ልጥፎች

አላዛሯ እምዬ ኢትዮጵያ እናቷንም አገኘች።

ምስል
አላዛሯ ኢትዮጵያ ራሷን አገኘች። አላዛሯ ኢትዮጵያ እናቷንም አገኘች። አላዛሯ ኢትዮጵያ ውስጧንም አገኘች! „አድርገህልኛል እና ለዘላለም አመሰግንሃለሁ።“ መዝሙር ፶፩ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ© ሥላሴ 26.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·       መ ቅድመ አንስት። ኢትዮጵያ ዓለም ናት። ኢትዮጵያ መለያ ናት። ኢትዮጵያ ነባቢት ናት። ኢትዮጵያ ሥነ- ህይወት ናት። ኢትዮጵያ አናባቢም ናት። ኢትዮጵያ ተነባቢም ናት።፡ኢትዮጵያ ሥህነ - ነፃነት ናት። ኢትዮጵያ ብጡለ -ክብር ናት። ኢትዮጵያ የመሆን እጬጌ ናት። ኢትዮጵያ ጥልቅ ናት። ኢትዮጵያ የዕድማታ ቅኔ ማዕዶት ናት። ኢትዮጵያ ንጥር ትርጉም ናት። ኢትዮጵያ መነሻ መሠረት ናት። ኢትዮጵያ ሉላዊ ህሊና ናት። ኢትዮጵያ ድርብ ግርማ ናት። ኢትዮጵያ ህላዊ ሞገስ ናት። ኢትዮጵያ ስመኝሽ ናት። ኢትዮጵያ ስናፍቅሽ ናት። ኢትዮጵያ ተስፋ ናት። ኢትዮጵያ ተናፋቂ ፋና ናት። ኢትዮጵያ ትርጉም ናት። ኢትዮጵያ አዲስ አመት ናት። አገር ሃይማኖት ነው። አገር አካል ነው። ኢትዮጵያም ሃይማኖትም አካልም ናት። ኢትዮጵያ ውስጥም ናት። አዎን! ኢትዮጵያ ውስጧን እንሆ አገኘች። ውስጧን ብቻ ሳይሆን አላዛሯ ኢትዮጵያ እናቷን ጥበብ ሰጣት።  ለለበጣ ሳይሆን፤ ለፖለቲካ ፍጆታ ሳይሆን፤ ቀልብ ለማሳቢያ ሳይሆን፤ ለጊዜያዊ የሥልጣን ሹመት ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጧን ውስጥ ያደረገች እናቷን  በእርግጥም አገኘች። ኢትዮጵያ የኖረ የተከመረ መከራ ቢኖርባትም፤ ችግሯ እፍ ተብሎ በአንድ ጊዜ ባይተንም፤ ግን መተንፈሻ ቧንቧዋን አግኝታላች ብዬ አምናለሁኝ። የራሄልን ዕንባ የሰማ አምላክ እንሆ አደማጣት እላለሁኝ። ኢትዮጵያ የሚለውን ሥሟን መቀበል ጋዳ በሆነበት ዘመን፤ እንሆ አላዛሯ

በሴቶች እና በአብይ ዙሪያ ሥርጉተ በታህሳስ 26/2017 ምን ብላ ነበር?

ምስል
        አብይ ኬኛ!  ክፍል ሦስት -  ለቅኖች ብቻ።            አብይ ለእኛም  ለሴቶች አናባቢያችን                         Vowels ነው። „ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ማልዶ በተነሳ ጊዜ፤ አስቀድሞ ሰባት አጋንንት ላወጣላት ለመግድላዊት ማርያም ታዬ።  እርስዋ ሄዳ  ከእርሱ ጋር ሆነው ለነበሩት፤ ሲያዝኑና ሲያለቅሱ ሳሉ አወራችላቸው። እነርሱም ህያው እንደሆነ  ለእርስዋም አንደታዬ ሲሰሙ አላመኑም። ከዚህ በኋዋላ ከእነርሱ ለሁለት ወደ ባላገር ሴሄዱ፤ በመንገድ በሌላ  መላዐክ ተገለጠ። እንርሱም ሄደው ለሌሎች ሄደው አወሩ፤ እነዚያን ደግሞ አለመኗቸውም። ኋላም በማዕድ  ሳሉ ለአስራአንዱ /ሐዋርያት/ ተገለጠ። ተነሥቶም ያዩትን ስላላመኗቸው፤ አለማመናቸውን የልባቸውን  ጥንካሬ ነቀፈ። እንዲህም አላቸው፤ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።  ያመነንም፤ የተጠመቀም፤ ይድናል። ያለመነ ግን ይፈረድበታል“    (የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ  ፲፮ ከቁጥር ፱ አስከ ፲፯። ዮሖንስ ወንጌል ምዕራፍ ፳ ከቁጥር ፩ ጀምሮ … )  የበለጠ ሚስጢሩን ለማዬት የዬሖንስ ወንጌል ምዕራፍ ፫ ከቁጥር ፩ ጀምሮ ያለውንም በጥልቀት መመልከት ይቻላል። በመንፈሳዊ ህያዊነት ቃለ ህይወቱ መረቡን በረቂቅነት በውስጣችን ይዘራል። ይሄም ነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሚስጢር። የክርስትናም። ዶር አብይ አህመድ አኮ የቅኔ ማዕዛ ናቸው። እሳቸው ስላነሱት ነው እኔም የጹሁፌ ባርኮት ያደረኩት። ከሥርጉተ ሥላሴ ታህሳስ 26/ 2017 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ·           በ ር።   ቃል እና ተግባር! በሙሉ ተስፋ እጠብቃለሁኝ የድርጊት እመቤትነትን! በመሆን ! እውነት እና ኪዳን በ