አብን የህልውና ድርጅት ነው።

እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በደህና መጡልኝ።

„ወደ እሳትም ቅጥር ገብቼ በበረድ
 ድንጋይዎች የተሠራ ታላቅ ቤት ቀርብሁ።“
መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ 9 ቁጥር 45
ብን ህልውና ርጅት ው።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute
©Selassie
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
04.01.2020




እንዴት ናችሁ ክብሮቼ? ደህና ናችሁን?
ብን የህልውና ተጋድሎን አደራ የተሸከመ ድርጅት እንጂ ለሽልማት፣ ለዝና ኮሮጆ የተደራጀ ድርጅት ሊሆን አይገባም። የህልውና ተጋድሎ መሪው የህዝብ እንባ፣ የመኖር ጥማት፣ ዘር የመተካት ተስፋ ነው ጥሪው።

ይህን አብን ጠንቅቆ ሊያውቀው ይገባል። አብን ለኬክ ቆረሳ ከተዘጋጁ ድርጅቶች በተልዕኮ በፍፁም ሁኔታ የተለዬ ነው። ፆሚ ድርጅት ነው አብን። ከብዙ ዘመናይ ነገሮች እንዲታቀብ የሚያስገድደው የተልዕኮው ግዝፈት ነው።

ተልዕኮው ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት ከዕንባ ነው የሚነሳው። የትግልህ መስመር በዚህ ከታነፀ ዘመናይነት፣ ክብር፣ ዝና፣ መቀናጣት ትዝ አይልህም። መአህድ የተነሳውም በዚህ መንፈስ ነበር።

ስለዚህ የአደረጃጀት መርሁን እና ተልዕኳው አሁን አገር ቤት ካሉት ድርጅቶች በፍፁም ሁኔታ የተለዬ ነው። ተጣምሬ እሰራለሁ ካለ ለህልውና ከሚታገል ድርጅት ጋር ብቻ መሆን ይኖርበታል።

በዚህ ላይ ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። ይህን በጥንቃቄ ማድረግ ካልቻለ ለሌላ 50/60 ዓመት መከረኛውን የአማራ ህዝብ በቁሙ ይቀብረዋል። በሌላ በኩል የሶልዳሪቲ ተጋድሎውንም በረድ ይቸልስበታ።

ከበረደው በኋላ የሚደክም ነፍስ አይኖርም። ይህ የመአህድ ተልዕኮ ሲስተጓጎል በደረሰው ፍዳ ታይቷል። አማራ ለመታሰር እንኳን በትውስት የፖለቲካ ማንነት ነው አሳሩን ያዬው።

ሁልጊዜ እኔ እንደምናገረው እኔ እምታገለው ላልተፈጠሩት ገና የዛሬ 20/30 ዓመት ለሚፈጠሩት ልጆች ነው።

በዚህ ስሌት ስንሄድ አብን ያልተገባ ጥምረት ከፈፀመ ገና ላልተወለዱት ልጆችንም የመኖር ራዕይ ይወስናል። የአብን መሠረቱ የአማራ ህዝብን አገር አልባ የሚያደርገውን ፀረ አማራ መንፈስ ወደ ቀልቡ መመለስ ነው።

ደግሞ በመሽኮርመም ሳይሆን በትግል መሥመር ጥራት፣ በውሳኔ ብቃት የሚወሰን ነው። በርቱ። አይዟችሁ።

የአማራ ተጋድሎ በፅናት ይቀጥላል።

ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።