ለለመደበት ገዳይ መንፈስ፣ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ሰኔል ቢያሰናዳስ?


እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።

„ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል
ሰነፍ ልጅ ግን ለ አናቱ ኃዘን ነው።“
መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ 10 ቁጥር 1



ለለመደበት ገዳይ መንፈስ፣
ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ
ሰኔል ቢያሰናዳስ?

ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute
©Selassie
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
04.01.2020

የለመደበት ገዳይ መንፈስ የአዲስ አበባ ወጣቶችን ሰብስቦ ከምትሞቱ ምረጡን ሲል ሰባዕዊነትን ደመራ አድርጎታል። ዴሞክራት ነኝንም በቹቻ ምኞት ሸኝቶታል።

በዚህ በሰሞኑ የጠሚር አብይ አህመድ ንግግር ብቻ የኢትዮጵያው ምርጫ ቦርድ የነፃ እና ፍትኃዊ ምርጫ ሞቶ“ እንጦርጦስ ተልኳል።

ከሹመት ማግስት ሁሉም ክልል ስብሰባ ተካሂዷል፣ ከድሬ እና ከአዲስ አበባ በስተቀር። የት የሚታወቀውን ይሆን አዲስ አበቤ ዛሬ የሚፈለገው?

መሪዬ ብሎ በራሱ ወጪ ህይወቱን ገብሮ ግን ዓመት ሳይሞላ በጠራራ ፀኃይ የተረሸነው? በደል ይረሳል ወይስ ይለመዳል?

1300 ወጣት ጦላይ የተወረወረ፣ ይህም አልበቃ ብሎ የምትኖረው በኪራይ አገር ነው ተብሎ የሥነ ልቦና ጦርነት የተከፈተበት ህዝብ ዛሬ እንዴት ተናፈቀ? በደል ይረሳል ወይንስ ይለመዳል?

በመኖሩ ተፈርዶ የመሰብሰብ፣ መሪውን የመምረጥ፣ ተቃውሞውን የመግለፅ የተከለከለው ምንዱብ እንዴት ታወሳቸው የኖቤል ተሸላሚው ጠቅላይ ሚኒስተር?

በሃይማኖቱ ግፍ ሲደርስ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የታገተው?
ብሄራዊ መብቱ ተነፍጎ የለበሰው ልብስ በአደባባይ የወለቀው፣ መኖሩ የተቀማው፣ እሱ በማያውቀው ሁኔታ ዴሞግራፊ የተሠራበት።

አንዲት ቀን አይዞህ ተብሎ የማያውቀው እንደ ፋኖ ሲባንኑ ትዝ አላቸው እና ጠሚር አብይ አህመድ ሰበሰቡት። መቼስ ጌታ አይደሉ ይህም ይሁን አንተ ደኃ ነህ፣ ደኃ ከሆንክ ዘንዳ መብት ተሰጥቶህ አልተፈጠርክም።

መብት አለኝ ብለህ የእኔን የጨረቃ ቤትን (ብልፅግናን) ካልመረጥክ ታገኛተልህ። ሞት ይጠብቅኃል። ድምፅ ከመስጠት እና ሞትን ምረጥጥጥ? ምጥ።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ለምርጫ ኮሮጆ ከሚያዘጋጅ ሞት ለታቀደላቸው ምንዱባን ምንአለ ቹቹ፣ ሰኔል እና ሳጥን ቢያዘጋጅ። እኔ ያዳመጥኩት የሞት ዓዋጅ እንጂ የምርጫ ቅስቀሳ አይደለም እና።

ግን ግን ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የምርጫ ቅስቀሳ የጊዜ ሰሌዳ ዓውጇልን? የሰማችሁ እባካቹህ ሊንኩን ወዲህ በሉት? ሞት ሰንቆ ምርጫ አለን? እም።

ምርጫ በእርግጫ በፍጥጫ የትውልድ ምክነት።

የኔዎቹ ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።