የብላቴ ሎሬት ጸጋዬ የታቦትነት ንግሥና እጬጌው ዘመን ዘውድ ደፋለት! ተመስገን!
እንኳን ደህና መጡልኝ። መሬት እራሱ ዘመንን ዳኘች፤ ለቅኔው ልዑል ዘውድ ደፋች። ተመስገን! „ ምንም እንኳን በለስም ባታፈራ፣ በወይን ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፣ የወይራ ሥራ ቢጓል እርሾችም መብልን ባይሰጡ በጎችም ከበረት ቢጠፉ ላሞችም በጋጥ ውስጥ ባይገኙ እኔ ግን በ እግዚአብሄር ደስ ይለኛል፤ በመዳህኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። “ ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯ ቁጥር ፲፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ታቦቴ! „የማይድን በሽታ ሳክም የማያድግ ችግኝ ሳርም የሰው ህይወት ስከረክም እኔ ለኔ ኖሬ አላውቅም።“ ዛሬን ዋዜማውን ሳስብ በውስጡ አንድ ትልቅ ቁመነገር ይዟል። ያ ቁምነገር የአንድ ንጹህ ፍጥረት መንፈስ ወደ ቅኖች መንፈስ ይጠጋል በዘወትርኛ። አሁን ሻማ አብርቻለሁኝ። ሌላም አቅም የለኝም እንጂ ባደረግለት በወደድኩኝ። የአቅሜን ለማድረግ ደግሞ በፍርደ ገምድሎች ህሊናዬ ታስሮ እንዲቀመጥ በግፍ የተፈረደብኝ ዜጋ ነኝ። ጭምቷ ሲዊዘርላንድ ባንድም በሌላም ለቅኔው ልዑል ለብላቴ ጸጋዬ ሥም አዲስ አይደለችም። በዛ ጥንካሬ እና ብርታት ቀጥሎ ቢሆን ጸጋዬ ራዲዮ እና ጸጋዬ ድህረ ገጽ ሲዊዝም የጸጋዬ ሚዲያም እኩል ተፎካካሪ ሆኖ መውጣ ሙሉ አቅም ነበረ