ልጥፎች

እሸት ራዕይን ምራቁን በዋጣ ቻይነት ምህንድስና ብቻ አዋጭ ነው።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ጠንቃቃነት ያተርፋል እንጂ አያከስርም።  „ ምንም እንኳን በለስም ባታፈራ፣ በወይን ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፣   የወይራ ሥራ ቢጓል እርሾችም መብልን ባይሰጡ በጎችም ከበረት ቢጠፉ ላሞችም በጋጥ ውስጥ ባይገኙ   እኔ ግን በ እግዚአብሄር ደስ ይለኛል፤ በመዳህኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። “ ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯ ቁጥር ፲፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 26.02.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።                                ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት አላችሁልኝ። ደህና ናችሁ ወይ? በአንድ ጉዳይ ዙሪያ ትንሽ ነገር ልል አሰብኩኝ። አብን ሚሊዮነም አዳራሽ በተከታታይ ጠይቆ እንዳልተፈቀደለት ይልቁንም OMN እንደተፈቀደለት ገልፆል። በዚህ አብን ተከፍቷል። ተገልለኩኝ እያለ ነው። ይህን መጠበቅ ያስፈልጋል። ስለምን? አሁንም የዞግ ፖለቲካ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው። አውራው ፓርቲ ደግሞ ኦዴፓ ነው። የምናደምጣቸው ዝበት ያለባቸው ነገሮች ከኦዴፓ የመነጩ ሳይሆኑ ከራሱ ከኢትዮጵያ የዞግ ፖሊሲ ነው የሚመነጨው። አድሎ፤ መገለለ፤ መጫን፤ ጭቆና ዴሞክራሲ በሌለበት አገር ግድ ነው። ተጋድሎው እኮ ሁሉን እኩል የሚያደርግ ቋሚ ሥርዓት ይፈጠር ነው። ለዛ ደግሞ በአንድ ጀንበር የሚሆን አይደለም።  የለውጥ መሪዎቹ እራሱ እኮ ከዞግ ድርጅት የወጡ ናቸው። ሥነ - ልቦናቸው፤ ልምዳቸው ተመክሯቸው በዛ ዶክተሪን የተቃኜ ነው። ከዚህ ለመፈታት ጊዜ ይጠይቃል። እያንዳንዱ መሪ ከራሱ ጋር እኮ አሁን ፍትጊያ ላይ ነው ያለው። ሬድ ሜድ እንዲሆኑም እንሻለን።  አሁን እኔ ዶር ለማ መገርሳ እና ዶ

የኢዴፓ እጩነት /አዲስነት ትልሞሽ/

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  የኢዴፓ እጩነት። የሚቀድመው   የትኛው ይሆን? ግን ገነገነ   ወይንስ ገነነ ልበል ከቶ! „የፃድቃን አፍ ጥበብን ያስተምራል፤ አንደበቱ ፍርድን ይናገራል።“ መዝሙር ምዕራፍ ፴፭ ቊጥር ፴ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 25.02.2018 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ትናንት በዋለው የአጋር ድርጅቶች ይሁን የአጋር ክልሎች ዓወደ ህዝባዊ ስብሰባ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ ወጥ ፓርቲነት ድርጅታቸው እንደሚሸጋገር አብስረዋል። ጉደኛው ኢህአዴግ ወደ „ኢትዮጵያዊ ፓርቲነት“ ሊለወጥ ደስ ይላል። ኢትዮጵያዊ ፓርቲነቱን ሲያልም ግን የቋንቋ ፌድራሊዝምን ተሸክም ይሆን?   ብቻ መሰናክሉን ማለፍ ከተቻለ ወሸኔ ነው ማለፊያ። መሰናክሉ የህሊና ለውጥን ነው የሚጠይቀው። የቅርቡን የወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ቃለ ምልልስ ብቻ በቂ ነው። ምን ያህል የዘለበ ገማና ኢትዮጵያ እንዳለባት። አሁን እንኳን በዬቦታው የራስን ሰው ለመሸጎጥ ማራቶኑ ተንጠራርቶ አገር እያመሰ ስጋት እያቀና መሆኑ ነው የሚደመጠው። የሳቸው ቸር ምኞት ግን ሁልጊዜም ይገርመኛል። እስኪ ያሳካላቸው … አሜን አሜን ይሁን ይሁን ብለናል።      ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ እኔ እንዲያውም ኦዴፓ አውራ ፓርቲ ሆኖ ለመውጣት ሥም ሲያድል ብአዴን ተቀብሎ አዴፓ ነኝ ከዛሬ ጀምሮ ሲል ምን አለ ኢዴፓ ብትባል ብዬም ነበር/ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ። / ማለቴ አማራ ክልል ነው እና ኢትዮጵያዊነትን ተሸከም የሚበላው በዬዘመኑ። እነ አቶ በረከት ስምዖን፤ እነ አቶ አዲሱ ለገሰ፤ እና አቶ ዮሴፍ ህላዊ፤ እነ አቶ ተፈራ ዋልዋ፤ እና አቶ አለምነህ መኮነን ምን ተዘርዝሮ ሲያልቅ ... አሁንም ስልጣን ምንችንም አይደለም

የኢትዮጵያ ህዝብ መኖርን ነው በትህትና እዬለመነ ያለው።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ርህርህና የመሰረት ድንጋይ። „በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ“  መዝሙር ፴፰ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 25.02.2018 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ይህ ኪዳን የሁልጊዜ እንዲሆን እመኛለሁኝ! ጤና ይስጥልኝ ውዶቼ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? ኦህዴድ እውን ኦዴፓ ከሆነ ልለው የምሻው ነገር ይኖረኛል ዛሬ። ከሁሉ በፊት፤ ከሁሉ አስቀድሞ መከወን ያለበት መሪዎቹን በዬደራጀው ያሉትን በፌድራልም ይሁን በክልሉ ሆነ በዞን ይሁን በወረዳ የሚያስቀምጣቸውን ወገኖች ሞራላዊ ሰብዕን መገንባት ያለበት ይመስለኛል። አውራ ፓርቲ ስለሆነ አብነቱ ከዛ ነው የሚጀምረው እና። ሁለቱም በፍጹም የተገራ ሰብዕናቸው ነው ህዝብ ከሰማይ እንደወረዱ መላዕክት የሚያቸው። እና ተከታዮቻቸውም እንደ እነሱ እንዲሆኑ ማድረግ ግድ ይላል። ከሁሉ አሰቀድሞ ከሁሉም በፊት የህዝብ ሃላፊነት ለመስጠት ከማቀዱ በፊት ሁሎችም በውስጣቸው የቋጠሩትን ቂም በቀል እና ቁርሾ እንዲያራግፉት ማድረግ ይጠበቅበታል - ኦዴፓ። በሩን ዝግት አድርጎ፤ ከሚዲያ ውጭ በሆነ ሁኔታ ይምከር - ኦዴፓ። በውነቱ እጅግ የሚያሳዝኑ ነገሮች ነው የሚታዩት። የሚደመጡት። የእኔ ለመባል የእኛ ማለትን ይጠይቃል። አብሶ እላፊ መሄዱ ነው የሚጎረብጠው ከሚፈጸው አሰቃቂ ኢ-ሰብእዊ ተግባር በላይ።   በአዲስ አባባ ጭፍጫፋ እና እስር ጉዳይ "ዘራፊ፤ ሃሺሸኛ፤ ሌባ ወሮበላ" ነበር የተባሉት የተሰዉትም የታሠሩትም ዜጎች። አሁን ደግሞ "ህገ ወጥ ወራሪዎች ናቸው" የሚባሉት በለገጣፎ ያሉ ነዋሪዎች ዜጎች። ትናንትም የነበረው እራሱ ኦህዴድ ነው፤ ዛሬም ያለው ኦህዴድ ነው ራ