ልጥፎች

ክቡር ተዋናይ ኪሮስ ኃ/ሥላሴ።

ምስል
                       ለባለግርማው የጥበብ ክህሎት                          ለተዋናይ ኪሮስ ኃ/ሥላሴ                             ምህረቱን ይላክ አዶናይ                                        „አሜን!“                               ከሥርጉተ ሥላሴ 25.05.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።) „ምንም እንኳን በለስም ባታፈራ፣ በወይን ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፤ የወይራ ሥራ ቢጓደል፤ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፤ በጎችም ከበረቱ ቢጠፉ፤ ላሞችም በጋጥ ውስጥ ባይገኙ፤ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመዳህኒቴ አምላክ ሐሴት አደርጋለሁኝ። ጌታ እግዚአብሄር ሃይሌ ነው። „አሜን!“ ይሁንልን! ይደረግልን! (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ከቁጥር ከ፲፯ እስከ ፲፰) የውስጥ መስመር ... ጥበብ ዘር የላትም፤ ጥበብም ፍቅር ናት፣ ጥበብ ቅርጽ የላትም፤ ጥበብ ብርሃን ናት፣ ጥበብ ፎርም የላትም፤ ጥበብ ነባቢት ናት፣ ጥበብ ቀለም የላት፤ ጥበብ የሁሉም ናት፣ ጥበብ መኖርም ናት መልካም ሐዋርያ ትርሲታዊ ሰናይ፣ ለፈቀዳት ሁሉ የምታደላድል የመንበር የበላይ። ·          ጥበብ እንዲህም ናት … የትህትና መዝሙር የአገልግሎት ዝክር የድካም ዕንቢልታ የጥንካሬ በር። መች ሆና ስታውቀው ጥበብ ወረተኛ የትውፊት ውሃዋ የዓይን ዘበኛዋ። ·          ጥበብ ፊት አትሰጥም … ጥበብ አይደለችም የጉድፍ አንቀልባ የልዩነት ዳባይ ጥበብ ጎታ የላት ለኩፉኝ እኩይ። ጥበብ ፊት አትሰጥም ለስንኩሉ ገደል ለሃሰት ቃል አባይ፤ ጥበብ አይደለችም የክፋት ኩነኔ የክፉ ላብ ብካይ። ሰነፍ ጥበብ የለች አልተፈጠ

Toni Dreher-Adenuga GNTM 2018.

ምስል
ሞዴል Toni Dreher-Adenuga    የ አፍሪካ የውስጥ ውበት የ2018                  የጀርመን ቆንጆ ሆና                   ዛሬ ተመረጠች። ከሥርጉተ ሥላሴ 24.05.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።)   „ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ፤ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፤ ከንጹህ ጋር ንጹህ ሆነህ ትገኛለህ፤ ከጠማማ ጋር ጠማማ ሆነህ ጥገኛለህ።“ (መዝሙር ምዕራፍ ፲፯ ከቁጥር ፳፭ እስከ ፳፮) እሺ የኔዎቹ አፍረካዊነት ዛሬ አማራበት። ቶኒሻ አሸነፈች። ያሸነፈችበት ፎቶ አሁን ያሁ ለጥፎታል ግን ጥራቱ እንብዛም ስለሆነብኝ ሌሎችን መምረጥ ግድ አለኝ። ብቻ ማሸነፍ እንዴት ደስ ይላል? እንዴትስ ይደላል? ደስታ እንዴት ውብ ነገር ነው። ዛሬ ግንቦት 24.2018 እ.አ.አ አቋጣጠር ያን ረጅም ፈተና ተሻግራ አፍሪካዊቷ የ18 ዓመቷ ቶኒ ድንቅዬ የጀርመን ምርጥ ቆንጆ ሆና ተመረጠች። ቶኔ ውበቷ ውስጧም ነው። የተመረጠችው እሷ ብቻ አይደለችም አፍሪካም እንጂ። የተመረጠችው እሷ ብቻ አይደለችም ሙሉ ሞራሏ አንጂ። ይህች የ18 ዓመት ወጣት ለጋራ ሥራ ብቁነቷን በትዕግስት የጠለፈች የመቻቻልም አብነት ናት። ቶኒ ሁልጊዜ ከፊቷ ፈግግታ የሚታይባት ፎሎቄ ወጣት ናት። ቶኒ ለካፋቸው የውድድሩ ተሳታፊዎች ሁሉ አጽናኝ፤ አበረታች፤ ሃይልና ጉልበት ሰጪ ጠይም ዕንቁ ናት። ቶኒ ተፈጠሯዋን ትወደዋለች። ቀለሟን ትውደዋለች። የሚሰጣትን የቤት ሥራ በአግባቡ ትክውናለች። ታዳምጣለች። ዓላማዋን ያወቀች ወጣት በመሆኗ ከጀርመንም ባለፈ ዓለም ዓቀፍ ዕድሎችን ወደፊት በስፋት እንደሚገጥማት በጣም እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቻላል። ሞድ የጋራ ጉዞ፤ የጋራ ሥራ፤ የጋራ ሃላፊነት፤ የጋራ አክብሮት፤ የጋራ ክንውን የሚጠይቅ ሲሆን መቻቻልን

የአማራ ተጋድሎና የኦሮሞ ንቅናቄ።

ምስል
          ህም።                                        ከሥርጉተ ሥላሴ 22.05.2015 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ)                               „እናንተ ሴቶች ሆይ የእግዚአብሄርን ቃል ስሙ፤ ጆራችሁም የአፉን ቃል ትቀበል።“                                                      (ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፳) ·          ጠብታ። „ራዕይ የሌለው መሪ ነጂ መሆን እንጂ መሪ መሆን አይችልም። (ከባለቅኔው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የተወሰደ)“ ተመስገን ብላለች ሥርጉትሻ። ቃሏ „ነጂ“ እራሷ አቤት ቅቤ ስታጠጣ። ተመስገን። ባለ ቅኔው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሰንበት ላይ ከውጪ ጉዟቸው ተመልስው እረፈት አላስፈለጋቸውም። ቀጥታ የሄዱት የውስጥን ቆሻሻ ጠረግ ለማድረግ በጋራ ከዶር ምህረት ደበበ ጋር ወደ አዘጋጁት ዓውደ የንጥህና ማስጠበቂያ ማዕከል ነበር 19.05.2018 እ.አ.አ። በቅድሚያ ግን ዶር ምህረት ደበበ እንኳን ደስ አለዎት። ምን ያህል ልቦናዎት ቅን ቢሆን ነው በጥረት ውስጥ ድል ዲል ያለለዎት። ለእርሰዎ የቀናችው ቀንም ትመጣልኝ ዘንድ እስቲ እባክዎትን ለአማኑኤል ይንገሩልኝ። „ኢትዮጵያ የአንተም የአንችም የእኔም ናት“ ተመስገን። „የኢትዮጵያን የቀደመ ክብሯ ይመለሳል!“ ተመስገን! ሌላም አንድ ተጨማሪ ተመስገን ላንሳ የዛሬ ሁለት ዓመት በአማራ የማንነት የህልውና አብዮት ላይ በተከታታይ እጽፍ ነበር። መቼም ለእኔ ቀላሉ ሥራ መጻፍ ነው። እንደ ቧንቧ ውሃ ስፈልግ መክፈት ሲያሻኝም መዝጋት እምችለው። እና ያን ጊዜ የፖለቲካ ድርጅቶችን ለመሆኑ ማንፌስቷችሁ ስለ ህጻናት ምን ይላል? ብዬ ሞግቻችሁ ነበር። ከዛ በፊትም ተዳብዬ እሰራበት