ልጥፎች

በእልኸኝነት የኢትዮጵያ ፖለቲካ አገር አጥተን እንደ ኩርድሾቹ … ? እናት ዓለም ገናናው ሥምሽ በክብርሽ፤ በሞገስሽ ልክ ይቀጥል ይሆን?

ምስል
    እንኳን ወደ ከበበቡሽ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።   በእ ልኸኝነት የኢትዮጵያ ፖለቲካ አገር አጥተን እንደ ኩርድሾቹ … ? ·       እናት ዓለም ገናናው ሥምሽ በክብርሽ፤ በሞገስሽ ልክ ይቀጥል ይሆን? ዕለተ አርብ ማዕዶተ - ኢትዮጵያ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚመራራ። „ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።“ (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17)   ·       ጠ ብታ! እንዴት አደራችሁ ቅን ቤተሰቦቼ? ልዕልት ኢትዮጵያስ እንዴት አለሽልኝ ናፍቆት ዓለሜ? ·       እ ፍታ ለአንድ አፍታ።   እልኸኝነት አቅም ሲኖርህ ቢያምርም ቢከፋም ሞክረው። አቅም በሌለህ ሁኔታ በባዶ እጅ እልኽኝነት ሽንፈትን ቢደርብ እንጂ አትራፊ አይሆንም። ለነገሩ እልህ አይደለም ለብሄራዊ ጉዳይ ለሦስት ጉልቻም አይሆንም። እልህ ከሦስት ጉልቻ ዝቅ ላለው የግል ማህበራዊ ግንኙነትም አይረዳም። ወጣት ሳይሆኑ የወጣት ባህሪን፤ ጎረምሳ ሳይሆኑ የጎረምሳን ባህሬ፤ ኮረዳ ሳይሆኑ የኮረዳን ባህሪ ሁነኝ ማለት የዕድሜ ጸጋ እና በረከትን ካለማገናዘብ የሚመነጭ ይመስለኛል። ይመስለኛል እኔ በጹሑፎቼ አዘውትራለሁኝ። ይሕ የሆነበት ምክንያት ጥናታዊ ተግባር ያልፈጸምኩበት ስለመሆኑ ለማጠዬቅ ነው። የሆነ ሆኖ የ60/የ70/የ80 ዓመቱ ፖለቲከኛም እልኸኛ ነው። ጎረምሳም ኮረዳም ልሁን ባይ ነው። ከልጆቹ፤ ከልጅ ልጆቹ እኩል። የሚገርመው እልኸኝነቱ ያበቀለ ቢኖረው መልካም በሆነ ነበር። የተካው እሳት የላሰ ወጣት ቢኖርም ይሁን እንበለው። ግን የለም። አንዳቸውም የላቸውም።   ምክንያቱም ተተኪ ማፍራት ፕሮጀክታቸው አይደለም። የሚፈሩትም ይኽነኑ ነው። ፕ/መራራ ጉዲና፤ ፕ/ በዬነ ጴ

Reyot - ርዕዮት፣ በራራ፣ የመካከለኛው ዘመን ታሪክና የፕሮፌሰር ጌታቸው ሀይሌ ውለታ፡፡ 06/11/21

ምስል

የጅጅጋው ዩንቨርሲቲ ረዳት ፕሮፊሶር ትንገርቱ ገ/ፃዲቅ የሚገርም ትንታኔ -እንዲሁም የአዲስ አበበ ወጣቶች የፖሊስ ...

ምስል

"በአዲስ አበባ ላይ ያንዣበበው አደጋ ኢትዮጵያን ሊያፈርሳት ይችላል" | ዶ/ር ሰማኸኝ ጋሹ

ምስል

Ethiopian Renaissance-የኢትዮጵያ ተሃድሶ

ምስል

ምጽዓተ ተዋህዶ። ጸጋዬ ራዲዮ 10 06 2021

ምስል

ጸጋዬ ራዲዮ የ27.05.2021 መሰናዶ ኢትዮጵያ እና አስቸጋሪ ጊዜዋ። (Äthiopien und seine schwie...

ምስል

Ethiopian Renaissance Part I Fekadu Bekele

ምስል

የኔታዋ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኢትዮጵያዊ፤ አፍሪካዊ ግሎባላዊት ናት! የኔታዋ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዩንቨርስም ናት!

ምስል
    እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ።     በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ። አሜን። ·        የኔታዋ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኢትዮጵያዊ፤ አፍሪካዊ ግሎባላዊት ናት! ·        የኔታዋ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዩንቨርስም ናት!   ዕለተ አርብ ማዕዶተ ኢትዮጵያ! በከቡብሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ሕይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ።   „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“ (ምሳሌ 16 ቁጥር 9)   ·        ዕለተ አርብ ማዕዶተ - ኢትዮጵያ!   የኔታዋ አርቶዶክስ ተዋህዶ አገረ ኢትዮጵያን በተፈጥሯዋ ልክ ያበጀች አንቱ ዓይነታ ሃይማኖት ናት። ዕውነት ከተደፈረ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የተፈጥሯዊነት በቅዱስ መንፈስም ናት። የሰውኛነት ውስጡ ናት። ይህቺ ቤተ-   ክርስትያን በጸበሏ ሁሉን በህመም የተንገላቱ ወገኖችን ሁሉ የፈወሰች። በፍቅር ያስተናገደች።  የፍቅራዊነት ያጠጣች፤ የሰበከች ሐዋርያም ናት። በጸሎቷ ለሁሉ አጥር ቅጥር ሆነ የኖረች ያኖረች ህልውናም ናት። ዕውቀት አፍልቃ አጽድቃ ያሰበለች ፈርጥ ኃይማኖት ናት። የሥልጣኔም ብሩህ ጎዳናም ናት … ዝማሬዋ፤ ማህሌቷ፤ መልዕክተ ዮኋንሷ፤ ሀሁ ገበታዋ፤ አቡጊዳዋ ለሁሉ እኩል የህሊና መስኖ ሆኖ ሰብዕናን ገንብቷል። አንፆዋልም። ቅድስቷ ቅድስናዋ በማለት ሳይሆን በተግባር ከብራ ያስከበረች የጽረ አርያም ቤተኛም ናት። ቅድስታችን ትምክህትን የናቀች በመከራ በቅላ፤ በመከራ ኖራ፤ መከራን ድል ያደረገች የድል ሁነኛ ተቋም፤ የችሎት ኮከብ አደባባይም ናት። በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ውስጥ ህፃፅ የለም። ግድፈት የለም። በዶግማ እና በቅኖናዋ ውስጥ ሳንክ የለም። ተዋህዶ