የአቤቶ ኦፌኮን የሃሳብ አድራሻው የት ነው?

የአቤቶ ኦፌኮን የሃሳብ
አድራሻው የት ነው?
„የሠራዊት ጌታ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል …
ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ“
 ሐጌ ፩ ከቁጥር ፭ እስከ ፮

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
30.12.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።



·       ብታ።

ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ? እንዴት ናችሁ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። ብቻ የትግራይ እና የኦሮሞ እናቶች የመንፈስ ብክነት፤ ጫን - ተደል ስጋት አሳስቦኝ ነው የሰነባበተው። ይላፍላችሁ ያላላቸው መከረኞች መቼም ናቸውና። ዛሬ በገረመኙ  የአምክንዮ ጥምዶች እና በፈጠጡ ሃቆች ዙሪያ አብዬ ሳይሆን አካል ተ- አማሳል አድርጌ ለማቅረብ አሰኘኜ እንዲህ …

·       ን የኦፌኮን የሃሳብ አድራሻው የት ነው?

ውዶቼ መቼም አዲስ አበባ እንደማትሉኝ ነው? ስለምን አቤቶ ኦፌኮን የሁለተኛ ጊዜ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ጥሶ ወለጋ መሄድን ደፈረው? ሰለለምን ተልዕኮ ነበር ነቀምት የሄደው? ለአቶ ዳውድ ኦነግ የመንፈስ  ጥሪት ምንጣፍ ለማንጠፍ? እኮ ስለምን?! ስለምን አርሲ አልሄደም? ስለምን ባሌ አልሄደም? ስለምን መቱ አልሄደም?

ስለምን የጅጅጋ መከራ የደበደባቸውን ንጹሃንን አሳር ለመጋራት ወደ ዛ አላቀናም? ስለምን ከሌሎች የኦሮሞ ድርጅቶች ተለይቶ የአቶ ዳውድ ኢብሳን ሞገደኛውን ኦነግን ጋር ለመሥራት ምርጫው ሆነ? ማንን ለማጥቃት? ማንን ለማንበርከክ? የማንን ቅም ለመስበር? የማንን የፍቅር አቅርቦት ለመሰነጣጠቅ? ማንን ለማፈረስ? ዛሬ ጉዳዬ ይህ ነው - ሌሎችንም ጎበጥ ያሉ ሃሳቦች ይኬድባቸዋል … ሊንካቸውን ግን አለጥፍም።

ምክንያቱም ይህን የመጠነ ሰፊ የሐሤት ሩህሩህ ዘመን ውስጥ ለማድረግ ለቆረጠ ሁሉንም መፈታተሽ ስለሚገባ፤ በዚህ የዝና ንግሥና በዚህ ዳጥ እና ምጥ ተቀላቅሎ ጉዞ የለምና … መልፋት ያስፈልጋል … ከልብም ማዳመጥ … መንፈስ አባካኞች ድርጅቶች ብቻ አይደሉም እና … ሁሉም ዘብ መቆም ይገባዋል ለዚህ እዮራዊ ዘመን።

·       ስጥን ፍለጋ አብረን …

ግን ይታያችሁ ይሆን አቤቶ ኦፌኮን ደንደን ባለ እልፍኙ ላይ እንዳለ። ለመሆኑ የኦፌኮን የሃሳብ አድራሻ የት ላይ ነው ያው? ሃሳቡ መሬት የያዘ ነውን? ወይንስ ጥልጥል? ማንን ተማምኗል?

አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ግልጽ ናቸው ስለሆነም ተፎካካሪ የሚለው ይገልጣቸዋል። ያው የህውሃት ባለመሃያ ያልሆኑትን ማለቴ ነው። እኔ ተፎካካሪ/ ተቀናቃኝ/ ተቃዋሚ እያልኩ ስጥፍ ነው የባጀሁት። ምክንያት ስላለኝ። ራሱን ያነገሠውን ሁሉ በተፎካካሪ ለማዬት ስለማልችል።

አቶ በቀለ ገርባ በኦህዴድ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ፕሪዝዲዬም ሰብሳቢውን እንኳን አድሬስ ማድረግን አልፈቀዱም ነበር። ይህ ኢትዮጵያዊነትን መናቅና መርገጥም ነው። በታሪክ የመጀመሪም ነው። በሌሎች አገሮች ቢሆን ያስከስስ ያስቀጣም ነበር። ስለዚህም ነው „ተፎካካሪ ከሚለው ውጭ ያሉ ነፍሶች እንዳሉ ስላመንኩበት ተቃዋሚ፤ ተቀናቃኝ የሚለውን ሁለቱን የሚገልጣቸው ስላሉ ነበር ሁለት ጣምራ ዕይታዬን ሳልቀላቅል የራሳቸውን ነፃነት ሰጥቼ ስጽፍ የነበረው። ለምሳሌ ኦፌኮ ተቀናቃኝ የሚለው ይገልጠዋል። 

ተፎካካሪ የሚለው ይበዛበታል - ለኦፌኮን። ግልጥነት የለውም። ድፍን ፍላጎት ነው ያለው። ቅናትም አለበት። በፍቅር ይቀናል።  በአድራጊነት አቅም ይቀናል። በስኬትም ይቀናል። በመበለጡ ይቀናል። በዶር ለማ መገርሳ ልዩ የሰማይ ስጦታ እና የማድረግ፤ የመመራት ልዩ መክሊታዊ ብቃት እና የበዛ የማይጠገብ ትሁት መንፈስ አቅም አብዝቶ ቀንቷል አቤቶ ኦፌኮን።

በጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ልዑቅ ስልጡን የሚሊዮኖች ተቀባይነትም ሆዱ ባርባር ብሎታል። ውስጡ ተሸባብሯል። ቀድሞ ነገር የ18 ቀኑ የኢህአዴግ የቀዝቃዘው ጦርነት ፍልሚያ ዕውቅና ለመስጠት አይደፍረውም አቤቶ ኦፌኮን። „ዝባችን አስፈታን“ ይላል፤ የግብጽ ታሪክ ስለሾለከው። ይህም ብቻ አይደለም  „ልቻ ቢለዋወጥ“ መሪ መፈከሩ ነው።

አቶ ዳውድ ኢብሳ 30 ሺህ እስረኛ ሲፈታ „በቂ“ አይደለም ሲሉ፤ ዶር መራራ ጉዲና ደግሞ „መኪናዬ እስከ አሁን አልተፈታችም“ ነበር አጀንዳቸው …. ውስጣቸውን ለመስጠት እርቀቱን ማዬት ይቻላል ለለማ መንፈስ ሆነ ለተገኘው ሁለገብ ድል እና ስክነት ላለው የመቻቻል ብጡል የአማራር ልቅና ጥበብ።

ከኦህዴዱ ከአቶ ካሳሁን ጎፌ ጋር ዶቼቨሌ ቀርበው በነበረበት ጊዜ የሰጡት ቃለ - ምልልስ ነበር። የአቶ ካሳሁን ብቃት ያዬሁበት አጋጣሚ ነበር። አሁን ገፋ የተደረጉ ይመስለኛ እኒያ ብልህ ሰው።

የፖለቲካ ሳይንቲስቱ ዶር መራራ ጉዲናም ሆኑም አቶ ዳውድ ኢብሳ ሊመክቱ አልተቻላቸውም ነበር። ዛሬ እኒያ የፖለቲካ ሊሂቅ ሚዲያ ላይም አይታዩም። እሳቸው ለኦሮምያ ፕሬስ ጉዳይ አንሰው ሌላ ሰው ነው መግለጫ ሲሰጥ እማስተውለው… ቅንን እውነተኛ ሰብዕናን ዘመን እራሱ የእንጀራ አባቱ ስለሆነ …

·       ቃዋሚነት/ ተቀናቃኝነት/ ተፎካካሪነት ።

የአቶ ዳውድ ኢብሳ ተቃዋሚው ኦነግ የሃሳብ መንግሥት ነው። በዬትም ዓለም እገነጣላለሁ የሚል አማፂ ተፈቅዶለት፤ ተዋጉ እያለ ትእዛዝ እዬሰጠ በርዕሰ መዲና ተቀምጦ ሲዘባነን ዓለም የተመለከተችው አሁን በኢትዮጵያ የፖለቲካ አያያዝ ጅልነት ነው። ይህ መቻቻል ሊባል ከቶም አይቻለውም። ይህ ትእግስት ሊባልም ከቶ አይቻለውም።  የኢትዮጵያን ሉዕላዊነትን የተቃረነ የፖለቲካ ክስረት እንጂ።

በሌላ በኩል ህውሃት የራሱን የኢህአዴግን ውሳኔ በጥሰት ላይ የሚገኝ ስለሆነ ለራሱ ለግንባሩ አዲስ ተጨማሪ ተፋላሚ ተቃዋሚ ድርጅት ነው። የታላቋ ትግራይ መንግሥት። ለዚህ የተቃዋሚ ከራስ ላፈነገጠ አንጃ ደግሞ አካሎቹ በፌድራል ደረጃ በተመቸ መቀመጣል ሥልጣን ላይ ይገኛሉ።

የህውሃት ውክሎች በፌድራሉ መንግሥት እዬወሰኑ፤ እዬፈረዱ ይገኛሉ በምንዱባን ነፍስ ላይ ጢባ ጢቦ ይጫወታሉ። ለዚህም እነ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂምን ለናሙና ማንሳት ይቻላል። ህግ ሳይመረቁ የህግ ተርጓሚን አገራዊ ጉባኤ ይመራሉ። ያቆስላል!

 በሌላ በኩል ትግራይ ለሚገኙ የሦስተኛው መንግሥት አካላትም ኢትዮጵያ ቅኝ ተገዝታ የበጀት ፈሰስ ወዳ ፈቅዳ ታደርጋለች። ለዛውም እያቆላመጠች። የትግራይ ሉዕላዊ መንግሥት ደግሞ በህግ ጥሰት ለሚጠዬቁ ተጠርጣሪዎች ሁሉ በመደበኛ ደሞዝ ይከፍላል። 

ማን ከልካይ ሲኖርበት። ወሸኔ ነው ስለውድቀቱ¡ ይህንንም የመሰለ ልግጫም ዓለም አስተናግዳ አታውቅም። ምን አልባት ሜሪኩሪ ላይ ከታሰበ የህውሃ ሳይንቲስቶች ዕድምታ ይጠይቀበት። ሌሎች ቀሪዎች ተፎካካሪ ድርጅቶች ማለት ይቻላል፤ ያው ፓርቲ ለማለት አይቻልም። መስፈርቱን ስላማያሟሉ። 

ብቻ እነዚህ ተፎካካሪ ድርጅቶች ግልጥ አቋም ያላቸው በኢትዮጵያ መንግሥት ሥር ኢህአዴግን ተፎካክረው ለማሸነፍ ወይንም ለመሸነፍ የተሰናዱ ናቸው። ያው ምርጫ ተብዬው ከተካሄደ ማለት ነው። እሱ እራሱ በሳል ሙግትን ይጠይቃል ከሰሞናቱ አንድ እለዋለሁኝ … ይጣፋል እንደማለት …

አዴ ኃን እና ኦዴግ የኢህአዴግ ክፍለ አካል ሆነዋል። ስለዚህ እነሱ ከቀውሱ ውስጥ ራሳቸውን ያወጡ የሰላም ምልክቶች ናቸው። ጦርነት ስለበቃን ስለ አንገሸገሸንም፤ ወሸኔ ብለናል። የልቤ ብለናቸዋል። ምርቃትም ታክሎላቸዋል። አሳረፉን!

ለነገሩ አማራ መሬት ላይ እራፊ መንፈስ አለን የሚሉ ሁሉ እንመጽ ቢሉም አልቆባቸዋል። ለጫዋታ ሟሟያ ግን የሚዲያውን ማይክ ካልደከመው ያሟሙቅላቸው። ባትሪው እስኪያልቅ ድረስ። 

ማገዶነት ጎንደር በቅቶታል። የጎንደር እናት 50 ዓመት ሙሉ በዙር የልጅ ብርንዶ ስታቀብል ኖራላች፤ እንድ ልጅ ለግለግ ብሎ ወጥቶ መጠሪያ እንዳላገኘች ከዚህ ዘመን በላይ ምስክር የለም። በነፃ ለምንሠራው እራሱ በስንት ፍዳ እና አደን ነው። መሬት ላይ ደግሞ አቶ መላኩ ፈንታ እንኳን ያዬነው ነው፤ ሰማዕቱ ቆመስ ስመኘው በቀለም ደመ ከልብ ነው።  ስለሆነም ጅልነቱ ይበቃል።

አመጽን ቢታሰብም መቅኖውን አዬር ላይ እንሳቀረዋለን። ከእንግዲህ ጎንደር የአማጽያን መናህሬያ አይሆንም። እጁን እየያዝ ለአብይ መንግሥት ማስረከብ አለበት የጎንደር ህዝብ። ጎንደር ለ አብይ መንግሥት ፍጹም ታማኝ መሆን አለበት! 

ጅሉ የቅማንት ሊሂቃንም ሙከራቸው ይከሽፋል … መለመላቸውን ነው የሚቀሩት። ከጎንደር ውጪ የት ቦታ የቅማንት ብሄረሰብ አለና ቀድሞ ነገር? ያው ተጋሩኛ ካልተሆነ እንደ አቶ ዳውዱ ኦነግ።

የሚገርመው ኦነግ ሠራዊት ጋር ተጋሩ ነበሩ ይህም "የተለመደ" ነው መባሉ ደግሞ ይገርም እስከ ወዲኛው ነው። ወይንም አልቆብናል መፈላስፉ። የአቶ ዳውድ ኢብሳ ኦነግ እኮ ኦሮምያ የምትባል አገር አለችንኝ ባይ ነው፤ እና ለስደት ይሆን የፖለቲከኛ ጥገኝነት እነ ታገሩ የተላኩት?

ብቻ ይህ ዘመን የማያሳዬው፤ የማያስመዝነው የሃቅ አንባ የለም። በዬትኛውም መስፈርት ዞግ ከሆነ ድርጅቱ የሌላ ዞግ አባልትን አይቀበልም፤ ሌላ ተልዕኮ ካልኖረው በስተረ፤ እንደ ቀደመው ኦህዴድ ህውሃት ለአዲስ ተውኔት የላካቸው ሰላዮች ስለመሆኑ ልብ ሊባል ይገባዋል ሃቅ የዳማ ጨዋታ አይደለምና ለፖለቲካ ኮሬክሽን ከሉዕላዊነት ጋር ሲቀላቀል ያማል።   

የኦነግ እና የህውሃት አጣማሪ አንባሳደሮች ቢባሉ ይቀላል እንደሆን እንጂ "የተለመደ" ነው ኤርትራ በነበሩ ድርጅቶች ሊባል ከቶውንም አይገባም። ለቅኑ ለለማ መንፈስ ሰለይም ፈተናም ነበር የተላከለት። ለዚህ እንዲያው ብናኝ ሙግት የሚሆን ሽራፊ አምክንዮ ማቅረብ አያቻልም። የሚቀረበው አምክንዮ ይህን እንደ መከራከሪያ ማቅረብ እራሱ የሃቅ ፍልስት ነው። ሃቅ ቀጥ ያለ ነው፤ ቁሮ ወይንም ለጠፍ አያሰኘውም።

·       ስለምን እኔ ኦፌኮን ተፎካከሪ ድርጅት አልለውም? 

ከለውጡ ጋር ልብ ለልብ ስላልተገናኘ ነው። መገኘት አልቻለም። ሌላ ሃይል ስልጣን ላይ ቢወጣ ይሻላዋል ለኦፌኮን ኦህዴድ /ኦዴፓ ከሚሆንበት። የሌላ ብሄር ብሄረሰብ አባላት ፖለቲካ ሳይንስ ያልተማሩ ጠ/ሚር ቢሆኑ ለኦፌኮን ምቹ ነበር። ለማሳጣትም ይመቸው ነበር። እበልጣለሁ ለማለትም ይደላው ነበር። 

አቤቶ ኦፌኮን ደስተኛ አይደለም ኦህዴድ /ኦዴፓ አውራ ፓርቲ ሆኖ መውጣቱ ከዬትኛውም የፖለቲካ ድርጅት በባሰ ሁኔታ ተበሳጭቷል። የማይደፈረው የለማ እና የ አብይ የመንፈስ ጥበብ አቅማቸው እራሱ መቅኖውን አሳጥቶታል። ብሄራዊ ሆነው ተቀባይነታቸው መጉላቱ ምቾት አልሰጣቸውም - ለኦፌኮኖች + ለጃዋርውያን። ኦዴፓ መሪውም ምክትሉም የፖለቲካ ሳይንቲስትነታቸው አልተዋጠለትም - ለአቤቶ ኦፌኮን። አንድ ለእናቱነቱ ስለ አመለጠው። ዘመን ይሰጣል ዘመን ይነሳል። መተካካትም አለ አይቀሬ ነው ... 

ስለሆነም ኦፌኮን ተፎካካሪ ለማለት አልችልም፤ ተቃዋሚ ለማለትም አልችልም ግን ተቀናቃኝ የሚለው ቃል ይመቸኛል። ከውጥኑ ጀምሮ „ለማ ፊቱ ኦሮሞ“ ከይመስላል ጀምሮ ያልጠራ የህሊና ስብቃት ስላለበት። 

"ለማ እና አብይን እንዳትነኩብኝ" ያለውን መንፈስ መንታ መንገድ ላይ መገተር አሰኘው … አደረገውም፤ ተሳክቶለታልም። 

... ግን ግን  የአቤቶ  ኦፌኮን የሃሳብ አሙ ምን ላይ ነው? ከመድረክ ጋር ነውን? ወይንስ ሲነጋ ሲነጋ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ሌሊት ሌሊት ከአቶ ዳውድ ኢብሳው ነፍስ ጋር የሙጥኝ ብሏለኝ? ወይንስ ከጃውርውያን ወይንስ ከጋቢሳውያን? ይህ ግልጽ ሊሆን ይገባል ለኢትዮጵያ ህዝብ። „አለባብሰው ቢያርሱት ባረም ይመለሱ“ እንዳይሆን>>

ያው ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩት ተቀናቃኝ ሆኖ መውጣቱን እኔ አውቃለሁኝ ሌላው ባያውቅም - የአቤቶ ኦፌኮንን። መንፈሱን በጥሞና ነው የተከታተልኩት። ዶር ለማ መገርሳን ሆነ ዶር አብይ አህመድን ንቅት ብቻ ሳይሆን ዕውቅና ለመስጠት ድፈረቱ ያነሰው ስለሆነ ከጅምሩም „ጉልቻ ቢለዋውጥ ወጥ አያጣፍጥም“ ብሎ መነሳቱ ይታወቃል።

በሌላ በኩል አቅም ስሌለን የተጽዕኖ ፈጣሪ የአንድነት መንግሥት ይፈጠር የሚልም አዲስ ሽል ይዞ ከች ብሎ ነበር። ባይሳከላትም ግን ሸጉጦ የያዘው ጉዳይ እንዳለ ይታወቃል።
አቤቱ ኦፌኮን መስከረም ሲያብት ደግሞ ኦነግን በብርቱ በመደገፍ ከጎን በመቆም በመድረኩ እኩል የመሳተፍ ትዕይንት አሳይቶናል ዘንከትም ጀርገድም እያለ። ጃዋርውያንም መንፈስ ቢሆንም ኒራሉ ስለሆነ እንዲህ በቀላሉ መፋታት የሚቻል አይሆንም።

ይህም ባልከፋ? አሁን የአቶ ዳውድ ኢብሳ ነፃ መሬት እርስት አለው ወይ ኦፌኮን ነው ዋናው ጥያቄ? ስንት ጋሻ መሬት የአቶ ዳውድ ኢብሳ ኦነግ ለአቤቶ ኦፌኮ ለገሰ? አቤቶ ኦፌኮ ግልጽ ቀጥተኛ ቅኔኛ ያልሆነ መግለጫ ሊሰጥ ይገባዋል። ህዝብ ማንዘርዘሪያ ስላለው ቁርጡን ማወቅ ስለሚገባው። "ቁርጥ ያጠግባል" እንደሚሉት ጎንደሮች። 

በህጋዊነት ተቀመጦ ህግ እንዲህ ሲጣስ እና ሲደረመስ እሱም እራሱ "ህገ መንግሥቱ ይከበር" የህውሃት ዓርማ ካልተውለበለ ሲል እንደ ነበረ ይታወቃል፤ እሱ ግን በተለያዬ ሁኔታ ህግ እዬጣሰ እና እዬረገጠ ደግሞ ተገኝቷል።

የሆነ ሆኖ አሁን ኦፌኮን መንፈሱ ያለው የሚመራው በዬትኛው መንፈስ ነው? የአቶ ዳውድ ኦነግ ወይንስ የኢትዮጵያ መንግሥት? የአቶ ዳውድ ኢብሳ ኦነግ ከህውሃት ጋር ያለው ግንኙነትም እዬታዬ ነው? እና አቤቶ ኦፌኮን የት ነው አድራሻው? ክህውሃት ጋር ኦነግ በፈጠረው የሃሳብ ጥምር መንግሥት ጋር ወይንስ የራሱን የሃሳብ ዘውድ ደፍቷል አቤቶ ኦፌኮን?

ይሄ እዬሸበላሉ በቃላት መጫወት ቁሞ፤ አድራሻው የት እንደሆነ የአቤቶ ኦፌኮ ሊታውቅ ይገባል። ዕድሜ ለመስከረም 5 /2011 ሁሉንም አሳይቶናል። አሁን ግን ቀልድ እና ቁምነገሩ መለዬት አለበት። አቤቶ ኦፌኮን ተቃዋሚ እንደ አቶ ዳውድ ኢብሳው ኦነግ ወይንስ ተቀናቃኝ እንደራሱ? ወይንስ እንደ ዝምተኞች የቀሩት ማህያ-አልቦሽ የፖለቲካ ተፎካካሪዎች?

መደቡ ይለይ … ቀለሙን ያሳዬን? ሊሂቃኑ ችግራቸው ኢትዮጵያን ከመጥላት፤ ባ ኢሷ ከፍ ማለት በመቅናትም የመነጨ ስለሆነ በዬዘመኑ ህውከት ነው የሚፈጥሩት … ለዛውም በዬዘመኑ እነሱው ነው የሚመሩት በደርግ ጊዜ እንኳን የነበሩትን 5 ድርጅቶች መሥራቾችም መሪዎችም እነሱው ናቸው የነበሩት እንደ መምህር አቻምዬለህ ጹሑፍ ከሆነ።

ህውሃት ደርግን ሲጥል እና ሽግግር ሲልም አበረው ነበሩ፤ አሁን ደግሞ  በዘመነ አብይ በ በአማራር ጥበቡ ብስለት እና ልቅና በበዛ የሚሊዮኖች ፍቅር ሳይኖሩ ባላበቶች ነን ብለው ይኸው ያምሳሉ በግልጥ እና በስውር … ቢያንስ እንዴት እንቆረቆርለት አለን ለሚሉት  የኦሮሞ ህብ እንዴት አያስቡም? እንዴት ያ አይጨንቃቸውም ሚሊዮን ወገን ሜዳ ላይ ፈሶ… ተጨማሪ ጦርነት? ት/ቤት እኮ ልጆች ሊሄዱ አልቻሉም? እንደ ገና ሌላ 50 ዓመት በቁሞ ቀር ፖለቲካ? ያማል!
  
·       ይለይለት።

በዬጊዜው በሚፊነዳ ፈንጅ ሃሳብ ሲበተን፤ ትውልድ ሲባክን መኖር የለበትም።  የኦሮሞ እናትም ተኝተህ በለኝ ከምትል ከትክሻዋ እንደ መዥገር ዘመን ይዞ ተዘመን ተጣብቀው የልጅ ብርንዶ ስታቀርብላቸው የኖረችላቸው አክተሮችን እና ድርጅቶችን በቃኝ ብላ ፊት ለፊት መውጣት ይኖርበታል። ስንት እንደ ሆነ የኦነግ ቅርንጫፍ አይታወቅም ሰሞኑን ደግሞ አንድ ገባ ተብሎ ሸር ጉድ አይቻለሁኝ? ወይ ማዕልቲ አለ ተጋሩ? 

የሆነ ሆኖ ያቺ ጨርቅ ለባሿ ፍደኛ የት እንደ ወደቀች አስታዋሽ የላትም። የአክተሮች እናት ነው የሚንቆለባበሱት፤ ክብር ግርማ ሞገስ ያገኙት እነሱ እንጂ እሷ ከነመፈጠሯም የሚያስታውሳት የለም። ምን አገኙ ልጃቸው ተገድለው በልጃቸው ሬሳ ላይ ተቀምጠው የተደበደቡት እናት? ለመሆኑ ሚዲያው እራሱ አስታውሷቸው ያውቃልን? ምስጋና አቅርቦላቸው ያውቃልን?  ለዕለት ጉሮሮ የሚበቃ ነገር ተቸረዋልን? አስታዋሽ አላቸውን?

·       ማይደመጥ የለም?

ሌላው ቀልድ እና ቁምነገሩ ኢትዮጵያን ተገንጣጥላ ተበጣጥሳ ማዬትን ለሚሹትም የተለዬ ክብር ብቻ ሳይሆን ለከፈሉት ዋጋ ዘውድ ይደፋላቸውም አለበት። ከፈልን የሚሉት ዋጋ እኮ ለኢትዮጵያ በሰላም አለመኖር ዘመን ተዘመን ያደረጉት የጫኑት መከራ ነው። ሉዑላዊነቷ እንዲደፈር ነው የታገሉት።

ይህን ከተቀበልን  ምን ችግር አለው ለአቤቶ ሙሱሎኒ ሃውልት ኢትዮጵያ ላይ ለማሰራት ፈንድ ራይዚንግ መጀመር ነው ወይንም ጎ ፈንድ ሚ ማቋቋም።

ኢትዮጵያ እንደ አገር እንዳትቀጥል ቀን ከሌት የተጉ ዛሬም እርር ድብን ብለው እያመሱ ለሚገኙት የሙሰሎኒ ግርፎች „ክብር የመስዋዕትነት ዋጋ¡“ ሲባል ይህ ትውልድ ከምን ላይ ሊቆም እንዳሰበ ይገርማል።

ለእነሱ ለቁሞ ቀር ሃሳብ ለተማገዱት ሰማዕታት ማን ይቆርቆርላቸው ይሆን? ለአክተሮች እንዲህ ዋስና ጠበቃ ሲኮን? ስንት መራራ ነገር አለ - እሬት።

ትንሽ  የአድማጭ ህሊናም መራራት የአባት ነው … በዚህም በዛም መንፈስን የሚጎዳ ነው የሚደመጠው፤ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ለተጋ ያ እንደ አስዋፆ ይቆጠርለት እና ዋጋ ይከፈለው? ? ? ? ? ? ?እም! ምጥ!

የእኔ ክብረቶች ሊንክ እንዳትሉኝ ፈልጋችሁ ፈታትሻችሁ ማግኘት ነው። የአላዛሯ ኢትዮጵያ መከራ ከጎመዘዛችሁ። የትውልዱ ብክነት ዘመን ከዘመን ካረመጠመጣችሁ፤ ሳሃ ለማውጣት፤ ለመክሰስ፤ ለማጣወር ብቻ ነገር እንዲህ እዬተሾከሾከ እንደ አጃ ይቀርባል። ይህ አዲስ ጉዞ እኮ ሁሉንም ነው የተማለደው። ከዚህ ላይ 50 ዓመት ቢጠበቅም ይህን መሰል መፍትሄ ኢትዮጵያ አታገኝም። ምክንያቱም ግራ በራ ስለሆነ…

ለአዲሱ ጉዞ መንፈሳችን ቅርብ ከሆነ … ውስጥን ሳይበትኑ ውስጥን ሳያንገላቱ ከእውነት ጎን መቆም ነው በዬጊዜው ስንጥር እና ስብጥር እያመረቱ መንፈስ ከመበተን። እሚመለከው ማኒፌስቶ ደጋፊውን እንኳን እንዴት አርቆ እንዴት አሳዶ እንደኖረ ይታወቃል … የሰው የክት እና ዘወትር በሰፈነበት የነፃነት ተጋድሎ የተኖረበት እኮ ነው። እና እኛ ያለደረግነውን ሌላው የጠ/ሚር አብይ መንግሥት በሰፋ ትእግስት በበዛ መቻል የሚያደረገው አንሶ ሌላ የሃሳብ ጫና ባልወለደ አንጀት መጫን ያቆስላል። 

·       ይከወን።

የተጠበቀም አይደለም እንዲህ ይሆናል ተብሎ። የግራ ፍልስፍና አራማጆች ከተሰጣቸው ታሪካዊ ፍዳ ሁሉ የተገላገሉበት ዘመን ነው አሁን። በዘመናቸው የተፈጠረው የማሌ ፍልስፍና ምን ያህል አገርን በሞራልም፤ በማዋዕለ መንፈስም፤ በትውልድ ብክነትም፤ በብልጽግናም፤ በስልጣኔም ራቁት እንዳስቀረ አክተሮቹ ያውቁታል፤ አሁን እነሱም ከመዳህ ወጥተው ነፍስ ዘርተው ቀና ብለው ለመታዬት የበቁት እነሱን ነፃ ባወጣው ሰውኛ እና ተፈጥሮኛ አዲስ ለማዊ ፍልስፍና ነው። ስለዚህ ተከታዮቻቸው፤ አድናቂዎቻቸው፤ ደጋፊዎቻቸው በሙሉ ተመስገን ማለት ይኖርባቸዋል። ያልተገባ ብክነት እና ክስረት ስለነበር። አቅም መፍራት እና መበትን በሽታም ነው። የተኖረው እንዲህ ነበር። 

ስለሆነም የሌለ ጫና በእነዛ ባተሌዎች ላይ ለመጣል … እንጣደፍ። እነሱን እዬወጉ ላሉ፤ ያደራጁትን እያፈረሱ ላሉ፤ የሰበሰቡትን እዬናዱ ላሉት፤ ለእነሱ ሳይሰስት ፍቅር የሰጠው እንዲጠራጠራቸው፤ እንዳያምናቸው ስንት ቀውስ ለፈጠሩ ክብር ኩራት እና ሽልማት ተሟጋች መሆን ያስገምታል … ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር እንደ ለመደበት ይሰደዳል … ለግልም ይሁን ለድርጅት ያለ የመንፈስ አክብሮት እና ቤተኝነት። የመንፈስ አክብሮት ረቂቅ ነው ... 

      
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር …

                                                   
















የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።