ልጥፎች

ጠ/ ሚር ዶር አብይ ለልዩ ሃይሉ ትህትና መቀለባቸውን እደግፈዋለሁ።

ምስል
መጋጋል ። „እግዚአብሄር የእውነት ዳኛ ነው፤ ሃይለኛም ታጋሽም ነው። ሁልጊዜ አይቆጣም“ ከሥርጉተ© ሥላሴ  13.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። በሰሞናቱ የልዩ ሃይል አመጥ ጉዳይ የሁለገብ ሊቀ ሊቃውነቱ ሻለቃ ዳዊት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አዳመጥኩት። ያው ሙያዊ ነው። እሳቸው ሉላዊ ዕውቀትም፤ ልዩ ተመክሮም ያላቸው ሊሂቅ እጬጌም ናቸው። በሌላ በኩል መጀመሪያ ላይ ከምንም ያልቆጠሩት ሁሉ አሁን ውይይቱ ሦስት ቀን ነበር ሲባል ማጋጋሉን ተያይዘውታል። መጀመሪያ ላይ ነው ጠረኑ ትክክል አለመሆኑን በርቀት ማዬት፤ ጠንከር ያለ ማሳሰቢያ ለመንግስት መስጠት። ቀደም ብሎ ጉዳዩን ማጥናት፤ መተንተን እና መረጃውን ከተለያዬ አቅጣጫ የመገምገም ምህንድስና ሊደረግበት ነበር የሚጋባው። ቀድሞ ነገር እንደዚህ ያለ ነገር ሲደመጥም ወዲያው ማብራሪያ መስጠትም የተገባ አይደለም። ችኮላ አያስፈልገውም። ተደሞ ያስፈልገዋል። ርጋታ እና ስክነትም ይጠይቃል። አሳድሮ አገላብጦ አይቶ ከስሜት ጋር ሳይስጠጉ፤ በራስ ፍላጎት ሳይቸነክሩ የጭብጡን ማንነት ብቻ በራሱ ማንነት ራሱን አስችሎ መመርመር ነበር የሚገባው። የሆነ ሆኖ እኔ አስተያዬቴን ዛሬ ልሰጥ የፈልግኩበት ምክንያት ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮወርጊስ ዕይታ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የወሰዱት እርምጃ ትክክል አይደለም የሚሉትን ነው። እሳቸው ዘመን ጠገብ ባለሙያ ስለሆኑ እሳቸውን አሻቅቤ መተቸት አልችልም። ክህሎቱም ተመክሮውም ብልጹግ ነው በሲቢሉም ሆነ በወታደራዊ። መሬት ላይም ሰርተውበታል። ነገር ግን እኔ እንደ ሰው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የወሰዱት እርምጃ ትክክል ነው ብዬ ነው እማስበው ። ጠ/ ሚር አብይ አህመድ እያስተማሩ ያሉት የሃሳብ አቅም ከባዱን ተራራ ንዶ፤ ደልድሎ፤ ሸካራውን ለግ

ግልጽነት ገዳም በመግባቱ ቋቅ ነገሰ።

ምስል
ግልጽነት ገዳም በመግባቱ ቋቅ ነገሠ። "እናንተ የሰው ልጆች እስከ መቼ ድረስ       ልባችሁን ታክብዳላችሁ?" ሐሰትንም ለምን ትሻላችሁ?"  መዝሙር ፬ ምዕራፍ ፪  ከሥርጉተ © ሥላሴ  15.10.2018  ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። እኔ የሚገርመኝ ብሄራዊ የኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማ የያዙት በአደባባይ ተረሽነው 1200 ነፍሶች ጦላይ ላይ ባለቤት፤ ጠያቂ ሁነኛ ድርጅት ሳይኖራቸው ፍዳቸውን እያዩ በሌላ በኩል ደግሞ የብሄራዊ ሰንደቅዓላማ ቀን ሰሞን ምክክር ውይይት ዲስኩር ይደመጣል። ይህን አጣጥሙ መጀመሪያ። እኔ አይደለም የምላችሁ ፋክት ነው የሚያፋጥጠው የጠ/ ሚር ጽ/ቤትን። እኔ እኮ የማይጠቅመው ነገር እንደሚጠቅም ሁሉ እንዲቀጥል የሚፈቀደልት ምክንያት ነው የማይገባኝ። ትናንት የኤርትራው ፕሬዘዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ ኢትዮጵያ ጎራ እንዳሉ አዳመጥን። ያዳመጥነውን አላምጠን መወጥ ይገባ ስለነበር እኔ አቶ ዳውድ ኢብሳ የኢትዮጵያን መንግሥት እያስደገደጉ ነው ብዬ ነው እማስበው ብዬ የጻፍኩትም ለዚህ ነው። አቶ ፍጹም አረጋ ደግሞ ይህን አስተባብለዋል በዓለም አቀፍ ሚዲያ ወጥተው። ሆደ ሰፊነት ይሆን 5 ወጣቶችን በአደባባይ አስረሽኖ 1200 ባለቤት አልባዎችን ጦላይ ፍዳ እያስከፈለ፤ የጫት፤ የሺሻ፤ የቁማር፤ የዝርፊያ ፓርቲ ተፈጥሮ የተለጠፈላቸው፤ ጎንደር እና ወሎ ተነጥለው ከዛ የመጡ ወንጀሎኞች ማለትስ ምን ማለት ነው? አይገባንም ይህ? ልብም ህሊናም አለን። ግልጽነት አዲስ ለውጥ አራማጆች መርህ ይሆናል ተብሎ ታውጆ እምናዬው እምንስማው ግን ድብቅነት እንደ ነገሠ ነው። ከስሜን አሜሪካ ከጠ/ ሚር ጉዞ መልስ ጀምሮ ያሉ ነገሮች በህልማችን ለምናምን ሰዎች ዕድምታውን እናውቀዋለን። ወንበሩ ባ

አቶ ዳውድ ኢብሳ የኢትዮጵያን መንግሥት እያስደገደጉት ነውን?

ምስል
አቶ ዳውድ ኢብሳ  የኢትዮጵያን መንግሥት እያስደገደጉት ነውን? „አንተን በፍራሃት ወደ ቅድስናህ መቅደስ እሰግዳለሁ።“ መዝሙር ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ©ሥላሴ 14.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። አቶ ካሳሁን ጎፌ መግለጫን የገባኝን ያህል ስጥፈው ቆፍጠን ያለ ነው ድፍረቱ ከኖረ ብዬ ነበር። አቃለው አሳንሰው ሲዩትም ደግሞ አይደለም ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመካከለኛው ምስራቅም አስጊ ነው ብዬ ነበር። የአፍ ወልምታ ለተባለውም ያልኩትን ብያለሁኝ። ሲጀመርም እኔ የአቶ ዳውድ ትምህክት መሰረት እንዳለው፤ በቀላል መታዬት እንደሌለበት ሞገደኛ እና ከባድ ውሳኔ ስለመሆኑ ገልጫለሁኝ። የ5ቱ የ ኦሮሞ ድርጅቶች ውሳኔም ከዚህ ጋር የሚዋደድ ነው። አሁን ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ በስኳር ፖለቲካ ኢትዮጵያ እንደ ገቡ አዳመጥኩኝ። ፍቅሩን ያሰንብትላቸው እንጂ እፍ ብለዋል። የጣሊያኑ መሪ ወደ ዛው አቅንተው እንደ ነበርም አድምጠን ነበር። እና ተመለሱ ይሆን ወይንስ ምጥዋ ላይ ተበለስ ጋር? ከዙፋን አስወርዶ በጥድፊያ ያሰመጣው የኤርትራን መንግሥት ምን ቢኖር ነው ብለን ማሰብ ግድ አለን። ደረታቸው ነፍተው ሲናገሩ የሰነበቱት አቶ ዳውድ ኢብሳ በሦስተኛ አገር ሽምግልና ከልሆና በጅ አልልም ያሉ ይመስላል። ሌላ ከሚመጣም ወዳጃቸው አገር ብትሆንላቸው ይሻላቸዋል። ነገም በ አገርነት እንቀጥላልን ባይም ናቸው። ወጣት መሪም ታች ካለ በቂ ነው ብለዋል። ምርጫው የሳቸው ነው። ማን ደፍሮ ይናገራል ጭጭ ረጭ ሆኗል። ከእትጌ ኤርትራ ቤት ዘው ከተባለ መውጫ የለም፤ ወይ መዋጥ ወይ አብሮ መስመጥ ነው … ግን ኢትዮጵያን ማን ነው እዬመራት ያለው? በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ኤርትራ ታጣዋለች ተብሎ የታሰበው ረጅም እጅ ይሁነኝ ተብሏል። ኦዴፓ

መቼ ነው የህወሃት መኳንነት ሃፍረት የሚባል የሚሰራላቸው?

ምስል
አለማፈረን ግባ በሉት ¡ „አህዛብ ለምን ያጉረመርማሉ?“ መዝሙር ፩ ቁጥር ፪ ከሥርጉተ ሥላሴ 13.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። የእንጀራ ልጆች ፍዳ! ጫጫታ በረከተ በማህበረ ተጋሩ ሠፈር። መቼም እኔ ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌሰቶ ጋር ተብጥብጦ የተጋቱ አለማፈር ብቻ መሆኑን እዬተረዳሁኝ ነው። እንዲያውም አያፍሩም አሁን አዬር መንገድ ላይ ባለው ገመና። የተጠናከረ የሎቢ ተግባር እንዳይካሄድ እኮ መቼም ኢትዮጵያ የሚል አንድ ተቋም ብቻ እሱ ስላለ ነው እንጂ የመብት ረገጣው እኮ የኦሽትዝ ግፍ ያዬለበት ነው። ሰብዕዊ መብት ይከበር የሚሉ አገሮች እኮ የ አዬር መንገዱን አሰራር እንደጸዬፉት ማድረግ ይቻላል። ግን ከ አዬሩ ላይ ያለው ንጹህ ብሄራዊ ሰንድቅ አላማ ቃልኪዳን ስለሚይዝ ነው ዝም የሚባለው።   አሁን እዛ ያሉ የተጋሩ ሃላፊዎች ሳር ቅጠሉ እሱ በእሱ ሲሆን ትንሽ ብጣቂ ነገር እንዴት ልብ አይሰራላቸውም? አያፈሩበትም፤ በር ስትከፍትም፤ ኮሪደርም፤ መጸዳጃ ቤትም፤ ካፍተሪያም፤ ሜዳውም ላይ ሁሉም ቤተ ተጋሩ ሲሆን አይቀፍም! ህሊና ያለው ጥፍር ላይ ነውን?  በሩ ራሱ እኮ ጠረኑ እነሱን እነሱን ነው የሚለው። ወለሉም እንዲሁ ነው። በእነሱ ዘመን እኮ ነው ሰው እያዬ እዬሰማ እግሩ የተቆረጠው ምክንያት ተፈልጎ። በእነሱ ዘመን ነው ወንድ ልጅ የተንኮላሸው፤ በእነሱ ዘመን ነው ዘራፋ እንዲህ ባህል የሆነው፤ ምን ያልታዬ መከራ አለና። ቃለ ምልልሱ ሲታይ ጠያቂውም ተጠያቂውም ዘገባ አቅራቢውም ዘገባውን አስተላላፊውም ያው ነው ቤተ ተጋሩ። እዛ አዬር መንገድ አንድ ነገር ሲፈጠር አንድ ሰው ለዬት ያለ ለማግኘት ይችግራል። በውነት ይቸግራል። በጣም ጸያፍ ነገር ነው። ዋ! ነው የሰማይ ጦሮ የታዘዘ ዕለት። አሁን