ኢትዮጵያዊነት ምንጩና አገነባቡ ከሃሳብ በላይ ነው።
ጥፈተኛው ማን
ነው?
„ከቀና ህግ ወጥተን ሳትን“
መጽሐፈ ጥበብ ምዕራፍ ፭ ቁጥር
፮
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ
መንፈስ!
እንዴት ናችሁ የኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ? በዛ ሰሞን
በአንድ የግል ቪዲዮ እስራኤል አገር አባቶች መደብደባቸውን አዳመጥን አዬንም፤ አሁን ደግሞ ኢትዮጵያ ሻሸመኔ ተመሳሳይ ነገር መፈጸሙን
አዬን። የቆዬ ስለመሆኑ አይደለም ጉዳዩ። ጉዟችን ወደዬት ነው?
ቀደም ባሉ ጊዜያት ላይ በመዶሻ ተቀጥቅጠው
ያለፉ ወገኖች አሉን፤ ተገድሎ ተዘቅዝቆ የተሰቀለ ወገንም አለን። መፈናቀሉ፤ መደፈሩ፤ መተዛዘን መመከኑም አለ። አጀንዳችንም አይደለም ከሚዲያ ማሟቂያ ባለፈ፤ ሰከን
ያለ ተግባር የቸርነት አንበሉ ዮሴፍ ገብሬ ከፈጸመው ውጭ። ያለፈውን ዓመት ትንሳኤን አብሮ ነው ያሳለፈው።
· ውጊያ?
ይህ የመንፈስ የነፍስ ውጊያ መንስኤው ምንድን ነው?
ምን ተማርንበት? ምን አቀድንበት? ምን አጨንበት? ምን አሰብንበት? ምን አስተረቀንበት፤ ምንስ ልንታረቅ አሰብንበት ይህ ነው የዛሬ ጉዳዬ።
· ምን አሰብንበት ስለ ውድቀታችን።
ወድቀናል። ወድቀናል ሁላችንም።
ስለምን? ትውልዳዊ ድርሻችን ለመወጣት አቅም ስሌለን - የመንፈስ ብርታት መቀኗችን ፈሰስ ስለሚል። በ2008 እንደ አውሮፓውያኑ
አቆጣጠር የጸጋዬ ድህረ ገጽን ስጀምር ዋናው ሞቶዬ „ትውልዳዊ ድርሻችን በህብረት እና በአንድነት እንወጣ“ ይል ነበር። ሁለተኛው አጋዥ ሞቶዬ እንደ
ቅመም „እልፍ ነን እና እልፍነታችን እልፍ እንድርገው“ ይል ነበር።
ለዚህም ለመጀመሪያ ጊዜ በድህረ ገጽ ደረጃ አንድ
የልጆች ፕሮግራም አዘጋጀሁኝ „የሎሬት ተስፋ“ ይላል ነበር ክፍሉ። አትኩሮቱም እርእሰ ጉዳዩ „አገር ማለት ምን ማለት ነው?“ የሚል
ነበር። የተሰናዳው ለልጆች ነበር።
ያው የሚያሠራ ጠፋና እና ቀረ። ስለምን? አገር ቃሉን
እንጂ ግዴታውን ወይንም ህብር ዶግማውን ስለማናውቀው፤ አቅም ባይኖረን አቅም ያላቸውን ሰዎች እምናደናቅፈው እንቅፋቱ እራሳችን ስለምንሆን። ስለመጠዬቅ ከሆነ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ተጠያቂ ነን - ሁላችንም።
አለመስራቱ መብት ነው የሚሰራን ማደናቀፍ ግን ተልዕኮው
የጸላዬ ሰናይ ነው። ሁላችንም አገር ማለት ምን ማለት ነው ከሚለው አውራ የነፍስ ጉዳይ ሳንነሳ ነው
ድርጅት የፖለቲካ፤ መዋቅር የማስፈጸሚያ አካል መዘርጋት ይገባን የነበረው። ሳንሳናዳ ነው የነፃነት ተጋድሎ የምንጀምረው። ዘውም ብለን እምንቀላቀለው። እራስን
እዬታገሉ መቼም ትውልዳዊ ድርሻ አይታሰብ እና። አሁን የምናፍሰው የዘራነውን ነው። እየሰበሰብን ማፍሰስ፤ እያፈሰስን መልቀም
ሰልጥነንበት የለምን? ቢመርም - ቢጎመዝዝም መቀበል ግድ ይላል።
· የነቀላ ወበራ።
አብሶ እንደ እኛ ያለ ባላብዙ ህብርነት ያለው ዜጋ
አገር የቆመችበትን ምሰሶ አውታሮቿን፤ ዘሃዎቿን፤ አንጓዎቿን፤ ሴሎቿን ጠንቅቆ ማውቅ በእጅጉ ያስፈልጋል። 27 ዓመት አንድ ትውልድ
ጠፍቷል። በጠፋው
ትውልድ ውስጥ እኛም አብረን ጭልጥ ብለን ጠፍተናል። በመንፈስ።
የትውልዱ ጥፋት ትልም መሰረቱ ኢትዮጵያዊነትን ነቀል ተኮር ስለ ነበር ነው።
በምንወስዳቸው እርምጃዎች ኢትዮጵያዊነት ሥረ - መሠረቱ
ስለመነቀሉ አናስበውም። አንዱን አቅርበን ሌላውን ስናርቅ፤ አንዱን አቅፈን ሌላውን ስናሸሽ ኢትዮጵያዊነት መንፈሱ ከእኛ ውስጥ እየሸሸ ስለመሆኑ
አናውቀውም።
ቋንቋ መስፈርታችን ነው። ዕውቀት መስፈርታችን ነው። ዕድሜ
መስፈርታችን
ነው። ተጽዕኖ ፈጣሪ መሰብሰብ መስፈርታችን ነው። ገንዘብ መሥፈርታችን ነው። ከዚህ ውጭ ያሉ ነፍሶች ኢትዮጵያ በሚለው ማዕቀፍ
ውስጥ ስለመኖራቸው ትዝ
አይለንም። ትዝ እንዲሉንም አንፈቅድም። ስለዚህ መውደቅ ሲባዛ በመውደቅ ደለቀብን።
ያልታማሩ፤ ከአንድ ቋንቋ ውጭ ሌላ ተጨማሪ ቋንቋ የማይችሉ፤
የመማር ዕድሉን ያላገኙ፤ ዕድሉን ቢያገኙም በተለያዬ ሁኔታ በዕድሉ መጠቀም ያልቻሉ፤ በተለያዬ ሁኔታ የጤናም ችግር ያላቸው በመሆናቸው
በኤኮኖሚ አቅማቸው ኮሰስ ያሉ ዜጎች በኢትዮጵያዊነት ማዕቀፍ ውስጥ የሉም አይታቀፉም። ነውር ነው።
በዚህ ሁኔታ ዜግነት የሚለውን ታላቅ የመኖር ፍልስፍና ለማስረጽ
- ለማብቀል
- ለማጽደቅ - ለማስበል
ችግር ነው። ቀስ በቀስ ማንፌስቷችን፤ ፕሮግራማችን በራሱ ኢትዮጵያዊነትን ተገዳዳሪ መሆኑን አናስተውለውም። በጭራሽ? ከቶ ድል የሚባለው
ሜሪኩሪ ላይ ነበርን የታሰበው ወይንስ ሰው ዜጋ በሚባለው ህሊና?ወልደ ግራነት።
· ፍላጎት።
በፍላጎት ደረጃ እንምጣ አንዱ ስለደንብሬ /ሉዕላዊነት
ተኮር/ ሊል ይችላል፤ ሌላው ስለ ጥበቤ ሊል ይችላል፤ ሌላው ደግሞ ስለፈጣሪዬ ሊል ይችላል፤ ሌላው ደግሞ ስለ ሃሳብ ነፃነት መግለጽ
ሊል ይችላል፤ ሌላው ደግሞ ስለመናገር ነፃነት ሊተጋ ይችላል፤ ሌላው ደግሞ ስለተፈጥሮ ሃብት ተኮር ሊሆን ይችላል፤ ሌላው ደግሞ ስለ ሃይማኖቱ
መላ ጊዜውን መስጠት የሚፈልግ ይሆናል፤ ሌላው ዲጅታል ዓለም ያሰኘዋል፤ ሌላው ስለተመጣጠነ ኢኮኖሚ አጀንዳው ይሆናል፤
ሌላው ደግሞ ተፈጥሮ አምላኪ ሊሆን ይችላል፤ ሌላው ለቤተሰቡ ብቻ መሆንን
የሚሻ ይኖራል፤ ሌላው ለራሱ ብቻ መኖርን የሚያስቀድም ሊሆን ይችላል፤ ሌላው ደግሞ ዞግ ተኮር በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሊታታር ይችላል፤
ሌላው ታሪክ
ቀመስ ነገሮች ላይ ሊያተኩር ይችላል፤ ሌላው ላርባን ነፍሱ ጥፍት እስኪል ተከታይ ሊሆን ይችላል፤
… ሌላው ፍልስፍና ነክ ጉዳዮች ላይ ሊያተኩር ይችላል፤
ሌላው እንሰሳት ተበድለዋል
ሊል ይችላል፤ ሌላው በአካባቢ ጥበቃ ላይ ብቻ ማተኮር ማዘወትር ህልሙ ይሆናል፤ ሌላው በቅርስ ጉዳይ ሊሆን ይችላል ትጋቱ፤ ሌላው ባህል
ነክ ጉዳዮች ላይ ሊሆን ይችላል፤
ሌላው ምርምር ተኮር ሊሆን ይችላል፤ ሌላው በጾታ ነክ ጉዳይ ሊባትል ይችላል፤
ሌላው በሰብዕዊነት
ላይ ሊመሰጥ ይችላል፤ ሌላው እናቶች ተኮር ላይ ብቻ ሙሉ ጊዜውን ሊሰጥ ይችላል፤ ሌላው ትችት ፈቃጅ ይሆናል፤
ሌላው ቋንቋ
ዘይቤ ላይ ሊያተኩር ይችላል፤ የሌላው ተደሞ ደግሞ ሞድ ላይ ላይ ሊሆን ይችላል፤ የሌላው ደግሞ እስፖርት ቀመስ ሁነቶች
ቀልቡን ሊስቡት ይችላሉ፤
ሌላው መጻፍ ላይ ሊመሰጥ ይቻላል፤ ሌላው ማንበብን
የሙጥኝ ሊል ይችላል። ሌላው በፖለቲካዊ ሁኔታዎች ላይ ሊጠመድ ይችላል፤ ብቻ መኖር ባፈራቸው መኖር፤ በሚሰጣቸው መኖር፤ በሸለማቸው ወዘተረፈ ጉዳዮች
ሁሉም የሰው ልጅ በምርጫው እና በፍላጎቱ ሊታደም መቻሉ ብሄራዊ ነፃነቱ ነው፤ ተፈጥሯዊ ነፃነቱ። ከማንም
እና ከምንም ተንበርክኮ ሆነ ተኮድኩዶ፤ ተጨብጦ ሆነ ተኮርኩሞ የማይለምነው። እንግዲህ ይህ ወደ ባህሪያት ጉዳይ ጫፉን ሳንነካ ፍላጎት ተኮርን
በጨረፍታ ነው …
እና … ይህን ሁሉ በእኔ ወረቀት ማንፌሰቶ ሥር ካልተዳደርክ
ዜጋዬ አይደለህም ከተባለ ኢትዮጵያዊነት አቅሙን ይፈታተነዋል፤ ትርጉሙንም ያዛባዋል፤ ኢትዮጵያዊነት ነፃነትም ነውና።
ኢትዮጵያዊነት ገናና ማንነት ነው። ይህ ገናና ማንነት
በነጠላ ዜማ የተገነባ አይደለም።
በፈተናዎች ውስጥ ነጥሮ የወጣ ማንነት ነው ኢትዮጵያዊነት። ለዚህ ነው ከ20 ዓመት በላይ በሑሁፎቼ መጨረሻ ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን
አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ኢትዮጵያዊነት የምለው።
· አገርና ህዝብ።
አገር ሲባል ሁሉንም አይነት የማህበረሰብ ፍላጎቶች፤
አስተሳሰቦች፤ ምልከታዎች፤ ራዕዮች፤ ባህሬዎች፤ ህልሞች፤ ግንኙነቶች፤ ስሜቶች፤ ራዕዮች ሁሉ አካቶ ነው። አገር ማለት ምን ማለት
ነው ለሚለው „አገር" በቃላት ክምችት ብቻ የሚተረጎም አይደለም። አገር በመኖር ውስጥ ነው የሚገለጠው። መቸም
መኖር ተተርጉሞ የማያልቅ ተፈጥሮ ነውና። አገር የሚለው ቃሉ እራሱ ዕውቅና ያለው
መንፈስ ነው።
በቀላል እንግለጸው ብንል … አገር ዓለም ዓቀፍ ዕውቅና
ባለው የተከለለ መሬት ወይንም መልክዕድራዊ አቀማመጥ ነው። ህዝብስ? በዚህ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ባለው መልካምድራዊ አቀማመጥ ወይንም
መሬት ውስጥ የሚኖር የሰዎች ማህበር ነው፤ ማህበረሰብ። የሰዎች ማህበር ደግሞ ህዝብ ነው።
ህዝብ ደግሞ ከለይ ከዘርዘርኳች በላይ በመኖር ውስጥ
ያሉ የሚገኙ ወዘተረፈ ፍላጎቶቹ - ራዕዮቹ - ስሜቶች - የተፈጥሮ ጸጋዎቹ - ሥነ - ባህሬዎች ከጽንሰት እስከ ህልፈት ብቻ ሳይሆን
ካለፈም በኋዋላ የሚኖር ሥም ያለውን ሰዋዊ፤ ተፈጥሮዊ ነገሮች ያቀፈ መጠነ ሰፊ የመኖር ትርጓሜ ነው። ግዑዛን ሳይቀሩ በአገር ውስጥ
ይካተታሉ። እነሱም አገር አላቸው። አፈር ጉዑዝ ነው፤ ድንጋይ ጉዑዝ ነው፤ ተራራ ጉዑዝ ነው፤ ሸንተረረ፤ ወንዝ ሁሉም ግዑዞች ናቸው ግን አገርነትን የሚሰጡ
ናቸው።
አንዱን ነጥለን ወይንም ጨልፈን አገር መሆን አይቻልም። አገርን ለመተርጎም ሆደ ሰፊነትን ይጠይቃል። በማቻቻል፤ በማስማማት፤ በማዋደድ፤
በማስተጋበር እናት ዥንጉርጉር ልጆቿን በምትይዘውን ጥበብ ያህል እንደ ባህሪዎች ብዛት፤ እና እንደ አፈጣጠሩ መቀበልን ይጠይቃል።
አሁን እናቴ ክብዬ ሴትም ወንድም ልጅ አላት። አንዳችንም ሌለኛችን አንመሰልም በባህሪም በፍላጎትም። የሚገረመው በመልክም አንመሳሰልም እንኳንስ
በመኖር ውስጥ ባሉ ፍላጎቶች እና ባህሪዎች። ግን ክብዬ ለሁላችንም እኩል ታስተናግዳናለች።
ሁላችንም አንጎረብጣትም። ፍጹም ሆነን አይደለም።
ስታሳድግን እጣታችሁን ተመልከቱት አንዱ ከአንዱ ያንሳል፤ አንዱ ካንዱ ይበልጣል፤ አንዱ ካንዱ ይወፍራል ግን አብረው ተባብረው
ማዳፍ ይሆናሉ እኛንም ያኑሩናል በአንዱ መወፈር አንዱ የካሳው አይቀናም፤ በአንዱ መርዘም አጭሩ አውራ ጣት አይቀናም አትቅኑ
በሰው እያለች ነው።
የባለቤቷን ወገኖችም ወዳጅ ስለሆነች ልጆቼ አንዱን
ብቻ ከወደዳችሁ ግንጥል ጌጥ ነው የሚሆነው እኔ ጸጉሬን ግማሹን ተሰርቼ ግማሹን ትቼ ገብያ ብወጣ ያምርብኛልን? ጆሮ
ጉትቻዋን ሁሉ አውልቃ ታሳዬኝ ነበር፤ የጎንደር ሰውስ አንዱን ብቻ አድርጌ ብሄድ አይስቅብኝም?
ስለዚህ የባሎቻችሁን ወገኖች ውደዱ
እያለች በልጅነት ትንገርን ነበር። ሳቅን እራሱ አትቆጥቡት ሁሉ ትለናለች፤ እሷም የወጣላት ሳቂተኛ ናት። እንደዚህ ሆነን አድገን
እንኳን ከክፉ ነገር ጋር ባንተባበርም መንገዳችን ግን የተለያዬ ነው …
ራዕያችን ፍላጎታችን የተለያዬ መስመርን ነው የተከተልነው …
አገር ብሎ የሚነሳ ነፍስ እንደዚህ መሆን አለበት። እንደ እናት። ተከታዮቹን
መርዝ ቀልቦ ሳይሆን ፈውስ ቀልቦ መቅረጽ አለበት። ከሊቅ እሰከ ደቀቂ ቃሉን አገርን መዘከር ሳይሆን በመሆን ውስጥ መሆን መቻል
አለበት። አንዱን ሳያንኳስሱ፤ አንዱን ከሌላው ሳያቀላቅሉ ወይንም የአንዱን ተፈጥሯዊ ጸጋ ሳይሰነጥቁ፤ ወይንም የአንዱም መክሊት
ሳይሰነጥሩ ወይንም ሳያገሉ፤ ወይንም በደቦ ሳያስገልሉ፤ ወይንም ሳይጫኑ ወይንም ሳይስጭኑ ወይንም ሳይነጣጥሉ መቀበል።
ዜግነትን ማዕከል ለማድረግ ይህን ፈተና ማለፍ ይጠይቃል። በወረቀት ላይ የሚቀረጸው እና በአንደበት የሚነገረው አገራዊ ብሄራዊ ማንነት መሬት ላይ
ካለው ዕውነት ጋር መገናኘት ካልቻለ ሃሳቡ ይዳጣል ወይንም ይፈናጠራል በዚህ ሂደት አውራ ሃዲዱ ይታወካል የኢትዮጵያዊነት መንፈሱ።
· ዜግነት።
ዜግነትን ክብር ለመስጠት አንድ የፖለቲካ ሊሂቅ፤
አንድ በማናቸውም ሁኔታ ያለ ዕውቅና ያለው ድርጅት ይሁን ሚዲያ ሰው ነህ፤ ሰው ከሆንክ መከበር አለብህ ብሎ መነሳት አለበት። ዜግንትን ሰጪም ነሽም የለም።
ሰብዕናውን በክፉ ተግባር የተነከረ ከሆነ ክፋቱን
ልንጸዬፈው ብንችል እንኳን „እርስዎ“
ብሎ መጀመር ግድ ይላል። ሰው ነውና። ወንድ ከሆነ „አቶ‘ ሴት ከሆነች ካገባች ወ/ሮ ካለገባች ወ/ት“ ቅጥያም ዕውቅና ካለ ማከል ማንን ይጎዳል? ይህ አክብሮት ትውፊት ነው። ካለስፈለገውም ካለስፈለጋትም ብፍላጎቷ ወይንም በፍላጎቱ ውስጥ መሆን።
አገርን
የገነባ ዘመናትን እንዳይለያዩ አድርጎ ያያዘ እትብት ነው ለኢትዮጵያዊነት
ሰውን አክብሮ መነሳት ነው ፍጠረተ ነገሩ። እራስን አክብሮ መነሳት ምስክሩም ለሌላው ክብር ለመስጠት በመፍቀድ ውስጥ
ይገለጻል። ወይ መውደቅ ወይ ደግሞ ማለፍ።
እኔ ሳድግ ትልቅ ሰውን ኢትዮጵውያን በአክብሮት ነው
የምንጠራው ወላጅ ይሁን አክስት - አጎቶቻችን፤ መምህራኖቻችን፤ ጎረቤቶቻችን፤ ታላላቆቻችን፤ የቁልምጫ የአክብሮት ሥም አለን።
እትዬ፤ ጋሼ፤ ጥላዬ፤ ወተተይ፤ አሽኰይ፤ አንባዬ፤
ጋሻዬ፤ እቴ አንጀቴ፤ እያያ፤ እታታ፤ እማማ፤ እማዬ፤ አባዬ፤ አባባ፤ እቴ ሆዴ፤ አህት አገኘሁ፤ ወንድም ዓለም፤ እታለም፤ እቴዋ፤
እሜትዬ፤
አያ መኩሬዬ፤ አያ ጥላዬ፤ እቴሜቴ ወዘተ … ዛሬ አገር ቤት ይኑር አይኑር አላውቅም፤ እኔ ሳድግ ግን እንዲህ ነው የነበረው። በዚህ
ሁሉ ኢትዮጵያዊነት ይገለጻል። በሌሎች ቋንቋዎችም መሰሉ እንደሚኖር አስባለሁኝ። ምክንያቱም ኢትዮጵያዊነት ምንጩና
አገነባቡ ከሃሳብ በላይ ነውና።
ትልቅ ሰው ሲመጣ ብድግ ማለት፤ አለቃ ሲመጣ ብድግ
ማለት፤ ከውጭ ቆይቶ ሰው ሲገባ ብድግ ማለት፤ ኖር! ማለት፤ መንገድ
ላይ በዕድሜ የሚበልጠውን የማስቀደም፤ ሬሳ፤ ሙሽራ ከሆነ አለማቋረጥ - ቁሞ በክብር ማሳለፍ፤ ከባድ ነገሮችን የተሸከሙ ሰዎችን
ማገዝ፤ ቢያንስ ቀደመው እንዲሄዱ መፍቀድ ይሄ ነው ኢትዮጵያዊነት እኔ እማውቀው።
ዛሬ ትልቅ ዓለም ዓቀፍ
ሚዲያ ላይ ተቀምጠህ ሃሳቡ የአንተ ስላልሆነ፤ ስለጠላኸው ብቻ አንጠልጥለህ ስትጠራው ኢትዮጵያዊነት የቆመበትን ምስሶ እራስህ እዬነቃቀልከው
ስለመሆኑ አይታይህም።
ምን ብክል ዘር እዬተተከለ ስለመሆኑ ማስተዋሉን ተነፍጎናል።
መምህር ተሁኖ የአንድ አገር መሪን „አንተ“ እያተባለ በጥላቻ ስሜት ሲጠራ የሙያ ልጆች፤ ተከታዮችን ምን እያሰተማርን ስለመሆኑ አይታሰብም፤
ማሰሮ እንኳን ጆሮ አለው እንኳንስ የሰው ልጅ። እርግጥ ነው የኪነ - ጥበብ ሰው ከሆነ አንተ አንቺ ይፈቀዳል። ቤተሰባዊ ትስሩ
መክሊታዊ ስለሆነ።
ታላላቆች የጥበብ ታቦቶች ይህን ቅኖና ነውም ያሰረከቡን።
አሁን ተፈጥሮው አገር
የሆነውን የቅኔው ልዑል ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን አንተ ብለን እንጠራዋለን፤ ጋሼ ደቤ፤ አለምዬ እንላለን። የሚገርመው እዚህ
ሲዊዝም አንተ/ አንቺ ነው የጥበብ ሰው የሚጠራራው ሚዲያ ላይ፤ የጥበብ ኮርስ ላይ ሁሉ …
ሌላው ቀርቶ የዮጋ ቤተሰብ እንዲሁ አንተ/
አንቺ ነው የሚባባሉት። የዮጋን ካነሳሁ ዘንዳ የቤተስቡ ትህትና እና ርህርህና ራሱ ተቋም ነው። ፍቅሩም ትብብሩም ፍጽምና አለው።
ያ ለጋስ እና ቸር ስጦታ መንፈስ ሲሰንቀው ጤና ነው። ልዩ የሰናይ ስጦታ።
· በጥቃት ውስጥ ያሉትን መንፈሶች በማዳን ነው ማሸነፍ የሚገኘው፤
ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌሰቶ እና መሰሎቹ ጸረ ኢትዮጵያ
መንፈሶችን አክሎ እነዚህን ኢትዮጵያዊነት የቆመባቸውን ምሰሶዎች ነጥሎ እንዲጠቁ ማድረግ የተፈጠሩበት ነው።
እኛ መሻላችን የሚታዬው እንሱን አንጠልጥልጥሎ በመጥራት አይደለም። እነሱ የተዋቀሩበትን ከይሲ መንፈስ
መንቀል የሚቻለው ኢትዮጵያዊነት ተጻሮ የሚነሳውን ንቀትን በ አክብሮት ተክቶ በማሳዬት ትውልዱን በመሆን ውስጥ ሆማሰተማር ሲቻል ብቻ ይሆናል። ማፍረስ የሰውን
ጭንቅላት ሳይሆን፤ መበተን የሰውን ጭንቅላት ሳይሆን የተነሳበትን ክፉ ሥርን ሃሳቡን ነው።
ክፉ ሃሳብ አራማጆችን እራሱ አክብሮ መነሳት ትወልድን ይማርበታል። መሰሉ በመፈጸም ነው እኛ የምንታወቀው በመናቅ አንጠልጥሎ በመጥራት። በዚህ ውስጥ ማሸነፍ አይመጣም ይልቁንም ተሸናፊዎች ነን። የእኛ ሽንፈት ተከታዩ ለትውፊታችን ነቀርሳ ተጨማሪ ቁስለት በመፍጠር ይሆናል። ኢትዮጵያዊነትን የሚበልጽገው በተዘመተብት አምክንዮ የማያዳግም የመሆን ገበር ሲበጅለት ብቻ ነው። እኔ
ያነሳሁት „አክብሮትን“ ብቻ ለዛውም አንዲት ዘለላ ጉዳይ ነው። ይህም ከአንድ ጎጆ ቤት አንድ እሳር የመምዘዝ ያህል ነው።
መሬት ላይ ከገበሬው ጋር በመንግሥት መዋቅር ሲሠራ እጅግ ብዙ ጉዳዮች ነው ያሉት። ራሱ "ማክበር" የፍቅራዊነት ት/ቤት ቢኖረን አንድ የትምህርት ክፍለ- ዘመን ሊሆን የሚችል ነው። የሚመረቁብት የሙያ ዓይነትም ነው እንደ ሥርጉትሻ ፍልስፍና።
የእጅ እና የራስ አሻራችን የተለያዬበት፤ የሰው ልጅ
ኮፒ የሌለውም ለዚኸው ነው ዘርፈ ብዙ የመኖር ጥበቦች ናቸው ያሉት። እስከዚህ ድረስ በጥልቀት የሰውን ተፈጥሮ ማንሰላሰል ይገባል። እንደ ሸሚዝ፤ ሱሪ፤ ቀሚስ የሚከዘን ምንም ነገር እንደሌለ መሬት ላይ እውነቱ ይነግረናል። ዕድሉ ተገኝቶ መሥራት ከተጀመረ …
ሊሂቆቹ አባቶቻችን ምን ያህል ከእኛ ቀድመው ዛሬን
እንደሰጡን ረቂቅ መሆናቸውን መታየት ያለበት ከዚህ አንጻር ነው። ለዚህ ነው ወላጆች „ወልደሽ ወልደህ እዬው“ የሚሉት …
አንዱን „ማክበር“ መፈጸም በተሳነን ቁጥር ቀስ በቀስ እኛው ጸረ ኢትዮጵያ ምልከታ ችግኝ አምራቾች ሆነን ቁጭ እንላለን። እነሱ ከሚፈልጉት መስመርም ቀጥ ብሎ መግባት ነው። ትውፊታችንም ሙት መሬት ላይ የሙጥኝ ይላል። ስለዚህ በትውልዱ ሽልከት ውስጥ ሁላችንም አለን ወይንም ራሳችን ሸርሽረናል።
… ታዲያ ምን ይፈረዳል? የዛሬ ልጅ አቨውን ቢደበድቡ - በደቦ፤ የዕድሜ እኩዮቹን ገድሎ
ዘቅዝቆ ቢያኝጠለጥሉ - በወበራ፤ ወይንም ገድሎ በመኪና ላይ ቢኬድበት ሎቱ ስብሃት ስለቃሉ፤
ወይንም በመዶሻ ቀጥቅጦ - በደቦ አምሳያ ፍጡርን ቢገድል …?! እኛም እኮ ትውፊታችን እየቀጠቀጥነው አይደለምን? "አንተ እና አንቺ" እያልን
ስናብጠለጥለው።
„መብት አለኝ ግዴታ የለብኝም“
ይላል ጋዜጠኛ አክቲቢስት ጸሐፊ፤ ካለ መብት የተፈጠረ ግዴታ፤ ካለ ግዴታ የተፈጠረ መብት ያለ ይመስል። በዬትም ዓለም እንዲህ የለም።
መብትን ለመጠዬቅ ግዴታን
ማሟላት ግድ ይላል። ግዴታን አሟልቶ ነው መብት የሚጠዬቀው። የሰው ልጅ ከእንሰሳም የሚለዬው ይህን መስተጋብር በህይወቱ ውስጥ
ስለሚተረጎምም ነው። ልቅ ዓለም የለምና … ህግ አልባም አገር የለም። ምን አልባት ልቅ ነፍስ ሊኖር ይችላል እንደ ተፈጠረ
…
በፖሊሲ ደረጃ አቅም ያለው አካል ኢትዮጵያዊነት ነፍሱን
እንደማያቆዬው፤ ሩሁን እንደማያስቀጥለው የ100 ዓመት ህልሙን እንደሚያራቁተው ስለሚያውቅ አዋጅ አውጥቶ እዬታገለው እኛ ደግሞ ለዛ ስንቅ አቀባይ። ተቀናቃኝ፤ ሞጋች፤ ተቃዋሚ ሃሳብ አራማጆችን የማክበር አቅሙ የለምና። ይህ ዕውነት ነው።
እሱ አካል አደራጅቶ፤ መዋቅር ዘርግቶ እዬታገለው እኛ ደግሞ አንዷን ዘለላ „ማክበር“ አቅቶን „አንተ አንቺ“
እያልን ስትዘነጣጥለው፤ ቋንቋ ሁለተኛ ሦስተኛ ካልቻልክ አንተ አይመለከትህም አንቺ አይመከትሽም ምንትሱ፤ የተማረ ያልታመረ ሲባል ለእሱ ማዳበሪያ፤
የዛ የጥፋት ተልዕኮ አስፈጻሚ ተቋም ህሊና ስለመሆን አይታሰብም።
· ህግ ተላላፊነት እንደ ጀብዱ።
ምንም ይሁን ምንም ህግ አለ ኢትዮጵያ፤ በዛ ህግ
ልትገዛ - ልትዳደር - ልትኖር ከፈቀድክ በፈለገው መልክ ጥፋት ሳይኖር ክስ መበደል አለ። እሱ ለደነገገው ህግ መገዛት አልቻለም ተብሎ ግን እርስዎ መከራ የተቀበሉለትን የህግ የበላይነት ህልም በመታበይ መዳፈር ምን ሊባል ይችላል?
ህግ አክብረው ነው ህግ ተላላፊዎችን መሞገት የሚገባ እንጂ በህግ ተበጥሶሽ አይደለም። ከህግ በላይ ማንም
የለም ኑሮም አያውቅም … የሃይማኖቱም ህግ እኮ አለ። የሃይማኖትም ቀኖና እና ዶግማ አለ። ማህበረሰቡ የደነገጋቸው ድንጋጌዎችም
አሉ - ብህሊና ሰሌዳ የተጻፉ። ለዚህ ነው እኔ ኢትዮጵያ በተፃፈም ባልተፃፍም ህግ ትተዳደራለችም የምለው። እንዲያውም ተፈጻሚው የማህበረሰቡ ያልተፃፈው ህግ ድንጋጌም ነው ከተፃፈው ይልቅ …
ምንም ሙያውም ብቃቱም ሰብዕናው አይኑራቸው ግን በኢትዮጵያ
ሥም ያሉ ዳኞች ነበሩ። ከሥሙ ፊት ለፊት ኢትዮጵያ የሚል ሃያል ተፈሪ ቃል በመንፈስ አለ። ኢትዮጵያም እራሷ ህግ ናት። እነሱን
ሳይሆን ፍ/ቤቱ ሲጠራ የፊቱ ሥያሜ ኢትዮጵያ የሚል መሆኑን መተለላፍ በራሱ ወፍራም ግድፈት ነው።
ስለዚህ ኢትዮጵያዊነት ከገባን ለዛ ክብር ከመቀመጫህ ዳኛ ተብሎ የተሰዬመው ሲጋባ መነሳት ምን ይገድል?
ምንስ ይቀራል? አይከፈለበትም፤ አትክፍልበት ከሁሉ ባላይ አክሰሱ ያላቸው ተተኪዎች ያን ይመለከታሉ።
መታብይ ትውድልን ቢያጠፋ እንጂ አይገነባም። ሁሉም
የዘራውን ነው አሁን እያፈሰ ያለው። ለነገሩ የትውልድ በመንፈስም በአካልም ብክነት አጀንዳ አይደለም። አጀንዳው ዘመን ይዞ ተዘመን
አንዱን አሳጥቶ ወይንም ኮንኖ ራስን ጽድቅ መንበር ላይ መኮፈስ ብቻ ነው። ለዚህም ነው ይህ አዲስ ፍልስፍና ከውጥኑ ወጀቡ ጠንቶ የባጀው።
· መከሰስ ሁሉንም ይመለከታል።
ሳስተናል። መሳሳታችን መሰረታዊ አምክንዮው እኛ እምንታገለውን
አለማወቃችን ነው። በትውፊታችን ጣር ከሳሽ እና ተከሳሽ፤ በዳይ እና ተባዳይ ባንሆን
ነው ቁም ነገሩ የእኔ ጹሑፍ። እኛው እራሳችን ፈቅድን ስንንደው የኖረውን ገመናም አለብን። ኢትዮጵያን ለመንቀል ከተጋው ክፉ መንፈስ
ጋር ለመታገል እሱ በሄደበት መስመር ተሂዶ አይደለም። አልነበረም። ይህ ወደ ዬትም ወደፊት አያደርሰንም።
አንድ ትልቅ ማህበረሰብ አልነበረም፤ አልተፈጠረም
ሲባል ኢትዮጵያዊነት አንደሚታመመ አይታወቅም። አገር የሚለው ጽንሰ ሃሳቡ
ቢገባን፤ ትርጉሙ ብንረዳው ሚስጢሩ አይደለም በህይወት ያለውን በህይወት ለሌሉትም ክብር ይገባ ነበር። አገር ስለመቆዬቷ የእነሱ
ሙሉ ተሳትፎ እና ቀናነት ተደምሮ ነው እና።
ቁንጽላዊ በሆነ ግብግብ የተፈጠሩ ዕሳቤዎች እና እኛ
ስንጓዝባቸው የነበሩ መንገዶች ወልጋዶች ናቸው። በዚህ ውስጥ ተሆኖ ነው ትውልዱ የሾለከው። ለኢትዮጵያዊነት
አለዛንለትም እኛው እራሳችን።
ለመሆኑ ትውልድን የሚያንጽ ምን የሚዲያ ተግባር አለን?
ራሱን የቻለ ድህረ ገጽ፤ ብሎግ፤ የአዬር ጊዜ ሰጥተነው እናውቃለን? ለመሆኑ ትወልድን የሚያንጽ የትምህርት ተቋማትስ አለን? በሞራል ማለቴ ነው ት/ሚር
ረስቼ አይደለም። መማር ፕሮፌሰር ደረጃ ቢደረስም ራስን ማሸነፍ ካልቻለ፤ እውነትን የሚሸሽ መማር ከሆነ ትርጉሙ መማር የሚለው ለእኔ ያንሰብኛል።
መማር በራሱ የትውልድ ትውፊት፤ የመንፈስ ጽንሰት ተጽናት ስለሆነ።
የሆነ ሆኖ አንድ ኢትዮጵያ ውስጥ በእነዚህ ሥያሜዎች
የሚጠራ መከባበር፤
መቻቻል፤
መቀበል፤
መታገዝ፤ መደማማጥ፤ ትህትና፤ ደግነት፤ ርህርህና፤ ቅንነት፤ አብሮነት፤ መሆን፤ ሥራ፤ ወዘተ የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ይሁን ኮሌጅ ይሁን
ዩንቨርስቲ አለን? በዚህ ሥም የሚጠራ ተቋምስ? መቼም እነኝህ ቅዱስ ቃላት ዞግም የላቸው፤ የትምህርት ደረጃም የላቸው፤ ቋንቋም የላቸውም፤ የልደት ሰርፍኬት
አይጠይቅባቸውም፤ የሃብት ደረጃ አይጠይቀብቻውም፤ የአንድ ማህበረሰብ አንጡራ ሃብታት አይደሉም ግን አንደፍራቸውም ስለምን?
በውስጡ ስለሌለን።
በመምሰል ውስጥ ያለው መኖር ሙጃ ነው። ሙጃው ደግሞ ለእነሳሳት መኖ እንኳን የማይውል። እያንዳንዳችን ስንፈጽም የኖርነው 50 ዓመት ሙሉ ኢትዮጵያ
የቆመችበትን ምሰሶ የሚያጠናክር ሳይሆን የሚንድ ነው የነበረው። ስለዚህ ተጠያቂነቱ የሁሉም ነው። ይህን
ለአንድ ድርጅት ጠቅልለን የምናሸከመው አይደለም።
አብረህ ቁጭ ተብሎ ማዕድ መቀመጥ የማይቻል? ሰው በመፈቅድ ውስጥ ከቶ ልዩነት የለውምን? ለመጨረሻ ጊዜ የማታዳምጠው፤ የማታዬው፤ የማይሞግትህ ሰው ሲያልፍ እንኳን ሃዘኑ እኩል አይሰማም።
እሱንም ነፃ ለማውጣት ከነበረ የነፃነቱ ተጋድሎ - ሃዘኑ ሊሰማን፤ ድንጋጤው ሊገባን ይገባል። ማዕከሉ ዜግነት ከነበረ
ፍልስፍናው። ባልነበርንበት ውስጥ ነበርን ዛሬ ላይ ራስን ነው የሚያስገምተው። ሃዘን የማይሰማው ኢትዮጵያዊነት አልተፈጠረም ወደፊትም
አይኖርም። ስለ ወገንህ መኖር በህይወት ከማሰብ ሞቱን ከሆነ፤ በመኖር ውስጥ አለፈጠር ነው። እራስንም መጠዬቅ እኔ የትኛው መደብ ነኝ ብሎ?
ሰው መኖር አለበት ፈጣሪ እስኪጠራው ድረስ። መኖር
የሌለበት ክፉ
ሃሳቡን ነው። ክፉ ሃሳቡን ደግሞ እሱን ስለገደለከው ወይንም ሰለ አስገደልከው አይሞትም።
መሰሎቹ ክፉ ሃሳቦች አሉና ምድር ላይ። እሱ በነበረበት ውስጥ አንተ ስለመኖርህ ክፉ ሃሰብህ ራሱ ምስክር ነው። ሰውን ማዕክል አለማድረግህ። ስለዚህ ተሸንፈሃል። ውሸትህም ነው አገር በሚለው ማዕቀፍ ውስጥ ስለመኖርህ።
በሌላ በኩል በተዘዋዋሪም ቂም ለትውልዱ ት/ቤት መክፈት መሆኑንም ተረስቷል። ታዘቢ ልጆች አሉና። በዚህ ክፉ ሃሳብ የያዘው ሰው ህልፈት ጮቤ አስረግጦም ከሆነ፤ በሌላ በኩል ቂም አርጋዥ ይልተገላገሉት የአገር ዕዳ መሆንም አለበት። ክፉ ሃሳብን በደግ ሃሳብ፤ ቂምን በይቅርታ ነው ማሸነፍ የሚቻለው። ትውልድ እሚገናበውም እንዲህ ነው።
ያ ሰው የወለዳቸው ልጆችም ይኖሩታል። በእነሱ ህሊና ውስጥ የባይታወርነት መንፈስ
እንዲወል እንዲያድር እና እንዲያሰብል መፍቀድ በራሱ ለትውልድ ጥፋት ሌላ የከንቱነት ተቋም ነው። ስለ አመለጠን ትውልድ ስንብሰከሰክ በመጪዎቹ ላይ ደግሞ ሌላ የርዶ ድንኳን ዘርግተን? በዚህ ውስጥ ኢትዮጵያዊነት አብሮ ቁስል፤ ንድድ፤ ጨጓራው ቅጥል ማለቱ አይተዬነም።
አንድ ትውልድ
ሾልኮ ከትውፊቱ አሁን እንኳን ከ18 ዓመት በታች ያሉት በአንድም በሌላም የከፍትንላቸው መንገድ ጠናና ነው። ከቂም ራስን ማጽዳት
ትልቁ ፈተና ነው።
የትውልድ ብክነት ሲባል ሞቱ ብቻ ሳይሆን በመንፈስ
ያጣናቸው፤ አሁንም እያጣናቸው ያሉ ልጆቻችን በሚመለከት ብሄራዊ ብቻ ሳይሆን ሉላዊም ነው።
በስደት ተወልደው የሚያድጉ፤ ብናኝ ፍቅር ሰጥተናቸው የማናውቅ፤ አድገው ትምህርት ላይ ያሉ፤
የጨረሱ፤ ጋብቻ ለመፈጸም የተሰናዱ ልጆች አሉን። ለእነሱ ሁሉ መታሰብ አለበት።
ይህ ትወልድ ደግሞ ጮሌም ነው። ልጋልብህ ቢባል በጅ የሚል አይደለም።
ትዝቡትም መጠነ ሰፊ ነው። የፈሰሰ ውሃ አይታፈስም። የመንፈስ ሃብት ከመራቆት በላይ ኪሳራ የለም። ለዚህ አዲስ ትውልድ ሉላዊ ዓለም የሰጠው፤ የሸለመው፤
የፈቀደለት ሥልጣኔም አለ። ስለዚህ ቢያንስ በእኛ ጥንቃቄ ጉድለት የሚፈጠሩ ግድፈቶችን ለማረም እኔም ጥፋተኛ ነኝ ብሎ መቀበል ይቅደም።
እኔም ለጥፋቱ ተጠያቂ ነኝ ተብሎ ይታሰብ። ነገ
የማይገኝ ነገር ሚዲያ ላይ ወጥተህ ስትናገር ቃሉ ከስሎ፤ በኖ፤ ተኖ የጉም ሽንት ሆኖ ሲቀር ትውልዱ እኔም ልሞክረው ማለቱ አይቀሬ
ነው። ተስፋ እና ተስፈኛውን የምንመራበት ዘይቤ ዕለታዊ ነውና። ነገ የሚል ነገር
አጀንዳችን ሆኖ አይውቅም። መቼም ይህ ሃሳብ ሞጋች ስለሆነ ሙግት ያሰኘው ይምጣ እና ይሞግተኝ። ቀኖች
ሳይሆኑ መሆኖች ቢመሩን
ነው ፍሬ ነገር።
ዛሬ እኔ ተመስገን እምለው ይህን በውል ያደመጠ ስንዱ
አቅም ማዕከላዊ መንግሥት ላይ አለን። ከሁሉም የተሻለ ሳይሆን ለሁላችንም በ አውንታዊነት ዱብ ዕዳ የሆነ የትውልዱን ብክነት በመንፈስም በአካልም
ሊመክት የሚችል በመሆን ውስጥ
ያለ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ፍልስፍና አዲስ ቀመር አለ። በዚህ እጽናናለሁ።
ለዚህም ቢሆን ማገዝ ያስፍልጋል። ቀጠሮ አያስፍልገውም።
ቅድመ ሁኔታ አያስፍልገውም። ራስን ይቀር ለማለት። ስለ ብሄራዊ እርቅ እና ሰላም ከመታሰቡ በፊት ራስን ይቅር ማለትም
ይጠይቃል። ራስን ይቅር ማለት የተከዘነው ቂም እና በቀለ ተጸይፎ መርዙን ከራስ ማውጣት ማለት ነው። ዛሬ እንኳን አለመቻሉን አሰተውያለሁኝና።
ዝም ብሎ በሌለ ነገር ላይ መንፈስን ከማንጠልጠል፤
ባለ ነገር ላይ ተነስቶ እራስን በዛ ማደረጀት ይጠይቃል። መደራጀት በመንፈስ ይሁን። የመንፈስን ቤት አጽድቶ። ቆሻሻን ከልቶ - ተጸይፎም።
ዘመኑ ከፈቀደው አዲስ መስመር ጋር ለመጓዝ ያለፈውን በመውቀስ ጊዜ ከማቃጠል
አዲሱን መስመር ለመከተል ራስን ማረምን ማስቀድም ይጠይቃል፤ ማንም ብፁዕን ስላልነበር። ኢትዮጵያዊነት ሲቆጠር ከአንድ ሰው እንደሚጀመር አምኖ መቀበል። ከዚህ ጋር እርቀ ሰላም ሳያወርዱ ዜግነት ላይ መነሳት አይቻልም። ቢሞከርም ትልሙ እንደለመደበት ይፈረካከሳል። አንድ ነገር ጸንቶ እንዲቀጥል ካስፈለገው ራስን አሸንፎ መነሳት
ይኖርበታል።
· 13ወራቶቹ ሥማቸው ሰኔ ነው። ለምን?
መታበይ ካለብን ከዛ መለያዬት፤ ማንአህሎኝነት ካለብን
ከዛ መጽዳት፤ ውሸት ካለብን ከዛ ራስን ማጠብ፤ ኢጎ አሉታዊ ከኖረብን ከዛም መፋታት፤ ቂም ካለብን ከዛም መለያዬት ዜግነት ላይ ለመነሳት እነዚህ ሁሉ ፈተናዎች ማለፍን በጥቂቱ ይጠይቃል። ለሁሉም ሁሉም ቀን ሰኔ ነው ለዘመኑ።
12 x 30= 360 ቀናት ሁሉ ፈተና ላይ ለመቀመጥ ሰኔ ነው ለደፋሮች።
አገር የሚገነባው፤ ትውልድ የሚታነጸው ራስን ባሸነፈ
ደፋር ቆራጥ አቅም እና ክህሎት የመሪነት ጥበብ ነውና። የለማ መንፈስ እና የአብይ መንፈስ ልቅና የሚመዘነው ከዚህ አንጻር ነው።
ላመኑበት አዲስ መስመር ደፋሮች ናቸው። ያልደፈሩት መስመር እና አምክንዮ ከቶም
የለም።
ለዚህ ነው የአላጋጮች ማህበር አስፈስፈው በጎጃቸው ዱለታ ላይ የሚገኙት። ከእንግዲህ አማራ ጠላቴ ነው ተብሎ አጀንዳ የለም።
አለቀ ደቀቀ።
እራሳችን ያዋረድነው እራሳችን ነን። እራሳችን ያቃለልነው
እራሳችን ነን። እራሳችን ያላከበረነውን
ማን እንዲያከበርል ከቶ ፈልግን?
· ደፋር ሲገኝማ!
አሁን ሁሉ ሰው ልብ አላለውም። ሥር ነቅል ለውጥ
ሲል እንኳን ይህ የፖለቲካ ፍለስፍና የሚባል ሳይንስ ተንሳፎ ይታያል። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ሙሉ ለሙሉ በህይወት ያለ
ይመስለዋል - ሰው። ያለው ትግራይ ላይ ብቻ ነው - ለዛውም ትግራይ ላይም አንድ እግሩን አንጠልጥሎ ነው። አቅሉን ተቀምቶ። ስለምን? ለታላቋ ትግራይ
መሥረታ ሁለት ቁምነገሮች አብይ ነበሩ።
1.
አንዱ አማራን በሁሉም መስክ መቅኖ
ማሳጣት - በመንቀል፤
2.
ሁለተኛው ቅድስት ኦርቶዶክ ተዋህዶ
ሃይማኖት ማባከን - በመዳፈር፤
እነዚህ የወያኔ ሃርነት ትግሬ ማንፌስቶ መሥራቾች
የተነሱበት አውራ አንኳር ዶግማ ነው። ምርኩዞችንም ሲፈጥሩም ባላዎቹ ማገራቸው ይኸው ነው። ስለምን ሲባል? ሁለቱም የኢትዮጵያዊነት
ጽኑ፤ የማይናወጹ ባላዎች
ናቸው ተብለው ይታመኑ ስለነበረ በጠላትነት እንዲጠፉ የታወጀባቸው ናቸው። በመንፈስ እራሱ እንዲፋቁ ነው የተሰራበት።
ሁለቱም አሁን ህላዊነታቸው እርግጥ ሆኗል። እንደ ሌላው ሊሂቅ አልተፎከረበትም፤ እንደ ሌላው የፖለቲካ ድርጅት ዓዋጅ አልተነገረለትም
ወይንም „ገዳይ ድል አድርጎ ሲገባ“ አልተባለለትም እንጂ ባለቅኔው ጠ/ሚር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን
አህቲ አድርገው
ወደ ቀድመው ክብርና ሞገሷ የመለሷት ዕለት የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ አንዱ እግሩ ተቆርጧል ወይንም ተጎምዷል።
ብልህነት መሪነት ሙሴነት እንዲህ ነው የሚገለጸው። „ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አገር ነው“ ሲሉ ምን ማለታቸው እንደሆነ የገባው
ያነበበው የተረጎመው የማሰጠረው የለም።
በአገር ምሥረታ ሂደት ትልቁን ድርሻ አብርከታለች
ይህቺ ቅድስት ሃይማኖት። ይህ ብቻ አይደለም በብሄራዊ ደረጃ አዲሱን ልደቷን ተዋህዶ በሚሊዬነም አዳራሽ ስታከበር የሁሉም ዕምነት ሊቀ ሊቃውንታት አቨው
የተናገሩንት ቁጭ ብላችሁ መርምሩት - ጥበቡን እና አህቲነቱን። ኢትዮጵያዊነት በዛ ውስጥ ምን ያህል ደም እና ሥጋ ሆኖ የመንፈስ ዶግማ እንደሆነ መርምሩት
- ቅኖቹ።
አገር ማለት እንደዛ ነው የሚገለጸው። እነዛ የሁሉም
ሃይማኖት
ሊቀ ሊቃናት በዕውነት ውስጥ ሆነው ነበር ቃለ ህይወት ያሰሙን።
ዜግነትን ማዕከል ያደረገ መንፈስ እንዲህ ነው በጥበብ ካለ መለከት፤ ካለ ዓዋጅ፤ ካለ የገብያ ግርግር ተግባር ላይ ቁምነገር የሚሠራው። ጎንደሮች ይህን „ሙያ በልብ“ ይሉታል። አክለውም „ልብ ያለው ሸብ ይሉታል“ ለዚህ ነው ኢትዮጵያን ቁም ነገር ያደረገ
መንፈስን እኔ ራሱን አስችዬ የጻፍኩት።
https://sergute.blogspot.com/2018/05/blog-post_38.html
የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌሰቶ ትግራይ ላይ ተንጠልጥሎ
ያለው አንዱ በፀረ አማራ አቋም ነው። አማራው ደግሞ ውስጡን በማጥናት፤ በመማር፤ በመመራመር ላይ ተጠምዷል። በንጥረ ነገሩ ዙሪያ
ያሉ አቅሞችን ባሊህ
እያለ ነው። ይህም ብቻ አይደለም ኤርትራ ላይ፤ ጅጅጋ ላይ ይፋ የሆነ የግድፈት ላፒስ ታውጇል። ሊሂቃኑ በይፋ ይቅርታ ጠይቀውበታል። የግርግሩ መከራ አጀንዳ አልባ የሆነ
መንፈስ ጥግ ስለሚያስፈልገው ነው አሁን እሚነሱ እሚወድቁት … መርዶው ነው ድንኳን አስጥሎ ቁዘማን ያስከተመ …
ኢትዮጵያዊነት ሲከበርም ሲኮነንም ከተሳሳተው አስተምኽሮ ወጥቶ ራስን
ውስጥን ማጽዳት ያስፈልጋል። ራስን ውስጥን ካጸዱ እግዜሩም ይቅር ብሎ መንገዱን ይጠርጋል … በስተቀር
ግን ያው ዳጥ ነው። በዳጥ ውስጥ መከራም አለ። ባሉት አለመገኘትን የመሰለ የገዘፈ ሬሳ ሃሳብ የለም እና …
ይህንን „ደርሶ መልስ“ የቴሌቪዥን ፊልም መግቢያውን ውዶቼ አስተውሉት …. እግሮች እንዴት ወደ ፊት እና ወደ ኋላ እንደሚመለሱ።
ራሱን የቻለ ጥበብ ነው በመሄድ ውስጥ ያለው መቅድሙ
መግቢያው አውራው
በሩ „የደርሶ መልስ“። „የደርሶ መልስ /ራስመሳም/ ፊልም“
እራሱ አጀማመሩ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ጉዞ ያመላክታል። መሄድ መመለስ …
„መሄድን“ ሆላንዶች አንድ አዲስ የዳንስ አርት ፈጥረውታል።
ከስሜን አሜሪካኖችም ከአውሮፓም ወጣ ያለ ነው። „መሄድን መጓዝን“
እንደ አንድ የዳንስ ጥበብ አካል አድርገውታል። እኔም ከዚህ በ2015 ለአንድ ቀን ዙሪክ ብሄራዊ ቲያትር አዳራሽ ውስጥ ኮርሱን
ተከታትዬ ነበር።
መቼም ነፃነት ቢባል እንደ ዳንስ አርት ነፃነት ያለበት አምክንዮ የለም። በዛ ውስጥ ያለ ነፃነት
በመዋለ ዕድሜዬ ኑሬበት አላውቅም። ቤተ ውስጥ እንኳን ያን ያህል ነፃነት ተስሞተኝ አያውቅም። የተሰማኝ ሐሴትም እንዲህ መለኪያ
የለውም።
እና „የደርሶ መልስን“ … በመሄድ ውስጥ ያሉ ትዕይንቶች መግቢያው ላይም ሦስት ክፍሎችም ላይ ራሱን
ችሎ የመሄድን ትዕይነት አይቸበታለሁኝ፤ ፊልሙ ርቀቱ የመሄድ የዳንስ ጥበብንም አክሏል፤ ክፍለ አካሉ አድርጎታል እንደማለት …
በሌላ በኩል የግርሜ ከሞት መመለስ እና ያዬውን ራይ
ሲገልጠው ዳጥ ላይ ያለ የእግር ትዕይንት ታያላችሁ … አዎን የእኛ ፍላጎት እና ራዕያችን ዳጥ የበዛበት ነው። በህልም ብቻ የተንጠለጠለ። ወይ አናድግ ወይ
አናሳድግ። ወይ አናሰብል ወይ አናሰበል። አገር በምንለው ውስጥ የክት እና የዘወትር ቤተኞችን አስበን ነውና እምንወጥነው። ዘላቂታነት አይታሰብም፤ ሲቋጠር ሲፈታ በዬፌርማታው፤ በዛ ላይ ወገን እና ተነጣይ አለ። ድርጅትም
ስናዋቅር ቅርበኛ እና ሩቀኛ …
… ለዚህም ነው ዳጡን አሸንፈን ወደ ፊት መጓዝ ያልተቻለው። ወደ ኋሊት ጎታቹ
ራዕዩና ጭብጡ ንጥል
እንጥል ስላለው።
ልዑል እግዚአብሄር ባይማለድን ኖሮ እንዚህን ፈርጦች ጥበብን መግቦ ባያስነሳ
እኛማ በዛው በዳጥ ውስጥ መዳከር ነበር ዕጣ ፍንታችን። ብልህነት የወለቀብን … የአመራር የአደረጃጃት ጥበብ ለጠብታ--------------?
· ንደት በነደደን ልክ።
ሌላው ቃላትን እዳሻን ነው የምንጠቀመው። አዳዲስ
ድርጅቶች „ተፈለፈሉ“ እንላለን። መፈልፈል ለእንቁላል፤ ለሽንብራ
እሸት፤ ለባቄላ ለአተር ለባህርማሽላ እሸት እንጂ ለሰው አይሆንም። ፈጽሞ!ሰብዕናን ማዳጥም ዲስክርምኔሽንም ነው።
ድርጅት ሰው ማለት ነው። ሰው አልባ ድርጅት የለም። ድርጅት ሁለት
እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች በሚያሰማማቸው ፍላጎት አቅማቸውን፤ ሃይላቸውን፤ ጉልበታቸውን፤ ክህሎታቸውን አማክለው የሚፈጥሩት
ተቋም ነው።
ስለዚህ ተቋሙ የተመሠረተበት ዓላማ የሰው ነው። ግቡም ስለሰው ነው። ሰው ደግሞ ዜጋ ነው።
እናም መፈልፈል ሊባል አይገባም። ሰው አይፈለፈለም። ጸያፍ አገላለጽ ነው። ብዙ ጊዜ ይህ ቃል ከአማራ ድርጅቶች ጋር ነው የሚገለጸው። አማራ አንጋችነቱ ስለሚፈለግ አሁን ራሴን አደራጃለሁ ሲል በከንቱ የባከነው አቅሙ ተለምዶ የህሊና ቁርጥማት ሆነ።
ሁሉንም ነፃ ያወጣው የአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎ የተነሳበት የህልውና ነፃነት ዓላማ አለው። የነፃነት ዓላማው በስማ በለው ሳይሆን
ራሱን በገበረበት መስዋዕትነት ልክ ድርጅቱን ፈጥሮ ፍላጎቱን በባለቤትነት የሚይዝለት ሁነኛ አካል ያስፈልገዋል። በመንፈሱ ውስጥ
ያለ - አማራ። ድሉን ለማን ያስረክብ? ታሪክ ትሩፋቱንስ? አማራ እኮ ታሪኩን መፃፍ የሚችለው ነፍስ ባለ ድርጅቱ አማካኝነት ነው።
ስለዚህ ድርጅት መፍጠሩ ግድ ይል ነበር። በነገራችን ላይ
የወያኔ ሃርነት ትግራይን አንዱን ባላ መቆሚያ እራፊ የነሳው ተጋድሎ ይኸው ነው።
ሌሎችም የሚነግዱበት ክስ ውልቅልቁ ስለወጣ ነው አሁን ማቄን ጨርቄን እያሉ የሚገኙት። „አማራነት ይከበር“ ሲባል ከቃል
ጀምሮ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል። "መፈልፈል? ? ?"
ዜግነት ማዕከሉ ያደረገ ድርጅት አጅንዳ ያለው ከሆነ፤ ሃሳብ እንደ ብልሆቹ ካለው ካለቀበት ወገቡን
ጠበቅ አድርጎ አጀንዳውን አሸናፊ አድርጎ ማውጣት መደበኛ ተግባሩ ነው። ሌላውም ዞግኑ መሠረት ያደረገውም ቢሆን ቀበቶውን ሳያውሸልሽል
አሸናፊ አድርጎ ሃሳቡን መዋጣት መብቱ ነው። መደፋፈር፤ መገፋፋት ከመጣ ትውልዱን ወደ አላስፈላጊ መስመር እንገፋዋለን።
አማራ በራሱ ጉዳይ ወሳኙ ራሱ ነው። በሚፈልገው መልክ የመደራጀትም፤ የመሟገትም፤ የመሳተፍም ሙሉ መብት አለው። ቢፈልግ በዜግነት ቢፈልግ በዞጉ። አማራ ከዬትኛውም ሚዲያ ይሁን የፖለቲካ ድርጅት ሰለተፈጥሮው ማንም መንገዱን ሊቀይስለት ከቶ አይችልም። ምህንድስናም ቢሆን የአባቶቹ ሌጋሲ የት ሄዶ? ብድር የሚያስቃርም ምንም ነገር ከቶም የለም። ራስን ችሎ መቆም ሊያቅተው ይሆን? ሁለት ዓመት እኮ ነው የፈጀበት 40 ዓመት ከተደራጀው በ እኩል ቁመና እውቅናውን ለማስከበር። ያንቀላፋውን የነፃነት ተጋድሎ ነፍስ ሆኖ፤ ንፈስ ፈጥሮ ነፍስ ዘርቶበታል።
ለዚህ ነው የአማራ ተጋድሎ ዋንኛ መርህ „አማራነት ይከበር!“
„እንከባባር!“ የሆነውም። በአንድም በሌላም የትናንትን ግድፈት መደገም እርቃንን ነው የሚያስቀረው፤
የትናት ጉዞ ምን ያህል አቅምን ፈትኖ ዘጭ እንዳደረገ ይታወቃል። በሌላ በኩል
ትዕግስት ሲያልቅ ፍቅር መሰደዱም ታይቷል። ተዉ እአልን። ቀሪ መንፈስን በእጅ ለማቆዬት ደንበር አልፎ መሄድ ዋጋ ያስከፍላል። የፈሰሰ አለመታፈሱም ታይቷልና …
ስለሆነም የእኛም ውስጥነትን ለማጽዳት ላውንደሪ ካልገዛን
ወደ ፊት እና ወደ ኋላ አይቀሬ ነው እንደማለት፤ በዚህ ማህል የትውልድ ብክነት ደግሞ ዳግም
ይከሰታል፤ ተከታዩ ሮል ሞዶሌ የሚለውም የራሱ ነፃነት ስላለው እምንመራው መንገድ ጥራት ያለው ሊሆን ይገባዋል።
ቢያንስ ስንዱዎች እዬደከሙበት ባለው አዲስ ፍልስፍና
አረም እንዳናበቅል መጠንቀቅም የአባት ነው፤ ቀስ አድርገው ሳይንጠራሩ ነው የያዙት። ንጉሥ ሰለሞን የ እግዚአብሄርን ቤት ሲያንጽ ያለው የጥበብ ልቅና ያህል ነው እኔ እማዬው። ያው መጤ አይደለሁም ለዚህ ሃሳብ ከውስጤ እንደ አንድ የትምህርት ክ/ ጊዜ ስለማጠነው።
አቤቱ ዜግነት ከተሆነ ፍልስፍናው ማከብረን ፊደል ይቆጠርበት። መግራት
ራስን፤ አካባቢን፤ መዋቅርን፤ ሚዲያን፤ ጸሐፍትን፤ ተንታኝንም፤ ተከታይንም ጭምር ነው። ተከታይም፤ መዋቅርም፤ ድርጅትም የትውልዱ
አካል ናቸው። በተጨማሪም የአገርም ቅርስም ትውፊትም ናቸው ለማግሥት።
ትውልዱን እዬመራ ያለው ቅዱስ ርሁሩህ መንፈስ ትሁት
ለጋ መንፈስ ውጥን ቢሆንም በወጉ በተሰናዳ ብቁ ዘላቂ ህሊና ስለሆነ ጉዞውን አህዱ ያለው፤ ቢያንስ እንዳሻን እምንወራኝበትን መስክ ሁሉ
በራሳችን እንዳናጨናግፈው …. ጥንቃቄ እንድናድርግ እንደማለት … ዜግነት ማዕከላችን ከሆነ … ዜግነት ፍልስፋናችን ዛሬ ላይ ከጣመን … መቼም
ትናንት ነበርንበት ተብዬ እንደማልሞገት ነው … ህይወቱን፤ መኖሩን አብረን ስላለንበት …
· ሳናልክክ ውርዴታችን
ዋጥ እንድርገው!
ውርዴት የሁሉም ነው። ክስረቱም የሁሉም ነው። ስብሰባ ትጠራለህ፤ የሚገኘው አብዛኛው ወጣቱ ነው፤ "ኢትዮጵያ ገና ያለተሰራች አገር ናት" ሰባኪን አድምጡ ትላለህ በአደባባይ። የተባጀው እንዲህ ነው ቁስል እያልን፤ እርር ኩምትር እያልን። ለዚህ ድውይ መንፈስ አንጣፊዊ አሸርጋጁ ደግሞ የጉድ ነው። ስለሆነም ለጥፋቱም
ሁሉም ነፍስ ተጠያቂ ነው። በተጠያቂነት ውስጥ መንግሥት፤ የፖለቲካ ድርጅቶች የሚባሉት፤ ሚዲያዎች፤ የማንፈሴቶ ቤተኞች ብቻ ሳይሆኑ ት/ቤቶች፤ ዩኑቨርስቲዎች፤
ኮሌጆች በትልቁ ወላጆችም ናቸው። በወሉ ሲታይ ደግሞ ማህበረሰቡ በሙሉ።
እኛ ጎረቤቶቻችን ሳይቀር ገርፈው ቀጥተው ነው ያሳደጉን። ጎረቤቶቻችን የወላጆቻችን ያህል እንፈራ ነበር ግድፈት ስንፈጽም እንዳያዩን፤ ልጆች የወላጆቻቸው ብቻ ሳይሆኑ የማህበረሰቡም ልጆች
ናቸው። ትውልዱ ካለበት የመንፈስ ያልጠራ መንፈስ ለማዳን በእኛነት ውስጥ እኛው ስለመኖራችን መጀመሪያ እናረጋግጥ።
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ
ሚስጢር ነው!
አብይ ኬኛ!
የኔዎቹ ክብረቶቼ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ