ህወሃት ከትከሻ ኦነግም ከአንቀልባ ወርደዋል።
ህውሃት ከትከሻ ኦነግም ከአንቀልባ ወርደዋል። “ለአመጸኞች ልጆች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር” ትንቢተ ኢሳያስ ፴ ቁጥር ፩ ከጸሐፊ አቶ መስፍን ማሞ ተሰማ ታህሳስ 2011 ዓ/ም (ዲሴምበር 2018) ሲድኒ አውስትራሊያ mmtessema@gmail.com ሠላም ለናንተ ይሁን! የትግላችንና የመሥዋዕትነታችን የመታሰራችንና የመሰደዳችን ውጤት የሆነው አብያዊው መንግሥት በኢትዮጵያ መንበር ላይ ሲቀመጥ ለ 27 ዓመት በምድሪቱ ላይ የሰቆቃና የርኩሰት የጥፋትና የዝርፊያ ሁሉ ቁንጮ የሆነው አሸባሪውና ዘረኛው ህወሃት ከኢትዮጵያ ትከሻ ላይ ያለጥርጥር ተመንጭቆ ወርዷል። የወረደውና የተዋረደው ህወሃት መቀሌ ትግራይ መሽጎ ይንደፋደፋል። በወላለቀ ጥርሱ እየገለፈጠ፤ በተሸበሸበ እጁ እያጨበጨበ በስታዲየምና በአዳራሽ እየተሰበሰበ የቁም ተዝካሩን ያወጣል። ማጋነን የመሰለው በቅርቡ በ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ የተካሄደውን ስብሰባ ይመልከት። በዚያ አዳራሽ የክፉ ሰዎች ስብስብ የሆነው ህወሃት ጣዕረ ሞት ላይ ስለመሆኑ አቶ ስብሃት ነጋ በአስረጅነት የቀረበ « አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም » የሚለው ብሂል ማሳያ ነው። 27 ዓመት ዲሞክራሲን ቤተ መንግሥት ሆኖ ሲሰይፍ የኖረው ህወሃት መቀሌ ላይ መሰየፍ ባቃታቸው የጃጁ እጆቹ እያጨበጨበ የፀረ ዲሞክራሲነቱን ተዝካር አውጥቷል። አሸባሪው ህወሃትና በኢትዮጵያ ምድር በአምሳያው ፈጥሮ የዘራቸው አሜኬላዎች ሁሉ በለውጡ ማዕበል ተጠራርገው የኢትዮጵያ ትንሣዔ ዕውን እንደሚሆን