ልጥፎች

ነገ ቀጥ ብሎ ቆሞ የተጠረገ ልብን ከሊቃናት ይጠብቃል!

ምስል
መኖርን ለማሰብ መሆንን መቀበል። „ጎለመስሁ አረጀሁም፤ ጻድቅ ሲጣል ዘሩም እህል ሲለምን አላዬሁም።“ መዝምሩ ዳዊት ፴፮ ቁጥር ፳፭ ከሥርጉተ©ሥላሴ  26.11.2018  ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ኑርልን አሜኑ! ክፉ አይንካብን ተስፋችን! አሜን! ·       መ ቅድመ ዕሳቤ። መኖር በነፃነት ልክ ይለካል። መለካትም በመኖር ልክ ይለካል። ነፃነትም በመኖር ልክ ይለካል። ነፃነት የአራት ፊደል ቅምረት ቢሆንም የሰው ልጅ መፈጠርን የሚገልጽ ታላቅ ቁምነገር ነው። የሰው ልጅ የተፈጠረው ለነፃነት ነው። የሰውን ልጅ የፈጠረውም ነጻነት ነው። ሰውነት እራሱ ነፃነት ነው። ስለሆነም የሰው ልጅ የተፈጠረበትን ነፃነቱን ሊጠብቅ ነው የተፈጠረው። የሰው ልጅ የተፈጠረውም ነፃነቱን ሊኖርበት ነው የተፈጠረለት። የሰው ልጅ የተፈጠረበት ምክንያትም በመፈጠር ነፃነት ነው። እግዚአብሄር አምላካችን የነፃነትም ፈጣሪም ንጉሥም ነው። ጌታ ቢባል ነፃነት የሰጠን የፈጠረልን እሱ ብቻ ነው ጌታ። ምድርም ለነፃነት የተፈጠረች ናት። ህዋም ለፃነት የተፈጠረ ነው። ተፍጥሮም ለነፃነት የተፈጠረ ነው። ጠባቂ ወታደራቸው ደግሞ ፍቅር ነው። ፍቅር የአግዚአብሄር  አካል የሌለው የቃሉ አገልጋይ የመንፈስ ድርጁ ሠራዊት ነው። ወልጋዳን መንፈስን የሚጋራ፤ የሚሞረድ። ሸካራውን አለስልሶ፤ ኮረኮንቹን የሚጠርግ።  ፍቅር ነፃነት ካገኜ ነፃነት ህልው ይሆናል። ነፃነት ህልው ከሆን ፍቅር ህልው ይሆናል። ሁለቱ በአንድ ሲዳመሩ ሰላምን ለዛውም የውስጥን ይፈጥራሉ። ሰላም ሰው ሰራሽ አይደለም። መዳህኒታችን እዬሱስ ክርስቶት የምድር ተልዕኮውን የመጨረሱ ዋዜማው የውስጡን ሰላም ትቶልን ስለመሄዱ አብስሮናል። የውስጥን ሰላም የተሰጠንን ስጦታ የምናውከው ደግሞ እኛው

የመጀመሪያው የሲወዘርላንድ ቶፕ ሞዴል ጠይም ዕንቁ ሴበር አሸነፈ!

ምስል
የመጀመሪያው የሲወዘርላንድ ቶፕ ሞዴል ውድድርን የጠይም ዕንቁ የ19 ዓመቱ ሴበር አሸነፈ! „ቆይቼ እግዚአብሄርን ደጅ ጠናሁት፤ እርሱም ዘንበል አልኝ። ጩኸቴንም ሰማኝ።“ መዝሙር ፵፱ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ  23.11.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ።                                           ሞዴል ማኑኤላ ፍራይ መሥራች።                                               ጠይሙ ዕነቁ ሰይበር አሸናፊ!                                           ሁለተኛ የወጣቸው ጠይም ዕንቁ። ሥ ሙ እራሱ የሚገርም ነው ሴበር። አትራፊ፤ አዳኝ፤ ተከላካይ፤ ተገን ወዘተ የሚሉ ሥሞች ይመስሉታል። ቤተሰቦቹም ስለፈጣሪያቸው ዕውቀታቸው ጥልቅ ስለመሆኑ ያመለክታል። ሥምን መላክ ስለሚያወጣው።                               ቤተሰብ ከድል ቀን ጋር። ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የሲዊዘርላንድ ውደድር ጠይም ዕንቁ አሸነፈ። ሲዊዘርላንድ ውስጥ አንዲህ ዓይነት ውድድር ሲካሄድ የመጀመሪያው ነው። ዝግጅቱን የጀመረቸው ብልኋ ሲዊዛዊቷ ማኑኤላ ፍራይ ናት። ትሁት ሰብዕና ያላት ተግባቢዋ፤ ፈግግታ የማይለዬት፤ ለስለሳዋ እና እና ታታሪዋ ዓለም አቀፍ ሞዴሏ ታላቅ ተግባር ነው የጀመረችው።   ለሲዊዘርላንድ እንግዲህ የመጀመሪያዋ መብራት መሆኗ ነው። ትባረክ ብያለሁኝ። የጀርመኗ ዓለም አቀፍ ሞዴል፤ በአገረ አሜሪካ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ፤ የአሜሪካ የልዩ መክሊት ዳኛ የሆኑት ወ/ሮ ሃይዲ ክሉም ከ10 ዓመት በላይ እጅግ በርካታ ወጣቶችን ያፈራ በዬዓመቱ የሚካሄድ የጀርመን ኔክስት ቶፕ ሞዴል ግዙፍ ፕሮጀክት አላቸው። ሞዴሏ በሚያ

የፈጣሪ፤ የእናት እና የልጅ ውለ ወግ -በቅኔ ዘጉባኤ ህዋዊ ጠረጴዛ።

ምስል
 የሰለሥቱ ጥምር ትምህርተ ተመክሮ። የፈጣሪ፤ የእናት እና የልጅ  የበሰለ፤ የበቀለ፤ ያሰበለ  ብልህ ውለ - ወግ።               „ልጄ ሆይ ቃሌን ብተቀበል፣ ትእዛዜን በአንተ ዘንድ ሸሽገህ ብትይዛት፣ ጆሮህን ጥበብን እንዲያድምጥ ታደርጋለህ፣ ልብህን ወደ ማስተዋል ታዘነብላለህ።“ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፪ ከቁጥር ፩ እስከ ፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ 21.11.2018 ከአገረ ደናግሏ ሲዊዝሻ። ·          እ ፍታ። እንዴት ናችሁ ቅኖቹ? የነፃነት ታጋይ ወገን ሲታሰር የሚከፋችሁ፤ ሲፈታ ደስ የሚላችሁ፤ ሰው ሲቸገር የሚጨንቀችሁ ሲቃለልለት ፍስሃ የሚኖራችሁ፤ ሰው ሲሰቃይ የሚመራችሁ ከስቃይ ሲፈወስ የምትፈኩ፤ ልጆች ከወላጆቻው ተለይተው ካቴና ሲባላቸው የምታነቡ ነፃ ሲሆኑ ደግሞ በሐሤት የምትፍነከነኩ ቸሮቹ የአገሬ የልዕልት ኢትዮጵያ ልጆች ከቶ እንዴት አላችሁልኝ? ተስፋ ካለ ምን ያስፈልጋል ትሉኝ ይሆን? ተስፋን ስንቅ የሚያደርጉ ስለተፈጠሩበት ሚስጢር ጥበብ ያላቸው ስለመሆኑስ? ሄውዞን የተቃኙ እንደማለት። አጥቁሮ ያከሰለን፤ ተስፋን የዋጠውን ቀን አል ደ መጥ ብሎ እንጂ ተስፋን ሰንቆ ማን ጦም ውሎ ያድራል? ጠ/ሚር አብይ አህመድ የተስፋ ባለቅኔ ናቸው።  ቅኔኛም ብቻ ሳይሆን ቃላት አዲስ የመፍጠርም፤ የማራባትም /የማግሰስ/፤ የማዘመንም እና ለህሊና ምቹ እና ጣፋጭ፤ ለጆሮም ድሎተኛ አድርጎ የማቅረብ አቅማቸው በመሪ ደረጃ በእኔ ዕድሜ የመጀመሪያው ናቸው። ጣዕሜ የሆኑትም ከዚህ አንጻር ይመስለኛል። ቅንነታቸው እና ርህርሀናቸው ደግሞ የህሊና ካሊም ነው። ·       ቅ ኝተ ተህሊና። የጠ/ ሚር አብይ አህመድ ንግግሮች ሌላ ሰው እንደሚጽፍላቸው የሚገምቱ አሉ። ይህን የቀደመ ን