አቤቱታ ለአቶ ዮናስ ደስታ፤ አዲስ - አባባ።
ቀለማችን።
ከሥርጉተ © ሥላሴ 26.06.2018 (ከጭምቷ - ሲዊዘርላንድ)
እኔ ደስታን አመሰገንሁ፣ ከጸሐይ በታች ከድካሙ እግዚአብሔር
„በሰጠው በህይወቱ ዘመን ይህ
ደስተው ከእርሱ ጋር ይኖራል።
(መጽሐፈ መክብብ
ምዕራፍ ፰ ቁጥር ፲፭)
ይድረስ ለአቶ ዮናስ ደስታ
በኢትዮጵያ የቅርስ ጥበቃ እና የምርምር ዋና ዳሬከተር፤
አዲስ አበባ።
·
መቅድም።
ናፍቆቶቼ የአገሬ ልጆች እንዴት ዋላችሁ አደራችሁኝ አመሻችሁ።
ይህ የምታዩት ምሥል በሉላዊ አህጉራት የተፈጥሮ ሐብቶች ላይ አንዳንድ ተግባራትን እከውናለሁኝ።
ያው ለእኔ የፍቅር ተፈጥሮ ማለት ተፈጥሮን ማክበር፤ መውደድ፤ በዛም ሐሴት ማግኘት ነው። ስለሆነም የፍቅራዊነት ብሎጌን ዲዛይን
ሳደርግ ለዬምዕራፉ እንዚህን የሰው ልጆችን ሐሴት የሚያመነጩ ተፈጥሯዊ ሉላዊ ጸጋዎችንም አካትቼ ነው። የተፈጠሮ መልክምድራዊ አቀመመጥ
ሆነ በውስጣቸው ያሉ ሃብቶች ማንነት አላቸው እና።
- · ምዕራፍ።
Ethiopia: ዶ/ር አብይ ለኤርትራ ሉዑካን ቡድን የተናገሩት አስገራሚ ንግግር | Dr. Abiy Speech to
Eritrean Delegates
ዛሬም ኢትዮጵያ አዲስ ምዕራፍ ላይ ናት። ከስውሩ መንግሥት የመንፍቅለ መንግሥት ሙከራ በሆዋላ
ጠ/ ሚር አሜኑ አብይ አህመድ ናፍቆታቸውን በመስመር ባልተለካ ቁሳዊ ሸቀጥ ሳይሆን ሰማያዊው ጌታ በገለጸላቸው የናፍቆት ብሄራዊ
ጥሪ ዕንባችን ያራጩናል። የት ነበሩ? የሰኛል። የኤርትራ ልኡክም የፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፍወርቂ አማካሪና የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ የማነ ገብረአብ እና የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ኦስማን ሳለህ ዘለማለማዊ ሰላምን ተምኝተዋል።
ቀኑም፤ ሌቱም፤ ወራቱም፤ ዘመኑም፤ ምዕቱም ሰላም ይለምልም ብሏል። ያ የመከራ ጉም ተላቀን ዛሬ
ላይ ተሁኖ የትንቱን የሞት እና የግድያ ዕንባ ተሻግረው ጠ/ ሚር አሜኑ አብይ አህመድ በግርማ ሞገስ ገፃቸው ፈካ ብሎ ያ የሚናፈቀውን
ፈገግታ ለግሰው ፍቅርን ሲሰብኩ እኔስ? አንተስ? አንቺስ ያሰኘኛል?
ለዚህ ነው ሥርጉትሻ የዓለሙን ማህብረስብ ይህን አስፈሪ የመኖር መከራ መሻገሪያችን የፍቅርን
ተፈጥሮ መርሆዎች በት/ ቤት ደረጃ ሥርዓተ ትምህርት ተዘጋጅቶለት፤ የህሊና የሰብዕና መሰናዶ ሲደረግ ብቻ ፍርሃት፤ ስጋት፤ ቂም፤
በቀል፤ ጠፍተው ሁላችንም አጀንዳችን ሰወ፤ ራያችን ተፈጥሯዊነት ይሆናል ብላ ስትሟገት የባጀችው።
ዛሬ የሚገርመው የሚደንቅው የፍቅር ተፈጥሮ የሰው ምንጭ መገኛ በሆነችው መሬቴ ላይ በድንቅነሽ
ቀዬ እንዲህ የፊደል ገባታ ሲሆን ከማንም እና ከምንም እኔ እና ብዕሬ፤ ጠባቧ ጎጄዬ በብርሃን ወጥቶልናል። ለዚህም ነበር እኔ ስሞግት
የባጀሁት ጠ/ ሚር አሜኑ አብይ አህመድ ዕለታዊ፤ አካባቢአዊ አይደሉም፤ ፓን አፍሪካኒሲት ብቻ ሳይሆኖ ለትቁርነትም የተለዬ ቀለም
ያለቸው ኢትዮጵያዊ ማርቲን ሉተር ኪንግ ብሄራዊ ቀንም ናቸው እያልኩ ስሟገት የባጀሁት።
ብሎጌ ውስጥ ያሉትን ቀናቸውን የተጻፈበትን
ማዬት ይቻላል። ከሳተነው ድህረ ገጽ ነበር ቀድመው የተለጠፉት፤ አሁን ወደ እኔ ሽፍት ያደረኩትም ግንቦት 1/2018 ነበር። ዘመኑ
የ እኔ ብዕር ነው የባድመ ዕድምታ በሥርጉተ ዕይታም ይኸው አሸነፈልኝ።
- · ፍቅራዊነት LoveIsm እና እድምታው
ፍቅራዊነት ቀለሙም አዲስ ነው። ፍቅራዊነት አዲስ ቀን ነው ይላል መግቢያው። የፍቅር ተፈጥሮ
ቋንቋ ደንበር አልቦሽ ነው። የዓለም ነፃነት የሚታወጀው ፕላኔታችን መዳኛዋን የፍቅር ተፈጥሮ መርህ ተኮር ጉባኤዎች፤ ኮንፍረንሶች፤
ወርክሾፖች፤ ተቋማት፤ ኮሌጆች፤ ዩንቨርስቲዎች ስትከፍት ብቻ ነው።
ፍቅር የመኖር ፍልስፍና ነው ግን ፈላስፋ የሌለው። ፍቅር የሳይንስ አንባ ነው ግን ሳይንቲስት
የሌለው። ፍቅር የምርምር ማዕክል ነው ግን ተማራማሪ ኤክስፐርት የሌለው። ፍቅር ትውልድ ነው ግን ለትወልዱ በቋሚነት ትምህርት የማይሰጥበት
የተረሳ የእውቀት ዘርፍ። እንደ ሙያም የማይታይ። መጸሐፍት፤ መጋዚኖች፤ ራዲዮ ፕሮግራሞች፤ የቴሌቪዥን ዝግጅቶች የሌሉት ባለቤት
አልባ ግን የመዳን የነፍስ አባት። የፍቅር ተፈጥሮ አዳነ ነው ሥሙ።
- የእኔ ቅኖች!
ቅኖቹ ስለሆናችሁ ነው ወደ እኔ ብሎግ ብቅ የምትሉት። ናፍቆቶቼ ሁሉንም ችላችሁ ነው የእኔ መንፈስ
ተሳታፊዎች ለመሆን የወሰናችሁ። ይህን ነበር በ2017 መጋቢት ላይ የጀመርከት።
ሰው ተፈጥሮ ግን በስጋት እንዴት
ይኑር ይባላል? እኔ „አሸባሪ“ የሚባሉት ሳይቀር መሪዎቹ ፍቅርን ስላልተማሩት ነው ይህን ጭካኔያዊ መንገድ የመረጡት። ስለዚህ ሃሳባቸውን
በውይይት የሚፈታበት መንገድ እንዲፈጠር ነው የምሻው። ቢያንስ በስካይፕ።
ሶርያ እኮ ከነቅርሷ ወድማለች። የሰኔ 16ቱ ህልም ይሄው ነበር። የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ
ነበር። የአዲሱ ካቢኔ ግልበጣ ለዛውም በአደባባይ በመግደል ነበር የታቀደው። ተከታይም
ጥቃት መጠበቅ ያስፈልጋል።
አዲስ አባባ ሰላሟ ከእንግዲህ አድጋ ውስጥ እንደሆነ ይሰማኛል። ዛሬ አንድ ሙግት አለ የአሜሪካው
የፌድራል የምርመራ ሥልጡን ሥራ መጀመሩ ከሉዕላዊነት ጋር ተያይዟል። ወይ መቀለድ የአፍሪካን ዓይን ለማጥፍት እኮ ነበር የተሴረው።
ፈጣሪ ልብ ይስጣቸው! አሜን!
ይህ ብጥብጥ ቢቀጥል እኮ የአፍሪካ ህብርት ጽ/ ቤት ወደ ሌላ ወደ ኪጋሊ ሊዛውር ይችላል። እኔ
እንዲያውም ሌላም ዓለም አቀፍ የሰላም አስከባሪ ሃይል ቢኖር ሁሉ መልካም ነው ባይ ነኝ። የተቀላቀለ ጉድ እኮ ነው። ማን ምኑ ታምኖ።
በፈጠሪ ጥበብ እኮ ነው ዛሬ የታደረው። ጉዳዩ ደግሞ ዘር ተኮር መሆኑ ጉዳዩን እጅግ ትብብት እና ውስብስብ ያደርገዋል። ጦርነት የሚለዬው የለም ህግም የለውም። ሁሉን ነው የሚያወድመው።
- · መኖሬን ስወደው።
የሆነ ሆኖ በቀዬ፤ በባዕቴ የማዬው ነገር መኖሬን እንደውደው አድርጎኛል። እግዚአብሄር ይመስገን
እዚህ ሲዊዝ የሚኖሩ ዕውነተኞቹ ኤርትራውያን ኑሮዬን አውከውት አያውቁም። በፍጹም። ስለዚህም አክብሮቴ ጥልቅ ነው። ሰላሜን አልበጠበጡኝም።
ሳድግ የማውቃቸውን ያህል ነው ሆነው ያገኘሁዋቸው። ወላጅ እናቴ በዚህ ዘመን ኤርትራዊ ልጅ አላት። አዎን! ከልጆቿ ልዩነት ሳይሆን
ከእኔ በላይ ትወደዋለች። ለነገሩ ከእኔ ጋር እኮ ተረሳስተናል።
አንድ ህዝብ ሁለት አገር፤ አንድ ህዝብ ሁለት ልብ፤ አንድ መንፈስ ሁለት አካል ፈጣሪ ግን የሠራን
ለዛሬ በመረጥኩት የተፈጥሮ መልክ፤ ቁመና፤ ወዝ፤ ማዕዛ፤ ውስጥ እና ጠረን ነው። ይህንስ ማን ይጋፋው? ይህንስ ማን ይሻረው?
ምላሹ መልካም ነው። ይህን ለማሳጣት ነበር ክፉዎች ጠቅላላ ካቢኔውን አመድ ለማድረግ አቅደው
የነበረው። ዛሬ ላይ አቶ ደመቀ መኮነን ራሱ እጅግ ነው ያሳዘኑኝ። ለመጀመሪያ ጊዜ የሴት አዲስ አፈ ጉባኤ ኖሮንም እሳቸውንም ክብርት
ሙፍሪያት ካሚል አጥተን ነበር። እንኳን ሙሉውን አዲስ ካቢኔም ፈጣሪ አምላክ አተረፈልን፤ ለ እነሱ ቤዛ የሆኑት ሰማዕታት እና የተጎዱትንም
ፈጣሪ መንፈሱን ይላክልኝ። አሜን!
የሆነ ሆኖ ሃዘን ተፍሳሃ ሆኗል። ፍቅር ከሰው ልጆች በላይ መቻቻልን ያውቅበታል። የሰው ልጅ
ምን ቢሰለጥን የ ዓለምን ሙሉ መከራ መፍትሄ ሊሰጠው አይችልም የፍቅር ተፈጥሮ ግን የመፍትሄ መዳህኒት በመዳፉ አለ።
ከትናንት መከራ ማግሥት ዛሬም መልካምነትን ይሰብካሉ ጠ/ ሚር አሜኑ አብይ አህመድ። ይሄው ለተላያዩ
ዓለምአቀፍ አካላት በመጋቢት 2015 ልኬ ባይሳካም እኔው ትንሽ ነገር ለመነሻ የሚሆን የቃላት ፖስተር ቻናል የጀመርኩት።
https://www.youtube.com/channel/UCb4Maqp24liAGdbPE553WGA/videos
·
የውድመት
መከራው።
ጦርነት ማንንም አይለይም፤ ሁሉንም ነው የሚያወድመው። ወንዞች፤ ተራሮች፤ አዕዋፋት፤ ዕጽዋት
ሁሉም ተጠቂዎች ናቸው። ስለዚህ ፕሮጀክቴ ስለፍቅራዊነት መርህ ተፈጥሮ ማወቅ ማለት ስለሰው ልጆች ሐሤት መፈጠሪያን ጥንቃቄ ማድረግን
አብክሮ ያስገንዝባል።
- · ስለዛሬው የቀለም ቅኔ።
ይህን መሠረት አድርጌ ከአፍሪካ ኢትዮጵያን እሰቀድሜ ስፈልግ ይህን የተፈጥሮ እጹብ ድንቅ የሆነ፤
ሰው ሸራሽ ያልሆነ የኢትዮጵያ ካርታ ጋር ገጥ ለገጥ ገጥምን። አንተ ማን ነህ? ማንስ ትባላለህ? ከዬት ነው ዞግህ? ብዬ ሊጋበውን
ጉግልን ጠዬኩት። ፎቶውን ባገኘውም ባለቤቱን ፈለግኩትም። መቼም ገድለኛ ኢትዮጵያዊ መንፈስ ነው። ምን ያህል ነፍሱ ከኢትዮጵያዊነት
ጋር የሰከነች ስለመሆኗ ሚስጢር ነው ራሱ ሰብዕናው። ማንነት እንዲህ በረቀቀ ቅኔ ይገለጻል። ይህ ከመጸሐፍም በላይ ነው። ይህ ከሙዙዬም
በላይ ነው። ይህ ጽድቅ ነው።
ስለሆነም ቀጥ አድርጎ ፊታውራሪ ጉግልሻ የልቤ ነው መቼም ያለምንም ፕሮቶኮል ከአንድ የቲውተር
አድርሻ ላይ አደረሰኝ። ወንዝ ነው። ግን ወንዙ የቀደመው በዬትኛውም ቅኝ ለመግዛት ባሰበ፤ በተመኘ፤ የውጪ ሐገር ዜጋ ሆነ መንግሥት
ያልተሰራ፤ ያልተሰመረ ሰማያዊ ሚስጢር ነበር። በአጥንት እና በደም
የተገነባ የቀደመችው የኢትዮጵያ ሞንዳላ ፍቅራዊ፤ አብሯዊ፤ እኛዊ መልካምድራዊ አቀማመጥ በሰማዩ ጌታ በአማኑኤል የተሠራ ነው። ተራራም
አለ። ኢትዮጵያን መልካዕምድራዊ አቀመመጥ ቁሞ የሚመሰክር።
የሆነ ሆኖ ይህም ወንዝ የሚስጢራዊነታችን እናት አናትም ነው። እትጌ ኤርትራም በማስተዋል ትታደምበት።
አምደ ህላዊ። ለዛሬ ጹሑፌ ዋነኛ እንዲሆን ስመርጠው ይህን ሥራዬ ብሎ ሳይሆን ሚስጢር ተገልጦላቸው ምስሉን ላጋሩን ኢትዮጵያዊ ወገኔ
ዝቅ ብዬ ላመስግን ወደድኩኝ። መቼም እንዴት ሊቀ ሊቃውንት እንደሆኑ
የዕድማታው አበው ያመሳጥሩት።
- ምንጭ፤
@MessiNega
20. Feb. 2015
Ethiopia map https://twitter.com/messinega
እርግጥ ነው ካርታውን በተለያዩ ሁኔታዎች ላይ ተጠቅሜበታለሁኝ። በፍቅር ተፈጥሮ ረቂቅነት የመጨረሻዎቹ
ምዕራፍ ላይም።
እኔ ለአንዲት ቀን ዕድሉ ቢኖረኝ ከዚህ ቦታ ኤርትራንም የጨመረ አንድ የወልዮሽ ሙዚዬም አሰራበት
ነበር። ይህ የግሼ ማርያም ሚስጢር የተገለጠበት አንዱ ገድለኛ ቦታ ነው። ሊጎበኝ፤ ሊታይ ሊከበር፤ እንደ ታቦት ሊከበከብ የሚገባ
ከትወልድ ወደ ትውልድ በቅርስነት ተመዝግቦ ሊቀመጥ የሚገባ ዕጹብ ድንቅ የተፈጥሮ ጸጋ ነው። ምህረት፤ ሰላም፤ ፍቅር ነው።
አላዛሯ ኢትዮጵያ ዓለምን ቀድማ የፍቅር የምህረት ቀን እኮ አወጀት ሰኔ 16.2010 የድንቅነሽ
ማዕልት።
„ኢትዮጵያ መንፈስ ናት፤ ኢትዮጵያ
ሚስጢር ናት፤ ኢትዮጵያ ሱሴ ናት“ ቢባል ሲያንስም ነው። ኢትዮጵጵያ ሰምዕትም፤ ሰማይና
ምድርም ናት ልበላት እኔ … ለዚህም ነው ለዓመታት በዘለቅ ሁኔታ ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ
ሚስጢር የሚለው ሞቶ ሁለመናዬ ሆኖ የኖረው። በሥርዓተ ተክሊል ተጋብተን ቆርበን ሰግደን ነው በዚህቺው በገዳማዊቷ ቀዬ አብረን የመነኮስነው
ከዕድማታው ጋራ።
- · ለአቶ ዮናስ ደስታ እንደ መከወኛ።
አቶ ዮናስ ደስታ በኢትዮጵያ የቅርስ ጥበቃ እና የምርምር ዋና ዴያርክተር ናቸው። ወጣት ናቸው።
በተደጋገሚ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ አቅም ያላቸው ወጣቶች አሉ እያልኩ ስጽፍ ከነበረው አንዱ እሳቸው ናቸው። ወጣቱ ሊሂቅ ኢትዮጵያ
በውስጣቸው ያለተቀናቃኝ እንድትፈርሽ የፈቀዱ ቅኔ ናቸው። ዛሬ ይህን አቤቱታ ሳቀርብ ይህን ቦታ በልባቸው ሰሌዳ እንዲቀርጹት እና የውስጥ ሃብታችን ዕውቅና እንዲያሰጡት ለማሳሰብ ነው - በትህትና።
ስለምን? ለዛሬ እርስ ይህን ምስል መረጥኩት? የሚለው
ሁሉም ወደ ሚስጢሩ ቢመልስ ራሱን ያገኛል። በራስ ማግኘት ውስጥ እኛዊነት ካለመንምም ቅድም ሁኔታ ይኖራል።
- · ወዲህ ነው ነገሩ …
ቀደምብዬ እንደገለጽኩት በፍቅራዊነት ላይ ሥሰራ በተፈጥሮም ላይ ነው። ድንጋይም የተፈጥሮ አካል
ነው። ድንጋይም አለትም በአገር ያለ ዜጋ ነው። የመጀመሪያው የሰው ልጅ መሳሪያ ከሹል ድንጋይ ነው። የመጀመሪያው አሳትም ከድንጋይ
ፍጭት የተገኘ ነው። ስለዚህም ተፈጥሮ ትርጉም የሚኖረው ተፈጥሮን ባከበረ የመንፈስ ዕውቅና ማዕቀፍ ውስጥ ነው።
እንዲያውም ወጣቱ ኢትዮጵያዊ አቶ ዮናስ ደስታ ሊሂቅ እንዲህ ይሉናል … እግረ መንገድም ጠ/
ሚር አብይ አህመድ እንዴት ብቃትን መምረጥ እንደሚችሉበት ማስተዋል ይቻላል። ገላጮችን ስትደመምቧቸው ኢትዮጵያዊነት ምን ያህል ግርማ
ሞገስ ሆኖ እንደበቀለ እንደ ጸደቀ መመዘን ይቻላል።
በሌላ በኩል „ኢትዮጵያዊነትን ከእኛ ወሰደ ከሌላም ወሰደ“ አይደል ስንባል የተባጀው፤ ዕውነት
ግን አይደለም። የአብይ መንፈስ ሆነ አብይ የእኔ የሚላቸው፤ የሚቀርባቸው ቅን ንጡህ ጸዓዳ መንፈሶች ሁሉ አጀንዳቸው የውስጥ እና
ጠረኑ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚል ነው። የልተሸመተ፤ ያልተለበጠ፤ ያልተቀዬጠ፤
ግን በረቂቁ ቅዱስ መንፈስ በወል ውል ኪዳኑን ማተቡ ያደረገ።
https://www.youtube.com/watch?v=AyY1kbD3MG8&t=2958s
Tech Science TV
Program Episode 39
ወደ ቀደመው ምልሰት ሲሆን … በፍቅራዊነት በቃላት ፖስተራዊ ቻናል ለይ የዓለምን መልካምድራዊ ተፍጥሮ እና ሃብታቱም ማህበርተኞች ናቸው።
ለአንዲት ቀን ባለሥልጣን ብሆን የባህልና የቅርስና የቱሪዝም ክፍል ባለስልጣን ብሆን የማደረግው
ይህን ቦታ ታላቅ የቅርስ ማዕከል ማድረግ ነው። የዛሬ
አቤቱታዬም ለአቶ ዮናስ ደስታ ይሄውን
ነው። እዚህ ቦታ ትልቅ ሙዚዬም ማዕከል መመስረት ቢቻል። መንገድ ማሰራት ቢቻል። ግሼ በነፍሱ እኮ ነው።
እርግጥ ቀደም
ብዬ እንደ ገለጽኩት ተራራም
አለ። በደም እና በአጥንት የተከበረውን የጥንት የጥዋቱን የኢትዮጵያን ደልዳ ሞንዳለ
ተክለ ገጽ ወይዘሮነት የሚገልጥ።
ባለፈው በሎሬቱ መታሰቢያ ሠርቸዋለሁኝ። ምን አልባት የቤት ሥራውን በዚህ ፖአሰተራዊ ቻናል ያለውም
ተራራ ወግ ቢደርሰው ምኞቴ ነው።
- · ክውና።
ዝም ተብሎ አይደለም ኢትዮጵያ ታላቅ አገር፤ የሰው መፈጠሪያ አገር፤ የከፋቸው ሁሉ መከፋታቸውን የሚታገሱበት አገር የምትባለው። ጥልቅ የሆነ የነጠረ ማንነት ያላት አገር ስለሆነች ነው። ይህ ወንዝ እና ተራራው ራሱ ምስክር ነው።
በመጨረሻው ትንሽ ከናፍቆት ጋር እንገናኝ እስቲ ጠረኑ
እያመረ ነው። በ2005 ለብርሃና መስቀል በጸጋዬ ራዲዮን የተሠራ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ