ልጥፎች

የፕሮፌስር መራራ መራር ማንፌስቶ።

ምስል
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። „እንሆም ሁሉም እሾኽ ሞልቶበታል። ፊቱንም ሳማ ሸፍኖታል፤ የድንጋዩም ቅጥር ፈርሷል።“ (መጽሐፈ ምሳሌ (ተግሳጽ) ምዕራፍ 24 ቁጥር 31) የፕሮፌስር መራራ መ ራ ር ማንፌስቶ። ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። 27.12.2019 ·        እፍታ። እንዴት ናችሁ የእኔ ቅኖች የኢትዮጵያ ቅኖችም ዛሬ የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና ከሰሞኑ በሰጡት መግለጫ ላይ እና ተያያዥ ጉዳያዎችን እንደ አንድ የአገር መሪ ያላቸውን ሰብዕና አክሎ እምለው ይኖረኛል። ትዕግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል እና። በቅድሚያ ግን የእኔ ውዶች ይህን ፎቶ ልጋብዛችሁ።  ትኩር ብላችሁ በማስተዋል በፈርጅ በፈርጁ ታስተውሉት ዘንድ በትሁት አክብሮት እለምናችሁ አለሁኝ። እዩት እስቲ። ፈትሹት እስቲ። የአንድ የአገር መሪ ቢሮ ነው። በመንፈሳችን መሪ ቢሆኑልን ብለን ስናስባቸው ስንናፍቃቸው፤ ስንመኝም ኑረናል። የሰው ልጅ እራሱን የሚያደራጀው በራሱ ልክ ነው። እራሱን የሚመራውም በራሱ አቅም ልክ ነው። ከቶ ኢትዮጵያዊ መሪነት እና የዚህ ቢሮ አደረጃጀት እና አያያዝ ተመጣጠኑ ይሆን። የፈረደባት ኢትዮጵያ ስንቱን ገመና ተሸከሚ ብለን አሳሯን እንዳበላናት ዛሬ ላይ ሳስበው ይሰቀጥጠኛል። በዚህ ዘመን ያላዬነው መከራ፤ ያልሰማነው መስቃ  የለምና። ደበደቡን። ሰለቁን። ሾከሾኩን እግዚአብሄር ይይላቸው። የምንፅናናበት የፖለቲካ ሊሂቅ የለንም። ተስፋ የምናደርግበት የፖለቲካ መሪም የለንም። ·        ዝርክርክነት ለአገር መሪነት ያበቃ ይሆን? ወግ አይቀር አይዋ ኮንፒተር ጉብ ብሏል። አሁን ይህ ቢሮ ነው ወይንስ የከብቶች ማደሪያ? ወይንስ የቆሻሻ

መንትዮሾቹ ከቁልቋል አጫዋችነት ወደ ኦዳ አራጋቢነት የተገለበጡት ልብጣዊ ነፍሶች።

ምስል
እ ንኳን ወደ ቀ ንበጥ ብ ሎግ በ ሰላም መ ጡልኝ። „ፊታቸውን ሳይሆን ጀርባቸውን   ሰጡኝ፣ በመከራቸው ጊዜ ግን ተነስተህ አድነን ይላሉ።“   ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፳፯ መ ንትዮሾቹ ከቁልቋል አ ጫዋችነት ወደ ኦዳ አራጋቢነት የተገለበጡት ልብጣዊ ነ ፍሶች። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·     እ ፍታ የሰማዩ አሻቦ ሲጠበቅ ትውር ሳይል በደመና ተደሞ የዓውደ ዓመቱ ሥርዓቱ እዬተፈጠመ ነው። ነፍስ ተ - እንቅስቃሴ የተገደበ ይመስላል። ጸጥ - ረጭታ እንደ ቤተ መቃብር ሆኗል። የቤቴ እርግቦች እራሱ እሱ አፋቸውን   የተባሉ ይመስል ኮሽታ የላቸውም። ድምጥም የለም። ብቻ እርጋታ በ - ጫታ ሰፍኗል- ዕለቱ። ግርማ ሞገሱ ግን ያስፈራል። ጭሯቸው ብቻ የተንጫረረው ግንዶኢን ባልስ ዳንስ ላይ ይገኛሉ፤ እቴጌዋ ከመንበሯ ብቅ ብላ አፈር እንደ ማለት አሰኝቷት ከንፈሯን ነፋ አድርጋ ሽው ትላለች። እንዴት ናችሁ የኔዎቹ ቅኔዎቹ የአገሬ ውዶች? ዕለቱን ባዕላችን ብላችሁ ለምታከብሩት ሁሉ መልካም የስኬት ዓውድ ዓመት አንዲሆንላችሁ እመኛለሁኝ። ትህትና ይታከልበታል። የ ወግ ገበታ። ዛሬ ስለ ግልብጥ ሲብሊንገኖችን ትንሽ ነገር መቋጠር ፈለግሁኝ። ለነገሩ እኛንም ገልብጠው ጋልበውናል - የዛሬን አያድርገው እና። ሁለቱም ሥም የለሾች ናቸው - ተዛሬ ላይ። ሥም የለሽነታቸው የሚያውቀው የቁልቋል አምላክ እና የኦዳ አምላክ ብቻ ናቸው። ግን ልበ - ጥፉን በሥም ይደግፉ እንዲሉ እነዛ ቅን፣ ደግ እና ቸር ወላጆች ምን የመሰለ ድንቅ ሥም አውጥተውላቸው ነበር። ልጅ ደመቀ መኮነን እና ልጅ ገዱ አንድርጋቸው ብለው። ነገር ግን ነፍስ አውቀው ፖለቲከኛ ከሆኑ ጀምረው የወላጆቻቸውን ሥጦታ