ልጥፎች

የአቤቶ ኦፌኮን የሃሳብ አድራሻው የት ነው?

ምስል
የአቤቶ ኦፌኮን የሃሳብ አድራሻው የት ነው? „የሠራዊት ጌታ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል … ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ“  ሐጌ ፩ ከቁጥር ፭ እስከ ፮ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 30.12.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·        ጠ ብታ። ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ? እንዴት ናችሁ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። ብቻ የትግራይ እና የኦሮሞ እናቶች የመንፈስ ብክነት፤ ጫን - ተደል ስጋት አሳስቦኝ ነው የሰነባበተው። ይላፍላችሁ ያላላቸው መከረኞች መቼም ናቸውና። ዛሬ በገረመኙ  የአምክንዮ ጥምዶች እና በፈጠጡ ሃቆች ዙሪያ አ ዳ ብዬ ሳይሆን አካል ተ- አማሳል አድርጌ ለማቅረብ አሰኘኜ እንዲህ … ·        ግ ን የኦፌኮን የሃሳብ አድራሻው የት ነው? ውዶቼ መቼም አዲስ አበባ እንደማትሉኝ ነው? ስለምን አቤቶ ኦፌኮን የሁለተኛ ጊዜ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ጥሶ ወለጋ መሄድን ደፈ ረው? ሰለለምን ተልዕኮ ነበር ነቀምት የሄደው? ለአቶ ዳውድ ኦነግ የመንፈስ  ጥሪት ምንጣፍ ለማንጠፍ? እኮ ስለምን?! ስለምን አርሲ አልሄደም? ስለምን ባሌ አልሄደም? ስለምን መቱ አልሄደም? ስለምን የጅጅጋ መከራ የደበደባቸውን ንጹሃንን አሳር ለመጋራት ወደ ዛ አ ላቀና ም? ስለምን ከሌሎች የኦሮሞ ድርጅቶች ተለይቶ የአቶ ዳውድ ኢብሳን ሞገደኛውን ኦነግን ጋር ለመሥራት ምርጫው ሆነ? ማንን ለማጥቃት? ማንን ለማንበርከክ? የማንን ቅ ስ ም ለመስበር? የማንን የፍቅር አቅርቦት ለመሰነጣጠቅ? ማንን ለማፈረስ? ዛሬ ጉዳዬ ይህ ነው - ሌሎችንም ጎበጥ ያሉ ሃሳቦች ይኬድባቸዋል … ሊንካቸውን ግን አለጥፍም። ምክንያቱም ይህን የመጠነ ሰፊ የሐሤት ሩህሩህ ዘመን ውስጥ ለማድረግ ለቆረጠ ሁሉንም መፈታ

ኢትዮጵያዊነት ምንጩና አገነባቡ ከሃሳብ በላይ ነው።

ምስል
ጥፈተኛው ማን ነው? „ከቀና ህግ ወጥተን ሳትን“ መጽሐፈ ጥበብ ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፮ ከሥርጉተ © ሥላሴ Sergute © Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ                                                               መንፈስ! እንዴት ናችሁ የኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ ? በዛ ሰሞን በአንድ የግል ቪዲዮ እስራኤል አገር አባቶች መደብደባቸውን አዳመጥን አዬንም፤ አሁን ደግሞ ኢትዮጵያ ሻሸመኔ ተመሳሳይ ነገር መፈጸሙን አዬን። የቆዬ ስለመሆኑ አይደለም ጉዳዩ። ጉዟችን ወደዬት ነው? ቀደም ባሉ ጊዜያት ላይ በመ ዶሻ ተቀጥቅጠው ያለፉ ወገኖች አሉን፤ ተገድሎ ተዘቅዝቆ የተሰቀለ ወገንም አለን። መፈናቀሉ፤ መደፈሩ፤ መተዛዘን መመ ከኑም አለ። አጀንዳችንም አይደለም ከሚዲያ ማሟቂያ ባለፈ፤ ሰከን ያለ ተግባር የቸርነት አንበሉ ዮሴፍ ገብሬ ከፈጸመው ውጭ። ያለፈውን ዓመት ትንሳኤን አብሮ ነው ያሳለፈው። ·        ው ጊ ያ ? ይህ የመንፈስ የነፍስ ውጊያ መንስኤው ምንድን ነው? ምን ተማርንበት? ምን አቀድንበት? ምን አጨንበት? ምን አሰብንበት? ምን አስተረቀንበት፤ ምንስ ል ንታረ ቅ አሰብንበት ይህ ነው የዛሬ ጉዳዬ። ·        ምን አሰብ ንበት ስለ ውድቀታችን። ወድቀ ና ል። ወድቀናል ሁላ ች ንም። ስለምን? ትውልዳዊ ድርሻችን ለመወጣት አቅም ስሌለን - የመንፈስ ብርታት መቀኗችን ፈሰስ ስለሚል። በ2008 እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር የጸጋዬ ድህረ ገጽን ስጀምር ዋናው ሞቶዬ „ትውልዳዊ ድርሻችን በህብረት እና በ አንድ ነት እንወጣ“ ይል ነበር። ሁለተኛው አጋዥ ሞቶዬ እንደ ቅመም „እልፍ ነን እና እልፍነ ታችን እልፍ እንድርገው“ ይል ነበር።  ለዚህም ለመጀመሪያ