጊዜ ምድርን በማዬ አይህ አጠመቃት፤ ከቃዬል ልጆችም ኃጢያት ሁሉ አነፃት።“(መጽሐፈ መቀብያን ምእራፍ  ፲፬ ቁጥር ፩)  
  • ·       እፍታ።

የኔዎቹ ቅኖቹ ይህ ጹሑፍ ቅኑ ዘሃበሻ ልጥፎልኝ የነበረ ነው በ10.12.2104። ልብ ላለው ህሊና ለላው ዛሬ አለዛሯ ኢትዮጵያ ያላችበት ሁኔታ ከቃዬል ልጆችም ሃጢያት ሁሉ ነፃ ለመሆን ተጋድሎ እያደረገች ያለችበ ጊዜ ነው።
አንድ የአገር መሪ በዬሄደበት ቦታ ሁሉ እንደ አረኖ በትር ለምልም የሆነ የወገን የምሥራች ይዞ የሚመለስበት፤ ስደተኛ እስረኛ ህሊናዎቹን አስፈትቶ እንደ እናት እቅፍ አድርጎ ሰብስቦ፤ የታመሙትን ተመጓቶ ከነካሳቸው በክብር ተቀበሎ፤ ወደ መሬታቸው በግርማ አስገብቶ፤ ከተመለሱም በሆዋላ ሄዶ ጠይቆ፤ የተጎዱትን በዬሆስፒታሉ ተንከራቶ ጠይቆ፤ ሰዎች በጎ እንዲያስቡ፤ ሃላፈነት እንዲሰማቸው፤ ወገኖቻቸውን ሄደው የተከፉትን እንዲያዩ፤ እንዲያጽናኑ የሚያደርግ።
የተማሙትን ደውሎ የሚያጽናን፤ አይዞህን የማይሰስት፤ ደሙን የሚለግስ፤ የሟች ሰምዕትን ቤተሰብን ስልክ ደውሎ የሚያጽናና፤ ስጋቶችን የጎረቤት አገሮችን በፍቅር ቀርቦ ፍርሃትን የሚመነጥር የፍቅር ጌታ፤ የመሆን ልኡል፤ የፈርሃ እግዚአብሄር እጬጌ፤ የ አላዛሯ ኢትዮጵያ የንስሃ አባት።
ግን እሱን ለመቀበል ዳገት ነበር ዳጥ፤ ተው እያልን እንኳን አድማጭ አልነበረነም። አሁን እሱን ለማሳጣት እሱን አካሉን ለማጉደል በአደባባይ እንዲህ ሞት ሲታወጅበት እንዴት ህሊናችን እንቅልፍ አግኝቶ ልንተኛ እንደምንችል ሁሉ ሳስበው የተከረመው ክራሞት ይሰቀጥጠኛል።
ይሄ የዜሮ ዘመን እንዲመለስ ነበር ተተግቶ የተሠራው ለውጥ እንፈልጋለን በሚለው ሚዲያ እና ጸሐፊ ሁሉ። እከሌ ተከሌ ማለት አይቻልም። አድማው ድምፁ … ለማህበረ ፈርዖን፤ ለማህበረ ደራጎን፤ ለማህበረ ሄሮድስ ቀልብ በማቀበል የተጋው ሁሉ ዛሬ የአሜሪካው የስብዕዊነት ልዕልናን ከፍ የሚያደርገውን የጥቃት ሥልጡን እርምጃ ሲሳማ፤ ጠልፎ ለመጣል ሲማስን፤ ቋንጃ ለመስበር መንፈስን ለማወክ ሰልማን ሲያደፍርስ የነበረው ሁሉ፤ ያሴረው ሁሉ የመርዶ ቀኑ ነው። ፈጣሪ የቀባውን ማንም ምንም ሊያሰቆመው አይችልም። ይሄው አሜሪካ አብራ በአደባባይ ተሰለፈች። የአሜሪካ የምርመራ ቢሮ (ኤፍ ቢ አይ (FBI)ኢትዮጵያ ይገኛል። ኢትዮጵያዊው ኪንግ ማርቱን ሉተር ላይ የተቃጣ ስለመሆኑ ተረገጡን ለማረጋገጥ። ከዚህ በላይ የክብር ጉልላት የለም። ቅብዕ የፈጣሪ ነው ከንቱዎች ከንቱነት ቆም አድርገው ወደ ራሳቸው እንዲመለሱ ይመከራሉ፤ የሆነ ሆኖ ይህ ዓለምአቀፉ ህግ ዛሬ በአደባባይ ኢትዮጵያ ላይ ዕውን እዬሆነ ነው ባለቤት ሙሴ አግኝቷል፤ ስለሆነም ዜሮም አለፈለት …
  • ·      ትናንት የነበረው ዕይታዬ ይሄ ነበር… የተጨመረ የተቀነሰ የለውም። ከቃለ ወንጌል በስተቀር።

ዜሮን በሞራ፤ በሁሉም የወደቀ ዱለኛ። (ሥርጉተ ሥላሴ)


ዛሬ እንደ አውሮፓውያኑ ቋጣጠር ታህሳስ 10 ቀን 2014 ነው። ይህ ቀን በዓለምአቀፍ ደረጃ በአንባገነኖች ጫና ሥር የተሰዉ ሰምዕት በጸሎት የሚታሰቡበት፤ በህይወት እያሉ ሰብዕናቸው ለሚጠቀጠቅ ምልዕት አትኩሮት በአፅህኖት የሚሰጥበት ብሩክ ቀን ነው። እንዲሁም ዓመታዊ ክንውኖችና ምላሻቸው በተደሞ የሚቃኝበት – 1948 ቅዱስ መንፈስን የተካኑ 30 ሁለንትናዊ የኑሮ ቃለ ወንጌላት የተወለዱበት ማዕልት።

እኛም ኢትዮጵውያን በሰብዕዊ መብት ጭፍለቃ የሚታወቀው አንባገነኑ የወያኔ ማንፌስቶና ማስፈጸሚያ መሳሪያዎቹ ሁሉ በወገን፣ በሀገር፣ በዳር ደንበር፣ በሰንደቅ፣ በታሪክ፣ በዕምነት፣ በባህል፣ በፍቅር፣ በአብሮነት፣ በማንነት፣ በዜግነት፣ ዙሪያ ያደረሰውን፤ በማድረስ ላይ ያለውን ጭቆና ለማስወገድ ለትጋት እራሳችን የምናሰናዳበት ልዩ ቀን ነው። ገና በዋዜማው የታዳጊ ሃና ዘግናኝ ግፍና በደል፤ የሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ በወያኔ ሠራዊት መወረር፤ የዘጠኙ ፓርቲ የትብብር መርሃ ግብር ግብር ሁሉም በዱላና እስር የገጣማቸው ግፍ በአርምሞ ይታሰባሉ።

ስለዚህ ይህን ቀን እኛ የምናስታውሰው ቀደምት ሰማዕቶቻችን የእነአሰፋ ማሩ፤ ሺብሬ ደሳለኝ፤ ዶርእምሩ ሥዩም፤  ዬእኔ ሰው ገብሬ፣ የህጻን ነብዩ፤ ከዚህ ባለፈ በዬስደት ሀገሩ ክልትምትም ሲሉ ላለፉ፤ እኛ ሳናወቃቸው በመርዝ ለተጨረሱት፤ እስር ቤት በድርብ በቀል መዶሻ ለሚቀጠቀጡት ወገኖቻችን ሁሉ ልባችነን ክፍት አድርገን የመንፈሳችነን ዓይን አብርተን ጥላቻን – ጥላቻ እንዳይወልደው፤ በቀል – በቀልን እንዳይወልደው እራሳችነን  በንፁህ ልቦና እና መንፈስ ወደ አምላካችን ዕንባችን በመላክ ይሆናል – በቃችሁ እንዲለን።

ድጋሚ ስደት፣ ድጋሚ መከራ፣ ድጋሚ ሰቀቀን፣ ድጋሚ ሰጋትና መጠቃቃት ከምንጩ የሚደርቅበትን አዲስ ንጹህ መንፈስ በመውለድ፤ ሰብዕዊ ህግትን በሥራ ለመተርጎም ህሊናችን ስንዱ በማደረግ ሊሆንም ይገባል – የመስዋዕት ሰማዕታት ውለታ።

የወመኔው ወያኔ ህግጋት እናት ህጉ፤ ህገ መንግሥቱ በሞራ የተጠቀለለ ዜሮ ነው። ለአፈጻጸም የሚያሰናዳቸው መመሪያዎች ቢሆኑ በሞራ የተጠቀለሉ ዜሮዎች በመሆናቸው ሰብዕዊ ህጋዊ መብቶችን ገዳይ ናቸው። በእናት ሀገር ኢትዮጵያ ዓለም ዓቀፉ ህግ የተባባሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሀገሮች እንዲፈጽሙት የደነገጉት ድንጋጌዎች ቢሆን ሥራ ላይ ሊውሉ የማይችሉ በሞራ የተሸፈኑ የዜሮ ድምሮች ናቸው። ክብሪት ብቻውን ብርሃንን፤ ሻማ ብቻውን ብርሃን አይሰጡም። ስለሆነም ሁለንትናዊው ዓለም ዐቀፍ የህግ አንቀፃትና ወያኔ ፈተና ውስጥ ናቸው። ወያኔ ፈተናውን የማለፍ አቅም የለውም። ስለዚህ ውጤቱም ዜሮ ነው።

·         ፈተናውና ውጤቱ በጥቂቱ።
አንቀጽ 1.  የሰው ልጅ ሁሉ ሲወለድ ነጻና በክብርና በመብትም እኩልነት ያለው ነው። የተፈጥሮ ማስተዋልና ሕሊና ስላለው አንዱ ሌላውን በወንድማማችነት መንፈስ መመልከት ይገባዋል።“ የወያኔ ማንፌስቶ ህሊና ካለው አልተወለደም። አስተዳደሩም እንዲሁ። ወንድማማችነትን ፍቆ ጠብን፣ ጥላቻን የዘራና ያዘመረ፤ በቤተሰብ የቆዩ ትውፊቶች ሁሉ ቀራኒዎ ያወጀ ስለሆነ ኢትዮጵያ ላይ ውጤቱ —- ዜሮ ነው።

አንቀጽ 2 እያንዳንዱ ሰው የዘር የቀለም የጾታ የቋንቋ የሃይማኖት የፖለቲካ ወይም የሌላ ዓይነት አስተሳሰብ የብሔራዊ ወይም የኀብረተሰብ ታሪክ የሀብት የትውልድ ወይም የሌላ ደረጃ ልዩነት ሳይኖሩ በዚሁ ውሳኔ የተዘረዘሩት መብቶችንና ነጻነቶች ሁሉ እንዲከበሩለት ይገባል። ከዚህም በተቀረ አንድ ሰው ከሚኖርበት አገር ወይም ግዛት የፖለቲካ የአገዛዝ ወይም የኢንተርናሽናል አቋም የተነሳ አገሩ ነጻም ሆነ በሞግዚትነት አስተዳደር ወይም እራሱን ችሎ የማይተዳደር አገር ተወላጅ ቢሆንም በማንኛውም ዓይነት ገደብ ያለው አገዛዝ ሥር ቢሆንም ልዩነት አይፈጸምበትም።“ ይህ ደግ ድንጋጌ በጎሳ ምጥ ውስጥ ባለች ሀገር የማይታሰብ ነው፤ ብሄራዊነት ህምውጤቱ –  ዜሮ ነው።

አንቀጽ 3 „እያንዳንዱ ሰው የመኖር፣ በነጻነትና በሰላም የመኖሩ መጠበቅ መብት አለው።“ መላ አካላቷ በጠበንጃ በታገተ ሀገር የሚኖሩ ህዝቦች ሰላምና ነፃነት አልባ ናቸው። እንዲያውም ፈጣሪ አምላክ ትቶልን የሄደው የውስጡን ሰላም ሆኖ ሳለ፤ በወያኔ ግን ስቅላት የተበዬነበት የፈጣሪ ሥጦታም ጭምር ነው። ስለሆነም …. ውጤቱ —- ዜሮ፤

አንቀጽ 4 „ማንም ሰው ቢሆን በባርነት አይገዛም። ባርነትና የባሪያ ንግድም በማንኛውም ዓይነት ክልክል ነው።“ የወያኔ ማንፌስቶ ያቀፈው ምርጥ ዘር ገዢ ሌላው ደግሞ ተገዢ ባሪያ ነው። ከዚህ በተጨማሪ  ሰሞኑን እንደ ጀርመኑ ZDF ቴሌቪዢን ዶክመንተሪ ዘገባ  የዘመናዊ የሠራተኛ ባርነት በሲዊዲኑ አሰሪ ካንፓኒ H&M ኢትዮጵውያን የመጨረሻ ክፍያ የሚያገኙና ለዘመናዊ ባርነት የተጋለጡ ስለመሆናቸው ምስክርነቱን ሰጥቷል። እንዲያውም ለባርነት የተዳረጉት ዬንፁህን የጉልበት ብዝበዛ ወሸኔና ማለፊያ ብሎ ወያኔ የሸለማቸውን ሺክ አላሙዲን ጨምሮ  እስኪበቃው ድረስ ዘገበው ወርፏቸዋል። ሀገረ ሲዊድን የባሪያ ጭቆናን በአዋጅ ካስረች በኋላ በእስያና በአፍሪካ የምታደርገው የእጅ አዙር ዬባርነት አገዛዝንም ዘገባው እስኪበቃው ነበር የከተከተው። ድርብርብ ባርነት በዘረኝነት ፖሊሲ ኢትዮጵያ ላይ ዘውድ ጭኗልና። ስለዚህ ውጤቱ …. ዜሮ ነው፤
አንቀጽ 5 ማንም ሰው ቢሆን የጭካኔ ስቃይ እንዳይደርስበት ወይም ከሰብዓዊ አፈጻጸም ውጭ የሆነ የተዋረድ ተግባር ወይም ቅጣት አይፈጸምበትም።“ ሩቅ ሳይኬድ በተከበሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የተፈጸመው  – ሰባዕዊ ድርጊት በስተጀርባው ካለው የጣር ድምጽ፤ የወንድማችን ዬአቡበከር የእግር ብረት ቃለ ምልልስ ከበቂ በላይ ነው … ስለሆነም የዚህ ድንጋጌ ተፈፃሚነት – ዜሮ ነው ኢትዮጵያ ላይ።

አንቀጽ 6 እያንዳንዱ ሰው በሕግ ፊት በሰው ዘርነቱ የመታወቅ መብት አለው።“ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ሰው ለመታዬት ለጎሳ ማደግደግ ያስፈልጋል። ይለፍ ያለው ጎጥ፤ ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ የሰው ሰውነቱ የሚለካው በጎጡ ነው። ስለዚህ – ዜሮ ይሆናል ውጤቱ።

አንቀጽ 7 ሰው ሁሉ በሕግ ፊት እኩል ነው። ያለአንዳች ልዩነትም ሕጉ ደህንነቱን እንዲጠበቅለት እኩል የሆነ መብት አለው። ይህንን ውሳኔ በመጣስ ከሚደረግ ልዩነት ለማድረግ ከሚነሳሳ እንዲጠበቅ ሁሉም የእኩል መብት አለው።“ ይህ አንቀፅ በአራዊት ጫካዊ ተመክሮ ፈጽሞ ሊታሰብ የማይችል፤ በክትና በዘወትር ዜግነት አሳሩን የሚያይ ድንጋጌ ነው። ስለሆነ – ዜሮ ነው።

አንቀጽ 8 እያንዳንዱ ሰው በሕገ መንግስቱ ወይም በሕግ የተሰጡትን መሠረታዊ መብቶች ከሚጥሱ ድርጊቶች ከፍተኛ በሆኑ ብሔራዊ የፍርድ ባለስልጣኖች ፍጹም በሆነ መንገድ እንዲወገድለት መብት አለው።“ የትኛው ህገ መንግሥት ማባጨዬዋው። ህም። እያንዳንዱ የወያኔ ጀሌ ንጉሥ ነው። እሱ ያሰረውን ቢቀዬር – ቢሞት ሌላው አይፈታውም እንኳንስ ያደገውን አንቀጽ ተግባር ላይ ለመዋል ስለዚህ ያው – ዜሮ።

አንቀጽ 9 ማንም ሰው ያለፍርድ ተይዞ እንዲታሰር ወይም በግዛት እንዲኖር አይደረግም።“ ይህ ዕለታዊ የኢትዮጵያ ህዝብ የፍዳ ክምር ምን ሆነና? – በውንብድና ሀገር እያስተዳደር ባለው በጭፍኑ ወያኔ እርግጫ የተደረመሰ አንቀፅ ነው ስለዚህ ውጤቱ  –  ዜሮ፤

አንቀጽ 10 እያንዳንዱ ሰው በመብቶቹና በግዴታዎቹ አፈጻጸም እንዲሁም በሚከሰስበት ማንኛውም ዓይነት የወንጀል ክስ ነጻ በሆነና በማያዳላ የፍርድ ሸንጎ በትክክለኛና በይፋ ጉዳዩ እንዲሰማለት የሙሉ እኩልነት መብት አለው።“ ይህ ድንጋጌ ህግና መንግሥት ፍርድ ቤትና ዳኛ ላላቸው ሀገሮች እንጂ እንደ እኛ እረኛ አልባ፤ ባለቤት አልባ፤ ለሆነ ስላልሆነ … በህጉ ውስጥ መኖር አይደለም በአጠገቡም የወያኔ መንፈስ የለም ስለዚህ ያው —- ዜሮ።

አንቀጽ 11  „1/ በወንጀል ክስ የተከሰሰ ማንኛውም ሰው ለመከላከያው አስፈላጊዎች የሆኑትን ሁሉ አቅርቦ በሚከራከርበት የይፋ ፍርድ ቤት በሕግ መሠረት ወንጀለኛ መሆኑ እስቲረጋገጥበት ድረስ ከወንጀል ነጻ እንደሆነ የመቆጠር መብት አለው።“ ይህ ሊሆን ይችላልንእእ –  ኢትዮጵያ ላይ የህልም ሠርግ ነው ስለዚህ ውጤቱ — ዜሮ፤

„2/ ማንም ሰው በብሔራዊ ወይም በኢንተርናሽናል ሕግ አንድ ነገር ወንጀል ሆኖ ባልተደነገገበት ጊዜ በፈጸመው ወይም ባልፈጸመው ማንኛውም ሥራ ወንጀለኛ ሆኖ አይከሰስም። ወይም ወንጀሉ በተፈጸመበት ጊዜ ከተደነገገው ቅጣት ይበልጥ አይፈረድበትም።“ ወያኔ እኮ ወንጀል ነው የሚለውን ፈብርኮ እራሱ ቀርፆ፤ አስገድዶ አስፈርሞ እኮ ነው የነፃነት አርበኞቻችን ግዞት ውስጥ መንፈሳቸውን እያነደደ የሚገኘው — አፈጻጸሙ እራሱ ሰቅጣጭ፤ መቀጣጫ የሚያደርግ፤ ሰው መሆንን የሚፈትን ስለሆነ – ውጤቱ – ዜሮ፤

አንቀጽ 12 ማንም ሰው በግል ኑሮው በቤተሰቡ ውስጥ በቤቱ ወይም በሚጻጻፈው ደብዳቤ በፍርድ ያልተለየ ጣልቃ ገብነት ወይም ክብሩን የሚነካና ስሙን የሚያጎድፍ ተቃውሞ አይፈጸምበትም። እያንዳንዱ ሰው ከእንደዚህ ያለ ጣልቃ ገብነት ወይም የሚጎዳ ተግባር ሕግ እንዲከላከልለት መብት አለው።“ በዜጎች ታሪክ ላይ ስንት ድርድር ተውኔት ነው ወያኔ የሚሠራው? … ክብርን እንዴት ነው የሚጥሰውአይደለም ዜጋን ሀገርን እንደ ሀገር ማዬት የማይችል፤ በክብሯና በማንነቷ፤ በታሪኳና በሉዕላዊቷ ላይ በሚያላግጥ ብህዝቦቿ ሞራል ላይ ሞት የፈረደ ስለሆነ ከዚህ ድንጋጌ ጋር እንዴት ብሎ ወያኔ ሊወዳጅ ይችላል?! ስለሆነም – ዜሮ፤

አንቀጽ 13  1/ እያንዳንዱ ሰው በየብሔራዊ ወሰን ክልሉ የመዘዋወርና የመኖር ነጻነት መብት አለው።“ ይቻላልንአይቻልም። እንኳንስ ይሄ ከባዕቱ እትብቱ ከተቀበረበት እንኳን መቀመጥ አይፈቀድለትም። ስንቱ ነው መንፈሱ በጭቃኔ የታረሰው – በደሉ ረመጥ ነው። ግፉ ቋያ ነው። ስለዚህ የድንጋጌው ውጤት – ዜሮ፤

„2/ እያንዳንዱ ሰው ከማንኛውም አገር ሆነ ከራሱ አገር ወጥቶ እንደገና ወደ አገሩ የመመለስ መብት አለው።“ 24  ዓት ዜጎች ሀገራቸውን ለቀው እንዲወጣ የሚያደርግ ግዑዝ ይቻላልንይሆናልንደንበር እዬዘለለ፤ ደንበር እዬጠሳ ስንት ወገኖቻችን ነው ወያኔ የበላውበተሰደድንበት ሀገር እንኳን ሊያስቀምጡን አልቻሉም በሆድ የገዛቸው ደጋፊዎቹ …. እንኳንስ ሌላ። የተከበሩ ዬአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ታላቅ እህት ምን ነበር የተፈጸመባቸው?! …. ስለዚህ መንፈሱ በዘመነ ወያኔ እንዳአለ የታጠሰ አንቀጽ ነው። እናም — ዜሮ፤

አንቀጽ፡ 14 „1/ እያንዳንዱ ሰው ከጭቆና ሸሽቶ በሌሎች አገሮች ጥገኝነትን የመጠየቅና በደህና የመኖር መብት አለው።“ ወያኔ እያለ እንዴት ተብሎ? …. በበቀል በተነከረ የደም ጥማቱ፤ በመርዝ በተገኘው ነገር ሁሉ እያደነ ሰላም ይነሳል እንጂ … ኢትዮጵያ ያሉት ብቻ ሳይሆን ተሰደንም አልተኛልንም ወያኔ ስለዚህ ውጤቱ – ዜሮ

„2/ ፖለቲካዊ ካልሆኑ ወንጀሎች ወይም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ዓላማዎችን ከሚቃረኑ ሥራዎች የተነሳ በሚደርሱ ክሶች ምክንያት ከሆነ ይህ መብት ሊያገለግል አይችልም።“ ወይ ጉድ ኢትጵውያን እኮ ፈርሃ እግዚአብሄር ያለን ለህገ እግዚአብሄር ሆነ ለሰው ሰራሽ ህግጋት ትሁትና ቅን መንፈስ ያለን ሰላማዊ ዜጎች ነን። አብዛኞቻችን ኢትዮጵውያን በተሰደድነብት ሀገር ጸጥ ለጥ ብለን ነው የምንኖረው። ለጎረቤት፣ ለሥራ ባልደራባዎች ሁሉ የምንመች። ህግ የማይገዛው ሥራዓት የማያስተደድረው ወያኔና ማንፌስቶው ብቻ ናቸው።

አንቀጽ፡15  „1/ እያንዳንዱ ሰው የዜግነት መብት አለው።“ ዜግነት በኢትዮጵያ ከተሰረዘ 24 ዓመት ሆነው። ዜግነት ትግሬነት ሆኗል። ስለዚህ ኢትዮጵያዊ ዜግነት እራሱ „ጽንፈኛ ብሄርተኛ“ እዬተባለ በጎሰኛው ወያኔ የሞት ፍርድ የታወጀበት ነው። የዜግነት ክብር ግርማና ሞገስ ፈተና ላይ ናቸው። ዜግነት ታስሯል። ወያኔ እንደ ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሚፈራውም አንዳችም ነገር የለም። ስለዚህ ያለው ጡንቻ ሁሉ የሚያርፈው ከዜግነት ላይ ነው። ስለዚህ የአፈጻጻሙ ክብርና ሂደቱ  – ዜሮ ነው።

„2/ ማንም ሰው ያለፍርድ ዜግነቱ አይወሰድበትም ወይም ዜግነቱን የመለወጥ መብት አይነፈገውም።“ ህም ነው …. ድንጋጌውንና በደሉን ማጠጋጋት ወይንም ማቀራረብ እንኳን አይቻልም ስለሆነም ይህም ዜሮ፤
አንቀጽ፡16  1/ አካለ መጠን የደረሱ ወንዶችና ሴቶች በዘር በዜግነት ወይም በሃይማኖት ልዩነት ሳይወሰኑ ጋብቻን የመፈጸምና ቤተሰብን የመመሥረት መብት አላቸው፤ ጋብቻ በመፈጸም በጋብቻ ጊዜና ጋብቻ በሚፈርስበትም ጊዜ እኩል መብት አላቸው።

2/ ጋብቻ የሚፈጸመው ጋብቻ ለመፈጸም በሚፈልጉ ሁለቱም ወገኖች በሚያደርጉት ነጻና ሙሉ ስምምነት መሠረት ብቻ ነው።
3/ ቤተሰብ በኀብረ ሰብ የተፈጥሮና መሰረታዊ ክፍል ስለሆነ በኀብረሰቡና በመንግሥቱም ደህንነቱ እንዲጠበቅለት ይገባል።

አነኝህን ድንጋጌዎች በነጠለ ትርጉማቸው ስንወስዳቸው በሞራ የተሸፈነ ብልጭልጭ የሚል አስመሳይ ደወሎች አሉበት። ወደ ውስጥ ስንዘልቅ ግን በሀገራችን በሚፈጸሙት ሶስት የጋብቻ ሥርዓቶች በሃይማኖታዊ፤ በባህላዊ እና በብሄራዊ ጋብቻ የጋብቻ ቀደምት ባህል፤ ትውፊትና ታሪክ ጠቀራ ለብሰዋል። የወልቃይትና የጠገዴ ሴቶች ልጆቻቸው በእናታቸው ሥም ነው የሚጠሩት፤ በአማራው ብሄረሰብ ልጅ እንዳይወልዱ የተሰጠው ክትባት የትድርን ዶግማ በቀጥታ የሚጻረር ነው። ወያኔ የጋብቻ መንፈስ ሸቀጥ እንዲሆን የሚደረገው ግፊት ብቻ ሳይሆን ጋብቻን ፍቅር ሳይሆን ዞግ – መራሽ እንዲሆን ስውር ተጽዕኖ ያደርጋል። ተጽዕኖውም ሆነ ተጠቂነቱም ከፍ ያለ ነው። ከዚህ በላይ በግፍ ስደቱ — እስራቱ – ሞቶ የጋብቻን ተፍጥሮ ድራሹን ነው ያጠፋው። ስለዚህ ከዋናው አምክንዮ ህግና ከአፈጻጻሙ ስውር ደባ አንፃር የውጤቱ ዝንባሌ ወደ ዜሮ ይሸኛል …

አንቀጽ፡17  „1/ እያንዳንዱ ሰው ብቻውን ወይም ከሌሎች ጋር በኀብረት ሆኖ የኀብረት ባለቤትነት መብት አለው።“ በጎሳ መንፈስ፤ በባለ ጊዜነት ዕይታ ከሆነ አዎን። እንደ ዜጋ ሲሰላ ግን ኢትዮጵያ ላይ አንቀጹ ከቦታው ተስርዟል። ስለሆነም ውጤቱ — ዜሮ።

„2/ ማንም ሰው ያለፍርድ ንብረቱ አይወሰድበትም።“ ፍርድ ቤት ሲኖረን ነው። እኛ ፍርድ ቤት፤ ለህዝብ ጥቅም የቆመ ሚዛን፤ ለሙያው ኪዳን ራሱን የሰጠ ርትሃዊ ሥርዓት የለንም። ስለዚህ ይህም ዜሮ

አንቀጽ፡18 እያንዳንዱ ሰው የሃሳብ የሕሊናና የሃይማኖት ነጻነት መብት አለው። ይህም መብት ሃይማኖቱን ወይም እምነቱን የመለወጥ ነጻነትንና ብቻውን ወይም ከሌሎች ጋር በኀብረት በይፋ ወይም በግል ሆኖ ሃይማኖቱን ወይም እምነቱን የማስተማር፣ በተግባር የመግለጽ የማምለክና የማክበር ነጻነትን ይጨምራል።“ ኢትዮጵያ ላይ የአንቀጹ ጭብጥ ተግባራዊነት መሃን ነው። ስለዚህ ቁልጭ ያለ — ዜሮ‘

አንቀጽ፡19 እያንዳንዱ ሰው የሐሳብና ሐሳቡን የመግለጽ መብት አለው። ይህም መብት ያለጣልቃ ገብነት በሐሳብ የመጽናትንና ዜናን ወይም ሐሳቦችን ያላንዳች የድንበር ገደብ የማግኘትን የመቀበልን ወይም የማካፈልን ነጻነትም ይጨምራል።“ ታላቁ የወያኔ የጥቃት ኢላማ ምን ሆነና – ያውም ወደል – ዜሮ

አንቀጽ፡20 „1/ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ በሰላም፡ የመሰብሰብና፡ ግንኙነት፡ የማድረግ፡ ነጻነት፡ መብት፡ አለው።“ ኢትዮጵያ ላይ የለውም። የሰሞኑ  ዬሰማያዊ ቢሮ ፎቶ ብቻ በቂ ነው። ስንቱስ ተዘርዝሮ ያልቅና። ስለዚህ ውጤቱ – ዜሮ፤

„2/ ማንም፡ ሰው፡ የአንድ፡ ማኀበር፡ አባል፡ እንዲሆን፡ አይገደድም።“ ወያኔ አስገድዶ – በገንዘብ ገዝቶ ነው አባል የሚያደርገው፤ አባልነት በፈቃደኝነት መርሁ ተዘቅዝቆ የተሰቀለ ነው። ስለዚህ – ዜሮ

አንቀጽ፡21 1/ እያንዳንዱ፡ ሰው፡በቀጥታ፡ ወይም፡ ነጻ፡ በሆነ፡ መንገድ፡ በተመረጡ፡ እንደራሴዎች፡ አማካኝነት፡ በአገሩ፡ መንግስት፡ የመካፈል፡ መብት፡ አለው:“ ወይ መዳህኒተ ዓለም አባቴ በጎጥ ሶሻሊዝም ይህ ቅዱስ መንፈስ በቢላዋ ነው ዓይኑን ወያኔ ያወጣው። ስለዚህ – ዜሮ

„2/ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ በአገሩ፡ የህዝብ፡ አገልግሎት፡ እኩል፡ የማግኘት፡ መብት፡ አለው።“ ለባለወርቅ ሊሆን ይችላል። ለግዕፋኑ ግን አይሠራም። ስልሆነም – ዜሮ።

„3/ የመንግስት፡ ሥልጣን፡ መሠረቱ፡ የሕዝቡ፡ ፈቃድ፡ መሆን፡ አለበት። ይህም፡ ፈቃድ፡ ለሁሉም፡ እኩል፡ በሆነ፡ በምሥጢር፡ በሚደረግ፡ የድምፅ፡ መስጠት፡ ምርጫ፡ ወይም፡ በተመሳሳይ፡ ሁኔታ፡ በየጊዜውና፡ በትክክል፡ በሚፈጸሙ፡ ምርጫዎች፡ እንዲገለጽ፡ መሆን፡ አለበት።“ አውሬን የሚፈቅድ፤ አራጅን የሚፈቅድ፤ አግላይን የሚፈቅድ፤ ገዳይን የሚፈቅድ ህዝብ የለም። ስለሆነም ድንጋጌው መልካም ሆኖ ሳለ በጎሳ ገዢወች የታፈነው ዬኢትዮጵያ ህዝብ ፍርፋሪውን ወይንም የድንጋጌውን ጸበለ ጻዲቅ ሊያገኝ አልቻለም። በቃህኝካለ እኮ ቆዬ። 97 እኮ ንቅንቅ ብሎ ወጥቶ ነበር ባዶውን ያስቀረው። ረሃብን የሚፈቅድ ማን አለናክብር መጣስን የሚሻ ማን አለናስለዚህ ዜሮን በሞራ ጠቅሎ የዓለምን ህዝብ የሚያባጭልበት የእዬአራት አመቱ ምርጫ ከህዝብ ፈቃድ ውጪ በተጎማጀ አውሬያዊ መንገዱ ያስፈጽመዋል። በመሆኑ የድንጋጌው ድርጊተኝነት ኢትዮጵያ ላይ … ጠፍጣፋ ዜሮ።

አንቀጽ፡22 እያንዳንዱ፡ ሰው፡ የኀብረ፡ ሰብ፡ አባል፡ እንደመሆኑ፡ በኀብረ፡ ሰብ፡ ደህንነቱ፡ እንዲጠበቅ፡ መብት፡ አለው። እንዲሁም፡ በብሔራዊ፡ ጥረትና፡ በኢንተርናሽናል፡ መተባበር፡ አማካይነትና፡ በእያንዳንዱ፡ መንግስት፡ ድርጅትም፡ የሀብት፡ ምንጮች፡ መሰረት፡ ለክብሩና፡ ለሰብዓዊ፡ አቅሙ፡ ነጻ፡ እድገት፡ የግድ፡ አስፈላጊ፡ የሆኑት፡ የኤኮኖሚ፡ የማኀበራዊ፡ ኑሮና፡ የባህል፡ መብቶች፡ በተግባር፡ እንዲገለጹለት፡ መብት፡ አለው።“ ህዝባዊ መንግሥት ሲኖር፤ በህዝብ ፈቃድ ሥልጣን የተሰጠው ሃላፊነት የሚሰማው ሥልጡን ሥርዓት ሲኖር ብቻ፤ በአስተሳሰብ ድህነት ለተወረረው ዬወያኔ ሥርዓት ግንዛቤ  ግን – ሳይፈጽመው ዜሮ ላይ አስክኖታል።

አንቀጽ፡23  „1/ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ የመሥራት፡ የሥራ፡ ነጻ፡ ምርጫና፡ ለሥራም፡ ትክክለኛና፡ ተስማሚ፡ የአሠራር፡ ሁኔታዎችና፡ ሥራም፡ እንዳያጣ፡ መብት፡ አለው።“ አለን ይሄ ኢትዮጵያ ላይ ….?! የድንጋጌው መሪ የጎጥ ድርጅት አባልነት ብቻ ነው። ስለዚህ ለምልዕቱ የድናጋጌው ትርፋማነት ኢትዮጵያ ላይ — ዝክንትል ሮ።

„2/ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ያላንዳች፡ ልዩነት፡ ማድረግ፡ ለአንድ፡ ዓይነት፡ ሥራ፡ እኩል፡ የሆነ፡ ደመወዝ፡ የማግኘት፡ መብት፡ አለው።“ ኢትዮጵያዊነቱን ለሚያስቀድም ብቁ ዜጋ፤ ነፃነት  እኔ መጀመር አለበት ለሚል ብልህ፤ አቅም ላለው ዜጋ ይህ አንቀጽ አይሰራም። — ለድውያኔ፣ ለደካሞች፣ ለአቅመ ቢሶች  ዬአስተሳስብ ድህነት ለረበባቸው ግን ይሠራል። ስለዚህ ህገ – ትርጓሜው የእኩል ተጠቃሚነትን ስለማይተረጉም — አድሎዊ ስለሆነ ኢትዮጵያ ላይ ውጤቱ – ደጎስ ያለ ዜሮ።

„3/ በሥራ፡ ላይ፡ ያለ፡ ሰው፡ ለእራሱና፡ ለቤተሰቡ፡ ለሰብዓዊ፡ ክብር፡ ተገቢ፡ የሆነ፡ ኑሮን፡ የሚያስገኝለትና፡ ካስፈለገም፡ በሌሎች፡ የኀብረሰብ፡ ደህንነት፡ መጠበቂያ፡ ዘዴዎች፡ የተደገፈ፡ ትክክለኛና፡ ተስማሚ፡ ዋጋውን፡ የማግኘት፡ መብት፡ አለው።“ ያው ለጎሳው ሊሠራ ይችል ይሆናል። ለኢትዮጵያዊነት ግን ኢትዮጵያ ላይ ጣር ነው። ስለዚህ – ከዜሮም ጎባጣው።

„4/ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ ጥቅሞቹን፡ ለማስከበር፡ የሙያ፡ ማኀበሮችን፡ ለማቋቋምና፡ ማኀበርተኛ፡ ለመሆን፡ መብት፡ አለው።“ በጎሳ መንፈስ ብቻ ለተደራጀ። በብሄራዊነትን ለመግደል ለሚተባባር ሃይል ብቻ አልጋ ባልጋ ነው መንገዱ ነው። ለነፃነት ዘንካቲት ግን የሀገራዊነትን መንፈስ ለፈቀደ አይሠራም ድንጋጌው ሽባ ነው ስለዚህ ማርኩ – ዜሮ።
አንቀጽ፡24 እያንዳንዱ፡ ሰው፡ የዕረፍትና፡ የመዝናናት፡ እንዲሁም፡ በአግባብ፡ የተወሰኑ፡ የሥራ፡ ሰዓቶች፡ እንዲኖሩትና፡ በየጊዜው፡ የዕረፍት፡ ጊዜያትን፡ ከደመወዝ፡ ጋር፡ የማግኘት፡ መብት፡ አለው።“ ይሄን ድንጋጌ አንባቢ ብቻ ሳይሆን በህይወቱ ያሉ ይለኩት።

አንቀጽ፡25 1/ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ ለእራሱና፡ ለቤተሰቡ፡ ጤንነትና፡ ደህንነት፡ ምግብ፣ ልብስ፣ ቤትና፡ ሕክምና፡ አስፈላጊ፡ የማኀበራዊ፡ ኑሮ፡ አገልግሎቶችም፡ ጭምር፡ የሚበቃ፡ የኑሮ፡ ደረጃ፡ ለማግኘት፡ መብት፡ አለው። ሥራ፡ ሳይቀጠር፡ ቢቀር፡ ቢታመም፡ ለመሥራት፡ ባይችል፡ ባል፡ ወይም፡ ሚስት፡ ቢሞት፡ ቢያረጅ፡ ወይም፡ ከቁጥጥሩ፡ ውጭ፡ በሆኑ፡ ምክንያቶች፡ መሰናከል፡ ቢገጥመው፡ ደህንነቱ፡ እንዲጠበቅለት፡ መብት፡ አለው።

„2/ ወላድነትና፡ ሕጻንነት፡ ልዩ፡ ጥንቃቄና፡ እርዳታ፡ የማግኘት፡ መብት፡ አላቸው፤ በጋብቻ፡ ወይም፡ ያለጋብቻ፡ የሚወለዱ፡ ሕጻናትም፡ የተመሳሳይ፡ የደህንነታቸው፡ መጠበቅ፡ መብት፡ አላቸው።“ ሁለቱም ንዑሳን ድንጋጌዎች ድምጽ የሚመራት ሀገር ስትኖረን ነው። ከዓለም ሶስት የመጨረሻ ደሃ ሀገሮች አንዷ ኢትዮጵያ ናት። ሟርቱ ተሳክቶለታል። ኢትዮጵያ ስንት ትውልድ ሊከፍለው እንደሚችል አይተወቅም በዕዳ የተዘፈቀች፤ በብዙ ውስብስብ ፈተናዎች ለመፍታት የሚፈልገው መዋዕለ መንፈስ እራሱ … ህም። ለማንኛውም በሁለመናዋ በወያኔ እስር ለተፈረደባት ሀገር የህልም ገነት የሆነ አንቀጽ ነው። ስለዚህ የወደቀ ለቅሞ ለመብላት ተራ፤ ለዛም የሚጥል በሌለበት ሀገር  ስለሆነ የድንጋጌው ተፈጻሚነት ለጥቂት ወንበዴዎችና ቤተሰቦቻቸው ብቻ ይሆናል – ዜሮ።

አንቀጽ፡26 1/ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ የመማር፡ መብት፡ አለው። ትምህርት፡ ቢያንስ፡ ቢያንስ፡ በአንደኛ፡ ደረጃና፡ መሰረታዊ፡ ደረጃዎች፡ በነጻ፡ ሊሆን፡ ይገባል። የአንደኛ፡ ደረጃ፡ ትምህርት፡ መማር፡ ግዴታ፡ ነው። የቴክኒክና፡ የልዩ፡ ልዩ፡ ሙያ፡ ትምህርት፡ በጠቅላላው፡ የከፍተኛ፡ ደረጃ፡ ደግሞ፡ በችሎታ፡ መሠረት፡ ለሁሉም፡ እኩል፡ መሰጠት፡ አለበት።

2/ ትምህርት፡ ለእያንዳንዱ፡ ሰው፡ ሁኔታ፡ ማሻሻያና፡ ለሰብዓዊ፡ መብቶችም፡ መሠረታዊ፡ ነጻነቶች፡ ክብር፡ ማዳበርያ፡ የሚውል፡ መሆን፡ አለበት። እንዲሁም፡ የተለያየ፡ ዘር፡ ወይም፡ ሃይማኖት፡ ባሏቸው፡ ሕዝቦች፡ መካከል፡ ሁሉ፡ መግባባትን፡ ተቻችሎ፡ የመኖርንና፡ የመተባበርን፡ መንፈስ፡ የሚያጠነክርና፡ የተባበሩት፡ መንግሥታት፡ ድርጅት፡ ሰላምን፡ ለመጠበቅ፡ የሚፈጽማቸው፡ ተግባሮች፡ እንዲስፋፋ፡ የሚያበረታቱ፡ መሆን፡ አለበት።

3/ ወላጆች፡ ለልጆቻቸው፡ ለመስጠት፡ የሚፈልጉትን፡ ትምህርት፡ ለመምረጥ፡ የቅድሚያ፡ መብት፡ አላችው።“ እንኝህን የሥልጣኔ መሠረት የሆኑት የዕውቀት ግንባታና መሠረት በጥቅሉ ሲታይ፤ የትምህርቱ ደረጃም የሚለካውና የሚመዘነው ከሥርዓቱ ጥንካሬና ከጠንካራ ፖሊሲዎቹ ከሚፈልቁ ጉልበታም ተግባራት ነው። በዘመነ ወያኔ ታላቅ ውድቀት ከደረሰባቸው አንዱ ትምህርትና የትምህርት ተዋዖው ነው። የትምህርት ሥርጭቱ ያልተመጣጠነ አድሎ የዘፈነበትና ነገን ያሳረር፤ ዬትናንትን ታሪካዊ ሃብታትን ያለርህራሄ ያቃጠለ ነው። ዝርክርክ „የእነ ተሎ ተሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ“  ለዜሮም መቅኑ የፈሰሰ – ዜሮ፤

አንቀጽ፡27 1/ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ በኀብረተ ሰቡ፡ የባህል፡ ኑሮ፡ በነጻ፡ መካፈልና፡ በኪነ፡ ጥበብ፡ ለመጠቀም፡ በሳይንስ፡ እርምጃና፡ በጥቅሞቹም፡ ለመሳተፍ፡ መብት፡ አለው።

2/ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ ከደረሰው፡ ማንኛውም፡ የሳይንስ፡ የድርሰትና፡ የኪነ፡ ጥበብ፡ ሥራ፡ የሚያገኘው፡ የሞራሉንና፡ የሃብት፡ ጥቅሞች፡ እንዲከበሩለት፡ መብት፡ አለው።“ ዬትውልድ መጸሐፍ የሆነው አርቲስት ወጋዬሁ ንጋቱን ያልተካ የትውልድ ማገር የሆነውን አርቲስት ደበበ እሸቱን የህዝብ ሃብትነቱን ያሰረ፤ ጸጋውን የለጎመ። አዬበአንድ ባለቅኔ ቴዲ አፍሮ የሚደረሰው ፍዳና መከራ በቂ ነው። ከብሄራዊነት የሚነሱ ማናቸውም አምክንዮዎች የሚመጠብቃቸው ዱላ ነው። ስለዚህ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከጎሳ ማኒፌስቶ ወራጅ ውሃ የተጠለለ ከሆነ – ምን አልባት። በተረፈ ለዛውም ለሥነ ጥበብ ነፃነት የጋዜጠኞች የጸሐፍት ፍልሰት ምንጩ ምን ሆነና። የዚህ ዬፍትህ ሥርዓት የተስተካካለ ይሆናል ብሎ ማሰብ ጮርቃነት ነው። ለዚህም ነው ዬነፃነት ትግሉ ብጥቅጣቂ ነገሮችን ዘግቶ አጠቃላይና ሥር ነቀል በሆኑ ሁኔታዎች ላይ አቅሙንም ጉልበቱንም የመንፈስ ሃብታትም መፍስስ አለበት የሚባለው። ከአጠቃላዩ የጎጥ አስተዳደር መንፈስ የጥልቅ ግልጽ ጥቃቱና ከሥውር ደባው ስንነሳ የዚህ አንቀጽ ተፈጻሚነት ኢትዮጵያ ላይ – የተድበለበለ ዜሮ ነው።

አንቀጽ፡28 እያንዳንዱ፡ ሰው፡ በዚህ፡ ውሳኔ፡ ውስጥ፡ የተዘረዘሩት፡ መብቶችና፡ ነጻነቶች፡ በሙሉ፡ በተግባር፡ እንዲውሉ፡ ለሚደረግባቸው፡ የኀብረሰብና፡ የኢንተርናሽናል፡ ሥርዓት፡ የመጠቀም፡ መብት፡ አለው።“ ለመብቱ ባይታወር የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ግዴታውን ለመፈጸም ይችላል። ይህ ማለት ብዙሃኑ ነፃነቱን ተነጥቆ ለተነጠቀው ነፃነት ዘብ ቁሞ ያድራል። ከጣና የተሳባው የመብራት ሃይል ትግራይ እስኪደርስ ድረስ ያለፈባቸው መንገዶችን እንደጨለመባቸው ሲሆን፤ ነገር ግን የመብራቱን ወጋግራ ባለፈባቸው ቦታዎች ያሉ ንጹኃን ቁመው ሲጠብቁ ውለው ያደራሉ። ማለት ብዙሃኑ ለማይጠቀምበት ቁሞ መብራት ይዞ ቁርስ ራት ምሳ ያበላል – ለባለጊዜው። እሱ ግን እንደ ተራበ። ለዛውም አንጡራ ሃብቱ ሆኖ። የበደሉ ልክ እኮ የለውም። ለነጌቶቹ መብራት ይዞ –  ለብዙሃኑ ግን ምንም – ያው ዜሮ።

አንቀጽ፡29  1/ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ የራሱ፡ ነጻነትና፡ ሙሉ፡ መሻሻል፡ በሚያገኝበት፡ ኀብረሰብ፡ ውስጥ፡ የሚፈጽማቸው፡ ግዴታዎች፡ ይኖሩበታል።

2/ እያንዳንዱ፡ ሰው፡ በመብቶቹ፡ በነጻነቶቹ፡ በሚጠቀምበት፡ ጊዜ፡ የሚታገደው፡ የሌሎችን፡ መብቶችና፡ ነጻነቶች፡ በሚገባ፡ ለማሰከበር፡ ብቻ፡ በተደነገጉ፡ ሕጎችና፡ የግብረ፡ ገብነትን፡ የጠቅላላውን፡ ሕዝብ፡ ፀጥታና፡ ደህንነት፡ በዴሞክራቲክ፡ ማኀበራዊ፡ ኑሮ፡ ትክክለኛ፡ የሆነው፡ ተፈላጊ፡ ጉዳይ፡ ለማርካት፡ በተወሰነው፡ ብቻ፡ ነው።

3/ እነዚህ፡ መብቶችና፡ ነፃነቶች፡ በማንኛውም፡ ሁኔታ፡ የተባበሩት፡ መንግሥታት፡ ድርጅት፡ መሰረት፡ ዓላማዎች፡ ተቃራኒ፡ በሆነ፡ መንገድ፡ ሊፈጸሙ፡ አይገባቸውም።“ ህግ መተላለፍ ከወያኔ በስተቀር ኢትዮጵያዊ ተፈጥሮ አይፈቅደውም። ስለዚህ ህግ ጣሹ ወያኔ ለህግጋቱ ሳይገዛ እዬዳጠና እዬደፈጠጠ የሚሄደውን ነገር ማስቆም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግዴታ ነው።

አንቀጽ፡30 በዚህ ውሳኔ ከላይ የተዘረዘረው ሁሉ በዚሁ ውስጥ የተጠቀሱትን ማናቸውም መብቶች ወይም ነጻነቶች ለማበላሸት በታሰበ ማንኛውም ዓይነት ተግባር ለማዋል ወይም ድርጊትን ለመፈጸም ለማንኛውም መንግሥት ወይም ድርጅት ወይም ሰው የተባሉ አይተረጎሙም“ ወገኖቼ  እነዚህ ድንጋጌዎች ለዬሀገሮች ማስተማሪያ ብቻ ሳይሆኑ እንዲፈጸሙ፤ የህግ ጥበቃና ድጋፍ፤ እንዲሁም ክትትልና ቁጥጥር ሊደረግባቸው የሚገቡ የነባቢተ – ነፍስ ንጹህ የአዬር መስጫ ቧንቧዎች ናቸው። የተባበሩት መንግሥታት አባል ሀገሮች አኃታዊ ህገ መንግሥት፤ እናት ህግ ብለው ይሻል ይመስለኛል።

1948 በኋላም ቢሆን በተለያዩ ጊዜያቶች ብዙ የማጠናከሪያ፤ የማጉያ አትኩሮት ተስጥቷቸዋል። በተለይ 2007 እና 2008 ጥልቅ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሰፊ አምክንዮዊ መንፈሶች በተጨማሪነት አድገዋል፤ ግን በወያኔ ባዶ ናቸው። ወያኔ የመስሚያ ታንቡሩ የተነፈስ ነውና። 2007 እና 2008 ሰፊ አትኩሮት የተሰጣቸው ጥልቅ የሰብዕና ህላዊ ጉዳዮች Durban Declaration constitutes  – racism, racial discrimnation, xenophobia and related intolerance በመፈጸም የድርጊት ጀግኖች ተብለው ለናሙና ከተመረጡት ሀገሮች ጥቂቶችን እስኪ ላንሳ።

አንዷ አርመንያ ነበረች። አረመንያ በፆታ እኩልነት ፍጹም የሆነ ጥበቃና ክትትል የምታደርገው ህግ በማውጣት ብቻ ሳይሆን፤ ለወጣው ህግ ጠንከራ ጠበቂ ተጨማሪ ህግ አውጥታ ሥራ ላይ በማዋል ነው፤ ድንቋ አርመንያ የሥራ ባርነት በፍጹም ሁኔታ የተወገደባት ሀገር ናት። ስለ ሰብዕዊ መብት በህጋዊ ትምህርት ቤቶች፣ በክበቦች፣ በካንፓሶች በነፃ ውይይት ይደረግበታል። አብሶ ለወጣቶች በትጋት እንደ ሃይማኖታዊ ዶግማ ይሰበከል። በአርመንያ 8 ክፍል ላይ እንደ አንድ የትምህርት ሳብጀክት የሰብዕዊ መብት (Human Rights) ትምህርት ለተማሪዎች ይሰጣል።

ለንጽጽር እንዲረዳም – ከእማማ አፍሪካ ውስጥም ቢሆን አልጀሪያ ለተምሳሌ የተመረጠች ሀገር ናት። በብዙ ፈተና ውስጥ ያለፈችው አልጀርያ ለዚህ ክብር የበቃች ሀገር ናት። 60 ብሄረሰቦች እናት የሆነቸው ቡርኪናፋሶ ዘረኝነትን፤ ግለላን፣ የሰው ልጅ ጥላቻን፤ ንቀትን በአዋጅ ያስቀረች ለሰብዕዊ መብት መከበር ጥልቅ ፍላጎቶች ተስማማች ሀገር ናት። ቀደምቷ የሰው ልጅ መፈጠሪያ እናት ሀገር ፍርጃ ደግሞ በጎሳ መከታከት። ባለፈም ሰብዕዊ መብት ቃሉን መጥራት የማይፈቀድባት፤ የሰብዕዊ መብት አፈጻጸም የሲኦልና ዬሃሞት ሀገር አድርጓታል – ወያኔ። አንዲት ስንጥር ደግ ነገር ፈጽሞ ማግኘት አይቻልም። ሀገር ማለት እኮ የእኔ ውዶች ዓለም አቅፍ ዕውቅና ባለው ድንበር ውስጥ የሰዎች ማህበር ማለት ነው። ማህበሩ ከተጠቀጠቀ፣ ከፈረሰ፣ ከተዘለለ ሀገር የለም። የሀገር መነሻው ሰው ነው። ማናቸውም ፍላጎት መነሻው ከሰው ምቹ ተፈጥሮ መሆን አለበት። ወያኔ ግን ተነሳፎ ነው ያለው። መነሻ ቢስ – ከንቱ ስለሆነ። ቀድሞ ነገር ለሰው ልጅ ማህበራዊ እድገት ንቀት ብቻ ሳይሆን እድገቱን የሚጸዬፍ ወያኔ ብቻ።

ክብሮቼ ልክውነው ….  ቁምነገሩ እኛስ ህልማችን ምንድን ይሆንእነዚህን ህግጋት በውስጣችን አድርገን፣ ነገ የምናልማት ኢትዮጵያን በመንፈሳችን ይዘን፣ የአርነት ትግሉን ስናጠነክር ብቻ ለውጤት እንበቃለን። ግን አራሳችን ማዘዝ ስንችል ብቻ ነው። እንደገናም እኛስ በሌሎቹ ላይ ህግን ተላልፈን ምን በደል ፈጸምን ይሆንይሄ ሌላው የነገ የኢትዮጵያ ጥልቅ ፈተና ነው። ዛሬ አረሙ ካልጸዳ ነገም ይህ በደል ይፈጸማል። ከዚህ ላይ አንድ ምሳሌትን ላንሳ አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ  „2/ እያንዳንዱ ሰው ከማንኛውም አገር ሆነ ከራሱ አገር ወጥቶ እንደገና ወደ አገሩ የመመለስ መብት አለው።“  ወገኖቻችን ኢትዮጵያ ሀገራቸውን አይተው የሚመጡትን ወንጀለኛ እናደርጋቸዋለን። ሲያስፈልግም መረብ ዘርግተን ማህበራዊ ግንኙነታቸውን ሁሉ ጢስ እናለብሰዋለን። አቅማችን ከበላው መሰረታዊ ጉዳይ አውራው ስለሆነ ነው ይህን ያነሳሁት። ይህ የተገባ አይደለም። የሚችሉ መሄዳቸው ዓለምዓቀፍ መብታቸው ነው። ኢትዮጵያ እጅግ እንደ ሰው የምትናፈቅ ሀገር ናት። 

መቀመጫውን ፓሪስ ያደረገ አንድ ዓለማቀፋዊ ዬኢኮኖሚ እድገት አያያዝና አገልግሎትን ጥራት አበረታች ድርጅት Business Initiative Directions (BID) ጉባኤ የሽልማት ሥርዓት ላይ በሥርዓቱ የተገኙ አንድ አዛውንት ስለ ሀገር ናፍቆት ጠይቄያቸው እንዲህ ነበር ያሉኝ „መኪና ውስጥ ሆኖ ምግብ ታዞ፤ አስተናጋጅ መጥቶ የሚያሰተናግድባት ብቸኛ ሀገር እኮ ናት – ኢትዮጵያ ለምን አትናፍቅ?!“ ስለዚህ እውነት እኛ እራሳችን መለወጥ አለብን።

እምዬ ሀዘን ላይ ብትሆንም፤ ጉስቁልናዋን ሄዶ ማዬት የነፃነት ትግሉን ያጎለበተዋል እንጂ አያሰልለውም። ብዙ ዓይነት መረጃዎች፤ የዓይን ምስክሮች ይገኛሉ። በዚህ ዙሪያ እራሱን የቻለ ተከታታይ አቅም ያለው ተግባር ቢከውን ስንት ምርት ይታፈስበታል።  እርግጥ የወያኔን ባይረስ ተሸክመው የሚመጡ ሊኖሩ ይችላሉ። እኛ አቅም አለን። እውነት አለን። ቁጭ ብለን ሞግተን የእኛ ሃብት ማድረግ እንችላለን። ዝም ብሎ በጅምላ ማዋከቡ፤ ማግለሉ ግን እንደ ለእኔ ህግን መተላለፍ ይመስለኛል። „ህግ ተላላፊዎችን ጠላሁ“ አለ ነብዬ እግዚአብሄር ዳዊት። ህግ ወያኔ ጣሰ ለማለት እኛ እራሳችነን በህግ ሥር ማሳደርን ይጠይቅ ይመስለኛል። አንዳንድ ጊዜ ከሰብዕዊ መብት የተነሱ ሃይማኖታዊ ሆኑ ዓለምዓቀፍ ህግጋት ጋር የመራራቅ ችግርም ያለብን ይመስለኛል።

ይህም ብቻ አይደለም በኪነጥበብ ዘርፍም አንቀጽ 27 ሃብትነቱ የህዝብ ሆኖ ለጥበበኛው የሚጣለው ማዕቀብ የብዙሃኑ ታዳሚ መብትን ገጣል። አንቀጽ 18 ቢሆን ሃስብን – ፍላጎትን – ዕይታን  – ተቃውሞን – ድጋፍን የመግልጽ ነፃነት በትክክል መፈጸም ካልቻልን ነገን ያቀጭጫል። አሁን እኔ ዘሃበሻ ነፃነቴን ባያውጅልኝ በምን እንገናኝ ነበር። ነፃነት የሰው ልጅ ባገኘ ቁጥር ውስጡን ገልጦ ያሳያል። ውስጡን ግልጦ ባሳዬ ቁጥር ደግሞ የመፍትሄው አቅጣጫ ይታወቃል። አይደለም ከሚያግዝ፣ ዬማያግዝ ሃሳብም ልግሞ በውስጥ ከሚያዝ ቢወጣ፤ ያበጠው መተንፈሻ ቧንቧ ይሠራለትን እና መግሉ እንዲወጣ፤ ቁስሉ እንደ አባት አደሩ እንዲድን መፈወሻ ያገኛል። የማይድን ሲሆን ደግም አገላብጦ አይቶ በማሰናበት ጊዜን በአግባቡ ማስተዳደር ይቻላል።። ግን ለማድመጥ ስንፈቅድ ብቻ ነው። እኛ እራሳችን ነፃነትን ለሌለው ነፃነት በመስጠት መደባችን የት ላይ ይሆን?!

አያድርግብኛ እንጂ አንድ ምሳሌ ባነሳ „እኔ ወያኔ ብሆን¡“ ሎቱ ስብሃት ስለቃሉ ይቅር ይበለኝ አምላኬ ጋዜጠኛ ተመስገንን አላስርም ነበር። ስለምን? „የቅርብ ሟዕት የቹቻ መንከሪያ ይሆናል“ ይላል ጎንደሬ ሲተርት። ትእግስቱ ተመስገን ትልቅ ዋርካ ነበር። ከትንሿ ሰቀቅን ተነስቶ የህዝብን የውስጥ ስሜት እንደ ሃኪም መርምሮ፤ ትችቱን – መፍትሄውን – ቁልፉን በድፍረት ይናገራል። ፈውሱ ነበር ለወያኔ ግን በምን አቅልሽንፍላ የተሜ ትንተናው የተቋም ያህል ከልብ ነበር። 

ደፋር ትችቱ ነገን አቃንቶ የማምጣት ልዩ አቅም ነበረው። ከህዝብ ውስጣዊ የሞቀ ወይንም ለብ ያለ ወይንም የበረደው ስሜት ተነስቶ የሚሰጠው ትንተና ለወያኔ መዳኛው መፈወሻው ልዩ ማሰልጠኛው ነበር። ሌላው አዛውንቱ ብዕረኛ ጋዜጠኛ እስክንድር የመንፈስ ዓይን ነበር። ሌሎች የብዕር አርበኞቻችንም ዕድሉን ቢያገኙ መዳህኒትም – መዳኛ ነበሩ። ለአንድ ሥልጡን ማህበረሰብ ህዋሱ የደፋር ጋዜጠኞች መኖር ነበር። ግን አልተቻለም። የነፃነት እራህብን በራህብ ቆላው፤ የነፃነት እርሃብን በራህብ አንገረገበው ጆፌው አሞራ።

አብርሽም ቢሆን ወያኔ  ከሚመካበት ማህበረሰብ የወጣ ወጣት ስለነበር፤ ጭራቁ የጎጥ ዶክተሬን በአዲሱ ትውልድ ዕይታ ምን እንደሚመስል ሳዕሊው ነበር። አቅም ስሌለው ወያኔ ብዕርን ፈርቶ ሃሳብን ሸሽቶ አሰረ። ኢትዮጵያን ሻማ አልባ አድርጎ ጭጋጋማ ጨለማ አለበሳት። ስለዚህ የእኛ ትግል ነገም የሃሳብ ብልጫ የሚመራት፤ የጠራ የሃስብ ጭማቂ የሚያስተዳድራት ሀገር ለመፍጠር ከሆነ፤ በዚህ ዙሪያ መጠራቅቁን ይፍታህ ማለት ያለብን ይመስለኛል። አራሳችን ለራሳችን ካሜራ መሆን አለብን።

አንቀጽ 20. ንዑስ አንቀጽ 2 አባልነት በፈቃደኝነትን ያከበረ ስለመሆኑ አበክሮ ያስገነዝባል። ስለሆነም ፈቅዶ የአንድ ፓርቲ አባል ለሚሆን፤ ወይንም ፈቅዶም ለማይሆኑ እኩል አክብሮትና የቤተሰባዊ ፍቅር የመስጠት እቅምን አምጠን መውለድ አለብን። ይህ ለዛሬ ብቻ አይደለም – ለነገም። ዛሬ ተሞርዶ ጎባጣውን ካላቃናነው ነገንም ያበልዘዋል።

ይህን ታላቅ የወንጌል ቃል ያነገሠ  ቀን ስናከብር ድንጋጌዎችን የዕለት ህይወታችን እንዲመሩት መፈቀዳችን እያረጋገጥን መሆን አለብን። በስተቀር አስክንድር – እስክንድር፤ የእኔ ሰው የእኔ ሰው፤ እርዮት እርዮት፤ በላይነሽ ባላይነሽ፤ አቡቦከር አቡበከር፤ በቀለ በቀለ፤ ውብሸት – ውብሸት ማለቱ ብቻውን ነገን አብርቶ አያመጣም። ስለዚህ ህጎችን ከወዲሁ ከእራስ ጋር አዋህዶ አክብሮቱን ድርጊት ላይ ለማዋል መትጋት ግድ ይለናል – እኛ እራሳችነን፤ እኛ ከዛ ቦታ ብንሆን በማለት ፈታኝ ነገሮችን ሁሉ ዛሬ መልክ ካላስያዝናቸው ነገ እዬመረቀዙ ለዛ መከረኛ ህዝብ ዕንባ ቀጣይነት ማዳበሬያ ይሆናሉ። ማሸነፍ የሚነሳው ከራስ ነው። ለሚወዱት ፍላጎት አራስ ነብር ሳይሆኑ እራስን ማሸነፍ ጀግነንት ነው – ደስታ ነው – ብሩህ ተስፋም ነው።

የኔዎቹ ረጅም ጊዜ አቆዬኋችሁ – የግድ ስለነበር። አመሰግንኳችሁ። ትእግስታችሁን አደንቅኩኝ። መሸቢያ የሥራ ቀናት ከመጪው ሰንበት ጋር እንዲሆን ተመኘሁ – በአክብሮት። ደህና ሰንብቱልኝ።
ህግ የሚመራው ተናፋቂና ተወዳጅ ሥርዓት አምላካችን መርቆ ይስጠን!
ለህገ – ልቦና ነፍሳችን ይገዛ ዘንድ ልቦናችነን አምላካችን ይክፈት – ይርዳንም። አሜን!

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። December 10, 2014
·         ተጨማሪ ማረጋገጫ።
የታህሳስ 10 የ1948 ዓለምዓቀፍ የሰብዕው መብት ህግ በ ኢትዮጵያ በወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥርዕዎ መንግሥት በዜሮ የተባዛ መሆኑን ቅኑ ዘሃበሻ ድህረ ገጽ በታህሳስ 10፣ 2014 ጹሑፌን ለጥፎልኝ ነበር ፎቶው የ የኔሰው ገብሬ ነበር። ለነገሩ ዛሬ ቀን እዬወጣለት ስለሆነ አከታትዬ እለጥፈዋለሁኝ ሙሉውን። 

ዜሮን በሞራ፤ በሁሉም የወደቀ ዱለኛ። (ሥርጉተ ሥላሴ)



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።