ልጥፎች

አላዛሯ ኢትዮጵያ አምላክ አላት።

ምስል
የትውልዱ ብክነትን ለማስቆም ከቶ ለማን አቤት ይባል? „አቤቱ እስከ መቼ ፈጽመህ ትረሳኛለህ?“ መዝሙር ፲፪ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 08.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።                                  ከቶ የአማኑኤል አባታችን ሥጦታው እንዴት ይዞች ኋ ዋል? እኔ ፈጣሪ በቃቸሁ አለን የሚል ዕምነት ነበረኝ። ግን የሆነ አልመሰለኝም። ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል የሚስፈልገው የአዕምሮ ላውንደሪ ነው ። የ50 ዓመት የሴራ ፖለቲካ ባህል አሁንም አለ እንዳለ። ይህን እንለውጣለን ብለው የተነሱት የለውጥ ሐዋርያት ትግላቸው ከራሱ ከሊሂቃኑ ህሊና ጋርም ጭምር ነው። በምን ኦሞ አጥበው ከአዲሱ የአሰተሳሰብ መንፈስ ጋር ሊያዋድዱት እንሚቻላቸው ብርታቱን ይስጣቸው። እነኝህ የበቀልን ዓውደ ለመደምሰስ የተነሱ አዲስ ቡቃያዎች ያን  የቆዬውን የታቆረ የሴራ የሽምቅ ውጊያ አስወግደው የእነሱን ንጹህ ድንግል አሰተሳስብ እንዴት ማዋለድ እንደሚችሉ ፈተናው ውሃ ያዘለ ተራራ ሆኖ እዬታዬ ነው። ራሱ የፖለቲካ ሊሂቃኑ ለመለወጥ ያላቸው ፈቃድ ምን ያህል ይሆን? ራሳቸውን ማሸነፍ ቢችሉ አባሎቻቸውን፤ ደጋፊዎቻቸውን በዚህ አዲስ  የአስተሳብ ባህል ለመቀረጽ እንዲህ አይችግርም ነው። የዬትኛውም የፖለተካ ድርጅት ይሁን ንቅናቄ ይሁን ግንባር መጀመሪያ ከራስ የመነሳትን ተጋድሎ መጀመር ያለበት ይመሰላል። ራስን ሳይለውጡ ተከታይን ሆነ አባልን መለወጥ ፈጽሞ የሚቻል አይመስልም። ለውጡ ወረቀት ላይ አይደለም። ለውጡ ከውስጥ መሆን አለበት። አንድ ሊሂቅ የዘመተበትን ሌላኛውን ሊሂቅ ራሱ ሄዶ ይቅርታ አድርግልኝ ካላለ አሁንም ቦክሱ ቀጣይ ነው የሚሆነው። ተጎጆው ደግሞ ሰላም የመናፈቀው ህዝብ ነው። አሁንም እንደ ትናንቱ መካሰስ ስሞታ

የኢትጵያ ህዝብ የፍቅር ስጦታን ኤርትራ አደራውን የት ላይ አኖረችው?

ምስል
ፍቱት። „በፊቴም ደጃፉ ሁሉ የተከፈተ ነው፤ በእሳት ቅርጽም የተሠራ ነው።“ መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፶፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ 07.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።               እሙ በአንቺ የመንፈስ ድንግልና ብቻ የፍቅር ተፈጥሮ አደራ አለ።  ·        ፍቱት አንድ። እንዴት ናችሁ ውዶቼ? ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ ፍች ያጣሁለት ህልም አዬሁኝ። ስትፈጠር አንድ ጡት ያላት ሴት በህልሜ አዬሁኝ። በዚህ ነጮቹ ሲፈልጉ ጡታቸውን በሰው ሰራሽ እንደሚያስተልቁት በኦፕራሲዮን ወይንም እንደሚያሳድጉት አይደለም። የሴቶች ጡት በተፈጥሮው ግራ እና ቀኝ ደረት ላይ ነው የሚበቅለው። ይህን እናት ጡት የጠባው ሁሉ ያውቀዋል። ይህ በህልሜ ያዬሁት ግን ማህል ላይ የበቀለ፤ ቅርጹ ሆድ የሚመስል ነው። የደረት ሆድ ልበለው ይሆን? እንደዛ ነው እኔ ዛሬ ሌሊት ያዬሁት። እንደነዚህ ያሉ ገራሚ ህልሞች ሳይ ስነቃ ቤቴ ራሱ የእኔ መሆኑን እጠራጠራለሁኝ። አንድ ጊዜም „እኔ ድምጻችን ይሰማ ነኝ ስል እንዲህ የሚገረም ህልም አይቼ ነበር። ደፍሬ ልናገረው አልችልም እጅግ ከባድ ህልም ነበር ያየሁት።  ሌላ ጊዜ ደግሞ ሰማይ ላይ ብዙ ሰረጋላዎች የኢትዮጵያ ሰንድቅዓላማ ለብሰው አዬሁኝ። ሌላ ጊዜም አውስትራልያ በጋብቻ ልሄድ ወስኜ ነበር እና አውሮፕላን ሰማይ ላይ ቆሞ የማይንቀሳቀስ፤ የማይሄድ፤ ልክ እንደ መሬት ሞተሩን አውሮፕላኑ አጥፍቶ ግን ሰማይ ላይ ቆሞ  እንደ ኩሬ ውሃ ረግቶ አይሁኝ። ዛሬ ደግሞ ስትፈጠር የደረት ሆድ ያላት ግን ጡት የሆነ ጨፍ ያለው ልስላሴውም ተፈጥሮውም ጥራቱም ኢትዮጵያዊ የሆነ ጡት አዬሁኝ፤ እርግጥ ነው አንድ መሆኑ ከተፈጥሮ ውጪ ነው፤ ይዘቱ ጡት ነው፤ አፈጣጠሩ ማህል ላይ ነው ብቻ ከብዶኛል?