ልጥፎች

ሰሞናቱ ለረ/አውሮፕላን አብራሪ ሃይለመድህን እንዲሆን በጸሎት እንትጋ!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዛብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“ ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱ አማኑኤል ዛሬ እና ሰሞናቱን  አንድ የተባረከ ነገር  እንዲያደርግልን እማጸነዋለሁኝ። ይርዳን አንድዬ! ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 22.01.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።                                                     የተባረከ አሜን ለተባረከ ትውልድ! ዛሬ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሲዊዘርላንድ እንደሚመጡ ዜና አዳምጫለሁኝ። እመኛው እሻው የነበረ ቀን ነው። እዚህ አንድ ውድ የሆነ የኢትዮጵያ ጀግና አለን። ይህ ጀግና ጀግንነቱ በተግባሩ ብቻ ሳይሆን በሰብዕናውም ጭምር ነው ። ስለ አገሩ አብዝቶ ያስባል፤ ስለ አላዛሯ ኢትዮጵያ በበዛ ሁኔታ እስኪገርመኝ ድረስ ይጨነቃል። በፈጣሪው እጅግ ያምናል አብዝቶ ይጸልያል። በባህሪው ጨዋ ወልዶ ጨዋ ያሰደገው ከመልካም ቤተሰብ የተፈጠረ፤ አሳዳጊውን ይባርከው የሚያሰኝ ነው። በመልካም ቤተሰብ በጥንቃቄ ያደገ ወጣት በመሆኑ በሁለመናው እጅግ ቁጥብ ነው። ብዙ የማይናገር፤ ብዙ የማይል፤ ብስጭት የሌለበት በፍጹም ሁኔታ የተረገጋ ወጣት ነው።  ስላደረገው ብሄራዊ አር ያነት አብነት ያለው ብጡል ብሄራዊ የጥቁር አንበሳ ገድል እና ወጣትነቱን ሳይሳሳ የማገደበት፤ ህይወቱን የሰዋበት መንገዱን በፍጹም ሁኔታ ይህን በማድረጉ እና ነፍሱን ችግር ውስጥ ማስገባቱ የማይ ጸጽተው ስለ እናት ምድሩ ቀን ከሌት የሚያስብ ንቁ ደፋር ሩቅ ወጣት ነው። በጠ/ሚር አብይ አህመድ አመራርም እጅግ የተደሰተ ተስፋም ያደረገ ወጣት ነው ። ተስፋ ያደረገው ስለ እሱ ቀጣይ ኑሮ አይደለም። በፍጹም። ስለ ዘ

ዘመን ሲባረክ!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ዘመን ሲባረክ! „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“  ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ  Sergute©Selassie  ከእመ ዝምታ።                   የፈጣሪ ቅኔ! እንዲህ ነው ዘመን ሲባረክ! ሁሉን የሰጠው የጸጋ ቅኔ! የአሮን በትር መንገዱ ሁሉ ለምለም ነው! ኢትዮጵያን ቁም ነገር የማድረግ ዓላማ ያልኩትም ለዚህ ነው። እኒህ የተባራኩ የደግነት ቅዱስ አባት ዛሬ የመንፈስ ሃዲዳቸውን እንሆ አግኝተዋል። መልካሞች እንዲህ በመልካምነት ጋለሪ እሱ በወደደው እንደ ፈቃዱ ይገናኛሉ። ይህ ትልም የሰማይ እና የምድር ንጉሥ ክርስቶስ ነው። ቅዱሱ ፓፕ ፋርንስሲኮ ጸሎተ ሃሙስን በእስር ቤት ተገኝተው እስረኞችን ምንም የሃይማኖት ክትር ሳይሰራላቸው በ2013 እግር ያጠቡ ቅዱስ ናቸው፤ ተመሰገን! ከአሜኑ ጋርም ፈጣሪ እንዲህ በማይመረመር ጥበቡ አገናኛቸው። ተመስገን! ሐሤት አድርጌያለሁኝ። ፍቅር በመደብኛ ት/ቤት መሰጠት አለበት የሚለውን ሃሳቤን በ2015 ለሳቸውም ልኬላቸው ነበር። ከውስጤ በፍጽምና የማምናቸው ናቸውና። እኒህ የካተቶሊክ ሃይማኖት እጬጌ ተፈጥሯቸው ፍቅር ነው። ዓለም እንዲዚህ ዓይነት ቅዱሳን ቢበራከቱላት አስፈሪ አትሆንም ነበር። https://www.youtube.com/watch?v=bQfOhkweNCI Pope meets with Prime Minister of Ethiopia, Abiy Ahmed https://www.youtube.com/watch?v=hGTO57afPag&t=485s Ethiopia's Prime Minister Abiy Ahmed DR የኔዎቹ ኑሩልኝ መሸቢያ ጊዜ።

ጦርነት ህግ የለውም፤ ጦርነት ርህርሄ ያልፈጠረለት የክስረት ክስተት ነው።

ምስል
ጦርነት ህግአልቦሽ ነው! „የማላዬውን ነገር አንተ አስተምረኝ፤“ መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፴፬ ቁጥር ፴፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 20.01.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። „ ግመል ሰርቆ አጎንብሶ የሚል የአቶ ዳውድ ኢብሳ “ መግለጫን አዳመጥኩት - ከልቤ ሆኜ። በኦዴፓ እና በኦነግ መሃል ያለው  ጋብቻም ይሁን ፍቺ በውነቱ ይ ኼ ነው፤ ያ ኛው ነው ለማለት ይቸግራል። ለሰሚውም ለፈራጁም ግራ ነው ።   ግራ የሆነበት መሰረታዊ ምክንያት ሌላ ምንም ነገር ሳይሆን መሰከረም 5 እና ጦሱን፤ ቡራዩንና እና ሰቀቀኑን ስላዳመጥን ከባድ ነው ይህን ይኼነው ለማለት። ማን ምን እንደሆነ አሁንም መወ ሰ ንም መወ ገ ንም ይከብዳል። ሰርገኛ ጤፍ የሆነ ነገር ነው ።  ማን የዬትኛው ድርጅት ደጋፊ እንደሆን በቅጡ አይ ታ ወቅም። የትኛው ኦዴፓ የትኛው ኦነጋውያን እንደሆነ አንጥሮ ማውጣት መቼውንም የሚቻል አይደለም። ለውጡ እና ተጠቃሚው የኦሮሞ ማህበረስብ ገና ልብ ለልብ አልተገናኙምና።    የሆነ ሆኖ ከሆነ፤ የሆነውን በሆነው ነገር በትክክል መንግሥት መግለጽ ይጠ በ ቅበታል። አድሮ የሚገኝ ነገር። የፈለገ ይሆን የሆነውን እንቅጩን መናገር የተገባ ነው። አብሶ ለመንግሥት ታማኝነት ወሳኝ ስለሆነ። አድርገዋል የሚባለው ነገር አለ። መንግሥት ደግሞ አላደረኩም እያለ ነው። ቆይቶ ዕውነቱ ከተገኜ አብሶ መንግሥት አላደርኩም ባለው ላይ አድርጎ ከተገኜ ጥሩ አይሁንም። መታመንን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሊሂቃኑ ት/ቤት ገብተው መማር ያለባቸው ይመስለኛል። ስለምን? የወል ችግራቸው ስለሆነ። በመንፈስ አቅም ማፍራት እኮ ከመታደል በላይ ነው። መታመን ከጎደለ ደግሞ ያ ሃብት

የህውሃት ለቅሶ ... ግፍ አይሆንም? ጡር ፍሩ!

ምስል
የስሞታ ክምር አይሆንም እን ደ ተለመደው የልዕልና ብርንዶ !  እንኳን ደህና መጡልኝ።  „እጆቼን ሰልፍ ያስተምራል፤  በክንዴም የናስ ቀስት እገትራለሁ።“  መዝሙረ ዳዊት ፲፯ ቁጥር ፲፬“ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19.01.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። ·        ግ ርምታ! እንዴት ሰነበታችሁልኝ የእኔ ቅኖቹ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። በዬአቅጣጫው የሚሰማ አቤቱታ አንድ አይነት ነው - እንግሊዞች ሬድሜድ እንደሚሉት። የህውሃት ማንፌስቶ ማህበረተኞች የስሞታ ክምር በተለመደው የጭካኔ ብርንዶ የሰብዕ ቁርጥ አለመቀጠል የሁሉም የወል የለቅሶ ቤት ሆኗል። ሁሉም በአንድም በሌላም ተገፋን፤ ጥፋቱ ሁሉ ተጠቃሎ በአንድ ድርጅት ላይ ሆነ፤ የ27 ዐመቱ ዕዳ በእኛ ላይ ብቻ ተጣለብን፤ እምናመለከው የህውሃት ታቦት ሰሚ  አጣ እያሉ እያጣወሩ ነው። ከ2008 ዓመተ ምህረት በፊት ወደ ነበረው መመለስ አለበት እያሉን ነው፤ ወንዝ ወደ ላይ ወይንስ ወደ ታች ይሆን የሚፈሰው?!ለመሆኑ 2010 እራሱን መልሰን ማምጣት እንችል ይሆን?  ·        ብ ቻ እኛ እንዲህ እንላለን… 27 ዓመት ሙሉ የኢትዮጵያ ህዝብ የተሸከመውን በደል ብራናውም ብዕሩም አይችለውም እና ጡሩ ፍሩ እያልን ነው። እነሱ ለ9ወራት ከጨቋኝነት፤ ከገዢነት፤ ከበላይነት መ ወገዳቸ ው የከበዳቸው 27 ዓመት ሙሉ በባይተዋርነት አሳሩን እዬበላ መወለደኑ የጠላውን 100ሚሊዮን ምንዱብ ህዝብስ ምን ይል ይሆን? ብግፍ የፈሰሰው ደም እና ዕናባስ ከቶ ተገኝቶ ቢጠዬቅ ምን ይል ይሆን?  የሚገርመው ይህ የአብይ ዘመን ባይመጣ፤ ባይሳካ ሊመጣ የሚ ችለው ን በፍጹም ሁኔታ ያሰቡት አይመስለኝም። ያልከፋው ጥርሱን