ልጥፎች

ለምን ሲሰላ።

ምስል
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። „እግዚአብሄርን መፍራት ዘመንን ታረዝማለች። የኃጣኣን ዕድሜ ግን ታሳጥራለች።“ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ 10 ቁጥር 27 ለምን ሲ ሰ ላ። ሥርጉተ © ሥላሴ Sergute © Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። 04.01.2020 በኢትዮጵያ ተሰምተው የማይታወቁ የጭካኔ ድግግሞሽ በዙር እያዬን ነው። የኦዳ ሥርዕዎ መንግሥት ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ የጭካኔ ፋክክርም አያለሁ። ሥልጣን ጠቅልሎ መያዝ ብቻ ሳይሆን አማራ ክልል አቅም ብቅ እንዳይል በባሩድም በካቴናም ቅጣቱ ድንበር የለሽ ነው። ይህም ሆኖ የአማራ ክልል በባዶ እጁ ሆኖ ይቀናበታል። ስለዚህም አቻዊ ጭካኔ ተከስቶ ክልሉ ይወገዛል። ኦሮምያ ላይ የሰው ልጅ ተገድሎ ተዘቅዝቆ ሲሰቀል፣ አማራ ክልል ላይ ለጥናት የሄዱ ንፁኃን በድንጋይ ተቀጥቅጠው ተገደሉ። ኦሮሚያ ክልል ላይ ቤተክርስትያን ሲቃጠል አማራ ክልል ላይ መስጊድ ይቃጠላል። ኦሮምያ ላይ መፈናቀል ሲኖር አማራ ክልልም ላይ መፈናቀል ይከሰታል። ኦሮምያ ላይ የፓርክ ቃጠሎ ሲኖር አማራ ክልልም ላይ ይኽው መሰሉ ይከሰታል። በኦሮሚያ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ታግተው የደረሱበት ሁኔታ አይታወቅም ሲባል አማራ ክልል ህፃናት ታግተው ይረሸናሉ። በዚህ ውስጥ ኦሮምያ ለሚፈጠረው ቀውስ የኦዳ መንግሥት ዝምታን ይመርጣል፣ አማራ ክልል ሲሆን ደግሞ ግሎባሉ ዓለም እንዲያውቀው ከጠሚር ጀምሮ ልብ የተገጠመላቸው ወጥተው ሲያወግዙ ይደመጣል። ·        ሁለት ነገር።

ለለመደበት ገዳይ መንፈስ፣ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ሰኔል ቢያሰናዳስ?

ምስል
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። „ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል ሰነፍ ልጅ ግን ለ አናቱ ኃዘን ነው።“ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ 10 ቁጥር 1 ለለመደበት ገዳይ መንፈስ፣ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ሰኔል ቢያሰናዳስ ? ሥርጉተ © ሥላሴ Sergute © Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። 04.01.2020 የለመደበት ገዳይ መንፈስ የአዲስ አበባ ወጣቶችን ሰብስቦ ከምትሞቱ ምረጡን ሲል ሰባዕዊነትን ደመራ አድርጎታል። ዴሞክራት ነኝንም በቹቻ ምኞት ሸኝቶታል። በዚህ በሰሞኑ የጠሚር አብይ አህመድ ንግግር ብቻ የኢትዮጵያው ምርጫ ቦርድ „ የነፃ እና ፍትኃዊ ምርጫ ሞቶ“ እንጦርጦስ ተልኳል። ከሹመት ማግስት ሁሉም ክልል ስብሰባ ተካሂዷል፣ ከድሬ እና ከአዲስ አበባ በስተቀር። የት የሚታወቀውን ይሆን አዲስ አበቤ   ዛሬ የሚፈለገው ? መሪዬ ብሎ በራሱ ወጪ ህይወቱን ገብሮ ግን ዓመት ሳይሞላ በጠራራ ፀኃይ የተረሸነው ? በደል ይረሳል ወይስ ይለመዳል ? 1300 ወጣት ጦላይ የተወረወረ፣ ይህም አልበቃ ብሎ የምትኖረው በኪራይ አገር ነው ተብሎ የሥነ ልቦና ጦርነት የተከፈተበት ህዝብ ዛሬ እንዴት ተናፈቀ ? በደል ይረሳል ወይንስ ይለመዳል? በመኖሩ ተፈርዶ የመሰብሰብ፣ መሪውን የመምረጥ፣ ተቃውሞውን የመግለፅ የተከለከለው ምንዱብ እንዴት ታወሳቸው የኖቤል ተሸላሚው ጠቅላይ ሚኒስተር ? በሃይማኖቱ ግፍ ሲደርስ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የታገተው ? ብሄራዊ መብቱ ተነፍጎ የለበሰው ልብስ በአደባባይ የወለቀው፣ መኖ