እውነትን መደፈር መልካምነት ነው ተቋማዊ መድረግ ደግሞ ጀግንነት!

ደስታን በጥንቃቄ።
„መመካት እና መታበይ ትዕቢትም ባለጸግነትመን ያጠፉታል፤
       እንደዚሁም ሁሉ የትዕቢተኞችን ቤት ያጠፋሉ።“
መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፬

ከሥርጉተ©ሥላሴ 
21.08.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ
ትልቁን የአማራ ህዝብ ያልሆነውን ነበር በማለት አማራ ጨቋኝአማራው የገዢ መደብ ነው። አማራ ጠላታችን ነው በማለት ለፍፈናል : ተከራክረናል ይህም በሙሉ ስህተት ነበር። ነፃ ከወጣንም በሗላ ይህንን ስህተት ማስተካከል ሲገባን አላደረግነውም። ይህም እንደገና ትልቅ ስህተት ሆኗል። ስለዚህም ለተከበረው የአማራ ህዝብን በዚህ አጋጣሚ ይቅርታ እንጠይቃለን። ፍቅር ያሸንፋል!” ( አቶ የማነ ገብረአብ የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ቃል አቀባይ)
መንፈሱን መዋቅራዊ ማድረግ ይጠይቃል እንደ ሥርጉተ ሥላሴ።

  • መነሻ ሊንክ።

እሰይ ፀሎቴ ሰመረ አማራ በእግሩ መቆም ጀመረ!!
(ደመቀ እውነቱ)August 18, 2018


  • አገባብ።

እሺ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? እርእሱ ጸሐፊውን አይመለከትም። መረጃውን ያገኘሁበትን የለጠፍኩት ደስ የሚል ስንኝ አግኝቼበት ነው። ግን ደስታዬን ደግሞ በጥንቃቄ ማዬት እንደሚገባም ለማጠዬቅ ነው።

ለነገሩ እኛ ደስታችን በአግባቡ ስለመያዛችን፤ በአግባቡ ስለማስተዳደራችን ያው ራሳችን ፈትሽን ወቄቱን ማግኘት እንችላለን። እንዴያውም ሌላ ቦታ ሳንሄድ የዛሬ ዓመት ይህን ሰሞን ሁለመናችን ቴዲ ነበር ዛሬ ደግሞ ዓይንህ ላፈር ሆኗል። 

ያ ምንድነው? ደስታን አያያዛችን መጠን እና ልክ ስሌለው ነው።
የነፃነቱም ታይቷል ሰው ገድሎ ዘቅዝቆ ሰቅሎ ፌስታ ማድረግ ይህም ሌላው ነፃነት ማግኝት እና በነፃነት መጠቀም ምን ማለት እንደሆን፤ ወይንም ዴሚክራሲያዊ መብት እና ዴሞክራሲያዊ ግዴታን አጣጥሞ ማስተዳደር ምን እንደሚያጥረን/ አቅማችን የቱ ላይ እንደሆን ታይቷል።

እስር ቤት ውስጥ ያን ሁሉ ፍዳ ያሳለፈ የወንጀል እስረኛ መኖሪያ ቤቱን ሲያነድ ጉዳዩ አልነበረም። ለሁሉም ነገር ልክ እና መጠን ቢኖረን ዕድሜ ዘመናችን ሁሉ መርዶ እና ሟርት አድማጭ እና ከብካቢ ባልሆን ነበር።

የሆኖ ሆኖ በዚህ ጹሑፌ አቶ ደመቀ እውነቱ መጨረሻ ላይ ያሰፈሯት መልካም ነገር ደስ አሰኘችኝ አና በዛች ላይ ትንሽ ብዬ ደስታውን ደግሞ በጥንቃቄ መያዝ ወደ ሚለው አመራለሁኝ። ይህን ጹሁፍ ወደ 468 ወገኖቼ ሼር አድርገውታል። ልበ ገብ ነበር ማለት ነው።

ልበ ገቧ ደስታ፤ ግን በጥንቃቄ

ትልቁን የአማራ ህዝብ ያልሆነውን ነበር በማለት አማራ ጨቋኝ: አማራው የገዢ መደብ ነውአማራ ጠላታችን ነው በማለት ለፍፈናል : ተከራክረናል ይህም በሙሉ ስህተት ነበርነፃ ከወጣንም በሗላ ይህንን ስህተት ማስተካከል ሲገባን አላደረግነውም። ይህም እንደገና ትልቅ ስህተት ሆኗልስለዚህም ለተከበረው የአማራ ህዝብን በዚህ አጋጣሚ ይቅርታ እንጠይቃለንፍቅር ያሸንፋል!!” ( አቶ የማነ ገብረአብ የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ቃል አቀባይ)

„የሰው ልጅ ስህተት የማይሰራ የለም ትልቅነት የሚለካው ስህተትን አምኖ የሚቀበል ነውአቶ የማነ ትልቅ ሰው ናቸው“
ጸሐፊው አቶ ደመቀ እውነቱ ናቸው ይህን የጻፉት። አቶ የማነ ገብራብን "ትልቅ ሰው ናቸው" ያሉትን እኔም እጋራዋለሁኝ። 

በዛ በኤርትራ እና በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ልዑክ ውስጥ ነበሩ። እናም ያስተላለፉት መልክት ለዛ ነበረው። ከልቤ ነበር ያዳምጥኳቸው። አሁን ደግሞ ይህ ሲታከል ቃና ይኖረዋ፤ ውስጠቱም ጥልቅ ነው።

እውነት ለመነጋረ የኢትዮጵያ የ43 ዓመት የችግር መሰረት ይሄው ጉዳይ ነበር። የዚህ ሁሉ ግፍ እና ማዕት ጠሪም አማራ ባልዋለበት የተደሎተበት መስመር እና የከፈለው ፍዳ ነበር። የርዕዮት፤ የመደብ ወዘተ ይባል እንጂ ዋነኛው አንኳር ጉዳይ ጸረ አማራ የሆነው ንድፈ ሃሳብ ነው።

ዛሬ እንኳን የወያኔ ሃርነት ትግራይ 27 ዓመት ሙሉ ቅጥቅጥ አድርጎ እዬገዛቸው ተርትሮ ናሙና እያደረጋቸው ቀን ከሌት አማራ ነው በደለን ሲሉ የሚደመጡት እነ ፕ/ ህዝቃል ጋቢሳ። ሚኒያ ላይ የነበረው ጉባኤም እድማታው የዛ ቅኝት ነበር። እኛን ነው የሚታጋለው አቅም አለኝ የሚለው ሁሉ። ግን አማራን ታግሎ ማሸነፍ አይቻልም። ስለምን? ቅነነቱ - ቸርነቱ - ደግነቱ አማኝነቱ በራሱ ዘብ ሲለሚቆምለት።

ከአማራ ውጪ ያሉ ሊሂቃን አብዛኞቹ ፓርቲ ሲመሰርቱም ይህን መርዝ ታቅፈው ስለሚሆን ያው ጫጭተው ነው የሚቀሩት። ቢወትፉትም ተነዳድሎ ዘመን እዬከዳው ሲሄድ ገመናቸው የአደባባይ ሲሳይ ሆኖ ነው የሚታዬው። ዙረው ተመልሰው ያው ወጥተው ወርደውም መጥተው የሚጣበቁት ደግሞ ከዛው ማህበረስብ ነው። መንጠላጠያቸውም ጋዣ ጃግሬያቸውም - ያው በጥርስ የተያዘው አማራ ነው።

በገርድምዳሜ ይሁን በጋድም በፈለጉት መልክ ጻፉትም ተናገሩቱም ከዚህ ጸረ አማራ ፍልስፍና ራሳቸውን ያላዳኑ ሊሂቃን ያው በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሲያንደልጣቸው ማዬት የተለመደ ነው። ጠብ የሚል የተግባር እና የድል ብሥራት ዋዜማም የለም። 

ከዚህ መሰል ከንቱ ፍልስፍና ወጥቶ ራስንም ወቅሶ ትክክል አልነበረም ብሎ በአደባባይ መመስከር መቼም ደፋርነትም ጀግንነትም ነው። ይህም በመሆኑ እኔ ባልሰማውም በዚህ ጸሁፍ ማስረጃነት አቶ የማነ ገብረአብ የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ቃል አቀባይ የገብረ ከይሲን ተስፋዬ ገብርአብን ጃርታዊ ፍልስፍና ሙሉ ለሙሉ የናደ ታሪካዊ ምስክርነት ነው ብዬ አስባለሁኝ።

ይህ እምነት በሉላዊነትም ሲታይ የመቻቻል አብነታዊ መስመር ሆኖ ሊወሰድ ይገባል ባይ ነኝ። ስለዚህ በአጋጣሚ እኔም ላመሰግናቸው እሻለሁኝ። ትልቁ ችግር ለጥፋቱ ሃላፊነት የሚወስድ አካል አለመኖሩ፤ ኑሯችን - ነፍሳችን ሁሉ ሰላሙ የተነፈገ እንዲሆን የሚያደርገው ከራስ ጋር ለመታረቅ ያለው አቅም ውስኑነት ነው ብዬ አስባለሁኝ።

ከዚህ ጋር ግን አቅሙ፤ ሥልጣኑም ስላላቸው አቶ የማነ በሚዲያቸው ገፋ አድርገው ዕውነታውን ለቀጣዩ ትውልድ በመደበኛ ለማስተማር፤ ተከታታይነት ያለው ተግባር ሊፈጽሙበት ይገባል ብዬ እስባለሁኝ። ምክንያቱም መርዙ ትውልድን አጥፍቷል፤ ትውልድን አክስሏል። ትውልድን በርዟል። ከዚህ አልፎ ደግሞ እኛ ይቅርታ ጠያቂ እንድንሆን ሁሉ ይፈለጋል።

አሁን እነ ኦቦ ሌንጮ ለታ ኢትዮጵያዊነትን ተቀብለናል ይላሉ፤ ፍልስፍናቸው ደግሞ በሰው ላይ ጭካኔን መፈጸሙ አልቆመም፤ በህሊና ጸረ አማራ መርዙ አልተነቀለም። ይህም በዚህ ከእኛ በቀጠለው ትውልድ እዬታዬ ነው። ፍልስፍናው በራሱ ከሰብዕ ውጪ የሆነ ነው። ጠረኑ ሰዋዊ አይደለም። ሰይጣናዊ መንገድ ነው ጸረ አማራነት። ኢ ስብዕዊነት፤ ኢ- ተፈጥሯዊነትም ነው። 

 ይሄ ማለት ምን ማለት ነው? እንደ ሮል ሞዴል የሚታዩት ገፋ አድርገው ራሳቸው የተቀበሉትን እውነት ወደ ተግባር ለመቀዬር ጉልበታም ተግባር መከወን አላባቸው ብዬ አስባለሁኝ። ፖሊሲም ቢያስፍልግ እንዲሁ። ምክንያቱም ትውልድን አምክኗል ይህ ፍልስፍና። 

ይህ ጅምር ፋፍቶ እንዲቀጥል ከተፈለገ ራሱን የቻለ ሥርዓተ ትምህርትም ያስፈልገዋል ማለት ነው። በወጉ የተደራጀ፤ በወጉ የሚመራ፤ በወጉ ፍሬው የሚለካበት። እኛ ወደ እኛ ለሚመጣው ንጽህና ሁሉ ውስጣችን ስለምናውቀው ችግር የለብንም።

ከእኛም በላይ አምላካችን ልዑል እግዚአብሄር ልብ እና ኩላሊትን መርማሪ ነውና እሱ ዳኝነቱን ይሰጠዋል። በምን ሁኔታ በምን መንፈስ ውስጥ ኤርትራ ወደ እኛ መጣሁ ስትል እንደ ተቀበልናት እሱ አንድዬ ያውቀዋል። 

ሁሉንም እንዳልነበረ አድርገን እርግፍ አድርገን ትተን በሳቃችን፤ በፈገግታችን ላይ ነው የተጋነው። ብዙም ፖለቲካው ፍተሻ ውስጥ አልገባነም … ምንም ቅድመ ሁኔታ አላስቀመጥነም።

ስለዚህ እኔ ደስ ብሎኛል፤ ደስታውን ግን በጥንቃቄ መያዝ እንዳለብን አስባለሁኝ። በሌላ በኩል መንፈሱን በትውልዱ ህሊና የማስረጹም ተግባር የጀንበር ስለማይሆን ራሱን የቻለ ተግባር እና ሃላፊነት ይጠብቃቸዋል አቶ የማነ ገብረአብን።  አሁን እኔ በአቶ ደመቀ መኮነን ላይ ያለኝን ልባዊ የሆነ መንፈስ እጅግ ረጅም ጊዜ ወሰዶብኛል።

ንግግራቸውን የማደመጥ አቅም እንኳን አልነበረኝም። እህቶቼ አስምለውኝ እንኳን አላደረግኩትም። ስለምን? ጊዜ ያስፈልገኝ ስለነበር። አሁን ከቆሞስ ተስፋዬ ጌታቸው ቤት ሳያቸው ደግሞ አዬነ ቆባቸውን ስመለከተው ወስጣቸውን፤ ስዳስሰው ከዚህ በኋዋላ እሳቸውን ለመቀበል ጊዜ ማቃጠል የለብኝም ብዬ የወሰንኩት ትናንት ነበር።

ስለዚህም ነው ይሄን ደስታ በጥንቃቄ እይዘዋለሁኝ ያልኩት። ምክንያቱም የተገፋንበት ዘመን፤ የእኛ እርህርህና እና ለሁሉም ምቹነት ሌላው የሚሰጠው ዕውቅና እና ምላሹ ተባደግ ስለነበር በዚህ አያያዝም ጊዜ ያስፈልጋል ባይ ነኝ፤

መርዙ እጅግ አደገኛ እና በዬፌርማታው ማነቆ ሆኖ ሲደቁሰን፤ ሲሰልቀን፤ ሲለነቁጠን ስለቆዬ፤ ለነገሩ አሁንም አላባራም። እርግጥ ነው እኔ በግሌ ከኤርትራውያን የደረሰብኝ አንዳችም ጥቃት የለም። አብረንም አድገናል። ግን እንደ ማህበረስብ ሲታይ ያው ከተጠላው ማህበረስብ መፈጠሬ በተዘዋዋሪም በኩል የሥነ - ልቦና ጉዳት አልነበረውም ማለት አልችልም።

ይህ እርምጃ በ66ቱ ቅኝት ከተፈጠሩ የፖለቲካ ሊሂቃን ከ ከኢትዮጵውያንም ሆነ ከኤርትራውያን የመጀመሪያው ያደርጋቸዋል አቶ የማነገብረአብ፤ ደፋር እርምጃ ነው። ፈጽሞም የማይጠበቅ ነው።

ሁሉም ጸረ አማራነቱን በጉያው ይዞ ነው እሽሩሩ እያለ ዛሬም መርዙን በአሳቻ ሰዓት እዬተፋ ወይንም በስውር ሁኔታ እዬከወነ የሚገኘው። ዘመን እና ጊዜ ግን እንዲህ እውነትን አንጥሮ ሲያወጣው አብሶ ለአማራ ማህበረሰብ ትልቅ የድል ምዕራፍ ነው።

አፈጣጠራችን ሃላፊነትን በመውሰድ፤ ቀድሞ በመልካም ነገር በመገኘት፤ እንደ ዋርካ ለሁሉም ጥላ እና ከለላ በመሆን፤ እውነት ናቸው ብለን ባመንባቸው ጉዳዮች ደፍረን ወጥተን የምንሞግት ሁሉንም አቃፊ ማህበረስብ ነን። ነገር ግን የደረሰው እና አሁንም ያላባራው ግለት እና ለይቶ የማጥቃት፤ የማስጠቃት ጉዳይ ዛሬም አለማባራቱን ሳስበው ይገርመኛል።

እርግጥ ነው ዛሬ የሚያጽናናኝ አማራ „አማራ ነኝ“ ብሎ ራሱን መቀበሉ ብቻ ሳይሆን በሚመቸው መልክ እሱነቱን በሚገልጽባቸው እንደ አልባሌ እና እንደ ተራ ነገር አይቶ ቀልቡን ሳይለግሳቸው በቆዩት አባው/ እመው ትተውለት ባለፉት ሌጋሲዎች ዙሪያ ትውፊት ትሩፋት፤ ታሪክ ባህል፤ ወግ ልማድ - ተኮር ጉዳዮችን የእኔ ብሎ አስጠግቶ መትጋቱ ዛሬ ላይ እጅግ ያሰደስተኛል።

  • ·      ደስታውን በጥንቃቄ ስለመያዝ ሁለተኛው ምክንያቴ።


ባጠናቀቀነው ሳምንት የአማራ ክልላዊ መስተዳደር ለኤርትራ መንግሥት ያቀረበው ግብዣ እንደ ነበር አዳምጫለሁኝ። በዚህ ላይም ጽፌያለሁኝ። ከምን አንጻር ብዬ።

በመጀመሪያ ጊዜ  የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የአማራ ዴሚክራሲያዊ ሃይል አገር ገብቶ ለመታገል ገባ ተብሎ ምን ከመሰለ ሶፋ ላይ በተንጣለለ እልፍኝ ኢትዮጵያ ላይ አይቼው እንደ ገና ደግሞ እነዛው ሰዎች ተመልሰው ኤርትራ ላይ ተሂዶ ድርድር ማድረግ የልጆች ጨዋታ ነው ለእኔ። 

ኢትዮጵያ አገር አገር አልመስለኝ እስክትል ድረስ ነው የገረመኝ። የቀደሙት እኮ እንዴት ብልሆች ነበሩ። ከውሳኔ በፊት መሰክረው ዘከረው ነው፤  ለእርምጃ አይቸኩሉም ነበር። ዛሬ እኮ እማዬው ብዙው ነገር እንደ ጀማሪነት ነው … ፊደል የቀረጸ አፍካዊ አገር፤ ሥርዓት የዘረጋ አፍሪካዊ አገር፤ ነፃነቱን ያቆዬ አፍሪካዊ አገር፤ እንደገና በነገሮች ሁሉ ሀ ሲሆን ያሳስባል እንደ ትውልዱ አባልነት። 

የሆነ ሆኖ ያን መሰል ጉዳይ በምንም መስፈርት ትክክል ነው ብዬ አላምንም። እንደዚህ ካስፈለገው ኢትዮጵያ መግባት አልነበረበትም፤ ከገባ ደግሞ ሁለተኛ ዙር ውይይት ኤርትራ ሄዶ ማድረግ አልነበረበትም።

ቀድሞ ነገር ትጥቁን ከፈታ እኮ ሲቢል ሆኗል ማለት ነው፤ ስለዚህ ሌላ ምርጫ የለውም። ልክ እንደ ኦነግ አቶ ዳውድ ኢብሳ ማለት ነው። በትጥቃ ሲታገል የነበረ ትጥቁን ከፈታ በቃ ባዶ እጅ ነው ማለት ነው። በወጣበት እግሩ ተመልሶ በሚያስማማው ጉዳይ ተስማምቶ ትግሉን ሰላማዊ በሆነ መልኩ መቀጠል ነው። አልያም ሌላ ቦታ ፈልጎ ደግሞ ሄዶ መድምዶ መሞገት ነው። አሸናፊነትም አይደለም ይሄ።

የሆነ ሆኖ ለእኔ የዶር ለማ መገርሳም ሆነ የአቶ ንጉሱ ጥላሁን የኤርትራ ጉዞ ከልብ ጠብ የሚል የፋክት ጭብጥ የለውም።

  • ·      አንድ ክልል እንደ ሉዑላዊ አገር?

      
ሌላው ገራሚው ነገር ባለፈውም ጽፌዋለሁኝ፤ የአማራ ክልላዊ መንግሥት ከአንድ ሉዑላዊ መንግሥት ጋር የኦፌሴል የግብዣ ድርደሩ ይግርም ነው?

ይሄ ከመርህ አንጻር ኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግሥቷ ወደዬት እዬሄደ ነው ያሰኛል። እንግዲህ ነገ ደግሞ የትኛውም ክልል ከሌላ አገር ጋር መሰሉን ግንኙነት ይፈጽማሉ ማለት ነው። ለእኔ ይሄ ሥርአተ አልበኝነት ነው። ለነገሩ ሰው ተገድሎ ተዘቅዝቆ ተሰቅሎ ህዝብ ተሰብስቦ ገዳዮችን አጅቦ እያጨበጨበ ፌስታ የሚታይባት አገር ሆና የለምን?በ አደበባይ የተገደለ ኮኮብስ ይሄው ወር ሊደፍን ነው እኮ ጭጭ ከሆነ። 

የሆነ ሆኖ ለአንዲት ልዑላዊት አገር ለዛውም ኢትዮጵያን ለምታክል አገር እጅግ አደገኛ ዝንባሌ ነው። ይህን ዛሬ ማስተካከል ካልተቻለ „እናቴ በእንቁላሌ በቀጣሽኝ ያመጣል“

እርግጥ ነው ትግራይ ይህን ከሱዳን ጋር መፈጸሙን አውቃለሁኝ። ትግራይ መሪ ፓርቲ ነኝ ዘመኑ የትግራይ መሳፍንታት ነው ብሎ ያስብ ስለነበር ይህን አደረገ፤ ይህም ብቻ ሳይሆን የአማራ ክልልን ተዳፍሮ ኮ/ ደመቀ ዘውዱን የዜግነት ነፃነታቸውን ጥሶ የወሰደው እርምጃም ከዚህ መንጠራራት የመነጨ ነው። አሁን ያለው ነገር ሁሉ ልክን ካለማወቅ ያመጣው ጦስ ዛሬ ካለንበት አደረሰ።

የአማራ ብሄርተኝነት በዚህ አቅሙ እንዲወጣ ያስቻለውም ያ እጅግ ልክን እና መጠኑን ያላወቀ መንጠራራት ነበር። ወደፊትም አማራን በሚመለከት በዚህ መሰል ጉዞ ማንም የማንም የበታች እና ሎሌ ስላልሆነ ራስን አብቅቶ እንጂ በብራና እሰጣ ገባ መብት ሰጪም መብት ነሺም ሊኖር ከቶውንም አይቻለውም።

ወደ ቀደመው ሃሳቤ ምልስት ሳደርግ እኔ እንደ ሥርጉተ ሥላሴ አማራ ስለሆነ ብቻ ትክክል ሳይሆን፤ ትክክል ነው ብዬ እማንቆለባብስት ምንም ምክንያት የለኝም።

መርህን የጣሰ ግብዣ ነው፤ ስለሆነም ይሄ በአስቸኳይ መቆምም አለበት ብዬ አምናለሁኝ። ደረጃውን ያልጠበቀ ግንኙነት ነው። ጦሱ የዘመን ነው። ለዛወም ብአዴን? ቀድሞ ነገር ብአዴን ምን አቅም አለውና? ወጥቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት እኮ ሁለት ሰው ነው የሚታዬው፤ በቃ።  

ይህን እንደ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነትም በቅንነት በንጽህና የማስተናግደው አይደለም። ምክንያቱም ይህን መሰል ከሥርዓት የወጡ ግንኙነቶች ነገ ኢትዮጵያ የምትባል አገር እና ኢትዮጵያዊ የሚባል ዜጋም ስለሚያሳጣን ነው። 

እንደ ተበታተኑት እንደ ራሺያ፤ ዩጎዝላብያ የመሆን ዝንባሌ እና አዝማሚያም ነው የሚታዬኝ። ኤርትራ አገርነቷ ትንሽ መሆኗ ሳይሆን ድርጅቷም መሪዋም በሁሉም ዘርፍ ከብአዴን ጋር የማይመጣጠን ነው። ዝም ተብሎ ዘው የሚባልበት የፖለቲካ ቅኝት የለም። ዕድሜ ጠገብ፤ ተመክሮ ጠገብ ድርጅት ነው ሻብያ። የበቃ አቅም እና ክህሎት አለው ለዬትኛውም ዘርፋዊ ግንኙነት። 

ስለሆነም አቅምን ያልመጠን ግንኙነት መሆኑ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዊ ፋይዳውንም በፍጹም በፍጹም ይህ ከታሪክም፤ ከትውፊትም፤ ከፖለቲካዊ አቋምም ጋር በፍጹም በግሌ ልቀበለው የማልችል ጉዳይ ነው።

አማራነት አውራው ማንነቴ ኢትዮጵያዊነት ወስጥ እንጂ አማራነቴ አውራው ማንነቴን ጨፍልቆ ከሆን አልቀበለውም። አገር ሲኖረኝ ነው እኔ አማራ ነኝም፤ የተዋህዶ ልጅ ነኝም፤ ሴትም ነኝ፤ ዜግነትም አለኝ ማለት የምችለው። 

ልዑላዊት አገር ዜጋ መሆን እና አገር አልቦሽ መሆን፤ በነፃነት የኖረ ህዝብ መሆን እና በባርነት የኖረ ህዝብ መሆን ማለት ውጪ ሲወጣ ነው የሚታወቀው። በራሱ የሚሰጠው አቅም ህሊናዊ ነው። ግዝፈቱ የመንፈስ ነው።

አገሬ ኢትዮጵያ ልዑላዊት አገር ናት። ልዑላዊነቷን ጠብቃ በመኖሯ በዓለም አቅፍ ደረጃ ተከብራ ብቻ ሳይሆን አብነቷን የተከተሉ፤ መኩሪያችን ያሉ ሰንደቋን የእኛ ብለው የተቀበሉ እጅግ በርካታ አገሮች አሉ። ያን ክብሯን፤ ያን ሞገሷን፤ ያን ማህባዋን ዘመን ባመጣው መከፋት ሆነ እንደ ማህበረሰብ መገለል እንድታጣ ፈጽሞ አልፈቅድም።

ስለሆነም የኤርትራ መንግሥት ሊደራደር፤ ሊዋዋል፤ ሊነጋገር የሚችለው ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እንጂ ከዬክልሎች ጋር ሊሆን አይገባም። ይህን አድገመዋለሁኝ ሥርዓተ አልበኝነት ነው - ለእኔ። የኢትዮጵያን ሉዑላዊነትም የሚዳፈር እርምጃ ነው። ክብሯን ቁልቁል ያደረገ ሂደት ነው። አገራችን ኢትዮጵያ ናት። ዜግነታችንም ኢትዮጵያዊነት ነው።

የኤርትራ መንግሥት ግንኙነቱ በቀጥታ ከክልሎች ጋር ሳይሆን ይልቁንም ከማዕከላዊ መንግሥት ጋር ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ መሆን አለበት። ማዕከላዊ መንግሥት ጋር በሚኖረው ስምምነት ፈቃድ እና ውል መሰረት ሊሆን ይገባል።

ግንኙነቱ መንግሥታዊ ሳይሆን ግን እንደ ማንኛውም የሌላ አገር ዜጋ አማራ ክልልን ለ እረፍት ፈቅዶ መጉብኘት ከልካይ የለበትም። እንዲያውም ከሌሎች ኤርተራውያን ለእኛ ይቀርቡናል፤ ልዩነት ላውጣ ቢባልም የለንም። ያልታደልን ሆነን እንጂ።

እንደ ግለሰብ ለእረፍት ለማሰለፍ፤ ቤሰተሰብ ለመጠዬቅ ጋብቻም ሊኖር ይችላል በዚህ መልክ ቢከውን ችግር የለበትም። ነገር ግን ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ይፋዊ ጉብኝት ምን አቅም አለው የአማራ ክልላዊ መንግሥት የኤርትራን መንግሥት የመጋበዝ? ፖለቲካዊ ብቃቱም አቅሙም አይፈቅድለትም። ከውነት መነሳት ያስፈልጋል። ባዶ 6 የታሰሩ ዜጎችን ማስፈታት ያልቻለ?

ይህን ተልዕኮ ለመወጣትም የደህንነቱም ጉዳይ አለ።
የተደራጁ ሽፍቶች ባሉባት አገር አንድ ነገር ቢፈጠር የዘላለም ጠባሳ ነው የሚሆነው። ይህ ደግሞ አይቀሬ ነው።

እኔ የሚገርመኝ የአማራ ክልላዊ መንግሥት ሥንት ተግባር እያለበት ጊዜውን ሲያባክን የማያው በሚያስቁ ጉዳዮች ላይ ነው። አሁን የአቶ ንጉሡ ጥላሁን በሚሊኒዬም አዳራሽ ተገኝቶ ንጉሥ¡ ጃዋርን መቀበል ያን ያህል ብድግ ቁጭ ያልተጋባ ሥራ ፈትነት ነበር።

ይልቅ ወልቃይትን፤ ጠገዴን፤ ራያን፤ የመተከልን ጉዳይ መልስ እንዲያገኝ መትጋት የአባት ነበር።  ከዛ ያሉ የነጻነት አንበሶችን ጊዜ ሰጥቶ ማወያዬት ያልቻለው ብአዴን ለሳይበር ጀግና ያን ያህል ሲያደግድግ አማራነቴን እጅግ ነው የተጸዬፍኩት። አማራ እንዲህ አይደለም።

? ይልቅስ በባዶ 6 የሚማቅቁ ንጹሃን ለማስፈታት አይጥርም?  በራሱ በክልሉ የታሠሩ የፖለቲካ እስረኞችን በወጎ እንዲፈቱ አያደርግምን? በዬክልሉ የተበተኑት የአማራ ልጅ ስንት ፍዳና መከራ ነው ያሳልፉት፤ ዛሬም የሚያሳልፉት፤ ጊዜው ከኖረው ስለነሱ ቡድን አደራጅቶ ለችግራቸው አይደርስምን?

በዚህ ዓመት ኦሮምያ ከዱከም እስከ ቢሸፍቱ 80 ኢንደስትሪዎችን ለመጀመር የሚያስችል ስምምነት ከቻይና ጋር አዳምጫለሁኝ፤  ይህን በመሰሉ ጉዳዮች ላይ ከዓለም ከድህንት ወለል በታች ስለሆነው የአማራ ክልል አስቦ እና ሞግቶ መስራት ነበር ተግባር ማለትስ?

እንቦጭን ያህል መከራ ተሸክሞ የአማራ ክልል የሚሰራው ዘመናይነት እና ኬክ ቆረሳ ይመረኛል። አባይም በአረም ተከል መወጡን አዳምጫለሁኝ።

እራሱ ትራኮማ እኮ ከዓለም በከፍተኛ ደረጃ የሚያጠቃው አማራ ክልል ነው፤ አሁንም ያላባረው በሴት ወጣቶች ላይ ያለው እንደ ጥንቸል የመሞኮሪያነት ጣቢያነትም እዛው ውስጥ ነው፤ እንደዚህ ባሉ ህይወት ባላቸው ነገሮች ከመትጋት ይልቅ የፉክክር እና የእዩልኝ ነገር ላይ ማተኮር አብሶ 27 ዓመት ጨለማ ውስጥ ለኖረው አማራ የሚፈይደው አይኖርም።

ለዚህ ነው ይህን ደስታ በጥንቃቄ እይዘዋለሁ ያልኩት። አቶ የማነ ገብርአብ ያን ያህል ተጸጽተው ያቀረቡትን የይቅርታ መንፈስ ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩት የመጀመሪያውም ሊሂቅ ናቸው ከ66ቱ መከራን ከጫኑብን የፖለቲካ ሊሂቃን መካከል መሆናቸው ደስ ብሎኝ ግን ወደ አማራ መሬት የሚደረገውን የዴፕሎማሲያዊ ሁኔታ ግን እኔ በደንበር ስለማዬው ደስታዬም አለመሆኑን መግለጽ እሻለሁኝ።

ያልተገባ ግንኙነት ከትርፉ ኪሳራው ያመዝናል። ልቅነት  ኢትዮጵያን ለምታክል ታላቅ ዘመን ጠገብ አገር ፍጹም የማይመጥናት ብቻ ሳይሆን ለማናቸውም ውጪያዊ ግንኙነት ገደብ ሊበጅለት ይገባል።

የአማራ ክልል መጀመሪያ መታገል ያለበት አማራ እንደ ዜጋ የሚታይበት፤ ህጋዊ ጥበቃ የሚያገኝበትን መሰረታዊ የህልውና ጉዳይ እንጂ እንደዚህ መሰል አገራዊ የዲፕሎማሲ ጉዳይ  የእነሱም ድርሻም አይደለም። ጥንቃቄ ያስፈልጋል። „ሁሉ ተፈቅዶልኛል ሁሉ ግን አይጠቅመኝም“ ይላል ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ። ቢፈቅድላቸው እንኳን አሁን ያለው አቅማቸው ይህን ማስተናገድ አይችለውም።

እንኳንስ የማንችለውን ብንችል እንኳን ያለተገባውን እና የማይጠቅመውን ከ50 ዓመት በኋዋላ ሳይሆን ዛሬ አለመጥቀሙን አይተን በውጥኑ ማስቆም ያስፍልጋል። ነገ ደግሞ ሌላ ጣጣ እና ምንጣጣ ማምጣቱ አይቀሬ ነውና።

ሥርዓት የያዙ ግንኙነቶች አይዛቡም፤ እውነትም አይፋለስባቸውም፤ ዘላቂም ናቸው። መርህ መራሽ ክንውኖች ዘመን ጠገብ ሰብልን ያስገኛሉ።

አሁን ኤርትራ አንድ የኢትዮጵያ ክ/ አገር አይደለችም። ልዑአላዊት አገር ናት። ልዑላዊት አገር ደግሞ ግንኙነቷ ከልዑላዊ መንግሥት ጋር ነው። ይህን ማስጠበቅ መቻል ግድ ይለዋል የአብይ ካቤኔ። ህግ መከበር፤ መርህ መከበር ለሁሉም ፍትሃዊ ያደርጋል። ጉዞውንም የተሳካ ያደርጋል።

ወቅታዊነት፤ ወረተኝነት፤ አፍለኝነት ለግል ሰብዕና እንኳን አይበጅም እንኳንስ አገርን በዘላቂነት ለማስቀጠል። ለዛውም ኢትዮጵያ ወዘተረፈ ችግር ያለበት፤ ለውጡም ገና ያልጠና እና በብዙ ነገሮች እዬተናጠ ነው ያለው።

በስክነት የሚታዩ ነገሮች ሊኖሩ ይገባል። በዬቦታው የጥድፊያ ያለሰከኑ - ያልበሰሉ  - ጮርቃዊ ፉክክሮች የትም አያደርሱም።

ኤርትራውያን ላሊበላን ሊዩ፤ ፋሲልን ሊዩ፤ ጣንን ሊጎበኙ  የእርፍት ጊዜያቸውን ሊያሳልፉ ይችላሉ፤ ነገር ግን መንግሥታዊ ግንኙነትን በሚመለከት ማዕከላዊ መንግሥት አለ። ደግሞም ከበቂ በላይ ሊሆን ከሚገባው በላይ ነገር ሁሉ ተከውኗል። እኛም መንፈሳችን ሸልመናዋል። ሁሉንም ነገር እርስት አድርገን፤ ምንም እንዳልተፈጠረ አድርገን፤ ግንኙነቱን ሳንጠረጥረው ሳንመነጥረው ደስ ብሎን ተቀብለናዋል አገር ለ አገር ግንኙነቱን፤ ክልል ለአገር ግን እእ፤ አይመችም።
  • ·      ዝርግነት።

„ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል“ ይላሉ ጎንደሮች ሲተርቱ። ያልተገባ ግንኙነት መጨረሻው ውድቅት ነው። አገር አለችን ኢትዮጵያ የምትባል። ተወደደም ተጠላም ይህቺ አገር ሉዕላዊት አገር ናት። ሉዑላዊነቷ የሚጠበቀው ደግሞ ሁሉም በዬምድጃው ንጉሥ ነኝ ስላለ አይደለም።

መርህ አለ። መርሁ ደግሞ በሁሉም ዘንድ ሊከበር ይገባል። ማዕከላዊ መንግሥት ያላት አገር እንዲህ በዬፊናው ከሌላ አገር ጋር የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከተጀመረ ነገ ከዛሬው በላይ እጅግ አስፈሪ ነው የሚሆነው።

ብዙ ውስብስብ ነገሮች ነው ያሉበት። ለዛውም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፍልስፍና ግልጽ አይደለም፤ ድብስብስ፤ ድብቅብቅ ያለ ጉድ ነው። ይህን የተሸከመች አገር አሁን ደግሞ ሌላ ችግር ይህን መሰል ዝርግነት ማስተናገድ ጨለማ ነው ለእኔ። እስኪ አገር የገቡትን ተፎካካሪ ፓርቲዎች አስማምታ መክታ ለመቀጠል ያብቃት? ህም!

ስለነገ እኔ ይጨንቀኛል ከዛሬው በላይ። ስለማግስት ይገደኛል ከዛሬው በላይ ለእኔ። ጊዜያዊ ችግርን ለመፍታት ዘላቂ ችግር ማብቀል ስልተቢስነት ነው።

መሆን ያለበት በጊዜያዊ ችግር አፈታት ላይ ዘላቂ ችግርን አስቀድሞ ማዬት ነው ጠቃሚው ነገር። ዛሬ ያለውን መከራ ለመሸከም የችግሩ አፈታት ዘዴ ነገን የማያዳግም ስለመሆኑ እርግጥ መሆን ያስፈልጋል።

አንድን ችግር ስትፈታ ሌላ ወዘተረፈ ችግርን አብቅሎ መሆን አይገባውም። ይልቁንም ነጥለህ ያወጣኸው ችግር ከሥሩ ነቅለህ በመጣል ችግር ወላጅ አላማድረግ ነው የፖለቲካ ብልህነት።

መልካም ነገሮችም ቢሆን መታዬት ያለባቸው ከዚህ አንጻር ነው። መልካም ነገሮች ውስጥ ያሉ ስርክራኪ ጉዳዮች ማጣሪያ፤ ማንዘርዘሪያ ወንፊት ቀድሞ ሊዘጋጅላቸው ይገባል። ስለወደድነው ብቻ ሳይሆን የወደድነው ነገር እና ግብረ ምላሹን አስቀድሞ መመርመር ያስፈልጋል። መልካም ነገሮችችግር ፈጣሪ ሊሆኑ ባይችሉም እንኳን ቢሆን ብሎ የመፍቻ ቁልፎች በቅደም ተከተል ሊዘጋጁለት ይገባል።

እራሱን ያልቻለው ብአዴን በወዘተረፈ ችግር ተዘፍቆ ገና ራሱን ማጥራት ብቻ ሳይሆን ከቅኝ ተገዢነት ወጥቶ ራሱን ችሎ ለመቆም ሳይችል ይህን መሰል ብሄራዊ ጉዳይ እሸከማለሁ ብሎ መነሳቱ በራሱ የውስጡን መሻት እና ያለበትን አቅም ያለማወቅ ችግር ይመስለኛል።

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን ያሸነፈ ሚስጢር!

የኔዎቹ ኑሩልኝ።

ማለፊያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።