የጨረቃ ቤት {ብልጽግና} የመርኽ ጥሰት እና ልብዱ ስብሰባ።


እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።

„ተግሳጽን የሚወድ ዕውቀትን ይወዳል።“
ምሳሌ ምዕራፍ 12 ቁጥር 1

የጨረቃ ቤት የመርኽ
ጥሰት እና ልብዱ
 ብሰ
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
04.01.2020


 እፍታ።

ውዶቼ ይህ የዕለቱ መከወኛ ጹሑፌ ነው። የጨረቃ ቤት {ብልጽግና ፓርቲ?}ተመሰረትኩ ካለበት ጀምሮ ዝንፈቱን እንዲያስተካክል በፌስ ቡኬ ስወተውት ባጀሁኝ። ከዛ ሰሚ ሳይገኝ እንዲያውም ምርጫ ቦርድ ዕውቅና ሰጠው የሚል ዜና መጣ።

ይህ ጫን ያለ ችግር ነው ብዬላችሁ እኔ እህታችሁ „የዲሞክራሲ ጽንሰት ውርጃ“ ዘለግ ያለ ሙግት ለምርጫ ቦርድ አቀርብኵኝ። መርኽ መጣሱ ብቻ ሳይሆን የአገር መርኽ የሆነ ዕቅድ ከመሰረታዊ ሰነዶች ከፕሮግራሙ እና ከደንቡ ተነጥሎ ጸደቀ አልሰማነም። እረቂቅም አለ አላዳመጥነም።

ያው ሁለቱ መሰረታዊ ሰነዶች ህገ ወጥ በሆነም መንገድ ጸደቁ መባሉ እራሱ ሥርዓት ያልጠበቀ ቢሆንም እቅድ መዘለሉ ደግሞ የሚገርም ዓይነት ግድፈት ነበር። የሚገርማችሁ የአገር ውስጥ እና የውጭ አገር ሚዲያዎችም፤ ጋዜጠኞች፤ ተንታኞች የኢኮኖሚ ሊሂቃን እራሱ ጭራሽ ይህን ግድፈት ባሊህ አላሉትም ነበር። የሚገርም እኮ ነው።

ዕቅድ አልባ በምን ስሌት ፓርቲ ተብሎ ዕውቅና እንደተሰጠው ግራ ይገባችኋል። ያው የቤተ ዘመድ ውሎ ስለሆነ ነው እንጂ።
የሀነ ሆኖ ዘሃበሻ ይባረክ ስላተመው ጹሑፌን አሁን ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ  የኢህዴግ ነበር ሥ/አኮሜት ህወሃትን ሳይጨምር ተሰበሰበ ይኸውን ዕቅድ ሊያጸድቅ። ይህም ቢሆን ወደል ግድፈት ነው። ግን መኖሩ ቢያንስ ጥሩ ነገር ነው።

ለማረም መሰናዳታቸውም ሌላ መልካም ነገር ነው። ብዙውን ነገር እኔ እንደማስበው ሰው አያውቀውም፤ በመርኽ አንሞገትም ብለው ይመስለኛል ዝልኛቸውን የሚጓዙት።

የሆነ ሆኖ ትናንት ዜናውን እንዳነበብኩኝ ፌስ ቡኬ ላይ የለጠፍኩት ማስታወሻ እንሆ። የቀደመውን ታገናዝቡ ዘንድም ሊንኩን እለጥፋለሁኝ። ፌስ ቡኬም ብትገቡ ብልጽግና ተመሰረትኩ ካለበት ጀምሮ ለትውልድ የማይሆን የጨነገፈ ስለመሆኑ የጻፍኩትን ታገኛላችሁ። ሃሳቡ ጥሩ ሆኖ ሳለ አመሰራራቱ ግን የማጭበርበር ሂደት ነው ያዬሁበት። አመሰራራት በጣም ወሳኝ ጉዳይ ነው።

ቀደም ወደ አለው ጉዞዬ ሳመራ አሁንም ዘሃበሻ ባያትመው ኖሮ አያስተካክሉትም ነበር። ውድቀትም ነው። የሚገርመው የካቢኔ አባላቱ፤ የተወካዮች ምክር ቤት እንዴት እንደማይጠይቁ ደግሞስ ኢህዴግ ፈረሰ ከተባለ በዬትኛው ዕቅድ እንመራ ብለው አለመጠዬቃቸው።

·       ፌስ ቡኬ ላይ የተለጠፈው ጭብጥ። በ03/01/2020

ባለፈው ጊዜ ሥርዓት በጣሰ ሁኔታ የጨረቃው ቤት {ብልፅግናው} ደንብና ፕሮግራም ፀደቀ በሚል በዬሚዲያው ውይይት ነበር።

ሦስተኛው ሰነድ ስለመኖሩም ውሹን ያወሳ አልነበረም። ሁለም ፕሮግራም እና ደንብ ብቻ ነበር የሚለው። የተረሳ ትልቅ የጭንቅላት ጉዳይ ነገር ነበር፣ ስለ ዕቅድ እኔ ፌስቡኬ ላይም፣ ምርጫ ቦርድን የወቀስኩበት የዴሞክራሲ ፅንስ ውርጃ በሚለው ፁሁፌ የመርህ ጥሰት ብቻ ሳይሆን የሰነድ ጉድለትም የዕቅድ መዘለል እንዳለ ጫን ያለ ወቀሳ አቅርቤ ነበር።

አሁን ደጉ ሳተናው ገብቼ ሳነብ የጨረቃ ቤቱ ብልፅግናው የኢህአዴግ ነባር ሥራ አስፈፃሚ ኮሜቴ አባላትን ህወሃትን ሳይጨምር ስብሰባ እንደ ተቀመጠ አነበብኩኝ።

አዲስ ስም የጨረቃ ቤቱ ብልፅግና አመጣን ሲሉ ለረጅም ጊዜ የሞገትኩት፣ ምርጫ ቦርዱንም የወቀስኩበት፣ የፖለቲካ ተንታኞችም ፈፅሞ ያላነሱት ወሳኝ ጉዳይ ነበር ዕቅድ።ጭራሽም የተረሳ፣ የዛሬው አስቸኳይ ስብሰባ ሦስተኛውን መሠረታዊ የፓርቲ ሰነድ ዕቅድን ያለማካተት ግድፈት ለመለበድ ነው።

ድንገቴውና ደመነፍሱን የኦሮሙማ ድንብስ ጉዞ እንዲህ ይዘናከታል። ለነገሩ የካሜራ ፍቅር የት አድርሶ?
የጨረቃ ቤቱ {የብልጽግናው“ ሥ/አሰ/ኮሜቴው "ፓርቲው ይወያይባቸዋል ከተባሉት ጉዳዮች መካከል የኢኮኖሚ እድገት መሰረት ያደረገው 10 ዓመቱ መሪ ዕቅድ እና 2012 የምርጫ ስትራቴጂ ዋና ዋናዎቹ ናቸው ይላል።"

ይህም ቢሆን ሥርዓትን የተከተለ አይደለም። የትኛው ብሄራዊ ጉባኤ የመረጠው ማዕከላዊ ምክር ቤት?

 በዬትኛው ህጋዊ የማዕከላዊ ምክር ቤት የተመረጠው ሥራ አስፈፃሚ?

በዬትኛው ጉባኤ የፀደቀው ዕቅድ? የበታች አካላቱስ ተወያይተውበታል ወይ?

 እንደ ፌንጣ ከአንድ ግድፈት ወደ ሌላ እንዲህ በደመነፈስ የኢትዮጵያ ተስፋ ይባዝናል። ግልብነት። ይህን ዝርክርክነቱን ተሸክሞ ዝም የ አባት ነው የ50/60 ዓመት ይጸልቃል ድርጅታችን ደግሞ አለበት። መጀመሪያ ለ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ምስረታ የፓርቲ ዕቅድ ስለመኖሩ ዕውቅት ይኑር። ዝልቦ!

ይህ ወደል ግድፈትን ማስተካከል የነበረበት ምርጫ ቦርድ ዕውቅና ከመስጠቱ በፊት ነበር። ተስፋ ተዘቅዝቆ ሲሰቀል ገፀ ባህሪው እንዲህ ይገለፃል። አምልኮተ ሰው ህሊናንም እንዲህ ይጋርዳል።

የዴሞክራሲ ጽንሰት ውርጃ {ዘለግ ያለ ሙግት ከምርጫ ቦርድ ጋር}

መርኽ አልባ ጉዞ የትውልድ ጠንቅ ነው።

መልካም ሰንበት ቅኖቹ።
ኑሩልኝ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።