ልጥፎች

አንተ ሞት የማትለመድ ጉት። ሥጦታው ለግራባው ብአዴን እና ለጌታው ለኦነጉ ኦህዴድ ይሁንልኝ። 15.04.2021

ምስል

አንተ ሞት የማትለመድ ጉት ሥጦታ ለግርባው ብአዴን።

ምስል
  እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ። ዕለተ ሃሙስ ማዕዶተ አሰጋሪው በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ሕይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁኝ።“ (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17)   ·        አ ፍታ። ነፃጫጭ ባዘቶዎች ከሰማይ ወደ ምደር እዬወረዱ ለአፍታ ቆዩ። ሚያዚያን ሲዊዞች አንደልቡ ይሉታል። እንፈለገው የሚሆን ይሉታልም። ባይበዛም ብናኝ የባዘቶ ጥጥች አሉ። ትናንት ይብርድ ነበር። ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ቅልጥ ያለ ጠሐይ ሊወጣ ይችላል። ሚዚያ የፈለገውን የሚያደርግ ነው። አቶ ሽመልስ አብዲሳም የዶር ዳኛቸው አሰፋ የስለት ልጅ ልክ እንደ ወርሃ ሚዚያ ባህሬ ናቸው። እንደ ልቡ። ቅኖቹ እንዴት አደራችሁ? እናት ኢትዮጵያስ እንደምን እዬሆነች ነው? ዛሬ አባወራው አሰጋሪው ሃሙስ ነው። ማዕዶተ አሰጋሪው የቅኔው ልዑል የብላቴ ጸጋዬ ዕለት። የዛሬው የራዲዮ ዝግጅቴ በሞት ላይ ነው። ሞት እንዲኖር እንዲመራ፤ እንዲገዛ፤ እንዲያስተዳደር ተፈቅዶለታል ኢትዮጵያ ላይ። የሞተው ሰውኛው ሞራል፤ ተስፋ፤ ራዕይ፤ ቅርስ ውርስ፤ ተፈጥሮ፤ ማስብም ሳይቀር ነው። ሙት መሬት ላይ ስላለወ ግርባው ብአዴን ዛሬ ምን ይል ይሆን የጸጋዬ ራዲዮ? አብራችሁት ትሆኑ ዘንድ በትሁት አክብሩት ይጠይቃችኋል። Realaudio – Player ግን  ይጠይቃል በራዲዮ ሎራ ዕልፍኝ የጸጋዬን መንፈስ አርኬብ ላይ ቀጥሎ ለማድመጥ። በራሴ ዩቱብ ቻናልም እንዲሁ ከሥርጭቱ በኋላ እለጥፈዋለሁኝ። በቴሌግራም ፔጄ ላይም እንዲሁ። ላይፍ ላይ ሰዓቱ ሲደርስ ከ10 ደቂቃ ቀደም ብዬ ሼር አደርጋለሁኝ።   ·        ም ርኩዝ። https://www.lora.ch/sendungen/alle-sendunge

365 x 3 = 1095 x 24= 26,280

ምስል
  እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ    በሰላም መጡልኝ። ዕለተ ሰኞ ዕለተ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ሕይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።“ (ትንቢተ ዕንባቁም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17) ዕለተ ሰኞ ማዕዶት ጠባቂ ሁሉም አጀንዳ የሚሰናገድበት ዕለት ነው። መንፈሴ በይ ያለኝን ሁሉ ያለገደብ የሚኮለምበት። ዛሬ የቀናው አጀንዳ እንዴት ሰነበታችሁ? ሰንበት እንዴት አለፈ? ኢትዮጵያስ እንደምን እያሆነች ነው ይላል። ·          365 x 3 = 1095 x 24= 26,280   የቁጥር ተማሪ አይደለሁኝም። በቁጥር ትምህርት እጅግ ደካማ ነበርኩኝ። ስለዚህ ስህትት ሊኖርበት ቢችልም እርዕሴ አይፈረድበትም። እኔ የባይወሎጂ እና የኬሚስትሪ ጎበዝ ተማሪ ነበር የነበርኩት፤ እንዲያውም 11/12ኛ በደረጃ ነበር ተሸልሜ ያለፈኩት። የሆነ ሆኖ ወደ ዕርዕሰ ጉዳዬ ምልሰት ሳደርግ ሰውኛ ኢትዮጵያ ውስጥ በዬደቂቃው አደጋ ውስጥ ነው። ህዝብ እያለቀ ነው። ሞቱ ብቻ አይደለም በስጋት እና በሽብር ኢትዮጵያዊው ሰው ከጽንሰት ጀምሮ እዬተረሸነ ነው። ሰው አለን ለማለት አንችልም። እንዲያውም እኔ ቤት ሆኜ ሳስበው ኢትዮጵያ ውስጥ ምን ያህል የሥነ - ልቦና ባለሙያ ይኖር ይሆን እላለሁኝ። መጪው ጊዜ መርግ ነው። ችግሩ አልተጀመረም ብዬ ነው እማስበው። ·        ም ክንያቱም … ከአጤ ዝናቡ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጀምሮ የሥነ - ልቦና ህመም የለብኝም የሚል ሊኖር ስለመቻሉ እርግጠኛ አይደለሁም። እያንዳንዱ ደቂቃ በደም ውስጥ ያለፈ // ያለም ነው። እያንዳንዱ ደቂቃ በጭንቅ ውስጥ ነው የሚያልፈው// ያለም። „ከእኛ የሚሞተው ከሌላ አገር ጋር ሲነጻጸር ትንሽ ነው“ ባይ ሄሮ