ዕውነት አያፍርም። መርኽም አይርድም።

 

ዕውነት አያፍርም። መርኽም አይርድም።

 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
ዕውነት ለመርኽ፣ መርኽ ለዕውነት ባይተዋር አይደሉም። በመርህ ውስጥ ዕውነት ያሰበለ ነው። በዕውነት ውስጥም መርህ ዬፀደቀ ነው። ድልድያቸው ፋክት ነው።
በዚህ ውስጥ የሰከነ ሰብዕና፣ በዚህ ውስጥ አደብ የገዛ ሰብዕና፣ በዚህ ውስጥ ዬተረጋጋ ሰብዕና ወጀብ፣ አውሎ፣ አያላጋውም።
የመጣ - ቢመጣ፣ የሄደ - ቢሄድ አይደንቀውም። ዕውነት ጽኑ ነው። እርግጥ ነው ሠራዊት የለውም። መርህም ጽኑ ነው። እርግጥ ነው ሠራዊት የለውም። ፋክት ግን ለሁለቱም አይለያቸውም። የእግዚአብሔር ጥበቃም።
ዕውነት አቋሙ የሆነ ሰብዕና ሲፈላ - አይፈላም፣ ወይንም ተንተክትኮ እሮ አይሆንም።
ሲበርድም ቀዝቅዞ ወደ በረዶነት አይቀዬርም፣ ለብ ብልጭ ድርግም እያለ ሲልም አያንጎላችም። ምክንያት። ዕውነትም መርህም አይፈሉም፣ ወደ በረዶነትም አይቀዬሩም፣ ወይንም ለዘው አያፏሹኩም።
በተከተታይ ትጋት፣ በተፈጥሯቸው ልክ አሽተው በልካቸው መስመራቸውን ዝንፍ ሳያደርጉ ይጓዛሉ።
ስለዚህ በአንድ ወቅት የደገፋቸው በሌላ ወቅት ጥሏቸው ሊሄድ ይችላል። በአንድ ወቅት ያቃለላቸው እና ቸል ያላቸው ደግሞ ይመለስ እና ከጎናቸው ይቆማል። እነሱ ግን ያው እነሱ ናቸው። አይበልዙ፣ አይማርቱ።
የወቅት አሞጋሾቻው ጎርፋ ሲያመጣው እና ሲወስደው ያያሉ፣ ያስተውላሉ፣ ይመዝናሉ።
እነሱ ግን ጨለማ፣ ብርኃን፣ ቀን - ሌሊት፣ በጋ - ክረምት ፀደይ በልግ ቢፈራረቁም ምንጊዜም በወጥ ተፈጥሯቸው ይቀጥላሉ። ለክረምት ጋቢ ወይንም ካሊም፣ ለበጋ ቁምጣ ወይንም ቀለል ያለ አልባሳት አያሰኛቸውም።
በሰወች ያለው ዕውነት እና መርህ፣ በተቋማት ያለ ዕውነት እና መርህ መለኪያቸው ነው። ዕውነት ዬተለዬ አጤ ዬለውም። መርኽም የተለዬ ጳጳስ የለውም። ሥርዓት ሲጣስ በህግ አምላክ ይላሉ። አናርኪዝም ፀረ ትውልድ ስለሆነ።
ከደጋፊወቻቸው ጋር አብረው ሲሆኑ አብረው ይተጋሉ፣ ሲፋቱ በፍቅር ዲል ባለ ትህትና ይሸኛኛሉ። ተመልሰው እንደሚመጡ ግን ያውቃሉ።
ዕውነትን እና መርኽን የሚያጠና ሰብዕና፣ የሚያፈላልግ ሰብዕና ለጎርፋማ ውሎ አዳር፣ ለደርሶ መልስ ግጥግጥ እና ሽብሸባ አቅም አያፈስም። ዝምታ ላይ ይገድማል።
የዝምታ ቀለም ማንነቱ ልዩ ነው። አይቀልም፣ አይከብድም። አይብረቁረቅም ወይንም ድብ አይልም። ተደሞ በዕድምታ የተከደነ ሲሳይ።
#ኢትዮጵያ ዕውነት ናት።
#ኢትዮጵያ መርኽ ናት።
#ኢትዮጵያ ዝምተኛ ናት - እማ ዝምታ ህብራዊት።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
#ፎቶው የልጅነት ነው። በልጅነቴም ባህሌ ማተቤ ነበር። ዛሬ አገር ምድሩ ምልሰት ወደ ባህሉ ሆኗል። ተመስገን ነው።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
30/10/2022
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ ዬተፈጠረ ሚስጢር።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።