ልጥፎች

"የ ሀ ዲ ስ ፍ ቅ ር ... ┈┈•✦•┈┈

ምስል
  ይህም ዘመን ዬኛ ነበር? እንዲህ ያለ ዕውነተኛ ፍቅር እስከ መቃብር። ሕይወቱን የኖሩበት ዕንቁ። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ከአቶ ቴወድሮስ ዝናው ያገኜሁት ነው።   "የ ሀ ዲ ስ ፍ ቅ ር ... ┈┈•✦•┈┈ እወቁ ደራሲ እና ዲፕሎማት ሀዲስ ዓለማየሁ ለመጀመሪያ ጊዜ በሥራ ምክንያት ከኢትዮጵያ ውጭ የኖሩት ኢየሩሳሌም ነበር፡፡ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ቆንስል ሆነው ለሁለት ዓመታት አገልግለዋል፡፡ ከባለቤታቸው ወይዘሮ ክበበፀሐይ በላይ ጋር ተዋውቀው ለጋብቻ የበቁትም በዚህ ወቅት ነበር፡፡በጊዜው ወይዘሮ ክበበፀሐይ ከአያታቸው ጋር ኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር፡፡ ከ15 ዓመታት የፍቅርና የትዳር ሕይወት በኋላ ወይዘሮ ክበበፀሐይ አሜሪካ፣ ኒውዮርክ በህክምና ላይ እንዳሉ አረፉ፡፡ ሀዲስ ዓለማየሁ ከዚህ በኋላ እስከ ሕይወት ፍጻሜያቸው ድረስ ሌላ ሚስት አላገቡም፡፡ የአብራካቸውን ክፋይም አላዩም። ከባለቤታቸው ሞት በኋላ ሌላ ሚስት ለምን እንዳላገቡ በአንድ ወቅት ተጠይቀው ነበር፡፡ በሰጡትም መልስ በጣታቸው ላይ ያለውንና ከባለቤታቸው ሞት በኋላ ያላወለቁትን የጋብቻ ቀለበት እያሳዩ «ይህን ቀለበት ያሰረችልኝ ክበበፀሐይ ነች፡፡ እኔም ለእሷ አስሬያለሁ፡፡ እሷ ድንገት አረፈች፡፡ ... ቀለበቱን አልፈታችውም፡፡ ሳትፈታው አረፈች፡፡ ስለዚህ ይህን ቀለበት ከኔ ጣት ላይ ማን ያውልቀው? ካለ እሷ፣ ካለ ክበበፀሐይ ይህን ቀለበት ከጣቴ ላይ የሚፈታው የለም፡፡» ብለዋል። ከባለቤታቸው ሞት በኋላ መኖሪያ ቤታቸውን የሕጻናት ማሳደጊያ እንዲሆን አድርገዋል፡፡ ቀጨኔ መድኃኔዓለም አካባቢ «ክበበፀሐይ የሕጻናት ማሳደጊያ» በሚል መጠሪያ ተሠይሞ፣ አያሌ ወላጆቻቸውን በሞት የተነጠቁ ሕጻናት አድገውበታል፣ አሁንም እያደጉበት ይገኛል፡፡ ታላቁ ደራሲ ሀዲስ ዓለማየሁ ተወዳጁ

የልብ አውቃዋ ዕውነት መሰከረች። "ጎንደር" "አሳዬ ደርቤ"

  የልብ አውቃዋ ዕውነት መሰከረች። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ከእህት ከሰናይት አማረ ፔጅ አገኜሁት ዬብርቱው ፀሐፊ ዬአቶ አሳዬ ደርቤ መካች፣ ማርከሻ ጹሑፍ ነው። አልመቻችልኝ ብሎ በጎንደር ላይ ዬሚዘንበውን ዲን በሚመለከት ልጥፍ ካሰብኩ ቀናት ተቆጠሩ። እንሆ የልብ ዓውቃዋ ዕውነት መሰከረች። ተመስገን። "ጎንደር" "አሳዬ ደርቤ" ▬▬▬▬ "➔ሰሜን እዝ ሲወጋ ቀድማ የደረሰች ➔በጀርባዋ የአልቡርሐንን፣ የአልሲሲን፣ የደብረ ጽዮንን፣ የቅማንት ኮሚቴን ጥምር ጦር የተሸከመች፣ ➔በዚህ ጥምር ጦር በአገር ላይ የተቃጣን ከሰላሳ በላይ ወረራዎች ከመከላከያ ሠራዊቱና ከአማራ ልዩ ሃይል ጋር ሆና 30 ጊዜ የመከተች፤ ➔ወራቤ ባልሰማችበት ሁኔታ ወሎ ሲወረር ሃይማኖቱን ሃይማኖቴ፣ ማንነቱን ማንነቴ ብላ ገስግሳ በመድረስ በቦሩ ሜዳ እና በጦሳ ተራራ ላይ ታሪክ የማይዘነጋው ተጋድሎ የፈጸመች፣ ➔በኢሬቻ በዓል ላይ ቄሮዎች ሲገደሉ ‹‹ኦሮሚያ ላይ የሚፈስሰው ደም ከእኔ ጅማት የሚቀዳ ነው›› በሚል መርሕ ኦሮማራን መሥርታ የ27 ዓመቱን የማፊያ ቡድን ያስወገደች፤ ➔በእራሷ መስዋዕትነትና የሰላም እጦት ላይ የአገርን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ሦስት ዓመት ሙሉ የደከመች ጎንደር ▬▬▬ ➔አማራን እና ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ጎንደርን ማተራመስ›› የሚል የጥፋት ፕሮጀክት ባነገቡ ኃይሎች ከማተብ ውጭ ምንም አይነት የሐሳብ ልዩነት የሌላቸው ልጆቿ በጠላት መረብ ወድቀው ሰለባ ሲሆኑ የታዘበች፤ ➔በቀጣይ ክረምት ‹‹አማራ›› በሚል ማንነት ለሚሰነዘርባት ውጫዊ ጥቃት ውስጣዊ የእምነት ልዩነት ይፈጥሩ ዘንድ ድርጎ በሚሰፈርላቸው ቆብ እና ጥምጣም ለባሽ ፖለቲከኞች መንጋጋ ውስጥ የገባች፤ ➔ገዳይም ሆነ ሟች ልጆቿ ሆነው ሳለ ወራቤ እና ወሎ ምድር በበቀሉ የትሕ-

እዮራዊ ጥሪ ለትግራይ ሊቃናት እና ሊሂቃን። ሰማይም ተናገረ።

ምስል
  እዮራዊ ጥሪ ለትግራይ ሊቃናት እና ሊሂቃን።    #ሰማይም ተናገረ። ዕውነት ነው ኢትዮጵያ ዬእግዚአብሔር የአላህ አገር ናት። የዕንቁ ምልክት ከቀስት እንድን ዘንድ። በዬጊዜው በዬሰዓቱ። በዬዘመኑ በዬክስተቱ። በዬተደሞው በዬዕድምታው። ምልክት መሪ ጮራ ይላካል። ቢደመጥ። ተመስገን። "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   #ዕፍታ ። በመቀሌ እና በአዲግራት አካባቢ የመሪት መንቀጥቀጥ ተደመጠ ልክ እንደ 2010 የመጋቢቱ የእዮር ጥሪ ቀረበ። #እኔ ። ምዕራፍ 7 በብዙ አመክንዮዊ ጉዳዮች ላይ በተዕቅቦ ነው ያለሁት። እምጽፈው የህዝብ ጉዳት፣ የህዝብ የጉዳት ልክ፣ የህዝብ መንፈስ ከጉዳት ማገገም፣ በተፈጥሯዊ መልካም ነገሮች እና እኛ የግል ፍልስፍናዬ ብቻ ነው። ለዚህ ነው ተያዘ ተለቀ፣ ድርድር ንግግር፣ ድል ሽንፈት ቅርቤ ያልሆኑት። ምክንያት ላም እረኛ ምን አለ ጮርቃውም፣ ዕድሜ ጠገቡም፣ አውራውም፣ አባ ወራውም ፖለቲከኛ፣ ተቋማት "ላም እረኛ ምን አለ" ቀልቡን ሊመራው ባለመፍቀዱ። ከትነት፣ ከብነት፣ ከውጥን፣ በለጋ ከመቅረት፣ በተስፋ ሹፌር አልባነት መባዘን፣ አፍሶ በመልቀም፣ ለቅሞ በማፍሰስ ዬሜትር እርቀት ዬማይታዬው። የተሰበሰበ አቅም ቀርቶ የሚሰበስብ ሃሳብ የለም። በወረት በወረቱ አቅም ሲባክን ትውልድ ሲታጨድ ሥልጣኔ ወደ ኋላ 30 ዓመት ሲኳትን፣ ዝልቅ ጽናት ሲፈትን ውኃ ቅዳ ውኃ መልስ። #የሰማይ አናባቢ መልዕክት በምልሰት። የሚያስታውስ ከተገኜ …… ደጉ ሳተናው ላይ ከሳይንቲስቶች ያፈነገጠ ዕይታዬን አጋርቼ ነበር። መጋቢት 17/2010 ለመጋቢት 18/2010 እዮር ለተጋሩ ሊቃናት መልዕክት ላከ። የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ። ያን ጊዜ ሌት ተቀን ስብሰባ፣ መግለጫ ላይ ነበር ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ። እናም ሰማይ መልዕክት ላከ። እኔ እባካችሁ

#ወሮ አዜብ መስፍን እና ትናንት። ዬአማራን ተጋድሎ ለመጥለፍ ሲንደፋደፋ የተጣፈ ነው። ዛሬም የጠላፊ ናዳ ወጀብ ቢንጠውም።

ምስል
#ወሮ አዜብ መስፍን እና ትናንት።   ዬአማራን ተጋድሎ ለመጥለፍ ሲንደፋደፋ የተጣፈ ነው። ዛሬም የጠላፊ ናዳ ወጀብ ቢንጠውም። ዬአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ መንፈሱ እንዲህ ጥበቃ ይደረግለት ነበር። እዚህ እምሠራው ቁራጭ ነገር ነው። በጣሳ። ቀደም ባለው ጊዜ ግን በዚህ መልክ ነበር እምሰራው። ዘለግ ያለ ሙግት፣ በጥንግ ድርብ ብርታት። እንዴት አደርን? ደህና ነን? ዛሬ ሌሊት ነበር ዬገባሁት። ዬቤታችን መቀዬጥን ለማጽዳት። መቼም ዬዘንድሮ ጥር ያልቀማን ዬለም። ለዛ ነው ዝምታን መርጬ ዬምላትን ብዬ ሾለክ እምለው። ትናንት እና ዛሬ ዬብራና ዬጥዳት ቀን ነበር። ይቀጥላልም። ቤታችን ናፍቋቸው ተሰልፈው ዬሚጠብቁ ቅኖች አሉ። ለእነሱ እድል ይሰጣል። ባለፈው ወር አንድ ወንድማችን መግባት ፈልጎ ፌስቡክ አስቸግሮት በስንት ጣጣ ወደ ቤታችን መጣልን። እንኳን ደህና መጣህልን ወንድማችን ልለው ፈቀድኩኝ። ከአራት ዓመት በፊት ሙግቴ ይህን ይመስል ነበር። በረጅሙ ነበር እማስከነዳው። ዛሬ አንድ እርዕሰ ጉዳይ ፈልጌ ጉግል ስገባ ከች አደረግልኝ አጤ ጉግልሻ። ረጅም አትኩሮት ከህሊናዊነት ጋር ላለቸው ዬሚሆን ነው። እንዳለ ሼር ለማድረግ ፈቀድኩኝ። ግን ካልሆነ ማስታወቂያ ጋር ሆነብኝ። ነጥዬ ለማቅረብ ስል አልቻልኩም። በዚህ መልክ ተቻለ። መልካም ቀን። ደህና ዋሉልኝ። ቸሮቼ። • ጉራጅ – ውራጅ – ከሥርጉተ ሥላሴ January 18, 2017, 10:56 am ከሥርጉተ ሥላሴ 18.01.2017 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ።) „በአባቷ፡ ዬምታላግጥን፡ ዬእናቷን፡ ትእዛዝ፡ ዬምትንቅን፡ ዓይን፡ የሸለቆ፡ ቁራዎች፡ ይጎጠጉጧታል፥ አሞራዎች ይበሏታል። (መጽሐፈ ምሳሌ (ተግሣጽ) ምዕራፍ ፴ ቁጥር ፲፯) • ጠብታ። ለከት ክት ሆኖ አንከሊስ ሲያማትብ ቹፌ ተደፋበት ክህደት – በሥጋ ግንብ። ውቅራ

#ኢትዮጵያ "ጋለሞታ" አይደለችም። አበስኩ ገበርኩኝ! ስለአገላለፁ። "ህግ ተላላፊወችን ጠላሁኝ።" #ኢትዮጵያ የማንም "ውሽማም" አይደለችም። ማህከነ። "ለአንደበቴ ጠባቂ አኑርልኝ።"

ምስል
#ኢትዮጵያ "ጋለሞታ" አይደለችም። አበስኩ ገበርኩኝ! ስለአገላለፁ። "ህግ ተላላፊወችን ጠላሁኝ።" #ኢትዮጵያ የማንም "ውሽማም" አይደለችም። ማህከነ። "ለአንደበቴ ጠባቂ አኑርልኝ።"     • ይኽው ሊንኩ።አገር ከበለጠባችሁ፤ ዬጊዜ አታሞ ካልረታችሁ። https://www.youtube.com/watch?v=jaaelCVVHic&t=451s የአሁን ዋና ዋና መረጃዎች!DereNews Oct. 19 2022 #derenews #zenatube#Ethiopiannews# ኢትዮጵያ "ጋለሞታ" ስትባል፣ ኢትዮጵያ "ዬማንም ተወሻሚ" ስትባል አይጎረብጥም፣ አይቆረቁርም? ስለማን የምን ንጥረ ነገር ይሆን ዬሚተነፈሰው? ውስጣችን ለእናታችን እንዲህ ሸካራማ፣ ኮረኮንችማ፣ አሜኬላ በቀል። ከእናት አገር ጠረን ዕለታዊ ሰብዕና በልጦብን ይሆን? #በር ። ኢትዮጵያ ከቅኔም፣ ከስዋሰውም አልፋ እና ንራ ኢትዮጵያ #ሰማያዊ #ምስባኽክ ናት።።።።።።።።።።።።። ቫወልም ናት። አናባቢ። ኮንሰነትም ናት ተነባቢ። #ቅምሻ ። ጎንደር ላይ ሲዘንብ የባጀው የዲን በረድ አሁን ኢትዮጵያ ላይ ደግሞ መጥቷል። በተለይ "ኢትዮ" ብላችሁ ምንም ተቋም የምትከፍቱ፣ የምትጀምሩ ወገኖቼ በልኳ ለመሆን እሰቡበት። ኢትዮጵያ ረቂቅ መንፈስ ናት። የራሷ ዬሆነ አንጡራ ማንነት ያላት የድንቅነሽ ድንቅ ናት። ዲስፕሊኑን የመጠሪያዋን ዬሚመጥን፣ የሞራል አቅም ይጠይቃል። የአውራ አገር መጠሪያ ነውና። ዬማይፋድስ፣ ዬማይነጥፍ ፏፏቴ ሥም ነው ያላት ኢትዮጵያ አገራችን። ይህን ብዬ ዬፃፍኩት በ2014 ደጉ ዘሃበሻ እና ደጉ ሳተናው ላይ ነበር። በፀጋዬ ራዲዮም በተደጋጋሚ አቅርቤዋለሁኝ። በቅርቡም ጹሐፋን በንባብ ዩቱብ ቻናሌ ለጥ