ይድረስ ለማከብረዎት ለብ/ ጄ/ አሳምነው ጽጌ ።
ይድረስ ለማከብረዎት ለብ/ ጄ/ አሳምነው ጽጌ ባህርዳር። „ወርቅና ብዙ ቀይ እንቁ ይገኛል የእውቀት ከንፈር ግን የከበረች ጌጥ ናት።“ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳ ቁጥር ፲፭ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 08.01.2018 ከእማ ዝምታ - ከሲዊዝሻ። · መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=Swe0gQaJ8FU ETHIOPIA - '' አርበኞች ግንቦት 7 የውሸት ፖለቲካ እየተጠቀመ ነው። ' ' ቅሬታ አቅራቢ የግንባሩ ወታደር - NAHOO TV Nahoo TV Published on Jan 5, 2019 ጤና ይስጥልኝ የማከብረዎት ብ/ጄ አሳመንው ጽጌ እንዴት ሰነበቱ? ደህና ነዎት ወይ?እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሰዎት። መታመን እንዳይደርቅ አስቸኳይ ምላሽ ቢሰጥበት መልካም ነው ለጥያቄዬ ... ከዚህ ሩህሩህ ዘመን በላይስ ምን ይናፍቃል? ያላዩት አገር ካለሆነ በስተቀር? · ምክንያታዊ ጥያቄ በትህትና … ግን የግድ መልስ ሊሰጥበት የሚገባ። አንድ ቃለ ምልልስ አሁን አዳመጥኩኝ በናሆ ቲቪ። በግዳጅ ጊዜ ብዙ ፈተና ስላለ አብዛኛውን ጉዳይ እንደማንኛው ወታደራዊ ሥርዓት አዬሁት። እርግጥ የሚያሳዝኑ ነገሮች መኖራቸውን ሳስብ የድምጽ አልባዎቹ የኢትዮጵያ እናቶች ዕንባ ይቆም ዘንድ ፈጣሪ ይህን አዲስ ሰውኛ ዘመን ስላመጣ ተመስገን ማለቴ የዘወትር ግዳጄ ይሆናል። በሌላ በኩል ሃላፊነት እና ተጠያቂነት በዬትኛውም ደረጃ መቀበል እና መፈጸም ደግሞ የነገን የኢትዮጵያ መሪ የመሆን ዕድል ቢገጥም ብሎ