ምዕራብውያን ሆነ አውሮፓውያን በኢትዮጵያ #ተስፋ ላይ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ባይ ነኝ። ከተደጋገመ ግድፈትም ቢቆጠቡ ስል በትህትና ዕይታዬን አጋራለሁኝ።

 

May be an image of 1 personMay be an image of 2 people and text that says '0 omn o ท่'May be an image of 1 person, overcoat and hat

 

ዕራብውያን ሆነ አውሮፓውያን በኢትዮጵያ #ተስፋ ላይ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ባይ ነኝ። ከተደጋገመ ግድፈትም ቢቆጠቡ ስል በትህትና ዕይታዬን አጋራለሁኝ።

"አቤቱ በቁጣህ አትቅሰፈኝ፦

በማዕትህም አትገስፀኝ።"

(መዳ ምዕራፍ ፴፯ )

በማያቸው ሰሞንኛ ጉዳዮች ኢትዮጵያን ዳግም #ጨቀጨቅ ውስጥ ሊዘፍቅ የሚችሉ ውሳኔወች እንዳይኖሩ እሰጋለሁኝ። ኢትዮጵያ በማህበረ - ኦነግ መሪወች ልክንም መመዘን የተገባ አይመስለኝም። እንደ ሦስት ዓመት ህፃን ልብሱን አስተካክሎ መልበስ የማይችል። ቢሮውን በሥርዓት አደራጅቶ ለመምራት እንኳን አቅም የለሽ ሰብዕና የምስራቅ አፍሪካን፤ የአፍሪካ ቀንድን፤ የኢትዮጵያም ተስፋ ይሆናል ብሎ የምክር አገልግሎት መጠዬቅ፤ ለቀጣዩ የኢትዮጵያ ተስፋም እጩ ማድረግ #በፍፁም #ሁኔታ #ስህተት ነው።

32 ዓመታቱ የኢትዮጵያ መከራ እንዲያበቃ ከተፈለገ በሰው ልጅ ሰቆቃን ግድ የማይለው ሰብዕና፦ አጽናንቶ፤ አይዟችሁ ብሎ የማያውቅ ተፈጥሮ የመፍትሄ አካል አድርጎ መራመድ በብዙኃኑ ህልውና #የጭካኔ ውሳኔ ነው። ኢትዮጵያ አጽናኝ መንፈስ፤ አጽናኝ ቲም ያስፈልጋታል። ምዕራባውያን ሆኑ አውሮፓውያን ሰውን ማዕከሉ ያረገ ተፈጥሯዊ ሥርዓት ለኢትዮጵያ ያስፈልጋታል የሚል ግልጽ አቋምና ውሳኔ ላይ ሊደርሱ ይገባል። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ኢትዮጵውያን እንደ ጥንቸል የዶክተሪን መሞከሪያ ጣቢያ መሆኗ ዲታ አገሮች ሊያማቸው ይገባል።

ርህርህና፤ ደግነት፤ አጽናኝነት ትምህርት ቤት የላቸውም። ግን በተፈጥሮው ያልተበደለ እና በመልካም ቤተሰብ ውስጥ ያደገ ርህርህናን ውጭ ለሸመታ ሳይሄድ ውስጡ ተገርቶ፤ ውስጡ ሰላማዊ ሆኖ ያድጋል። ይኖራልም። ከዛ ለማህበረሰቡም ጠንቅ አይሆንም።

በተለይ ባሳለፍናቸው ስድስስት የምጥ ዓመታት፤ የጭንቅ ሰዓታት፤ የስጋት ደቂቃን ሁሉ ለሰከንድ ከኢትዮጵያ መከራ ጋር አብረው ለማዘን፦ ኢትዮጵያንም እግዚአብሄር ያጽናሽ ለማለት ያለደፈሩ የማህበረ ኦነግ መሠረቶች ዛሬ የመፍትሄ አምንጭነት እና ተደማጭነትን በምዕራብውያን ማግኜት ማለት ለእኔ #ሰባዕዊነት #ቀራንዮ እንደዋለ በኢትዮጵያ ይሰማኛል።

#ርህርህና #አይጠናም #ርህርህና #አይገዛም #ርህርህና #ዳር #ደንበር የለውም። ሰው መሆን ይበቃኛል ላለ ሁሉ በአምላካችን በአላህ የተሰጠ ፀጋ ነው። ይህን ጠቅጥቆ ከጨካኞች ያበረ ያበረ፤ ጭካኔን ያስተባበረ ለራሱም መዳኛ መንገድ ሊፈለግለት ሲገባ ቁንጮ የመፍትሄ አካልነትን ማጎናፀፍ በሰባዕዊነት ላይ የታወጀ ሥነ - ስቅለት ነው ለእኔ።

የተከበሩ አንባሳደር ማይክ ሃመር ሲመክሩ የሰነበቱት ከጭካኔ መንፈስ ካለው ሰብዕና ጋር መሆኑ #የተገባም #ፍትኃዊውም ነው ብዬ አላምንም። እንደገና 40 ዓመታት ኢትዮጵያ በጨቀጨቅ እንድትደክም የሚያደርግም እርምጃ ነው። ሰውን ጠላት አድርጎ የተነሳ ሰብዕና ህመምተኛ ነው። ስለሆነም የህክምና አገልግሎት ሊሰጠው ይገባል። በሥነ - ልቦናም #ጥቁ ሰብዕና ጭካኔ ኦክስጅኑ ስለሆነ የዘርፋ ባለሙያወች እርዳታ እንዲሰጡበት ማበረታት ይገባል።

አይደለም ለኢትዮጵያ ለኦሮሞ ህዝብም የኦነግ ኦረንቴሽን፦ ዶክተሪን በፀረ ሰውነት በበቀል ስንቅ የተፈጠረ ስለሆነ ለራሱ ድርጅቱ ለወጣበት ማህበረሰብም መጥፊያው ነው። የኦሮሞ እናቶች ዛሬም ዕንባን ታጥቀው እዬኖሩ ነው።

#ሱፍና #ገበርዲን #ሰባዕዊነት አይደለም። ሰባዕዊነት #የህሊና #ፃዕዳነት ነው።

እንዴት ናችሁ ውቦቼ።

ኑሩልኝ።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

19/05/2024

ጊዜ ራዲዮ ነው።

   

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።