ልጥፎች

የፖለቲካ ሥልጣን ትርምስ በቃኝ ማለት ብልህነት ነው፤

ምስል
የመፍትሄ መቋሚያ። „የሥራው ሁሉና የነገር ግዳጅ መጀመሪያ ምክር ነው።“ መፅሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፯ ቁጥር ፲፮ ከሥርጉተ©ሥላሴ 23.08.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ የፖለቲካ ሥልጣን ትርምስ በቃኝ ማለት ብልህነት ነው፤፡ የፖለቲካ ስልጣን ትርምስ በቃኝ ማለት ብልህነት ነው።  ራስንም የማሸነፍ ልዩ አቅም ነው። ስለሆነም  አመሰግነዎታለሁኝ።  ·      መነሻ። https://www.zehabesha.com/amharic/archives/93721 ‘ ለኢትዮጵያ ሕልውና አስጊ የሆኑ ድርጅቶች በመደመር ስም ያለ ቅድመ ሁኔታ መግባታቸው ያሰጋል ’ – ሻለቃ ዳዊት ወ / ጊዮርጊስ ·          ወግ! ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? ትናንት ማምሻ ላይ ይህን ቃለ ምልልስ አዳመጥኩተኝ። እርግጥ ነው ብዙም ደህና ስላልነበርኩኝ ምን እንደሚሰማኝ አልጻፍኩኝም። አሁን ትንሽ ልለት ፈለግኩኝ።  የለውጥ ተጋድሎ ሲጀመር VOA የአማርኛው ክፈለ ጊዜ ከሁለት የፖለቲካ ሊሂቃን ጋር ያደረገው ውይይት ነበር። ሦስት ተከታታይ ውይይት ነበረው። ተወያዮቹ ፕ/ ዳንኤል አበራ እና አቶ ያሬድ ጥበቡ ነበሩ። በውይይቱ ላይ ያልተመቹኝ ነገሮች ስለነበሩ „መቋሚያ“ በሚል እርስ ሃሳቤን ገልጬ ነበር። ከገለጽኩባቸው ነጥቦች አንዱ አቶ ያሬድ ጥበቡ በኢትዮጵያ ግጭት አያሰጋኝም ስላሉ ነበር። እኔ ደግሞ ዕድለኛ ነዎት እንቅልፍ ተኝተው ማደር ችለዋል፤ እኔ ግን እጅግ ያሰጋኛል ብዬ ሞግቻቸው ነበር። ያልኩትም አልቀረም እስከ 2 ሚሊዮን ወገኖቻችችን መፈናቀላቸው ብቻ ሳይሆን ከመፈናቅል ጋር ተያያዥ የሆኑ እጅግ አሰቃቂ የወገን ሰቆቃ ደርሷል። እንግዲህ ያን ጊዜ ነው። አሁን ደግሞ ባለው „የመደመር ፖለቲካ“

እውነትን መደፈር መልካምነት ነው ተቋማዊ መድረግ ደግሞ ጀግንነት!

ምስል
ደስታን በጥንቃቄ። „መመካት እና መታበይ ትዕቢትም ባለጸግነትመን ያጠፉታል፤        እንደዚሁም ሁሉ የትዕቢተኞችን ቤት ያጠፋሉ።“ መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፬ ከሥርጉተ©ሥላሴ  21.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ “ ትልቁን   የአማራ   ህዝብ   ያልሆነውን   ነበር   በማለት   አማራ   ጨቋኝ :  አማራው   የገዢ   መደብ   ነው ።  አማራ   ጠላታችን   ነው   በማለት   ለፍፈናል  :  ተከራክረናል ።  ይህም   በሙሉ   ስህተት   ነበር ።  ነፃ   ከወጣንም   በሗላ   ይህንን   ስህተት   ማስተካከል   ሲገባን   አላደረግነው ም።  ይህም   እንደገና   ትልቅ   ስህተት   ሆኗል ።  ስለዚህም   ለተከበረው   የአማራ   ህዝብን   በዚህ   አጋጣሚ   ይቅርታ   እንጠይቃለን ።  ፍቅር   ያሸንፋል !”  (  አቶ   የማነ   ገብረአብ   የፕሬዚዳንት   ኢሳያስ   ቃል   አቀባይ ) መንፈሱን መዋቅራዊ ማድረግ ይጠይቃል እንደ ሥርጉተ ሥላሴ። መነሻ ሊንክ። https://www.satenaw.com/amharic/archives/62729 እሰይ ፀሎቴ ሰመረ አማራ በእግሩ መቆም ጀመረ !! ( ደመቀ እውነቱ ) August 18, 2018 አገባብ። እሺ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? እርእሱ ጸሐፊውን አይመለከትም። መረጃውን ያገኘሁበትን የለጠፍኩት ደስ የሚል ስንኝ አግኝቼበት ነው። ግን ደስታዬን ደግሞ በጥንቃቄ ማዬት እንደሚገባም ለማጠዬቅ ነው። ለነገሩ እኛ ደስታችን በአግባቡ ስለመያዛችን፤ በአግባቡ ስለማስተዳደራችን ያው ራሳችን ፈትሽን ወቄቱን ማግኘት እንችላለን። እንዴያውም ሌላ ቦታ ሳንሄድ የዛሬ ዓመት ይህን ሰሞን ሁለመናችን ቴዲ ነበር ዛሬ ደግሞ ዓይ