ምክንያታዊነትን አንሳምመው።


እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በደህና መጡልኝ።


"እግዚአብሄር ፍጥረቱን ማረጋጋት ያውቃልና
ስለ ልጆቻቸውከምድር ስለተገኜው አዝማራም"
ልቦናቸው ይረጋጋል"
መጽሐፈ መቃብያ ምዕራፍ 3 ቁጥር 10

ክንያታዊነትን አንሳምመው።

ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute
©Selassie
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
04.01.2020


አብን ምክንያት ፈልገህ() ስታሳንስ ( )ምክንያት አልቦሹን ብአዴንን እንታገሥ ስትል() አንተ አንቺ እርስዎ ማን ነዎት? ግርም ይለኛል ሚዲያ ስለተመቼ ብቻ ምክንያታዊነት ሚዛን ማጣቱን ሳስተውል። እርግጥ ዝና የሚያስጎመጅ ከሆነ በኢትዮጵያ ቆይቷል።

ዝና ግን ሚዛን ከነሳው የሳሙና አረፋ ወይንም ጤዛ ነው። የቱ ዘልቆበት ታዬና። ሁሉ ነኮቶበት እያዬን ነው። የተሻለው የተከደነ ሲሳይ ሆኖ ድምጥን አጥፍቶ ተግባርን መከወን ነው።

የአማራ ተጋድሎ ብዙ ዋጋ ተከፍሎበታል። 60ዎቹ ታጋዮች ከተነሱ በኋላ ባለቤት ያልነበረው አማራ የጦስ ዶሮ ሆኗል። የሚያሳዝነው በሬ ካራጁ እንዲሉ አማራ እራሱን እዬገበረ ግን ስለራሱ ህሊናውን ነፍጎ የኖረ አሳዛኝ ፍጥረት ነው።
ለቀኑ ቀን ሰጥቶት ትውልድ የማይተካቸው / አሥራት ወልደዬስ ሲነሱ የኢትዮጵያ ሊሂቃን ተረባርበው አጠፏቸው። እራሱ አማራው ታገላቸው። የብአዴን ምሥረታም ከዚህው ዘለግ ካለ ግብ ጋር የተቆራኜ ነው።

የብአዴን ዘመን የፍዳ ዘመን ነው። አሁንም አማራን ለመታደግ ሳይሆን በአማራ ላይ ዴሞግራፊውን ለማስፈፀም ትጋቱን እያዬን ነው። ይህን ተሸከሙ የሚሉ ብዕሮች ደግሞ ተነስተዋል። የፖለቲካ ልምድ ማነስ ይመስለኛል።

ብአዴን ውስጥ እራሳቸውን ማወቅ ሲጀምሩ በሥውር ሴራ ተመትረዋል በባሩድ፣ በምግብ ብክለት ተወግደዋል። አቶ ተስፋዬ ጌታቸው በምግብ ብክለት ሌሎቹ በባሩድ። ይህ ቀደም ያለው 60ዎቹ ፖለቲካ ዘመናዊ በሆነ ሁኔታ ፀረ አማራነት በበቀል ተፈፅሟል።

የሚገርመው አማራን በግሎባል ለማሳጣት የተሄደበት መንገድ ቂመኛ መሆት ባይገባም ቀበቷችን ጠበቅ አድርገን ሶልዳሪቲ ፍለጋ እንድንማስን አቅም ሸልሞናል። ይህ ተረስቶ ነው አማራዊ ብዕር ለኦዳ ስገዱ ሲል የሚደመጠው። ማፈሪያ።
ለውጡን ለማምጣት ህይወታቸውን ያስያዙ ለቹቻ እና ለሰኔል፣ ሌሎች ለኖቤል። ይታደሉታል እንበለው ይሆን?

የሚገርመው 50/60 ዓመት እንገዛለን አርፋችሁ ተቀመጡም አለበት። ለእነሱ የድል መባቻ እነ ዶር አንባቸው መኮነን መገበር ግድ ሆነ። ልክ የፕ / አሥራት ወልደዬስ ተውኔት ነው የተፈፀመው። ለወሬ ነጋሪ ሳይቀር እሬሳቸው በር ተዘግቶ ተሰቃይቶ አፈር ቀመሰ።

አብን ጮርቃ ድርጅት ነው። ይህ ጮርቃ ድርጅት ሲያስፈልግ ከሥልሳዎቹ ጋር እያፎካከሩ በዬሚዲያው ሲያብጠለጥሉ ያልበሰለ ወዘተ እያሉ ባጁ። ለማብሰል ምን አደረጉ ሲባል ከዘመነኞች ጋር ዝናን ከማጠራቀም ያለፈ የተከወነ ነገር የለም።

ስለ ሰባዕዊነት ግድ የሚለው፣ የአማራን ፖለቲካ ቁጭ በል ተነስ እያሉ ከማብጠልጠል በእኩያው አንድ ቀን እስረኞችን ሄዶ ለመጠዬቅ ተሞክሮ ይሆን? ሰብአዊነት፣ ሚዛናዊነት ማለት ይሄ ነው። በዬጊዜው የዘመነኞች ሚዲያን ከማሟሟቅ። ከማድመቅ።

አይመለከተኝም ያለ ሰው ፍዳው የጣለበትን የአማራ ፖለቲካ ቁም ተሰቀሉን ትቶ ያመኑበትን መስመር ጠበቅ አድርጎ መያዝ ነው። ጓዝን ጠቅልሎ መቀላቀል።
ሌላው ቀርቶ አብን የቀደመው የብአዴን ሊሂቅ ቢኖር ፈተናው ይቀልለት ነበር። አሁን በቅናት ድብን ካሉት ጋር ነው ፍዳውን እያዬ ያለው።

በዛ ላይ በኦዳ መንግሥት ካቴና የታዘዘበት ድርጅት ነው። በዚህ ላይ ተጨምሮ በአብን ላይ የመንፈስ ሽፍትነት እንዲኖር መሥራት ሲኦልነት ነው።
ለብአዴን ፕሮፖጋንዲስት ከመሆን በላይም የሚያሳፍር ምንም ነገር የለም። የመንግሥት ሚዲያ እና እራሳቸው ጠሚሩ በቂ ናቸው ለፕሮፖጋንዳው። ጠቅላይ ሚኒስተሩ እኮ እራሳቸው ራዳዮ ናቸው። 24 ሰአት ነው አገልግሎት የሚሰጡት።

ምርጫ ሲደርስ ለጋብቻ ዝምድና ኮረጆ ለቀማ ወደ ጎንደርም ያቀኑ ይሆናል። መቼስ መቼ ናቸውና። ይብቃኝ።

ልብ ያለው ሸብ እንደ ጎንደሮች።

ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።