ለምን ሲሰላ።



እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።

„እግዚአብሄርን መፍራት ዘመንን ታረዝማለች።
የኃጣኣን ዕድሜ ግን ታሳጥራለች።“
መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ 10 ቁጥር 27

ለምን ላ።

ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute
©Selassie
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
04.01.2020


በኢትዮጵያ ተሰምተው የማይታወቁ የጭካኔ ድግግሞሽ በዙር እያዬን ነው። የኦዳ ሥርዕዎ መንግሥት ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ የጭካኔ ፋክክርም አያለሁ።

ሥልጣን ጠቅልሎ መያዝ ብቻ ሳይሆን አማራ ክልል አቅም ብቅ እንዳይል በባሩድም በካቴናም ቅጣቱ ድንበር የለሽ ነው።

ይህም ሆኖ የአማራ ክልል በባዶ እጁ ሆኖ ይቀናበታል። ስለዚህም አቻዊ ጭካኔ ተከስቶ ክልሉ ይወገዛል። ኦሮምያ ላይ የሰው ልጅ ተገድሎ ተዘቅዝቆ ሲሰቀል፣ አማራ ክልል ላይ ለጥናት የሄዱ ንፁኃን በድንጋይ ተቀጥቅጠው ተገደሉ።

ኦሮሚያ ክልል ላይ ቤተክርስትያን ሲቃጠል አማራ ክልል ላይ መስጊድ ይቃጠላል።
ኦሮምያ ላይ መፈናቀል ሲኖር አማራ ክልልም ላይ መፈናቀል ይከሰታል። ኦሮምያ ላይ የፓርክ ቃጠሎ ሲኖር አማራ ክልልም ላይ ይኽው መሰሉ ይከሰታል።

በኦሮሚያ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ታግተው የደረሱበት ሁኔታ አይታወቅም ሲባል አማራ ክልል ህፃናት ታግተው ይረሸናሉ።

በዚህ ውስጥ ኦሮምያ ለሚፈጠረው ቀውስ የኦዳ መንግሥት ዝምታን ይመርጣል፣ አማራ ክልል ሲሆን ደግሞ ግሎባሉ ዓለም እንዲያውቀው ከጠሚር ጀምሮ ልብ የተገጠመላቸው ወጥተው ሲያወግዙ ይደመጣል።

·       ሁለት ነገር።

1) የሰው ሰው የፈጠረው እና በፈቃዱ የተፈጠረ መደብ የተለዬለት ይመስላል።
2) ሁለተኛው ነገር አሸባሪው ቡድን አማራ ክልል ላይ ህጋዊ ዕውቅና ተሰጥቶት እንዳለም ይሰማኛል።

·       የመንግሥት ደህንነት የትንበያ አቅም ኩርኩድነት።
እንደ ሥርጉተ ሥላሴ ዕምነት ኢትዮጵያን የሚጠብቅ የደህንነት ተቋም እንደሌለ አምንበታለሁ። አይደለም ቀድሞ ለችግሩ ትንበያ መፈፀም ህዝብ የችግር ምልክት አዬሁ ሲል እንኳን ይህን ተከታትሎ የሚያመክን የደህንነት ተቋም የለም። በጀቱ ለዚህ ድርጅት የሚመደበው ወንዝ ውስጥ ሰምጦ እንደሚቀር መርከብ አዬዋለሁኝ እኔ በግሌ።
·       በቀል እና ሥውር አልጋው።

በቀል ቁንጮ ላይ አለ። የአሳ ግማቱ ከጭንቅላቱ እንዲሉ። ያለው መንግሥታዊ ጫና ሁሉ በአይነት የተሸከመው የአማራ ክልል እጥፍ ድርብ የበቀል መወጣጫ፣ የመከራ መጫኛ ሆኗል።

ከላይ ያነሳኋቸው ተመሳሳይ የጥፋት ድርጊቶች የሚታዩት አማራ ክልል እንጂ ሌላ ክልል አላስተውልም። በዚህ ውስጥ የማዬው ቁምነገር የኦሮሙማ ቁንጥንጥ ፖለቲካ የሥነ ልቦና ቀውስና የበታችነት ስሜት እንዳለበት እረዳለሁ።

ያንን ለማካካስ ሊቆጣጠረው ያልቻለውን ጭካኔ አማራ ክልል ላይ መፈፀም አውራ አጀንዳው እንዳደረገው አስተውያለሁ። እናንተስ የእኔዎቹ ምን ትላላችሁ?

የሚገርመው ይህን ዕውነት ለመሸንጎር የሚተጉ ሥውር እጆ በለበጣ ተሞሽረው ሚዛን ነን ብለው ማስጨፈራቸው ነው። ስክነት ባጣ ህሊና ሰከን በል ማለት መቼም ልብ ላልተገጠመልን ነፍሶች ይገባናል። ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልገንም እንደማለት።

ባይነህርሩን ምን አለ? ጉርሻቸውን አጣጥተው የክብር ኒሻናቸውን ከኦዳ ቤተ መንግሥት ቢጠብቁ መብት ነው። እንዲህ ንፋስ በቀወጠው ቁጥር ስብከታቸውን ከሚለቁ።

የአማራ አቅም የነቀለ አቅምን ከቻሉ ታቦት ያስቀርፁለት። ይህም መብት ነው መደመርን በቄንጥ ለማስተማር ከሚዳዳቸው።

ዕውነት ለዕንባ መቆም ነው። ይህ ሁሉ ጦር የሚደራጀው አማራነትን ለማክሰም ነው። እነሱ ደግሞ ሥቃዩን እረመጥ ውስጥ ይጨምሩታል። የሌሉ።

በማስተዋል ሂደቶችን ማጥናት መንገዳችን ይቀይሳል።
የጨረቃ ቤት ፓርቲ ስብሰባ ድክመቱን ለመለበድ ተሰበሰበ።

የኔዎቹ ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።