የልብ አውቃዋ ዕውነት መሰከረች። "ጎንደር" "አሳዬ ደርቤ"

 

የልብ አውቃዋ ዕውነት መሰከረች።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
ከእህት ከሰናይት አማረ ፔጅ አገኜሁት ዬብርቱው ፀሐፊ ዬአቶ አሳዬ ደርቤ መካች፣ ማርከሻ ጹሑፍ ነው። አልመቻችልኝ ብሎ በጎንደር ላይ ዬሚዘንበውን ዲን በሚመለከት ልጥፍ ካሰብኩ ቀናት ተቆጠሩ። እንሆ የልብ ዓውቃዋ ዕውነት መሰከረች። ተመስገን።
"ጎንደር"
"አሳዬ ደርቤ"
▬▬▬▬
"➔ሰሜን እዝ ሲወጋ ቀድማ የደረሰች
➔በጀርባዋ የአልቡርሐንን፣ የአልሲሲን፣ የደብረ ጽዮንን፣ የቅማንት ኮሚቴን ጥምር ጦር የተሸከመች፣
➔በዚህ ጥምር ጦር በአገር ላይ የተቃጣን ከሰላሳ በላይ ወረራዎች ከመከላከያ ሠራዊቱና ከአማራ ልዩ ሃይል ጋር ሆና 30 ጊዜ የመከተች፤
➔ወራቤ ባልሰማችበት ሁኔታ ወሎ ሲወረር ሃይማኖቱን ሃይማኖቴ፣ ማንነቱን ማንነቴ ብላ ገስግሳ በመድረስ በቦሩ ሜዳ እና በጦሳ ተራራ ላይ ታሪክ የማይዘነጋው ተጋድሎ የፈጸመች፣
➔በኢሬቻ በዓል ላይ ቄሮዎች ሲገደሉ ‹‹ኦሮሚያ ላይ የሚፈስሰው ደም ከእኔ ጅማት የሚቀዳ ነው›› በሚል መርሕ ኦሮማራን መሥርታ የ27 ዓመቱን የማፊያ ቡድን ያስወገደች፤
➔በእራሷ መስዋዕትነትና የሰላም እጦት ላይ የአገርን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ሦስት ዓመት ሙሉ የደከመች
ጎንደር
▬▬▬
➔አማራን እና ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ጎንደርን ማተራመስ›› የሚል የጥፋት ፕሮጀክት ባነገቡ ኃይሎች ከማተብ ውጭ ምንም አይነት የሐሳብ ልዩነት የሌላቸው ልጆቿ በጠላት መረብ ወድቀው ሰለባ ሲሆኑ የታዘበች፤
➔በቀጣይ ክረምት ‹‹አማራ›› በሚል ማንነት ለሚሰነዘርባት ውጫዊ ጥቃት ውስጣዊ የእምነት ልዩነት ይፈጥሩ ዘንድ ድርጎ በሚሰፈርላቸው ቆብ እና ጥምጣም ለባሽ ፖለቲከኞች መንጋጋ ውስጥ የገባች፤
➔ገዳይም ሆነ ሟች ልጆቿ ሆነው ሳለ ወራቤ እና ወሎ ምድር በበቀሉ የትሕ-ኦነግ ፈረሶች ‹‹ወገኖቼን ገደልሽብኝ›› ተብላ የተለያዩ እምነት ያላቸውን ፋኖዎቿን ትጥቅ አስፈትታ እጇን ለትሕ-ኦነግ ታስረክብ ዘንድ የተጠየቀች፤
➔አራት ዓመት ሙሉ አገራዊ ጠላት ተሸክማ ክርስቲያንና ሙስሊም ልጆቿን ስትገብር ማንነቷን አስታውሰው የተሳለቁባት ኃይሎች፣ በሰሞኑ ውስጣዊ ጥቃት ቱርክ ድረስ በሚሰማ ድምጽ ‹‹ጨፍጫፊ›› ተብላ የተወገዘች፣
ጎንደር
▬▬▬
➔በፌስቡክ ፖስት ቀርቶ በታንክ ጥይት የማይበታተኑ፣ እምነትን መሰረት አድርጎ ጠላት የሚጠነስሰውን ሤራ ማንነትን መሰረት አድርገው የሚተነትኑ ብልህ እና ጀግና ልጆች ያሏት…
➔በእንዲህ አይነቱ የኢንተርኔት ዘመቻ ቀርቶ በዙሪያዋ ለከበባት እልፍ አእላፍ ጠላት እጇን አሳልፋ የማትሰጥ..
እናም እልኻለሁ…
ተስፋ መቁረጥ ከከበደህ ቶምቦላ ሞክር!"


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።