ልጥፎች

አቶ ፍጹም አረጋ ከሃላፊነታቸው ተነሱ።

ምስል
አዲስ የፕሬስ ሴክረታሪ ለውጥ በጠ/ሚር ጽ/ቤት። „አቤቱ በልቤ ሁሉ አመሰግንህ አለሁ።   ተአምራትህንም ሁሉ እናገራለሁ።“ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ© ሥላሴ  05.11.2018 ከገዳማዊቷ አገር ከሲዊዝ። በአዲሳዊነት ቀመር ፋታ ሳይሰጥ እዬገሰገሰ ያለው የጥጋናዊ ለውጥ ማዕበል ዛሬ ደግሞ አዲስ ነገር እያሰደመጠን ነው። አንዱንም በቅጡ አጣጥመን ሆድ ዕቀውን ዛረጋግፈን ፈትሸን ሳንቃኘው በዬዕለቱ በአዲሳዊነት መርህ ግብር ወደ ፊት የሚገሰግሰው የለማ አብይ ካቢኔ አሁን አዳምጡኝ እያለን ነው። በፎቶ በተደገፈ አጫጭር መረጃዎችን በማዕከልነት ሲያሰተናግዱ የቆዩት አቶ ፍጹም አረጋ በሌላ መተካታቸውን አዲስ ዜና እያደመጥን ነው። "ከአረጋ" ሥያሜ አንድ ቀነሰ እንደ ማለት፤ አቶ ፍጹም "አረጋ" አቶ አዲሱ አረጋ አቶ ዳዊት "አረጋ።" የሆነ ሆኖ እርእሱ እንዲህ ይላል። „Ethiopia:ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ስር የተቋቋመው የፕሬስ ሴክሬታሪ በይፋ ስራ መጀመሩን አስታወቀ“ ማድመጡን ትንታኔውን ለእናንተው የቤት ሥራ ሰጥቼ ሥርጉትሻ ሹልክ … https://www.youtube.com/watch?v=rBfiQz1fH0Q ሰላም ሲሆኑበት ችግርን የመፍተት አቅሙ አንቱ ነው። መሸቢያ ጊዜ። ትሁት አካባሪያችሁ።

ከወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም የአማራ ተጋድሎ ግብ አይጠብቅም!

ምስል
የሴቶች የፖለቲካ ዕውቅና ማግኘትን አንገት ማስደፋት ትልቅ የታሪክ ፍቀት ነው። „አቤቱ ምህረትህን ለዘላለም እዘምራለሁ እውነትህንም በአፌ ለልጅ ልጅ እናገራለሁ።“ መዝሙር ፹፭ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ  05.11.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። የሴቶች የፖለቲካ ዕውቅና ማግኘትን አንገት ማስደፋት ትልቅ የታሪክ ፍቀት ነው። የኢትዮጵያ ሴቶች በማንኛውም መስከ ለዘመናት የአገር አንድነት እና ሉዑላዊነትን ለማስከበር ጉልህ ተጋድሎ ያደረጉ ናቸው። የኢትዮጵያ ሴቶች ያልተሳተፉበት፤ ያልተሰዉበት አንድም የትግል መስክ አልነበረም። በሌላ በኩል በኢትዮጵያ የአገር ግንባታም የኢትዮጵያ ሴቶች ሁለገብ ተሳትፏቸው ቢልቅ እንጂ የሚያንስ አይደለም። የኢትዮጵያ ሴቶች ብልህነታቸውን፤ መክሊታቸውን፤ ጸጋቸውን፤ ስጦታቸውን፤ ጥበባቸውን፤ ብልህነታቸውን፤ ሁለመናቸው ሳይቆጠቡ ሳይሳሱ የሰጡ ድንቅ ፍጥረቶች ናቸው። የኢትዮጵያ ሴቶች በማናቸውም መሰክ የግንባር ቀደሙን ድርሻ በመውሰድ እኩልነታቸውን በዬዘመኑ በዬምዕራፉ አስመስከረዋል። ቀደም ባለው ጊዜም ቢሆን ለሴቶች የፖለቲካ ዕውቅና በመስጠት አጤዎች የአንስት እቴጌዎችን ምክራቸውን በማድመጥ፤ ብልህነታቸውን በመቀበል የብዙ ዕድል ባለቤት መሆን መቻላቸውን ታሪክ ያስረዳል። በ60ዎቹ የማርክስስት ሌኒኒስት ፍልስፍና ተጋድሎ ሂደቶች ውስጥም ሴቶች እኩል ተሳትፎ ቢያደርጉም ከፖለቲካ የተገለሉበት፤ እንዳሉም ያማይቆጠሩበት ለመስዋዕትነት ብቻ የሚፈለጉ የበይ ተመልካቾች ነበሩ። ከዚህም ሌላ የሰው ልጅ አቅርቦት ላይ ብቻ አትኩሮት ከማድረግ ውጪ ሴቶች ዜግነታቸውን በስልት የተነፈጉበት ወቅት ነበር። „እንዳያማ ጥራው እንዳይበላም ግፋው“ ዓይነት ነበር። አሁን ባለው የአማራ እና የኦሮሞ ተጋድሎ በተገኘው የለወ

ከብርት ፕሬዚዳንት ሳሀለ ወርቅ ዘወዴ ትውፊት ናቸው!

ምስል
መልካምነት ይበጃል። „ወደ ደጋግ ሰዎች የሚላኩ ሪቂቃን የሆኑ መላዕከት ብርሃን ናቸው።“ መጽሐፈ መቃብያ ከልዕ ምዕራፍ ፳ ቁጥር ፲ ከሥርጉተ©ሥላሴ 04.11.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።                       ዋው! የኮ/ ጎሹ ወልዴ ክብር አከበርኩት። ምኞቴም ተሳካ ተመስገን! የጭብጤ መነሻ አሉታዊ ነገሮች አቅም ማግኘት አይገባቸውም ነው። ክፉ ነገር ይወረናል። ክፉ ነገር ይገዛናል። ክፉ ነገር ያሰተዳድረናል - ፈቅደንለት። ቀና በሆኑ ጉዳዮች ላይ እንኳን ስምምነቱ ያን ያህል ነው። ታዲያ በዬት ታልፎ መልካም ነገሮች ሥር ይኑራቸው። ፍሬስ እንዴት ያፈሩ? መልካሞችን መልካም ለማለት ካልተደፈረ፤ መልካም ያልሆኑት መልካም አይደለም ማለት ካልቻልን ታዲያ እኛ ሰው መሆናችን ከምኑ ላይ ነው? እውነት ለመናገር አሉታዊ ነገር ወረራው መልካሞችን እንዳናይ ሸብቦናል። መለዬት አልቻልንም። በጣም ጥሩ የሆኑ መልካም ነገሮች ይታያል ኢትዮጵያ ውስጥ። እጅግ የሚመስጡ ጥሩ ነገሮች አሉ ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ፤ አሁን ሴቶችን የፖለቲካ ዕውቅና በመስጠት እረግድ ሉላዊ አብዮት በአብነት እዬተካሄደ ነው ልብ ላለው ልበ ህሊና ብርሃን ላለው፤ እነዚህ አቅም እንዲያገኙ፤ እንዲራቡ፤ እንዲበራከቱ መትጋት ቀርቶ ደግመን ደጋግመን ከክፉ ነገሮች ጋር ልውስውስ አድርገን ግርዶሽ ሰርተን፤ ዝንቅንቅ አድርገን መልካምነትን የተፈጠረበትን ቀን እንዲረግም እናደርገዋለን። ግን ስለምን? የሰው መለያው እኮ ክፉ እና ደጉን የሚለይበት ህሊና ስላለው ነው። ያ ህሊናው እንኳንስ መልካም ነገሮች እያሉ ወደ መልካም ነገር የሚወስዱ ጥሩ ዜናዎች፤ ውጥኖች፤ ጅምሮች፤ ፈሎች፤ ቀንበጥ ሃሳቦች እንኳን ሲኖሩ እነዛ ሃይል ብርታት አግኝተው የመልካም ነገሮች ቤተኛ

የአማራ ተጋድሎ ቀዳሚ ተግባር ለሰላም ዘብ መቆም ነው!

ምስል
የአማራ ተጋድሎ ቀዳሚ ተግባር ለክልሉ ህዝብ ሰላም ዘብ መቆም ነው። „አግዚአብሄርን የሚፈለግ ልብ ደስ ይበለው።“ መጽሐፈ መዋዕል ቀዳማዊ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፲ 03.11.2-18 ከሥርጉተ©ሥላሴ ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። አማራ ከዚህ መሪው ጎን መቆም ግድ ይለዋል።  ጦርነት አውዳሚ ነው። ከጦርነት የሚገኝ ትርፍ ቢኖር አመድ እና ቂም በቀል  ብቻ   ነው። ቂም እና በቀል ደግሞ ለቀጣዩ ትውልድ ጸር ነው። ጥቂት ሰዎች  ለውጥ  አልመጣም ይላሉ። በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በቀና የሚዩት አንዳችም ነገር  አለመኖሩ ሰው ከምን ተሠራ እስከማለት እደርሳለሁኝ። ፍጹምነት ከሰው  መጠበቅ ዓይነት ነው። ግድፈት የለም ማለቴ አይደለም። ግድፈት ራሱ ሰውኛ   እንጂ ሮበትኛ አይደለም። ብቻ ሁሉንም ድፍጥጥ ሲያደርጉት የትኛው  ፕላኔት እንዳሉ ይገርመኛል።  እንደ ሥርጉተ ሥላሴ ግን የአማራ የማንነት የህልውና ተጋድሎ ለውጤት የበቃ ነው  ባይ  ነኝ። ኮሽታ የማያሳማ፤ ዕወጁልኝ የማይል ለውጥ አለ። ቀውስ የለም ማለቴ  ግን አይደለም። የግርግር ሙሽሮች በእጃቸው የሰሩት ቀውስ አለ። ያው ሁሉ  የሥልጣን ጥመኛ አይደለ።  ያ ያው ሁሉ የቤተመንግሥት ቀይ ምንጣፍ ምኞተኛ አይደለምን? የአማራ የማንነት ህልውና ተጋድሎው መሰረታዊ ጥያቄዎች መፈታት ለመቻል  የሥርዓቱ አዋራሪሶች ከሥልጣነ ገብታቸው በስልት ማስነሳት ነበር የመጀመሪያው  ረድፈኛ ተግባር። ይህ በሚደንቅ ሁኔታ ተከናውኗል። ርዕዮቱም ቢሆን ሞራው  ነው ያለው። ይህ ስለተከናወነም በሁለቱ የአገር መሰረት ሃይማኖቶች ተፈጥሮ  የነበረው የ27 ዓመት ስንጥቅ ተገጥሟል። ተቋም ለሚበላው ከኦርቶዶክስ  ተዋህዶ እና ከእስልምና በላይ የሚኖሩት ለገሃድዋ ዓለም