ልጥፎች

ጠንቃቃ መሆን ያተርፋል እንጂ አያከስርም።

ምስል
ሞት የፖለቲካ አቋም የለውም። „እግርህንም ወደ ፍቅር አንድነት ጎዳና አቅና፣ የእግዚአብሔር ዓይኖች ወዳጆቹን ይመለከታሉና፤ ጆሮውም ልመናቸውን ይሰማልና ፍቅርን ፈልጋት ተከተላት።“ (መጽሐፈ መቃብያ ምዕራፍ ፳፪ ቁጥር ፰) ከሥርጉተ©ሥላሴ 26.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።) በቃችሁ ቢለን ይህን የድንገተኛ ህውከት ቢያስታግስልን ምን አለ ፈጣሪ? ዛሬም አዲስ መርዶ አዬሁኝ። የአባይ ግድቡ የሙያው ማህንዲስ ከመኪናቸው ውስጥ ህይወታቸው አልፎ ተገኜ ይላል ክፉው ዜና። ዜናው ያገኘሁት ከአማራ ሚዲያ ነው።  እኔ የአባይ ግድብን ጉዳይ በገለልተኝነት ነበር እምከታተለው። አልተቃውምኩትም አልደገፍኩትም። ምክንያቱም በማህል ያለው የፖለቲካ ጨዋታ ቀልቤን ሚዛናዊ አድርጎ አንዱን ሊያስወስነኝ ስላልቻል። ይህ ፕሮጀክት በጣም በዙ ኢትዮጵውያን ልባቸውን የሰጡት ብቻ ሳይሆን ህይወታቸውን ለመገበር የተሰለፉበት ነበር፤ ይህም ብቻ ሳይሆን በበዛ ተስፋ ፍንድቅድቅ የሚሉም ባለሙያዎችን አዳምጣለሁኝ። እኔ ደግሞ ሳይሞቀኝም ሳይቀዝቅዘኝም ነው የኖርኩት።  የመንፈስ ነፃነት ነው ለእኔ ገዢዬ። ቁስ ብፈልግ ሲዊዝ ተቀብሬ አልቅመጠም ነበር። የተሻሉ ዕድሎች ስለነበሩኝ። ጉዳዬ ሰው በመንፈሱ ነፃ መሆን አለበት ነው። አሁንም ይህን አዲስ ለውጥ እምደግፈው የመንፈስ ነፃነት ያስፍናል የሚል ተስፋ ስላለኝ ነው። ጭንቅላት የተቆለፈበት ገነት ለእኔ ገሃነም ነው የፈለገ ዓይነት የኑሮ ደረጃ ይኑረው ...መንፈሴን ለመቆጣጠር ገና አንዲት ስንዝር እራመዳለሁ የሚል ማንኛውም ሰው ዕድል የለውም ከእኔ ጋር የመቀጠል። ምክንያቱም የራሱ መንፈስ አለውና ... መንፈስን በቅኝት ከመስጠት፤ ከመፍቀድ ሞት በስንት ጣዕሙ ...    የተስፋው

ወይ ፍርጃ? ጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማ ደግሞ ይወርድብናል? አማራን በሙሉ "ኦነጋውያን" ብሎናል፤

ምስል
መቼ ይሆን ራስን ማዬት የምትማሩት? „የብስ ለዛፍ ባሕር ለማዕባል ተስጥታለችና  ሁለቱም ፈራሽ ነገር አስቡ አልሁት“ (መጸሐፈ ዕዝራ ሱታኤል ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፲፱) ከሥርጉተ©ሥላሴ  23.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ) ·        መነሻ። የኦሮሞው ህወሓት እና የአማራው ኦነግ | ካሳሁን ይልማ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/93107#comments ·        ሰሞኑን። ሰሞኑን አንድ ጹሑፍ የኢሳቱ ጋዜጠኛ አቶ ካሳሁን ይልማ አስነብቦናል። እርእሱ ዱላ ይባል፤ መዶሻ ይባል አይታወቅም። በቃ እልሁን እስኪበቃው ድረስ ነው የተወጣበት። ያጣው ነገር አለ ማለት ነው። የፖለቲካ ድርጅት እና ማህበረሰብም ጽንሰ ሃሳቡ ተደባልቆበታል። „የኦሮሞው ህውሃት እና  የአማራው ኦነግ“ ይለናል።  ለነገሩ ብረት መዝጊያ የሚሆን ምንትሶ ካለ ምን አለ? መንበር እንዳወጣ ነው… የሚታደለው።  የፖለቲካ ድርጅቱ ይህን እንኳን አንድ ፓርቲ እና አንድ ማህበረሰብ ወይንም ህዝብ ምን ማለት እንደሆነ አላስጠናውም። ምን አለ የቤተመንግሥት ሰውነት ይህችን እንኳን አጣርቶ ቢያስተምረው? ግን ምን ይሆናል ባቋራጭ ሰው ካሰበው የእግዜሩ አሸነፈ እና የሚሆነው ሆነ። ነገም ምን ሊሆን እንደሚችል አይታወቅም … ኦነግ የፖለቲካ ድርጅት ነው። አማራ ደግሞ ማህብረሰብ ነው። የራሱ ሥነ ልቦና፤ የራሱ ባህል፤ የራሱ ቋንቋ፤ የራሱ ወግ እና ልማድ፤ የእኔ የሚለው ማንነት  ወዘተ ያለው ...  አማራው ሁሉ ኦነግ ሆነ ነው የሚለን አቤቶው ጋዜጠኛ አቶ ካሳሁን ይልማ። ልክ የወያኔ ሃርነት ትግራይ አማራ የሆነ ሁሉ "ግንቦት 7 ነው አሸባሪም ነው" እንደሚለን ማለት ነው።   

ጋዜጠኛ ተምስገን ደሳለኝ እንኳን ወደ አማራ ተጋድሎ መንፈስ መጣህልን!

ምስል
„ጀግንነት ሰው መሆን ከሚለው ሲነሳ ትውፊት ይሆናል።“   „ኤርምያስ ባሮክን እንዲህ ሲል አዘዘው … አንተ ግን ሂድ ከአፌም የጸፍኸውን የእግዚአብሄርን ቃል በፆም ቀን በእግዚአብሄር ቤት በህዝቡ ጆሮ በክርታሱ አንበብ ደግሞም ከከተሞቻቸው በሚወጡ በይሁዳ ሰዎች ሁሉ ጆሮ አንብበው“ (ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፴፮ ቁጥር ፮)  ከሥርጉተ© ሥላሴ 23.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።) ·        መነሻ። „ወይ ባልዘፈንሽ ከዘፈንሽ ደግሞ ባላሳፈርሽ ነው።“ ምነው የአማራ ብዙሃን የመገናኛ ወኪል ቁርጥ አደረጋችሁት ጎመዳችሁት ፍሰቱን። ሙሉ ቢሆን ለዳኝነትም ይረዳም ነበር።  ይህ ግን ቁንጽላዊ ነው የሚሆነው፤ ቢሆን ግን ሁለት ነገሮችን ማንሳት ግድ ይላል። ሙሉ ስዕል ለማዬት ባልችልም በአገላለጹ ላይ ጋዜጠኛ ተምስገን ደስለኝ የአማራን ተጋድሎ እና የገዱን መንፈስ ውስጥነት ዕውቅና የመስጠት ዝንባሌው ለእኔ ድንገቴ ነበር።  እንደሚመስለኝ ያላባራው የአማራ መፈናቀል እና ማዕከላዊ መንግሥት የሰጠው ተባደግ አያያዝ ወደ ራሱ እንዲመለከት ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለነፍሱ ድንግልዬ መልዕክት እንደላከችለት አስባለሁኝ።  እኔንም ወደ አማራ ተጋድሎ ጥቅልል ብዬ እንድገባ ያደረገኝ የቪዥን ኢትዮጵያ የጉባኤ አመራር አሳታፊነት፤ እንዲሁም ሚዛናዊነት አድሏዊ አያያዝ ስነበረው ነው። አንዳንድ አጋጣሚዎች አትኩሮትን የሚስቡ ብቻ ሳይሆን ዘላቂ አቅም በመፍጠር ረገድም እጬጌዎች ናቸው። https://www.youtube.com/watch?v=_CNYkBGZseM&t=2s ደራሲና ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከአማራ ቴሌቪዥን ጋር ያደረገው ቆይታ፡፡   ·        መክፈቻ። ተሜ እ