ልጥፎች

አህዱ ራዲዮ እና ዕድምታው በጥቂቱ።

ምስል
አህዱ አሰገዱ። „ተግሳጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቆጣ፤ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ ቁጣው ፈጥና ትነዳለችና። መዝሙር ፪ ምዕራፍ ፲፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ 12.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።                                               የላቀው ሊሂቅ! ·       ግ ራሞተ ሰሞናቱ።፡ አህዱ በሚባል ራዲዮ አቶ ሌንጮ ለታ እና አቶ በቀለ ገርባ ቃለ ምልልስ አድርገዋል። ትንሽ በትንሹ እንዬው እስቲ ብዬ አስባለሁኝ። በውይይቱ የተሻለ የመልስ መስጠት ጥበብ በአቶ ሌንጮ ለታ አይቻለሁኝ ስልታዊ እና ግልጻዊ ለመሆን ጥረዋል። የአቶ በቀለ ገርባ ደግሞ ወደ መንፈስ ለመቀረብ ማዶኛ ሆኗል - ለእኔ። ያልመድኩት ነገር የሳቸው ጉዳይ ነው። ጊዜ ያስፈልገኛል።  አድማጮች ሲጠይቁ ነበር። ጠያቂዎች እና አስተያዬት ሰጪዎች አቶ ሌንጮ ለታን ከፍ አድርገው „ክቡር“ እያሉ ማቅረባቸው አቶ በቀለ ገርባን አልተመቻቸውም የመረጋጋት ሁኔታ አላዬሁባቸውም። እኔ ሁለመናን ነው የምከተታለው።  ይህን ሳይ ሚሊዮኖች የሰገዱለት  የአብይ ለማ ፍቅረ አክብሮት እንዴት እንዳስተናገዱት ወፌን ጠይቅኳት። ይገባል አይደል። በሁለቱ ሊሂቃንም ብዙ ሰው ነው የሚጸፈው አክብሮ። ወዶ ናፍቆ አልቆ እና .... እናማ አቶ ሌንጮ ለታን አምስገነው አድማጮች ሲናገሩ ፊድባኩን ለኩት፤  ይህን ወስጠቱን ቪዲዮውን እያዬ መገመት ነው። https://www.youtube.com/watch?v=ifs2-94ibME አቶ በቀለ ገርባ አቶ ሌንጮ ለታ በአሐዱ ሬዲዮ bekele gerba lencho leta interview on ahadu radio አቶ በቀለ ገርባ ባላፈውም ጊዜ ሥሜ በክፉ ተነሳ፤ እን እከሌ አሳንሰው አዩኝ  ብለው እ

የህሊና ሪህ

ምስል
የህሊና ሪህ። „እኔ ግን ንጉሤን ሾምሁ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ።“ መዝሙር ፪ ቁጥር ፮ ከሥርጉተ©ሥላሴ 12.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። መነሻ። https://www.zehabesha.com/amharic/archives/91906 « እኔን እጎዳለሁ ብለህ መሃል ሰፋሪውን አድማ አስተማርክ » | አቻምየለህ ታምሩ ነገረን ነገር ሲያመጣው .. . እኔ አማራ የሆንኩት አቶ አቻምየለህ ታምሩ በቪዥን ኢትዮጵያ ጉባኤ ላይ ተጋብዞ ጊዜ ፈጀህ ተብሎ ሁለት ደቂቃ ሲለምን እና ሌሎች ደግሞ የተሰጣቸውን ዕውቅና አክብሮት ሳይ ነበር በዛች ቅጽበት አማራነቴ ውስጤን ያሟሸው። ጥቃት አልወድም!  እና ሁልጊዜ ሥሙን ሳይ የአቻምን የእኔ አማራነት የመሆን ፈቀድ ከሱ ነፍስ ጋር የተያዘዘ ስለመሆኑ አዘክረዋለሁኝ። የአማራነቴ ሥጦታ የመጣው ከአቻም መገለል ጋር በፅኑ የተያየዘ ነው። ከእንግዲህ ወደኋላ እንደ አልመለስ አድርጎ ደግሞ ቅኑ የጎጃም ህዝብ በደሙ አትሞበታል። የጎጃምን የመሆን ልቅና ያዬሁበት ዘመን በዚህ የአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎ አብዮት ዘመን ነው።  የጎጃም ህዝብ የቅኔ ጉባኤ አቅም እና ቃልኪዳን አማራነቴን የበለጠ አድምቆልኛል።   እሰቃለሁኝ እኔ እዚህ በአማራ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት በአማራ ክልል ብቻ አማራነትህን ጣል ቲያትር ሲተውን። እሚሆን አይደለም። በልዩ ሁኔታ አማራኔቴ ልክ እንደ ፆታዬ ክብሬ ሆኗል። የአብይ ሌጋሲ ይልቅ ባይደክም ደስ ይለኛል። ሥርጉተ ሥላሴ እኮ ሞገደኛ ናት። የእሷን ልብ፤ የሷን ፍቅር፤ የእሷን ታማኝነት ለማግኘት ብዙ መድከም ያስፈልጋል። እኔ ስላልኩት ሳይሆን ከልጅነት እስከ እውቀት የሚያውቁኝ ሰዎች ያውቁኛል። አብሬያቸው የሠራሁት እንደ ዕድል

ሥነ ግጥም - ለአረጋጊ ባለመክሊት ዬኛው።

ምስል
„አቤቱ የፊትህ ብርሃን በላያችን ታወቀ።“   መዝሙር ፩ ቁጥር፮ ከሥርጉተ©ሥላሴ 11.10.2018 ከጭምቷ ሰዊዘርላንድ *** ያን ቀን „ቀኑ“ ተከስቶ ወፍ ጎሽ! ብሎት ያዬሁ ለታ ስብሰለሰል ስወያይ „ከቀኑ“ ጋር እንዲያ ለ እ ፍታ መተከዜን ዘብ አቁሜ ለ አ ፍታ ብቻ ብቻ ህልም ሲፈታ እንዲያ እና እንዲህ ሲፈታታ፤ የነፍስ ውሽክታ - በመልካም የልብ ስንኝ ፈገግታ፤ የቅኔ ቤት፤ የዋሸራ፤ የመንፈቀ ሌሊት - ልዑቅ ዕድምታ ተረገጥ ሆነ የመገኘት የኔታ! ያለተረዱት ቢፈልጉት፤ ባይፈልጉት ያልፈለጉት ሳይረዱት፤ ባይረዱት የተረዱት በእሺታ አይሆ ንም ን አ ረዱት! ሲሆን ሲሆን ማታማታ የነበረ ለናት እንጂ አልነበረም ለህምታ። ሲያማክረው የሩቅ አገር ወፍ ያወጣው ያለስርቅታ ያ ቀንዲሉ የዘመን ተደሞታ፤ በአርምሞ - በክህሎቱ ተመስጦ ያለውካታ ቀነ የሰጠው የቅንነት ብርቱ እርካታ፤ የአባት አደር የወልዮሽ የሎሬቱ ገበታ! የህልመኛ ባዕት ብጡልነት ትርታ ያልነበረ ለቱሙታ፤ ግን እንጂ በቅብዕው ያልነበረው ቅሬታ ስለ ምህረት ተስፋው ስለዘለቄታ የንጽህና ድንግልና ግርምታ፤ የዘመን ሙሉ ስንዳታ! ሴራን ላይወዳጅ፤ ላይ ዳ በል ከካኳቴ ጋራ ከሆታ ቂምን ላይቋጥር፤ ሊሆንለት ብቻ ብቻ ለይሁንታ፤ የርህርህና አንበል ያ ብላቴና፤ ያ ከርታታ ከልብ እንጂ ማዳመጥን ማህተሙ የተመታ። በሩቅ ምናብ ሆኖ ሰታዘበው፤ ... ጥድፊያ ሲሮጥ ሲያሯሩጥ በትዝበቱ ሲከትብ ሲመሰጥ በእጬጌታ፤ አድብየለሽ ሲባክን ሲጋት የሲቃ ኩልልታ ... የጠዛ እልልታ ያ ባተሌ ልበቅኑ ይታደማል በጸጥታ። ሲያድጥ ሊያላልጥ የሸር ጎርምጥ አይ ተድሮ ሲኮበልል ሊሸመጥጥ

ቤተ መንግሥት ክራንች ላይ ያሉ ወገኖቸን ሲያከብር ማዬት ናፈቀኝ።

ምስል
ኢትዮጵያዊነት የውስጥ ሲሆን የመከራ ቋት ያመነጫል። „በጎውን ማን ያሳዬናል የሚሉ ብዙ ናቸው። አቤቱ የፊት ብርሃን በላያችን ታወቀ።" መዝመረ ዳዊት ፪ ቁጥር ፮ ከሥርጉተ © ሥላሴ  11.10.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ።                   የኔዎቹ እግራቸውን በደንብ አድርጋችሁ እዩት አደራ! መነሻ። https://ethiomedia.com/2018/10/08/famed-former-pilot-returns-to-ethiopia-after-years-in-eritrea-prison / Famed former pilot returns to Ethiopia after years in Eritrea prison እያማጥኩን ተመለከትኩተኝ የዚህን አራትዓይናማ ጀግና የእግር እጣቶች። እያለቀስኩኝ ተመለከትኩኝ የዚህን አርበኛ የሰራ አካላት። ወስጤ እርር ኩምትር በሎ አዬሁት የዚህን ብርቱ ሰው የህሊና ቁስለት። ከጠላት እጅ መግባት ይህን ያህል ዋጋ ያስከፍላል። ኢትዮጵያ ብትገኝም ይህን መሰል ሰቆቃ ይፈጸምበታል። ቁም ነገሩ አሁን ባለው የፍቅራዊነት ጉዞ ምን ያህሉን እጅ ለመፈወስ፤ ለመካስ ዝግጁነት አለ ነው። የቀሩትስ የኢትዮጵያ ልጆች እስረኞች በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ? መቼነውስ ከጎደለው አካላቸው፤ ቅስሙ ከተሰበረው ሥነ - ልቦናቸው ጋር ለአፈራቸው የሚበቁት? ኢትዮጵያዊነት እንዲህ ይገለጻል። ለአንዱ ረመጥ ለሌላው ደግሞ ገነት፤ ለአንዱ የክብር መንበር ለሌላው ደግሞ የመከራ ግዞት። አዎን ኢትጵያዊነት ለቅኖች ሩህሩህ አይደለም። ለገሮች እራስ እግሩ መንገዱ ሁሉ ትሬኮላታ ነው። ኢትዮጵያ በሚቀኑበት ሰብዕና ውስጥ ልክ እንደ ጀግናው ፓይለት ኮ/ ታደስ ሙሉነህ የጥቃት ጎራዴውን መሽጓል። የኢትዮጵውያን የብቃት ልክ እ