በምልስት ዕውነት እና ዘመኗ! ለጸሐፊ አቶ ወንድይራድ አሳማማው ጹሑፍ መልስ።
እንኳን ደህና መጡልኝ።
በምልስት ዕውነት እና ዘመኗ!
„እግዚአብሄርም አለ ፣--- ሰውን በመልካችን እንደ
ምሳሌያችን እንፍጠር“ ኦሪት ዘፍጥረት ፩ ቁጥር ፳፮
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
23.02.2019
ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።
መነሻ።
አብይ አህመድ – ጃዋር ሙሀመድ እና ሌንጮ ለታ – አንድም ሦስትም ናቸው!
(ወንድይራድ አስማማው) ሸር ያደረገው 658
February 22, 2019
· እፍታ።
ውዶቼ እንዴት አላችሁልኝ? ደህና ናችሁ ወይ እኔ ከባለ ዕንባማዋ ከአላዛሯ ኢትዮጵያ ናፍቆት ከእናንተ ስስት በስተቀር ደህና ነኝ - አምላኬ ክብሩ ይስፋ። ትናንት አንድ ጹሑፍ ሳተናው ላይ ተለጥፎ አነብብኩኝ። በዛው መድረክ መመሞገት ቢገባኝ ከእንግዲህ ቅኖችን ማስቸገር የተገባ ስላለሆነ በእኔ ብሎግ መጻፍ ግድ ብሎኛል።
በምን ስሌት ጠ/ሚር አብይ አህመድን ጸሐፊው ከአባ ገዳ ጃዋር መሃመድ እና ከአቶ ሌንጮ ለታ ጋር እንዳወደዱት የሚገርም ነው። ስለምን ዶር ለማን መገርሳስ ተዋቸው? ከቆረጡ ቆርጦ መጣጣፍ ነው። አባገዳ ጃዋር ሆኑ አቶ ሌንጮ ለታ ኦሮሞ ፈርስት ናቸው። በዛ ላይ ስለሰው ያላቸው አቋም የተከረኮመ ነው። ሰው ማለት ለእንሱ የኦሮሞ ደም ያለበት ብቻ ነውና።
ቀድሞ ነገር „ኢትዮጵያ አገራችን“ ብሎውም አይቀበሉም። ወዳጆቻቸውም እንደ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ዓይነቶቹ እነሱን እንዳይከፋቸው „አገሪቱ“ ነው የሚሉት።ለማማሻ ነው ያቺ መከረኛ የምትፈለገው፤ መላ የኢትዮጵያ ህዝብ ቢቃጠል፤ ቢነድ ኢትዮጵያ ምደረ በዳ ብትሆን አጀንዳቸው አይደለም ለ አቶ ሌንጮ ሆነ ለአቶ ጃዋር። በጠቅላላውም ለኦነጋውያን።
ታሪኬ፤ ትውፊቴ፤ ትሩፋቴ የሚሉትም የላቸውም በኢትዮጵያ ማህደር ውስጥ። ህመማቸው እንድተሞት የሚፈልጓት አገር ጨርሶኑ ልትሞት አለመቻሏ ነው። የእነሱ ፍልስፍና ኢትዮጵያ የሞተች ዕለት የእኛ ተንሳኤ ነው ባይ ናቸው። ይህ ደግሞ ሲሞቅ በማንኬያ ሲቀዘቅዝ በእጅ የኖሩበት የዘመኑበት፤ የሰለጠኑበት ጉዳይ ነው። የፍልስፍና ደቀ መዝሙራቸው አባ አዋጉ አቶ ተስፋዬ ናቸው ምጽዋ ተቀምጠው ማቅ ለማልበስ ኢትዮጵያን በትጋት በተቧደነ ሁኔታ እዬሠሩ ያሉበት።
እኔ አባ ገዳ ጃዋር መሃመድ አገር ሲገባ አዲሱ ቦኮሃርም ብዬ ነበር። የሆነውም ይኸው ነው። የሆነ ሆኖ ማስተካከለም፤ ማመዛዘንም ማወዳደርም የሚቻለው መወዳደር ከሚችል ጋር ነው። በደማቸው ኦሮሞ መሆናቸው፤ እንደ ሰው በሴት ማህጸን ተጸንሰው ሰው ሆነው መፈጠራቸው ጠ/ሚር አብይን ከ እነዚህ ሁሉት ወገኖች ጋር ሊያመሳስል ቢችልም ተፈጥሯቸው፤ የህሊናቸው ሥልጣኔ፤ የራዕይ አደረጃጃተቸው እና አመራራቸው፤ የማግስት ምህንድስናቸው ግን ፈጽሞ የሁለት አገር ሰዎች ናቸው። ማገናኘት ፈጽሞ አይቻልም። አፈራለሁ እንዲዚህ ላሉት ወገኖቼ እኔ በግሌ።
ስለሆነም ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ እጩነት ሲመጡ አባገዳ ጃዋር መሃመድ የሰጠውን ቃለ ምልልስ ታዳምጡ ዘንድ በትሁት መንፈስ እጋብዛለሁኝ። የትናንቱ የለገጣፎ የሞት መንደርም ላይ የተገኙት የእሱ መንፈስ ዕንብርት ጽኑ ባለርስቶች የሆኑት አቶ ንጉሡ ጥላሁን እና አቶ አዲሱ አረጋ ናቸው።
„ሕወሓት ለማ መገርሳን ለጠቅላይ ሚኒስተርነት ለምን አልፈለገችውም?
– ጀዋር መሐመድ ያብራራል | ከሳዲቅ አህመድ ጋር ተወያይቷል“
· አደብ።
ቅኖቹ አደብ ያላችሁ ስለሆነ በዚህ ብሎግ የምትሳተፉት በመጀመሪያ ይህ መንፈስ እንዴት ከጃውርውያን መንፈስ ጋር ሊጋባ እንደቻለ ህሊናችሁ ይፍረደው። ሌላው ጸሐፊውን ብዙ እማልፈርድባቸው በቅርቡ ዶር ብርሃነመስቀል አበበ የሚባሉ ሊሂቅ „አብይ የኦነግ ወራሽ ነው“ ሲሉ አንድ ውይይት ላይ ደፍረው ተናግረው „ለሳቸውም አያድርግባቸው ለእኛም አያደርግብን“ ብዬ ጽፌ ነበር።
ሙሁሩ ከሁለት ሦስት ዓመት በፊት በምን አቋም ላይ እንደነበሩም መፈተሽ ነው በምልሰት። ብቻ ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ሆኖ የአማራ ተጋድሎም ተጥቅልሎ የለውጡ ወራሽነት ለኦነግ ተስጥቷል። ባለ ሚዲያዎች እነሱው ስለሆኑ እሚሞገት ጠፍቶ ታሪክን እንዲህ ሲዘብጥ ጋዜጠኞች እራሱ ዝም ብለው ይለፍ ይሰጣሉ።
የሆነ ሆኖ በዚህ በምንሰማው ሰቆቃ ውስጥ የ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሆነ የዶር ለማ መገርሳ ድርሻ እስከምን ነው የሚለውን ለባለተደሞዎች መስጠት ነው። ሰንበታም ሱልልታም ከንቲባ የነበሩት ኢንጂነር ታከለ ኡማ ናቸው የነበሩት። እሳቸው ዛሬ አዲስ አባባ ላይ ጎዳና ተዳዳሪ ጋር ፎቶ ሲነሱ ትናንት ምን ሠርተው ነበር ማለት ይገባል? እሳቸውን ወደ ሥልጣን የመጡበት መንገድ ማስወቀስ ስለበረበት ሁላችንም ተረባርበንበታል።
በአንድ ወቅት አቶ አባ ዱላ ገመዳ ያላቸውን የማደራጀት አቅም የ ኢሳቱ ጋዜጠኛ እና ጸሐፊ አቶ ኤርምዬስ ለገሰ ገለጥ አድርጎ አስነብቦን ነበር። በአዬር መንገድ ተርሚናልም ላይ ታላቅ ሰው ሆነው አይቻቸዋለሁኝ አቶ አባ ዱላ ገመዳ ግርም ብሎኝ ጽፌበታለሁኝ። ከተሳሰትኩም እታረማለሁኝ በቦርዱም ውስጥ አንዲት ዜና ሽው ብላኛለች። ያ የአቶ አባ ገዳ የተደራጀ አርሲኛ መንፈስ ነው አቶ ንጉሱ ጥላሁን አምጥቶ ቁንጮ ያደረገው። ትግሉ ቀላል አይደለም። ህውሃት አለ፤ ለውጡን በሚደግፉ ውስጥ ለውጡን እኛ መምራት አለብን የሚሉ አሉ። መከራው ዥንጉርጉር ነው ጉዳዩ። ሰሞኑን እኮ አባ ገዳ ጃዋር መሃመድ አፋር ክልል በክብር ሲገባ ሰፊ የሆነ አቀባባል ተደርጎለት ህዝቡንም አወያይቶታል። በሀጂነት ቋንቋ። ይህ ሥልጣን እና ክታብ እንዴት ስለምን ብሎ መመርምር ይገባል? የሥልጣን መከፋፈል እንዳለ ቤተ መንግሥት ላይ ግልጽ ነው። ስንት ገዢ ስንት ጠ/ሚር ኢትዮጵያ እንዳላት እዮር ይመርምረው።
በሀምሌው ዝምታ ብዙ ነገር ተከስቷል። ከሰሜን አሜሪካ ብጽዕን ቅዱሳን ሲገቡ አድባራት በምስራቅ ኢትዮጵያ ዞን ደመራ ሆኑ ሰማዕታት ታረዱ፤ ግንቦት 7 አገር በገባ ማግስት ቡራዩ እና አዲስ አባባ ነፍስ ተገበረ፤ ትናንት ኢሳት ሲገባ ለገጣፎ በግፍ በበቀል ነደደ … ይህ ሰውኛ ነውን? ኢትዮጵያ እንድትፈርስ ከሚፈልጉ የተደራጀ የታቀደ ድርጊት ነው - እኔን የሚገባኝ ይሄው ነው። እምጠብቀው በቃኝ ስልጣኔን ተረከቡ ቀን ብቻ ነው። ይህ ደግሞ መጠበቅ ነው።
እኔ እምለው ዶር ለማ መገርሳ ይሁን ዶር አብይ አህመድ ሚናቸውን ቢለዩ እና ያቃታቸውን ነገር ለህዝብ የመንፈስ ገብያ ቢያቀርቡ ምልካም ነው። የኦነግ ሠራዊት ገባ ሲባል ከነትጥቁ ነው እኔ ያዬሁት። የፈለገ ጥፋት ይጥፋ ኦሮሞ ከህግ በላይ ከሆነ ለይቶለት ቁርጡ ይታወቅ።
ያ ሁሉ ባንክ ተዘርፎ አቀባባሉ የጉድ ነበር። የጉሌለው መንግሥትም ነኪ የለውም። ሚዲያውም እንዲሁ ሲያጫርስ ውሎ እያደረ ጎሽ እዬተባለለት ነው። ይህም ብቻ አይደለም የትጥቅ ትግሎ አውራው መሪ አንድ እራሴንም ብቀር ሲሉ ለቢቢሲ አማርኛው ክፍል ቃላቸውን ሰጥተዋል። ድራማው ይኸው ነው። እንዳይከሰሰ፤ በወንጀል እንዳይጠዬቅ የሚፈልግ ነፍስ በቁልምጥ ላይ ሆኖ ያሻውን እንዳሻው የጠላት አገርን እንዲያደርግ ሌላ ባለሥልጣን እንዳለ ቁልጭ ብሎ ያሳያል።
ችግሩ እኛ የምንስማማበት አጀንዳ የለንም። ቁጭ ብሎ መንፈስ ቤት ሲናድ አዬ እያሉ ተራን መጠበቅ ብቻ ነው። እነ ጠ/ሚር አብይ አህመድም ለውጥ አጨናጋፊ ከማለት ውጪ ፍርጥ አድርገው መናገርም እርምጃ መውሰድም ታግተዋል። እገታውን ለ ዓለም ማህበረሰብ ቢያስውቁ መፍትሄ ይገኝለትም ነበር። እኔ እማስበው ካለ ቁጠባ አገር የገባው ታጋይ ሁሉ መጨረሻው ይናፍቀኛል። ቀጣዩ ፈንጂ አለና …
የሆነ ሆኖ ቀደም ባለው ጊዜ ዶር አብይ አህመድ በነበራቸው አገራዊ እራይ እና ሰውኛ ተፈጥሮ እኔ ሳልሆን የተናገሩትን ውዶቼ የተወሰኑት ስለለጠፍኩኝ ቃል በቃል መዝኑት። እውን ይህ መንፈስ ከ አባ ገዳ ጃዋር መሃመድ እና ከአቶ ሌንጮ ለታ ጋር ካመሳሰለ።
በሙሉ ከሥር ያሉት ጥቅሶች ዶር አብይ አህመድ ጠ/ሚር ከመሆናቸው በፊት የተናገሩት እና ተፈጥሯቸውን ቁልጭ አድርጎ ነው የሚያሳዬው። በዚህ 50 ዓመት በሴራ ፖለቲካ በዳከራ አርንቋ እንዳ አንንያን እንደ አዛርያን እንደ ሚሳዬል ይወጣው ተብለው እሳት ውስጥ የተጣሉ ነፍስ ናቸው። ያማ ባይሆን ኑሮ „ለተባረከች አገር የተባረከ ትውልድ“ መንፈስ ይዞ መንፈሳቸው ባልተነሳ ነበር። እጅግ ሰፊ ራዕይ ነበራቸው … ቀድሞ ነገር በግራ በቀኝ እዬተዋከቡ ሃሳባቸው ምን ተነክቶ ነበር። ያው ባንታደል ነው።
የጠ/ሚር አብይ አህመድ የተፈጠሩበት ዕውነት በዚህ ውስጥ አለ ብዬ አምናለሁ፤
· „ ሰው ሲፈጠር ሰው ነው። ዕጹብ ድንቅ ፍጡር ነው። ማሰብ ያለበት በዚያው ልክ መጠን ነው። መመለስ ያለበት በዛው ልኩ ነው። ማንነቱን ያጣ ዕለት ብዙ ክፉ ነገር ይሸከማል። ሁለት ሰው ሁነው እዬተጓዙ አንደኛው በጎርፍ ውስጥ ጊንጥ ያያል። ጊንጥ ስትናደፍ በጣም የምታም ነገር ነች። እና ጎርፍ ሊወስዳት ስትሰቃይ ያያል፤ እጁን ዘርግቶ ሊያድናት ሲሞክር ነደፈችው። በጣም ያማል፤ ታውቃላችሁ። አመመው፤ ትንሽ ቆይቶ ሲያያት በጣም ትሰቃያለች፤ አሁንም ድጋሚ ሲዘረጋ ነደፈችው። እና ጓደኛው አብሮት የነበረው „አንተ ሞኝ አልገባህም እሷ ልትገድልህ እዬሞከረች ነው። አንተ ልታድናት ራስህን ታስጠቃለህ ብሎ ነቀፈው።“ ሞኝ ያልገባህ አለው ያኛው ሰውዬ፤ ግን ሸሚዙን ቀዶ ጠቅልሎ ሦስተኛውን ጊዜ ሲሞክራት አዳነት። እና ለጓደኛው አንተ ብዙን ጊዜ ጊንጦች ስታይ ጊንጦችን ትሆናለህ አለው። እኔ ሰው ነኝ፤ የተፈጠርኩት ለማዳን፤ ለማሻገር ለማብቃት፤ ለመርዳት ነው። ጊንጥ ደግሞ የተፈጠረችው ጥቃት የተሰነዘረ ስለመሰላት ለመንደፍ ነው። እሷም ስራዋን ነው የሰራቸው። እኔም ሥራዬን ነው የሰራሁት። ማዳን ሥራዬ ስለሆነ። ለምንድን ነው አንተ እኔን ታጥቀህ ጊንጥ እንድሆን እምትመክረኝ አለው። የእኔ ተግባር ማዳን ሆኖ ሳለ ስትሞት ዝም እንድል ለምን አለው።“
· „ክፋት ስታዩ ያን ለማድረግ የምትሞክሩ ከሆነ ተሸንፋችኋዋል ማለት ነው። የሰው ልጅ በጎን ለማወቅ ያለው ጥረቱ ተሽንፏል።“
· „ፓሪስን በንባብ ያስተዋወቀኝን ሰው ከደጅ አገኘሁት፤ በእናንተ መካከል ሆኖ ሃሳብ መሰንዘር ቀላል አይደለም፤ ብዕርና እስክርቢቶ እንድናገናኝ ያበረታታችሁን፤ ከማንበብ ውስጥ ዕውቀት፤ ጥበብ እንደሚፈልቅ መንገድ ያሳኛችሁን ታላላቅ ሰዎች አላችሁ።“
· „ሰው ተፈጥሮን ማንበብ ካልቻለ፤ ንባቡን ማጋራት ካልቻለ፤
ህይወት መቀጠል አይቻለውም“
· „ … በኦርቶዶክስ ሃይማኖት አባቶች ጥዋት … ጥዋት እዬተነሱ ዳዊት መድገም፤ የተለመደ ባህል ነበር። ወንጌልን ለማሰራጨት ብቻ ሳይሆን፤ እምነትን ለማሰራጨት ብቻ ሳይሆን፤ ጥዋት ተነስቶ ቀድሞ ዳዊት መድገም ባህል ነበር። ለአሁኖቹ አገልጋዮች አንድዛ መሆን እርግጠኛ አይደለሁም። በልጅነት ግን ይህን አስተውል ነበር። በእስልምና እምነትም ይህ ባህል ነበር። ጥዋት …ጥዋት ተነስቶ ቁራዕን ይቀራል።“
· „በአሁኑ ጊዜ ዕውቀት ደርጅቶ የሚቀርብበት አንባቢ እያገኘ ስላልሆነ፤ በከፍተኛ ደረጃ የሃብት እጦት ብቻ ሳይሆን የጭንቅላት ድርቀትም እያገጠመን ነው“
· „ ጭንቅላት ትልቁን ኢነርጂ ከምንመገበው 25% ገደማ ኦክስጂን የሚወስደው ጭንቅላት ነው። የምንመገበው ምግብ አብዛኛው የሚሄደው ወደ ጭንቅላታችን ነው። የእግራችነን በብዙ ዕጥፍ ጉልበት የሚወስደው ጭንቅላት የሚመግበው መጋቢ ስላጣ ባዶ ሆኖ መኖር የግድ ሆኖታል ኢትዮጵያ ውስጥ።“
· „ቅድም ኮነሬል እንዳሉት የህንዱ ታሪክ ዛሬ ጁቡቲ አሁን 45 ዲግሪ ሴልሸዬስ ነው ሙቀቱ። ናይሮቢ ብትሄዱ በጣም ይሞቃል። ካርቱም ይሞቃል። ተፈጥሮ እንደዚህ አድሎ የሰጠንን ሐገር ተገንዝበን ተጠቅመን፤ ለመለወጥ ያልቻልነበት ዋንኛ ሚስጢር ጥበብን የመፈለግ፤ ጥበብ Wisdom የመፈለግ፤ ዕወቀትን የመፈለግ ዝንባሌኛችን ፍራንክ ከመለቃቀም ጋር ሲነጻጸር፤ በእጅጉ የተለያዬ በመሆኑ ነው“
· „እንደ ሐገር ዕውቀት የማንሻ ከሆነ፤ እንደ ሐገር ዕውቀትን የማንፈልግ ከሆነ፤ ያንንም ኢንከሬጄ እማናደርግ ከሆነ፤ ሄዶ ሄዶ ይሄ ጥቁር ጠበሳ የሆነው ታሪካችን፤ ተከታይ መሆኑ አይቀሬ ነው“
· „ይህን ችግር ለማቅረፍ ደራስያን፤ በሰላ ብዕራችሁ ትውልድን Generationማስተማር፤ የማያውቁ ግን የሚያውቁ ሰዎች ካሉ እነሱንም መሞገት፤ የእናንተ ትልቅ ሃላፊነት መስሎ ይሰማኛል።“
· „ በእናንተ ብዕር ውስጥ ፖለቲካ ሊዳሰስ ይገባል፤ ሃይማኖት ሊዳሰስ ይገባዋል፤ ግብረ ገብንት ሊዳስስ ይገባዋል። በዚህ ሂደት ውስጥ ትውልድ የማዳን፤ እና ይህችን ሐገር የማስቀጠል ሃላፊነት ከማንም በላይ በሚጽፉ፤ ከምንም በላይ ተፈጥሮን ማዬት ማስተዋል፤ ጥበብን ማዬት በሚችሉ ሰዎች፤ ሃላፊነት የወደቀ መሆኑን እንድትገነዘቡ፤ ማሳስብ እፈልጋለሁ“
· „ኢትዮጵያ ውስጥ ወጣቶች፤ ለማንበብ፤ ለማወቅ የሚያደርጉት ጥረት የሳሳበት አንዱ ምክንያት branding ነው። ጸሑፍ መጻፍ ደራስያን አሉ። ሃሳብ አፍላቂዎች አሉ። የፈለቀውን ሃሳብ ከወረቀት ጋር የሚያዋህዱ ሰዎች አሉ። ድርስት ሆኖ ከወጣ በኋዋላ የሚያሳትሙ አሉ። የሚያከፋፍሉ አሉ። መልሶም የሚያነቡ አሉ። ይህ ሰንሰለት ነው። ከዚህ ውስጥ አንዱ ሲበጠስ፤ ጠቅላላ ኢንደስትሪው የሚወድቀው። ይህ ደግሞ እንዳይሆን ቅድም እንዳልኩት አንዱ ደግሞ የbranding ችግር ነው።“
· „ጸሐፊዎች አንዱ ማክበሪያ መንግዳችሁ ጸሐፊዎችን ማክብር ነው። የወጣውን ጸሁፍ ራሽናል ሆኖ ክሪቲሳያዝድ ማድረግ የሙያ ግዴታ ነው። ግን መጸሐፉን በራሱ እዬደነቅን መሆን አለበት። መጸሐፍ የሚደነቅ ነገር መሆኑን እዬተናገርን፤ ማንበብ የሚያስወድስ መሆኑን እዬተናገርን፤ እዛ ውስጥ ደግሞ የሚታዩ ስንክሳሮችን፤ ነቅሶ ማውጣት እና ማረም ተገቢ ነው። ነገር ግን በጋዜጦቻችን የሚታዬው ጸሐፍት ሲሞጋገሱ፤ ሲወዳደሱ ሳይሆን፤ ሲወቃቀሱ ሲረጋገሙ ነው። ነገቲብ ኢንርጂ ደግሞ በራሱ የመደመር እና የማጥፋት ሃይል አለው። ስለምንዘራው ነገር፤ በቃላችን ስለምንናገረው ነገር በጣም መጠንቀቅ ያስፈልጋል። እሱን ሰለምናጭድ መጨረሻ ላይ። በቅርቡ በተረጋገጠው የሳይንስ ውጤት የሚያመለክተው ውሃ በተደጋጋሚ ረግመው በምርምር የተረጋገጠ ነው፤ በመጨረሻ በጣም የተራራቅ የሚያስጠላ ሞሎኪውል ሲሆን በአንጻሩ የተመረቀ ወይንም የተቀደሰ/ ብለስ የተደረገ ውሃ ጠበል እንደሚባለው ሞለኪሉ ጥግጊቱ የሚያምርና የሚታይ ሆኗል። ሰው 75% ውሃ ነው። 6% አፈር ነው። 4% እሳት ነው፤ የተቀረው አዬር ነው። በውስጣችን ያለው አብዛኛው ፐርስንት ውሃ በተደጋጋሚ ከምነዘራው ክፉ ቃል የተነሳ ሞለኪሉ ካንሰር፤ ሞለኪሉ ጨጓራ፤ ሞለኪሉ ስኳር እዬሆነ ነው።“
· „ 4% ፋዬር /እሳት፤ ገበርን እያደረገን፤ ትውልድ የማይከባበርበት፤ እማይዋደድበት፤ ነገን የማያይበት፤ ሀገር እዬሆነ ነው። ባህል፤ ወጋችን፤ ባልዩችን እዬጠፋ ነው። ይህን የማስቀጠል ግዴታ አለብን። ይህ መሆን ስላለበት ነው ዛሬ፤ በጣም አጣብቂኝ የሆነ ጊዜ ቢሆንም ይህንን ዕድል፤ ላለማጥፋት በእናንተ መካከል፤ ልገኝ የወሰንኩት።“
· „ከዚህ ውጪ ደራስያን ብዙ ጊዜያቸው የመከበር፤ የመደመጥ ዕድላቸው በጣም አናሳ ነው፤ በቅርቡ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት መጥተው በነበረ ጊዜ ንግግር ሲያደርጉ በአፍሪካ ማዲባ ብለው ፕ/ ማንዴላን ያነሱ ነበር፤ ሲያነሱ ስለ ትግላቸው፤ ስለፖለቲካ አመራራቸው አላነሱም፤ ማዲባ እንደዚህ ብሏል ነው ያሉት።“ „ጹሑፋቸውን ነው ሜንሽን ያደረጉት፤ ኦባማ ጥቁር ከለርም ስለላቸው ብዙም አልገረመኝ ነበር፤ በቅርቡ የኮሪያ ፕሬዚዳንት ፓርክ ሲመጡ ባደረጉት ንግግር መልሰው ማዲባን ኮት አድርገዋል። ኮት ሲያደርጓቸው የእሳቸውን የአስተዳደር ሥርዓት አንዲህና አንዲያ ነው አይደለም ያሉት። በመጸሐፉ እንዲህ ብሏል ነው ያሉት። ስለዚህ ዛሬ በቂ ክፍያ ላይከፈላችሁ ይችላል፤ ላትወደሱ ትችላላችሁ፤ ሳልጠራጠር የምናገረው ግን ሁሌም ሊያስወሳ የሚችል ሥራ ጥላችሁ ታልፋላችሁ።“
· „ይሄ ብቻ አይደለም የፓርክ ንግግር፤ ሎሬት ጸጋዬንም አስታውሷል። ሎሬት ጸጋዬን ደፍረን መናገር የምንችል ኢትዮጵውያን ስንቶቻችን እንደሆን አላወቅም? ከእናንተ ማህበር ውጪ ስንወጣ እሳቸው ሲናገሩት ስሰማ ግን በጣም ነው ያስደመመኝ። ለካስ የኛው ሎሬት በእኛ በቂ ክብርና ውዳሴ ባያገኙም ለዓለም ያተረፉት፤ ያፈለቁት ዕውቀት ነበረ የሚል መልዕክት አስተላልፎልኛል“
· „ይህ ግን በምናብ ተጉዞ ደመናን አልፎ አዳዲስ ያልተዳሰሱ እውቀቶችን፤ ማፈለቅ ካልቻለ፤ ኢማጅነሽን ፓዎራችን ሳንገታ መጓዝ ካልቻለን በሀገር እድገት ውስጥ በሀገር ኢኮኖሚ ውስጥ ፊክሽን ብቻውን በቂ አይደለም። Wright brothers አዬር ፈጠሩ ሲባል ሰምቻለሁ። ግን አልፈጠሩም። Wright brothersሳይሆኑ ከ1000 ዓመት በፊት የግሪክ ፈላስፎች አዬርን ከነዲዛይኑ ፈጥረዋል። ግን አልበሩበትም። ስዕሉ ዛሬም አለ። እነሱ ኢማጂን ያደረጉትን፤ በዋኋላ ላይ Wright brothers ሪያላይዝድ አድርገውታል። ኢማጅኔሽንና ሪአላይዜሽን የማይነጣጠሉ፤ ወንድማማች ናቸው። ኢማጅን ሳይደረግ ሪያላይዝድ ስለማይደረግ። በግሪክ ፍልስፍና ዘመን ውስጥከ ከዖሽን በታች ሃብት ሊገኝ እንደሚችል ፈላስፋዎች ኢማጅን አድርገዋል። ኦሽን በግሪክ ትልቁ ነዳጅ፤ ምግብ፤ መዳህኒት ያለበት መሆኑ ተረጋግጧል። በብራዚል፣ በህንድ፤ አሜሪካና ኩባም፤ ካስታረቀቸው አንዱ ድልድይ በኦሽን ግራፊክ የተደረገው ጥናት የጋራ የምርምር ሥራ ነው። ይሄ ኢማጅን የተደረገው አንግዲህ ከሺህ ዓመት በፊት ነው። ስለዚህ ዛሬ ኢማጅን እምታደርጉት ነገር፤ በሆነ ጊዜ ትውልድ ወደ ተግባር ቀይሮ ከድህንት፤ ከችግር ብዛት ሊላቀቅ የሚችልበትን መሆኑን ማሰብ ያስፈልጋል። ከዚህ አንጻር ሁለት ሰዎች ማንሳት፤ ማስታወስ ጥሩ ነው የሚሆነው፤ አንደኛው „የይሁን ዓለም“ ደራሲ ይኑሩ አይኑሩ አላውቅም ከ25 ዓመት በፊት በአቶ ደጉ በሚባሉ ሰው ተደርሷል። በመቸቱ በሳተሳሰቡ፤ በቀረጻቸው ካራክተሮች ኢማጅነሪ የሆነ የያኔን ወይንም የዛሬን በሙሉ የማያሳይ ወደፊት የሚያሳይ ጹሑፍ ነበር።“
· „እንደኒዚህ አይነቶችን የማይጨበጡ የማይዳሰሱ የኢማጅኔሽን ሃሳቦችን ማቆዬት ይገባል፤ እኛ ዛሬ ባንረዳው፤ ባንጠቀምበትም ትውልድ ነገ ወስዶ ችግር የሚፈታበትንና ካለበት ሁኔታ የሚሸጋግርበት ስለሆነ መጸሐፍ፤ ብሄርን ከብሄር የሚያገናኝ ድልድይ ነው፤ ባህል ከባህል የሚያገናኝ የሚያሰተሳስር ድልድይ ነው“
· „ መጸሐፍት ሰውና ሰው እንዲከባብር እንዲዋደድ የሚያደርገ ትልቅ ሃብት ነው። ሃብት ይዘን ደሃ ተብለን እንዳንቀር፤ ብዕሮቻችሁ ስለተው ባህላችነን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ፤ አንድነታችነን የሚያጠናክሩ፤ ሰላማችን የሚያጎሉ ከሆነ እኔ ካለጥርጥር ላረጋግጥላችሁ የምፈልገው ኢትዮጵያ ትልቅ ሐገር ናት! ምንም ጥርጥር የለውም ቅድም ከተባለው ሳይሆን ከማንም የተሻለ ጭንቅላት፤ ከማንም የተሻለ የማደረግ አቅም፤ እኛ ውስጥ አለ። እኛ ያጣነው ዊዝድም ነው። ጥበብን ፍለጋ ነው። ጥበብን የፈለግ እንደሆነ። ለዛም እምንደመር ከሆነ፤ ካለምንም ጥርጥር ቅድም እምናውሳቸው ጥቋቁር ታሪኮች በቅርቡ ይፋቃል የሚል ሙሉ ዕምነት አለኝ።“
· „ሳይንስና ቴክኖሎጂ በዚህ ዓመት፤ ከመንግሥት በጀት ውስጥ ፈንድ በማፈላለግ ስድስት ላይብራሪዎች፤ በክልል እያደራጀ ነው ያለው። ከላይብራሪ ጋር ተያይዞ እኛ ያለን ፍልስፍና ኦፕን ላይብራሪ የሚባል ነው፤ በቅርቡ ቢሯችን ለመጎብኘት ስለሚፈቀድ ትጎበኙን አላችሁ“
· „ …. ጽንሰ ሃሳቡ የሚነሳው መጸሐፍ መስረቅ፤ እና ለተለያዬ ነገር ቀዶ መጠቀም፤ በዬትኛውም ዓለም ነበር። እኛም ጋ ይኖራል። ግን ሳም ሃው ያነን ሪስክ መሸከም መቻል አለብን። የኋዋላ ኋዋላ ቀዶ የጠቀለለበት ሰው ሳይቀር ገዝቶ ዶኔት ማድረግ ይጀምራል። ይህ እንዲሆን ደግሞ መጀመሪያ አብሌብል ማድረግ ያስፈልጋል። እኛ ቆልፈን መጸሐፍን ካልፈረምክ፤ መታወቂያ ካለመጣህ እያልን እያቀብን ሳይሆን አንብበው ስትፈልግም ስረቀው ችግር የለውም በኋዋላ መልስህ ዶኔታ ታደርገዋለህ፤ ምክንያቱም መጸሐፍ ሰርቆ ማስቀመጥ ቦታ ማጠበብ ነው ዛሬ፤ …. ዋና ዓላማው የዕውቀት ትራንስፈር ማድረግ ነው። እዛ ማህል የሚገኝ ንግድ አይደለም“
· „ሰው ከሌለው በደመቀው ከተማ በቀትር ብትጓዝ ይጨለምሃል፤ ትፈራልህ“
· „ነገ ሰዎች አጀንዳ ቀርጸው አስቀምጠው ልትዋጉበት የሚገባ ሜዳ ይሄ ነው ሲሉን፤ ከዚህ አልፈን ወጥተን መታሰብ ያለበትን፤ እንዲህ ዓይነቶችን ሰዎች ለአንተ እንደፈለጉ ሲናገሩ፤ ሌላው የመናገር መብት እንዳለው ማወቅ አለባቸው። እኔም መናገር እችላለሁ። አንተ ግን ይህን የማትፈቅድ ከሆነ ይህ ጸረ ዴሞክራሲ ነው። የትኛውም ሃሳብ ይውጣ፤ ይነገር፤ ይጻፍ፤ ነገር ግን ይህን ሃሳብ የሚቀረን ካለ ሌልኛውንም ለማድመጥ ዝግጁ ልንሆን ይገባል።“
· „መማር ከልብ ለልብ ግንኙነት ውጪ የሚሆን ስላልሆነ፤ ከሌብነት ጋርም ክፉ ሥር መሆኑን ማምን ያስፈልጋል - ሌብነት። በአንታይ ኮራብሽን ንቅናቄ ብቻ ሳይሆን፤ ክፉ ሥር ነው። ለምንድነው ክፉ ሥር የሚሆነው? ብዙ ለመስረቅ የሚሞክሩ ጓደኞቻችን ያዬነው ነገር፤ የመጀመሪያ ጥፋት ኢትዮጵያ ላይ አይደለም። ውሸት ነው እናንተ ተሰርቀናል ብላችሁ እንዳታስቡ። አልተሰረቃችሁም። በጣም ምስኪን ሰው ዲግሪ፤ ማስተርስ ከያዘ በኋላ ስልጣን ይይዝና፤ 11 ሰዓት 30 ሲሄድ ፍርፍር ሰርታ፤ ቡና አፍልታ፤ ውሃ አዘጋጅታ በጣም የምትቀበለው ሚስት ነበረችው። ልክ ስልጣን ሲይዝ በዚህኛው ኪሱ 10 ሺህ፤ በዚህኛው ኪሱ ደግሞ 29 ሺህ ያለውን፤ ማን እንደ ወሰደው አያውቅም። ከዬት እንደወደቀም አያውቅም። እሱ ሦስት ሰዓት በኮርቫ ሲገባ፤ እሷ ደግሞ በማርቸዲዝ „ዳዲ አይ ዊል ካም ሱን ብላ“ ቦሌ። እምትመለሰው አፍተር ሚድ ናይት፤ ወይንም ሲነጋጋ። ሰውዬው መጀመሪያ የሚያፈርሰው አኒስቲቲሹኑን ቤቱን ነው። ሰርቆ ያነን ክፉ ነገር ቤት ይዞ ይሄዳል። ምርጥ ሚስቱን ያጣል። ምርጥ ልጆቹን ያጣል። ስለዚህ ክፉ ሥር ነው የሚያጠፋው አንተን ነው። ሲደመር ቆይቶ ሀገር ሊበድል ይችላል። መጀመሪያ ግን የመትከስረው አንተ ነህ። ኢህን ማሳዬት ያስፈልጋል።“
· „ወጣቱን በሁለት ጎራ ለይተን ልናዬው እንችላለን። በአንድ በኩል በጣም ፈጣን ጭንቅላት ያለው። ተሎ መማር የሚችል። በምክንያት ከነገርከው ማድመጥ ማመን፤ መስራት የሚችል ሃይል ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ግልፍተኛ ነው። ስሜታዊ ነው። ይህነን እንዴት አስታርቀን ለምንፈልገው ዓላማ እናውላለን ነው። አንደኛው የግልፍተኛ ወይንም የኢሞሽናል ሰዎችን ማስታገሻ መንገድ የሚናገሩበት፤ የሚተነፍሱበት፤ አውድ ማስፋት ነው። በሶሻል ሚዲያ ይሁን በኮንቤንሽናል ሚዲያም ይሁን። ሃሳባቸውን እዬሰጡ፤ ሃሳባቸው ደግሞ እዬተገራ፤ እዬታረመ ሲሄድ ሰዎቹ ሞር ሻርፕ እዬሆኑ፤ እያደጉ፤ እየበቀሉ ይሄዳሉ። ይሄ በአንድ ወቅት ውስጥ የሚሠራ ሥራ አይደለም። በት/ቤት፤ በሃይማኖት ተቋማት፤ በወላጆች፤ በተለያዩ ሶሻል ፋብሪክስ፤ እና እንደዚሁም በሚዲያው ጭምር፤ በሚሰራ ሥራ ነው ትውልድ የሚቀረጽበት።“
·
„አሁን ባለው ሁኔታ ሰፋፊ ውይይት ከወጣቶች ጋር እያደረግን ነው። ወጣቶች ብናደምጣቸው ሃሳብ እንዳላቸው። ብናደምጣቸው አገር ገንቢ መሆናቸውን፤ ሲነገራቸው የሚሰሙ መሆናቸውን፤ ለማዬት ችለናል። በኢትዮጵያ ህዝብ አብዛኛው ወጣት ነው። ኦሮምያን እንደምሳሌ የወሰድን እንደሆን ከ47% በላይ ኦሮሞ ከ15 ዓመት በታች ነው። ይሄንን እያደገ ያለ ኢመርጂንግ ሃይል፤ የዘነጋ ኢኮኖሚ፤ የዘነጋ ፖለቲካ መሻገር አይችልም። „
„አሁን ባለው ሁኔታ ሰፋፊ ውይይት ከወጣቶች ጋር እያደረግን ነው። ወጣቶች ብናደምጣቸው ሃሳብ እንዳላቸው። ብናደምጣቸው አገር ገንቢ መሆናቸውን፤ ሲነገራቸው የሚሰሙ መሆናቸውን፤ ለማዬት ችለናል። በኢትዮጵያ ህዝብ አብዛኛው ወጣት ነው። ኦሮምያን እንደምሳሌ የወሰድን እንደሆን ከ47% በላይ ኦሮሞ ከ15 ዓመት በታች ነው። ይሄንን እያደገ ያለ ኢመርጂንግ ሃይል፤ የዘነጋ ኢኮኖሚ፤ የዘነጋ ፖለቲካ መሻገር አይችልም። „
· „ ዛሬ ታምራላችሁ“
· „ወደ ሐረርጌ የመጣነው በአሁኑ ጊዜ ዓለም እያጣች ያለችውን ፍቅር እናንተ ዘንድ በብዛት እያመረታችሁ ስለሆነ እንዳታክፈሉን ብለን ነው። ምክንያቱም ባሁኑ ጊዜ ፍቅር ማጣት የአገር ችግር ስለሆነ። በአለም ሆነ በአገራችን ችግር እንዲፈጠር ምክንያት እዬሆነ ያለ የእርስ በርስ ፍቅር ማጣት በሐረርጌዎች ዘንድ በብዛት እያመረተ ነው። ወደ እኛ እንድታስላልፉልን፤ ኤክስፖርት እንደታደርጉልን እንፈልጋለን። ምክንያቱም እዬበላን ተርበናል። እዬጠጣን ተጠምተናል። ያለውን ፍቅር በመካፈል ሰላምና ፍቅራችን በዝቶልን መኖር እንፈልጋለን።“
· „ካለንደር ስል በሥነ ፈለክ ሳይንስ Astronomical Science በቦረና እና በወላድባ አካባቢ የተገኙት መረጃዎች አንደሚያመለክቱት፤ ኢትዮጵያም ከራሽያም፤ ከአሜሪካንም በፊት በስፔስ ሳይንስ የጠለቀ እውቀት ያላቸው ወላጆች የተሻለ ዕውቀት እንደነበራቸው የሚያመላክቱ መረጃዎች እዬተገኙ ነው። ለምሳሌ በቦረና ተማርን የምትሉ ሰዎች የውልደት ቀናችሁን የምታከብሩት ተሳስታችኋዋል፤ ግንቦት ስምንት ዛሬ እና ግንቦት ስምነት በሚቀጥለው ዓመት የተለያዩ ስታሮች፣ ጋላክሲዎች፣ ኮኮቦች የሚያርፉበት ስለሆነ በፍጹም ቀኑ አንድ አይደለም። የሚል ተማርን የምንል ሰዎችን የሞሞግት /ቻሌንጅ/ የሚያደርግ ሃሳብ ያነሳሉ።“
· „ኢትዮጵውያን ሃሳባቸውን ለመጻፍ፤ ለማከፈል ለመናገር የሚቆጠቡ ህዝቦች ስለሆኑ፤ ለመጻፍ የሚደፍር ማንኛውም ሰው ሲኖር ሊበረታታ ይገባዋል። መጻፉ በራሱ ምስጋና የሚገባው መሆኑን ከአመን በኋላ፤ አፃፃፍ ስርአቱ፤ የሚጠቀምበት ቋንቋ፤ ከመደመር ይለቅ በታኝ መሆኑ፤ እነዚህ በሂደት እያረምን መሄድ አለብን። አሁን ያለው ትሬንድ የሚጽፉ ሰዎችን ስለ እኛ ክፉ ነገር ስለጻፉ ብቻ መጥላት ሰይሆን መጻፋቸው መልካም መሆኑን ካዬን በኋላ መግራት ይኖርብናል።“
· „ ሁለተኛው እናንተን ባለ ዕዳ የማደርግበት ቲንኪንግ ነው። እዚህ ሀገር ትልቁ በሽታ ቲንኪንግ ስለሆነ። ከዛም እንዳነሳሁት ድርቀታችን ልክ የለውም፤ ከቲንኪንግ ፕርስፔክቲንግ አንጻር። ለምሳሌ ቀላሉን ነገር ለማንሳት ሳይንቲፊካሊ የሚታወቅ ነው።ኮራብሽን የሚባል ችግር ኢትዮጵያ ውስጥ አለ። ሁላችሁም ታውቃላችሁ፤ ኮራብትድ የሆነው መንግስት፤ ኮራብትድ የሆነ ጋዜጠኛ ፤ ኮራብትድ የሆነ ታክሲ ሹፌር፤ ኮራብትድ የሆነ የቀበሌ ሊቀምንበር፤ ኮራብትድ የሆነ መምህር፤ ኮራብትድ የሆነ ተማሪ፤ ኮራብትድ የሆነ ሶስይቲ ነው እዬተፈጠረ ያለው። እከሌ እና እከሌ የለውም። ለምሳሌ ከዚህ ብሄራዊ አደባባይ ጋ 100 ሰው መኪና ይዞ 10 ሚ/ር 10 ዋና ዴያሪክተር 10 ታክሲ ሹፌር ቢመጡ ከመቶው ውስጥ በዬትኛው ደረጃ ቢሆኑ ትራፊክ ከሌለ 5ሰው እንኳን ላይትን አይቶ አይቆምም። ጥሶ ነው የሚሄደው። ኮራብትድ ነው ሰዉ ጭንቅላቱ። ብታምኑም ባታምኑም፤ ጓደኛ ልጅ ዩንቨርስቲ ውስጥ ኪኤጂ ተሰርቆበት አልቅሶ መጥቶ መምህሩን፤ ስናንገረው ያገኘነው እንትን በጣም የሚያሳዝን ነው። የእንትና ዘር የእንትና ዘር ስለሆነ ኪኤጂ ላይ ማርክ ቀንሶ አንዷን አንደኛ አንደኛውን ሦስተኛ አደረገ። ምንም ፋይዳ ሌለው ነገር። ጭንቅላት ለማይረባ ነገር ይሠራል።“
· „በማንም ዓይን ቢታይ እና ቢፈተሽ ልብን ሞልቶ የሚያናግር ጥንታዊ ሥልጣኔና እና ዕልፍ ዘመናትን ያስቆጠረ ታሪክ የተላበሰች ሀገር ባለቤቶች ስለመሆናችን ኢትዮጵውያን መስካሪያን አያሻንም። እናውቃለን። ያውቃሉ። በዚያው መጠን እና ልክ ዛሬ የድሃ ድሃ መሆናችን አንገታችን ያስደፋን የታሪክ ጠበሳ መሆኑ የሚጠፋው ይኖራል ተብሎ አይታሰብም። ያን መሰል የታሪክ እና የሥልጣኔ ታሪክ የተላበሰች ሀገር በምን ማዕታዊ ክብሯ ተገፎ፤ እናዋ ደብዝዞ፤ አሁን ለምንገኝበት የኋዋላ ቀርነት ውርስ እና ቅርስ ተዳረገች የሚለው ጥያቄ እንደ ትናቱ ሁሉ በብዞዎች አንጎል ይመላለሳል። ይጠዬቃል። መልስ ይሰጣል። መልሱ እንደ መላሹ የተለያዬ ቢሆንም፤ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘው ማዕታዊ መቅሰፍት፤ ከተከተልነው፤ ከተሳሳተ የፖሊቲካ እና የኢኮኖሚ ብርቱ ቁርኝት እንዳለው በዘመን ሂደት መሻሸል ያላሳዬው መንግሥታዊ አስተዳደር የድሃ ድሃ መሆናችን ምስክር ሊሆን ይችላል። „
· „ዋናው ዕይታችን ህዝብ መሆን አለበት። እንደዚህ የሚያምር መንገድ፤ እንዲሁም የሚያምር ሥነ - ህንጻ ሰው ከሌለበት ሰው መሆን አይችልም። ዲፍኒሽኑን በርከት ያሉ ሰዎች በቋሚነት ቤት ያደረጉበት ነው እንጂ፤ ከተማ በጣም የሚያማሩ ህንጻ ያለበት እና ሰፋፊ መንገድ ያለበት አይደለም። ከተማ ይህ ነገር ያምራል፤ ሰው ኬለበት ግን ወና ነው። በጠራራ ጸሐይ እዚህ ውስጥ መሄድ ያስፈራል።“
„አንድ ሰው ብቻውን በቀን ብርሃን መሄድ አይችልም። ሰው ከሌለ ውበት መሆኑ ቀርቶ የፍርሃት ምንጭ መሆን ይችላል። ፍርሃት ደግሞ ያለው ጨለማ ውስጥ ነው። በብርሃን ውስጥ ፍርሃት የሚወጣው ብርሃን መሆን ሲሳነው ነው ማለት ነው። ስለዚህ ዕይታችን ሰው ላይ መሆን አለበት።“
· „ኦህዲድ በእድገት ውስጥ ያለ ድርጅት ነው። በርካታ ቻሌንጆች እዬገጠሙት ያነን እዬፈታ የመጣ ድርጅት ነው። ችግር ባይኖር ኖሮ መሰብሰብ ባላስፈለገ ነበር። ኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግር ባይኖራት ኖሮ 60/ 70 የፖለቲካ ፓርቲ ባላስፈለገ ነበር። መደማመጥ ስሌለ፤ መስማማት ስሌለ ነው እንጂ 60 ፓርቲ አያስፈልገንም ነበር። ይሄ ችግር ደግሞ የሚፈታው በማኩረፍ አይደለም። የእኔ ሃሳብ ካልተደመጠ ብቻ በማለት አይደለም። በመቀራረብ ነው። ማስተዋል የሚገባን ኦሮምያ 300 ሚሊዮን ህዝብ ማስተናገድ የሚያስችል ፖቴንሻያል አለው። የኢትዮጵያ ህዝብ 100 ሚሊዮን አይሞላም። እንኳን ብሄር ብሄረሰቦች ጁቡቲም፤ ኤርትራም ሱዳንም ቢመጡ በህግ፤ በሥርዓት እሰከ ሰሩ ድረስ አብሮ መኖር፤ አብሮ ማደግ አስፈላጊ ነገር ነው። ዱባይ ያደገችው ውሃ ኢንፖርት አድርጋ፤ አፈር ኢንፖርት አድርጋ፤ ድንጋይ ኢንፖርት አድርጋ፤ ሰውም ኢንፖርት አድርጋ ነው።“
· „ሃሳብ መሆኑ የሚታወቀው በቃል ሲገለጽ ነው። ቃል ካልወጣ በአእምሮ ውስጥ ብቻውን ቢብሰለሰል ሃሳብ ሊሆን አይችልም፤ ቢሆንም ለባለቤቱ ብቻ ነው የሚሆነው። ቃል ጉልበት አለው። ይተክላል፣ ይነቅላል። ትውልድ ይፈጥራል፤ ትውልድ ያጠፋል። ፍቅር ይዘራል ጥላቻን ይዘራል። በቃል ውስጥ ብዙ መማር ብቻ ሳይሆን፤ ሐገርንም መሥራት ይቻላል።
·
„ኢትዮጵያ የፈረሰችውም የተሠራቸውም በቃል ስለሆነ። ሁለቱንም ነገር ለመለማመድ እንደዚህ ዓይነት ፓብሊክ ስፒች ሰዎች ሃሳባቸውን ኦርጋናይዝድ አድርገው ለብዙሃን ሸር የሚያደርጉበት መድረክ ማግኘት ለእኛ ትልቅ ዕድል ነው። ምዕራባውያን ከጥቂት ምዕተ ዓመታት በፊት ከፍ ያለ ቦታ ላይ ሆኖ በርከት ላለ ሰው ሃሳብን ማካፈል፤ የዕምነትም፤ የፖለቲካም ሌላም ፍልስፍና ሊሆን ይችላል ከፍ ያለ ቦታ ሆኖ በሚያምር ድምጽ ለብዙሃን ሃሳብን ማካፈል የተለመደ ልማድ ነበር። ያ ልማድ ጠቅሟቸዋል።
„ኢትዮጵያ የፈረሰችውም የተሠራቸውም በቃል ስለሆነ። ሁለቱንም ነገር ለመለማመድ እንደዚህ ዓይነት ፓብሊክ ስፒች ሰዎች ሃሳባቸውን ኦርጋናይዝድ አድርገው ለብዙሃን ሸር የሚያደርጉበት መድረክ ማግኘት ለእኛ ትልቅ ዕድል ነው። ምዕራባውያን ከጥቂት ምዕተ ዓመታት በፊት ከፍ ያለ ቦታ ላይ ሆኖ በርከት ላለ ሰው ሃሳብን ማካፈል፤ የዕምነትም፤ የፖለቲካም ሌላም ፍልስፍና ሊሆን ይችላል ከፍ ያለ ቦታ ሆኖ በሚያምር ድምጽ ለብዙሃን ሃሳብን ማካፈል የተለመደ ልማድ ነበር። ያ ልማድ ጠቅሟቸዋል።
· „ዛሬ ምዕራብውያን በዬትኛውም መድረክ ሳይቸገሩ ሃሳባቸውን ያካፍላሉ፤ እኛ ደግሞ ሳንቸገር እናማለን። ሃሳብን እንደፈለግን ለመናገር ማህበረሰቡ ልምምዱ እንብዛም ስለሆነ። „
· „በሁለት ጉዳዮች ላይ አተኩሬ መናገር እፈልጋለሁኝ። የመጀመሪያው እውቀት ነው። እውቀት በጣም ያስፈልጋል። እውቀት ለእኛ በእጅጉ የሚያስፈልገን ዋናው ምክንያት ነገሮችን የምናይበት የማያ መነጸራችን የሚጸዳው፤ የሚያስተካክለው በዕውቀት ስለሆነ ነው። ለሁሉም ነገር ዕይታ ሲንሸዋረር፤ ሲበላሽ ያለንበት ገነትም ቢሆን፤ መልካም አገርም ቢሆን፤ እንድንጠላው፤ አንድንሸሸው ያደርጋል።
„ለዚህ ነው ሰው ኢትዮጵያን ሸሽቶ ሊቢያ ላይ የሚሞተው። ያለንበትን ነገር ገሃነም የሚያደርገው የምናይበት ዕይታ ብቻ ሳይሆን የሰውን ዕይታ ለማድመጥ፤ ለመካፈል የምናደርገው ዝግጁነትም ጭምር ነው። ሰይፍ መቅላት የሚችለው ሥራውን ማከናውን የሚቻለው/ የሚችለው በሸካራ ሞረድ የተሳለ እንደሆነ ነው። „
·
„ሸከራ ሞረድ ከሌለ ሰይፍ የሚል ሥም አለ ግን መቅላት አይችልም። ሰውም አመለካክቱ የማያ መነጸሩ የሚስተካከለው በእውቀት ነው። በየዕለቱ በሚያገኘው ዕውቀት ሰው አመለካከቱን እዬተገራ፤ እዬተቀረጽ ሙሉዑ ሰብዕና እንዲላበስ ያስችላል። ስለዚህ ዕውቀትን ሳንሸሽ፣ ሳንፈራ፣ ሳንጠዬፍ ለመፈለግ የምናደርገው ጥረት መሳኪያው መንገድ አካዳሚያ ብቻ ሳይሆን ፓብሊክ ስፒችም ጭምር ነው። „
„ሸከራ ሞረድ ከሌለ ሰይፍ የሚል ሥም አለ ግን መቅላት አይችልም። ሰውም አመለካክቱ የማያ መነጸሩ የሚስተካከለው በእውቀት ነው። በየዕለቱ በሚያገኘው ዕውቀት ሰው አመለካከቱን እዬተገራ፤ እዬተቀረጽ ሙሉዑ ሰብዕና እንዲላበስ ያስችላል። ስለዚህ ዕውቀትን ሳንሸሽ፣ ሳንፈራ፣ ሳንጠዬፍ ለመፈለግ የምናደርገው ጥረት መሳኪያው መንገድ አካዳሚያ ብቻ ሳይሆን ፓብሊክ ስፒችም ጭምር ነው። „
·
„ይህን ጉዳይ ደግምን ዳጋግመን ማሰብና መነጋገር ብቻ ሳይሆን አስፈላጊነቱን ማስፋት የሚያስፈልገው ከፍተኛው ችግር የእውቀት ባላቤቶች ብቻ ሳይሆን ዕወቀትን የሚያሰራጩበት ዓውድ አለመኖርም ጭምር ነው።“
„ይህን ጉዳይ ደግምን ዳጋግመን ማሰብና መነጋገር ብቻ ሳይሆን አስፈላጊነቱን ማስፋት የሚያስፈልገው ከፍተኛው ችግር የእውቀት ባላቤቶች ብቻ ሳይሆን ዕወቀትን የሚያሰራጩበት ዓውድ አለመኖርም ጭምር ነው።“
·
„እንግዲህ ዕውቀት በወጣትነት ዘመናችን አቅጣጫ የሚያመላክት፤ ተስፋ እንድንሰንቅ የሚያደርግ ነው። ዕውቅት ያላቸው ሰዎች ነገን ለመሥራት ዛሬ ይተጋሉ። በጉልምስና ወራት ደግሞ ራሳችነን ቤተሰቦቻችነን እንድናስተዳደር ገንዘብ ጄነሬት ማደረግ አንድንችል ያግዘናል። በሽምግልና ወራትም ምርኩዝ ይሆናል። የማያዋቁ ሰወች ላይፋቸው ሚዘረቭል የሚሆነው ሲጨርሱ ብቻ አይደለም፤ ሲጀምሩም ጭምር ነው። መጀመሪያም በወጣትንት ዘመን ለጫት የምናጠፋው ጊዜ እና ለመጸሐፍ የምናጠፋው ጊዜ ባላንሱን ከሳተ፣ ከዛ የጀመረ ብልሽት ይዘልቅና መጨረሻችንም አደገኛ እንዲሆን ያደርገዋል።“
„እንግዲህ ዕውቀት በወጣትነት ዘመናችን አቅጣጫ የሚያመላክት፤ ተስፋ እንድንሰንቅ የሚያደርግ ነው። ዕውቅት ያላቸው ሰዎች ነገን ለመሥራት ዛሬ ይተጋሉ። በጉልምስና ወራት ደግሞ ራሳችነን ቤተሰቦቻችነን እንድናስተዳደር ገንዘብ ጄነሬት ማደረግ አንድንችል ያግዘናል። በሽምግልና ወራትም ምርኩዝ ይሆናል። የማያዋቁ ሰወች ላይፋቸው ሚዘረቭል የሚሆነው ሲጨርሱ ብቻ አይደለም፤ ሲጀምሩም ጭምር ነው። መጀመሪያም በወጣትንት ዘመን ለጫት የምናጠፋው ጊዜ እና ለመጸሐፍ የምናጠፋው ጊዜ ባላንሱን ከሳተ፣ ከዛ የጀመረ ብልሽት ይዘልቅና መጨረሻችንም አደገኛ እንዲሆን ያደርገዋል።“
· „ዕውቀት መስጠት ማካፈል ብቻ ሳይሆን በወጉ መደራጀት አለበት። ዕውቀት በወጉ የሚደራጅበት በርካታ መንገዶች አሉ። እነሱን አልዘረዝርም። ነገር ግን እነሱ ሲሟሉ ስልጣኔ የሚባለው ነገር ይመጣል። ኢትዮጵያ ጨዋ አገር እንደሆነች በተደጋጋሚ ይነገራል። ኢትዮጵያ ግን መኪና ውጪ ማሳደር አይቻልም። ከጨዋነታችን ብዛት መኪና ውጪ ረስተን የገባን እንደሆነ ስንመለስ ስኮፕዮስ ስለማናገኝ ማለት ነው። ስልጣኔ ማለት ከዚህ ይጀምራል። ያለፋህበትን፤ ያልደከምክበትን ነገር አለመፈለግ። ስልጣኔ ያለፋህበትን ካለመፈለግ ይጀምራል።“
· „ሰላም ሲባል የውስጥ ሰላም፤ የራስ ሰላም፤ የጎረቤት ሰላም፤ የአብሮነት ሰላም ጭምር ስልጣኔ ውስጥ አለ። አንተ የምትሻውን መልካም ነገር ለጎረቤት ማሰብ፤ ልማት፣ ብልጽግና ሁሉ የሚገኙት፤ ትምህርት ዕውቀት ቃል በወጉና በሥርዓት መፍሰስ ሲችሉ ነው። ያን ማድረግ የሚችል ህዝብ፤ ማህበረሰብ የተሸከመውን ተራራ የሚያክል ችግር መከራ - እርዛት - ድህነት መሻገር ይችላል።“
· „ዕውቀትን በትክክል መጠቀም ስንችል፣ ካለምንም ጥርጥር አሁን ካለንበት ሁኔታ መሻገር ይቻላል። እውቀትን መፈለግ እና ማስተዳደር ግን በጣም ውድ ነው። ወጣ ገባ ይበዛዋል፤ ድካም ይበዛዋል፤ ከገንዘቡ ባሻገር። ነገር ግን ለእውቀት ከምናወጣው ወጪ በላይ ለመሃይምንት የምናወጣው ደግሞ በእጥፍ ድርብ ይበልጣል። አሁን ምርጫ የባለቤቱ ይሆናል። ትንሽ ኮስት አውጥተን በማወቅ ሁኔታችነን መቀዬር አልይም በጣም ብዙ ማውጣት እና በዚያም መገረፍ። ለምሳሌ ኢትዮጵያ ከበርካታ ከመካከለኛ ምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በብዙ ነገር ትሻላለች።
·
„ከእውቀት በስተቀረ። ለእውቀት በቂ ኢንበስትሜንት ማውጣት ዝግጁ ስላልሆን በመሃይምነት ለእነሱ ባርያ ለመሆን እንገደዳለን ማለት ነው። ስለዚህ በማወቅ ውስጥ ያለውን መልካም ነገር ማጨት አስፈላጊ ነው። ዕውቀት እንደ ላም ናት። ጡትም ቀንድም አላት። E = MC² ሄሮሽማ ላይ ሲወድቅ ቀንድ ነው። መብራት ሲያመነጭ እና ለኢነርጂ ሲውል ደግሞ ጡት ነው። እንዴት ነው የቀንድን አደጋ ተከላክለን እያለብን መጠቀም የምንችለው የሚለው ጉዳይ እንደ ግለሰብ እንደ ማህበረሰብ፤ የምናስበብት፤ የምንደክምበት ጉዳይ መሆን አለበት። ያወቀ ሁሉ ያለማል ማለት ስላልሆነ።“
„ከእውቀት በስተቀረ። ለእውቀት በቂ ኢንበስትሜንት ማውጣት ዝግጁ ስላልሆን በመሃይምነት ለእነሱ ባርያ ለመሆን እንገደዳለን ማለት ነው። ስለዚህ በማወቅ ውስጥ ያለውን መልካም ነገር ማጨት አስፈላጊ ነው። ዕውቀት እንደ ላም ናት። ጡትም ቀንድም አላት። E = MC² ሄሮሽማ ላይ ሲወድቅ ቀንድ ነው። መብራት ሲያመነጭ እና ለኢነርጂ ሲውል ደግሞ ጡት ነው። እንዴት ነው የቀንድን አደጋ ተከላክለን እያለብን መጠቀም የምንችለው የሚለው ጉዳይ እንደ ግለሰብ እንደ ማህበረሰብ፤ የምናስበብት፤ የምንደክምበት ጉዳይ መሆን አለበት። ያወቀ ሁሉ ያለማል ማለት ስላልሆነ።“
·
„ዕውቀት ለልማት፤ ዕውቀት ለውጤት የሚቀዬርበትን ነገር መፍጠር በእጅጉ ያስፈልጋል። አሁን ባለንበት የኖሌየጅ ኤጅ ዕውቀት ተሎ ተሎ ያረጃል። ዛሬ ይፈጠራል ነገ ያረጃል። የሚያረጀው ግን ለማያወቁት ነው። ለሚያውቁት መሠረት ነው የሚሆነው። የትናንትና ዕውቀት አዲስ ዕውቀት ሲጨመር ለዛሬው መሠረት ሆኖ ነው የሚያገለግለው። ለሚያውቁ ሰዎች።“
„ዕውቀት ለልማት፤ ዕውቀት ለውጤት የሚቀዬርበትን ነገር መፍጠር በእጅጉ ያስፈልጋል። አሁን ባለንበት የኖሌየጅ ኤጅ ዕውቀት ተሎ ተሎ ያረጃል። ዛሬ ይፈጠራል ነገ ያረጃል። የሚያረጀው ግን ለማያወቁት ነው። ለሚያውቁት መሠረት ነው የሚሆነው። የትናንትና ዕውቀት አዲስ ዕውቀት ሲጨመር ለዛሬው መሠረት ሆኖ ነው የሚያገለግለው። ለሚያውቁ ሰዎች።“
·
„ለማያውቁ ግን ሊያረጅባቸው ይችላል። በዬዕለቱ ማወቅ የሚያስፈልገው ባቡሩ ፈጣን ስለሆነ ነው። አሁን ባለው በኖሌጅ ኤጅ ለመጓዝ በዬዕለቱ መድከም በዬዕለቱ መልፋት እና ዕውቀትን ማደርጀት የማይችል ግለሰብም ይሁን ማህበረሰብ ባቡሩ ፌርማታ አይጠብቅም። እንቅስቃሴ ላይ እያለ እያወጣ ይጥላል። ልክ አሁን ኢትዮጵያን ከዓለም ጉዞ በከፍተኛ እርቀት አስፈንጥሮ እንደ ጣላት። ማለት ነው።““
„ለማያውቁ ግን ሊያረጅባቸው ይችላል። በዬዕለቱ ማወቅ የሚያስፈልገው ባቡሩ ፈጣን ስለሆነ ነው። አሁን ባለው በኖሌጅ ኤጅ ለመጓዝ በዬዕለቱ መድከም በዬዕለቱ መልፋት እና ዕውቀትን ማደርጀት የማይችል ግለሰብም ይሁን ማህበረሰብ ባቡሩ ፌርማታ አይጠብቅም። እንቅስቃሴ ላይ እያለ እያወጣ ይጥላል። ልክ አሁን ኢትዮጵያን ከዓለም ጉዞ በከፍተኛ እርቀት አስፈንጥሮ እንደ ጣላት። ማለት ነው።““
· „ልመና፣ ችግር፣ ጦርነት፣ ግጭት የሚባለው ነገር ከዕውቀት መደህዬት ጋር በቀጥታ የሚያያዝ ጉዳይ ነው። ሰው መተንፈሻ አውድ ከሌለው እጁን ይጠቀማል - ለድንጋይ። እንዲዚህ ዓይነት መንገድን ማስተካከል እና ከባቡሩ ጋር መጓዝ ያስፈልጋል። በድምሩ ዕውቀት የሚያስፈልገን ኢትዮጵያዊ ስለሆን ብቻ ሳይሆን፤ ሰውም ስለሆን ጭምር ዕውቀት ለሁሉም ሰው የተሰጠ ውድ ስጦታ ነው። የለፋ፣ የደከመ የሚያገኘው፤ የሚጠቀምበት፤ ያላገጠ ደግሞ የሚያጣው ነገር ነው። ዕውቀትን የምንፈልገበት ዋናው ምክንያት በህይወት ውስጥ በርካታ ችግሮች ስለሚገጥሙን፤ ከዚያ ችግር ማለፊያ መንገድ ስለሚሰጠን ነው። ሰው ቢፈልግም ባይፈልግም መፈተኑ አይቀርም።“
·
„በትምሀርት ወይንም በህይወት ይፈተናል። በትምህርት ስንፈትን ቢያንስ 50% ሰኪዩር ነው። ቴክስት ቡኩን እናውቀዋለን፤ ያነን ያነበበ ሰው 100 እንኳን ማምጣት ባይችል፤ 50 ሊያመጣ ይችላል። በህይወት ስንፈተን ግን ያልተዘጋጀን እንደሆነ አንዳንዴ ዜሮ የመሆን ዕድል አለው። ያ ፈተና የማያመልጥ መሆኑን አውቀን እራሳችን ማዘጋጀት እና ከችግር በላይ ለመሆን የሚያስችለን ደግሞ እንደዚህ ዓይነት መድረክ ሲዘጋጅ መጀመር ብቻ ሳይሆን በመጨረስ የዕውቀትን ዋጋ በማሳደግ ነው።“
„በትምሀርት ወይንም በህይወት ይፈተናል። በትምህርት ስንፈትን ቢያንስ 50% ሰኪዩር ነው። ቴክስት ቡኩን እናውቀዋለን፤ ያነን ያነበበ ሰው 100 እንኳን ማምጣት ባይችል፤ 50 ሊያመጣ ይችላል። በህይወት ስንፈተን ግን ያልተዘጋጀን እንደሆነ አንዳንዴ ዜሮ የመሆን ዕድል አለው። ያ ፈተና የማያመልጥ መሆኑን አውቀን እራሳችን ማዘጋጀት እና ከችግር በላይ ለመሆን የሚያስችለን ደግሞ እንደዚህ ዓይነት መድረክ ሲዘጋጅ መጀመር ብቻ ሳይሆን በመጨረስ የዕውቀትን ዋጋ በማሳደግ ነው።“
· „… መንጠባጠብ ካለ ዕውቀት አይደረጅም ማለት ነው። ይጀመራል ግን አይደረጅም። ካልደረጀ ደግሞ የሚጠበቅበትን ግብ አያሳካም። ንስር አሞራ በሰማይ ካሉ አሞራ ሁሉ የተለዬ ባህሪው፤ ዝናብ ሲመጣ ሁሉም የዐዕዋፋት ዘር መጠለያ ይፈልጋሉ። ይደበቃሉ። ንስር አሞራ ግን ዝናብ ሲይ ከደማና በላይ ጥሶ ያልፋል።“
·
„የዝናብን ምንጭ ወደ ታች ነው የሚያው። የችግርን ምንጭ ወደ ታች ማዬት እስካልቻልን ድረስ ማህበረሰብ አይሸጋገርም። ማንኛውም ችግር ሲነሳ ከችግሩ በላይ ሆነን ወደታች ችግሩን ማዬት፤ አንደሚያልፍ ማወቅ፤ ያን ለማሳለፍ የሚያስችለውን ድልድይ ደግሞ ዕውቀት አንደሆነ ማሰብ በእጅጉ ያስፈልጋል። „
„የዝናብን ምንጭ ወደ ታች ነው የሚያው። የችግርን ምንጭ ወደ ታች ማዬት እስካልቻልን ድረስ ማህበረሰብ አይሸጋገርም። ማንኛውም ችግር ሲነሳ ከችግሩ በላይ ሆነን ወደታች ችግሩን ማዬት፤ አንደሚያልፍ ማወቅ፤ ያን ለማሳለፍ የሚያስችለውን ድልድይ ደግሞ ዕውቀት አንደሆነ ማሰብ በእጅጉ ያስፈልጋል። „
·
„ከእውቅት ጋር በቀጥታ የሚያያዘው ጉዳይ አቲቲዩድ ነው፤ አመለካካት ነው። ይህን መድረክ እያንዳንዱ የመጣ ሰው እንዴት ነው የሚያው? ከዚህ በኋዋላ የሚኖረው ሌክቸር ሚዲያዎች አንዴት ይገለገሉበታል? የምናይበት መነጸር ትከክለኛ የሆነ እንደሆነ ዕወቀት እና በጎ አመለካከት ሲደመሩ ማህብረሰብ መቀዬር ይቻላል፤ ጨለማን ብቻውን መተቸት ግን ብርሃንን አያመጣም፤ ክፋትን መኮነን ደግነትን ሊሆን አይችልም። ኋላቀርነትን ማጥላላትም ሥልጣኔን ሊያመጣ አይችልም። „
„ከእውቅት ጋር በቀጥታ የሚያያዘው ጉዳይ አቲቲዩድ ነው፤ አመለካካት ነው። ይህን መድረክ እያንዳንዱ የመጣ ሰው እንዴት ነው የሚያው? ከዚህ በኋዋላ የሚኖረው ሌክቸር ሚዲያዎች አንዴት ይገለገሉበታል? የምናይበት መነጸር ትከክለኛ የሆነ እንደሆነ ዕወቀት እና በጎ አመለካከት ሲደመሩ ማህብረሰብ መቀዬር ይቻላል፤ ጨለማን ብቻውን መተቸት ግን ብርሃንን አያመጣም፤ ክፋትን መኮነን ደግነትን ሊሆን አይችልም። ኋላቀርነትን ማጥላላትም ሥልጣኔን ሊያመጣ አይችልም። „
·
„ጦርነትን መፍራትም ሰላም ሊሆን አይችልም። ራህብን አለመፈለግ፤ መጠዬፍ ጥጋብ ሊያመጣ አይችልም። ችግሩን መዋቅ አልትሜቴሊ መዳህኒት ነው ማለት አይደለም። ችግሩን በአወቀ አዕምሮ መፍትሄ ማፈላለግ በእጅጉ ያስፈልጋል።“
„ጦርነትን መፍራትም ሰላም ሊሆን አይችልም። ራህብን አለመፈለግ፤ መጠዬፍ ጥጋብ ሊያመጣ አይችልም። ችግሩን መዋቅ አልትሜቴሊ መዳህኒት ነው ማለት አይደለም። ችግሩን በአወቀ አዕምሮ መፍትሄ ማፈላለግ በእጅጉ ያስፈልጋል።“
· „ሃሳብ ይፈስስ! ሃሳብ ይለምልም!“
· „ዛሬ ልናገር የምፈልገው ሃሳብ በቆሎ በሳይንስ ከጤፍ ገዘፍ ትላለች፤ ወፍራም ናት፤ እረዘምም ትላለች፤ እና ጤፍን ወደ ታች እያዬች አሁን ሰው በከንቱ ይደክማል እንጂ ከጤፍ ማህጸን እንዴት ዱቄት ይወጣል ብሎ ይደክማል ትላለች። ያው ኢጎ እና አብሪት ዕወቀት በሌለበት ሁሉ ስላለ ማለት ነው። ነገረ ግን አንድ ኩንታል ጤፍ ወፍጮ ቤት ስትወስዱት የተሻለ ዱቄት የሚገኘው በጤፍ ውስጥ ነው።“
· „ዛሬ በጣም ጥቂት ሰው የሚመስል 1000 አንደ ሽህ ሰው በጣም ትንሽ ነው ጅማሮ ነው። ይህ ጅማሮ ግን ዘልቆ የኢትዮጵያን መጻኢ ሁኔታን አዳዲስ ሃሳብ የሚፈልቅበት፤ መነጋገር የማይፈራበት፤ በንግግር ውስጥ ማማር አንዳለ፤ እውቀት የሚገበይበት፤ ለመከራከር ለዲቤት ሳይሆን አርጊው ለማድረግ፤ ሰጥቶ ለመቀበል የምንዘጋጅ ትውልድ እንደንሆን ያስችላልና። ይህ ጅማሮ እንዲቀጥል ሁላችሁንም ዛሬ ያሳዬነውን ኮሚትሜንት ማስቀጠል አለብን።“
·
„ምንአልባት አንዳንዶቻችሁ ጠቀሜታው ዛሬ ይገባችሁ ይሆናል። አንዳንዶቻችሁ ሁለት ሦስት ሳምንት ሊወስድባችሁ ይችል ይሆናል። ግዴለም ዋጋ የተከፈለበት፤ የተደከመበት ነገር ውጤት ሊያመጣ ስለሚችል አብረን በመዝለቅ እንደዚህ ዓይነት መድረክ አስፈለጊ መሆኑን ለእኛ ቢቀር ለልጆቻችን፤ ለምንተዋት ኢትዮጵያ ለብዙዎች ትምህርት ስለሚሆን የሚዲያ ሰዎችም ከማስታወቂያ ባሻገር ሃሳብ የሚፈስበት፤ የማይገደብበት ልምምድ ዓውድ መሆኑን አስባችሁበት ከዚያ አንጻር አንድትሰሩ፤ የተገኛችሁትም ሰዎች ፈረንጆች እንደሚሉት እያንዳንዳችሁ አንዳንድ ሰው ኢንፍሎዬንስ በማድረግ እንደዚህ ዓይነት መድረክ ከተማችን ውስጥ አንዲሰፋ፤ እንዲያድግ ያ ሲሆን አሁን ያለው ውጥረት ሊረግብ እንደሚችል ነው የምገምተው። ጅማሯችሁ ያመረ ይሁን! ሃሳብ ይፈስስ! ሃሳብ ይለምልም! ከእያንዳንዳችን ትምህርት ይገኛል። በቆይታችሁ እንደምትደሰቱ ተስፋ አደርጋለሁ አመሰግናለሁ።“
„ምንአልባት አንዳንዶቻችሁ ጠቀሜታው ዛሬ ይገባችሁ ይሆናል። አንዳንዶቻችሁ ሁለት ሦስት ሳምንት ሊወስድባችሁ ይችል ይሆናል። ግዴለም ዋጋ የተከፈለበት፤ የተደከመበት ነገር ውጤት ሊያመጣ ስለሚችል አብረን በመዝለቅ እንደዚህ ዓይነት መድረክ አስፈለጊ መሆኑን ለእኛ ቢቀር ለልጆቻችን፤ ለምንተዋት ኢትዮጵያ ለብዙዎች ትምህርት ስለሚሆን የሚዲያ ሰዎችም ከማስታወቂያ ባሻገር ሃሳብ የሚፈስበት፤ የማይገደብበት ልምምድ ዓውድ መሆኑን አስባችሁበት ከዚያ አንጻር አንድትሰሩ፤ የተገኛችሁትም ሰዎች ፈረንጆች እንደሚሉት እያንዳንዳችሁ አንዳንድ ሰው ኢንፍሎዬንስ በማድረግ እንደዚህ ዓይነት መድረክ ከተማችን ውስጥ አንዲሰፋ፤ እንዲያድግ ያ ሲሆን አሁን ያለው ውጥረት ሊረግብ እንደሚችል ነው የምገምተው። ጅማሯችሁ ያመረ ይሁን! ሃሳብ ይፈስስ! ሃሳብ ይለምልም! ከእያንዳንዳችን ትምህርት ይገኛል። በቆይታችሁ እንደምትደሰቱ ተስፋ አደርጋለሁ አመሰግናለሁ።“
በዚህ ቅንነት በዚህ ንዑድነት በዚህ ግልጽነት በዚህ ለትውልድ ተቆርቋነት በዚህ የ እኛዊነት ፍልስፍና ውስጥ ለግማሽ ሰከንድ አባገዳ ጃዋር መሃመድ እና አቶ ሌንጮ ለታን ማግኘት ይቻላል ወይ? ፍርድ የህሊና እና የእውነት ጉዳይ ነው። ፍረዱት ውዶቼ። እንዲህ የነበሩ ይህን የተመኙ ፍጡር ስለምን ይህ ጭካኔ ከነበራቸው በጨካኙ የህወሃት ዘመን የሳይንስ እና የቴክኖሎጂ ሚ/ር በነበረበት ጊዜ በአድሎ በግለት በጭቆና ቢሮውን አላመሱትም? ስለምንስ ይህን ግልጽ እና ቁልጭ ያለ ብሩህ ተቆርቋሪነት አለሙ?
Ethiopia - Dr Abiy ፈረንጆቹን አሸማቆ መለሳቸዉ!!
ከዚህ ዕሳቤ አገር ነው የአባገዳ ጃዋር መሃመድ ፍልስፍና የሚታዬው? በዚህ ውስጥ ነው የአቶ ሌንጮ ለታ የዕድሜ ልክ የማይበቅል ፍልስፍና የሚገኘው? ለመሆኑ ለሁለቱ ኢትዮጵያ ምናቸው ናት?
ስለ ዞግ ከተነሳ የጠ/ሚር አብይ ምልከታ ይሄ ነው።
Ethiopia - Dr Abiy እንዴት ሰዉ በ1% ልዩነት ይሰቃያል?!
አሁን በቅርቡ ፕ/ መራራ ጉዲና የተናገሩት አንድ ብልህ ነገር አለ ባህርዳር ላይ በነበራቸው ቆይታ። „ውጭ ያለው ተፎካካሪ ሳይሰናዳ እንዳለ ገባ፤ እኛም ሳንሰናዳ ጠብቅን ከለውጡ ጋር ለማወሃድ ተቸገርን“ አሉ። ስብሰባ ላይ የገጠመው ገመና በቅኔም ጨለፍ አድርገው ገልጸውታል።
ቀድሞ ነገር አቶ ሌንጮ ለታ እኮ ግንቦት 7 እስኪመሾራቸው ድረስ ቃለ ምልልስ በአማርኛ አድርገው አያውቁም ነበር። እና ጁቡቲ፤ ፈረንሳይ፤ ጣሊያን፤ ግብጽ፤ ኤርትራ ላይ አገርን በወከለ ብሄራዊ ጉዳይ በአማርኛ ቋንቋ ንግግሩን የሚያደርግ መሪ በእኔ ዕድሜ አላዬሁም አልሰማሁም።
አማርኛ ቋንቋ የአፍሪካ ህብረት 6ኛ ቋንቋ እንዲሆን ሲወሰን በዛ ውስጥ ህብራዊ ኢትዮጵያዊነት እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም። የሶሞናቱ አክሳይ እርምጃ ከዚህው ጋር የተዋህደ ነው። ሌላው የፖለቲከ ድርጅት ነኝ የሚለው መሪ እስከዚህ ድረስ ገፍቶ ሄዶ አያደርገውም ፈጽሞ። ሌላው እኮ ምርጫ ስላጣ ነው አማርኛ ቋንቋን የሚናገረው እዬጠላው እና እዬተጸዬፈው። አንጡራ ጠላት እኮ ነው አማርኛ። ጥበብ ዕውቀት ፍልስፍና ሳይንስ ቋንቋ መሆኑ ቀርቶ።
ብቻ የኔወቹ ውዶቼ ጊዜ ሰጥታችሁ እንዚህ አገላለጾች በአቶ ሌንጮ ለታ እና በአባ ገዳ ጃዋር መሃመድ ውስጥ ካገኛችሁ እኔ እረታለሁኝ። ኢትዮጵያ እኮ አንጡራ ጠላታቸው ናት ለኦነጋውያን። „የመንፈስ ሚስጢር“ ተባለች ብለው እኮ ህምም በህምም የሚሆኑ ናቸው። ወያኔ 27 ዓመት ያደከማትን ኢትዮጵያ አሁን ደግሞ እንጨርሳት ነው እርብርቡ። የዚህ ማህበርተኛ ጠ/ሚር አብይ አህመድ አይደሉም። መብለጥ፤ መላቅ፤ ተዝቆ የማያልቅ እቅም እና ክህሎት አለመደፈሩ ነው የዚህ ሁሉ ትርምስ ሚስጢሩ። በስውርም በግልጽም ያለው ፕ/ መራራ ጉዲና እንዳሉት „የቡዳ ፖለቲካ“ ይኸው ነው።
- ባገኘው?
ውዶቼ ይህን በ2018 መግቢያ ላይ የጻፍኩት ነው ግርም ብሎኝ አባ ገዳ ጃዋር መሃመድ።
https://sergute.blogspot.com/2018/05/06.html ምጥን
… እንዲያው „ቸር ተመኝ ቸር እንድታገኝ“ አይደለ ብሂሉ ፈጣሪዬን ባገኘው እምጠይቀው ፖለቲከኛውን ወጣት ጆዋር መሃመድን ስለምን እንደፈጠረው እጠይቀው ነበር - አማኑኤልን? በመልካም ውስጥ ፈተና፤ በፈተና ውስጥ መልካምነት የሚገናኙበት መስመር እንዲኖር አስቦ ይሆን እላለሁኝ? ወይንስ በጨለማ እና በብርሃን ውህደት የሚፈጠር አንድ ተፈጥሮ የሁለቱ ዲቃላ የሆነ ሦስተኛ ነገር ሽቶ ይሆን እላለሁኝ፤ ወይንስ በደስታ እና በሃዘን በትራጄዲ እና በኮሜዲ ውህደት የሚፈጠር ሦስተኛ ተውኔት አስቦ ይሆን እላለሁኝ። አንድ ላይ ተዋህደው በሚፈጥሩት ተውኔት ማህል ሰውን እናዬው ዘንድ ፈቅዶ ይሆን እላለሁኝ።
የንግግሩ ፍሰት እና ንዝረት ሙቀቱ እዬጨመረ ሲሄድ፤ ምቱና አቅጣጫው በራሱ ሥም - የለሽ በሆነ ሁኔታ እታደምበታለሁኝ። ባገኘው የእኔን አማኑኤል ምክንያታዊ አቋሙን ፈጣሪዬ እንዲነግረኝ አጥብቄ እጠይቀው ነበር። እሱም ፍጡሩን ሲፈጥረው ካወቀው ነው ታዲያ? ለዚህም ነው በአሉታዊ የሚነሱበት ሃሳቦችን እንኳን እንዲህ ለማለት ፈልጎ ነው ብዬ ከማቃናት በስተቅር በሚያደርገው ነገር ሁሉ ብስጭት ዝር የማይልብኝ። የማልጽፍበትም።
ምክንያቱም / ምክንያታዊ አመክንዮዎ ለእኔ ግብረ- ምላሹ በሃሳቡ ቀውስ ውስጥ ዘው ብዬ እንዳልገባ በድንበር እንድከታተለው ብቻ ሆኛለሁኝ። ካልተገደድኩኝ ሥሙን ማንሳት ራሱ አልሻም። ጠልቼው ግን አይደለም። ቢሆንማ አላዳምጠውም ነበር።
ብቻ በወጣቱ ውስጥ ማወቅ እምፈልገው ሰብዕና እንዳለ ይሰማኛል። ይሄ „የስሜት ውጣ ውረድ ወጥነት፤ የሃብ ቋሚነት ዝልቅነት፤ የራዕይ ተከታታይነት እና ግባዕቱ“ የሚባል ሰብዕና ይመስለኛል የምፈልገው በታናሽ ወንድሜ ውስጥ - እርግጠኛ ባልሆንም። በእሱ ዙሪያ በአውንታዊ ይሁን በአሉታዊ የሚወጡ ጹሑፎች እራሱ ባለቤትም/ ባለቤት ያልሆነም ስሜት የለኝም - ሳነበው። ቀለም የለውም ስሜቴ።
ስለምን? እኔም እራሴ አላውቀውም፤ አንዳንድ ጊዜ ልጄ ቢሆንስ? መስመራችን በምን ይዘረጋ ነበር? አዲስ ቋንቋ ፈጥረን እንግባባ ይሆን የሚል ስሜት ሁሉ ያድርብኛል። የሰውን አፈጣጠር ትርጉመ - ብዙነት በጥልቀት ያሳዬኛል - ይመስለኛል። ግን ስለምን ይሆን? አላውቀውም - እኔው።
ሽብር መፍጠር ብቻ ሳይሆን ንጹሃን ሲሰቃዩ፤ ሲጎሳቀሉ ማዬት ህልም ነው። ይህ ተኑሮበታል። አሁን አዲሱ እጮኛ ደቡብ ነው። የጅጅጋው ፋይሉ ስለተዘጋ። ያን ነበር በሽታ ሽቶሽ ሲያበረታቱ የነበረው። ኢትዮጵያ ማዕት የወረደባት እኩይ መንፈስ አራማጆች ሲፈጠሩበት ነው። እንዲህ ዓይነት አገር ሕዝብ የመጥላት መከራ በሌላ አገር አይቼ አላውቅም። ጠላቶቿን አቅፋ እንሆ ዘመን ተዘመን ትታረዳላች አላዛሯ ኢትዮጵያ። ነገ ክርስትናም ወዮልህ ነው! ከግራኝ ግራ እንጂ ቀን ማሰብ አልተፈጠሩበትም።
ውዶቼ ጊዜ እውነትን ያነጥራል!
ወጀብም ያልፋል!
ስክነትም ይወለዳል!
የኔዎቹ ኑሩልኝ!
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ