"የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ሲጀመር ጥቁር፣ትውልደ ህንዳዊው አዲሱ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትር ይሳካለት አይሳካለት፣ በቢሮው ይቆይ አይቆይ ጊዜ የሚፈታው ሆኖ "
"…የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ሲጀመር ጥቁር፣ ያውም ኬኒያዊ መሠረት ያለው ጥቁር፣ በዚያ ላይ ሙስሊም የነበረ ኋላ ላይ እስልምናውን የለወጠ ሰው ነው። በነጮች ዓለም። የመጨረሻውን ወሳኝ የሥልጣን ቁልፍ በጠይም ቆዳ፣ ያውም በጥቁር ይያዛል ተብሎ በማይታሰብበት ሃገር፣ በዚያ ላይ ሃይማኖቱ ብዙዎችን በሚያስበረገግበት ሰፈር አሳምኖ፣ ቆመው አጨብጭበውለት፣ አንድ አይበቃንም ድገመን ብለው 8 ዓመት እንዲመራቸው ወደውና ፈቅደው የታላቋ አሜሪካ ፕሬዘዳንት ሆኖ መርቶ በክብር ሥልጣኑን ለቋል። ይሄ የሆነው በሰለጠነ ማኅበረሰብ ዘንድ ነው።
"…አሁን ደግሞ ልዑሉ ያገባት ሴት የቆዳ ከለሯ ነጣ ያለ አይደለም። የሚወለደው ልጅ ከለር ምን ሊመስል ይችላል? ብለው ንግሥቲቱ በጭንቀት ሊሞቱ በደረሱባት ሃገር ሌላ ክስተት ተፈጥሯል። እንግሊዝና ዘረኝነትን መንገር መቼም ለቀባሪ እንደማርዳት ነው። እናላችሁ እዚሁ ጎረቤት ሃገር እንግሊዝ ሌላ ኦባማዊ ታሪክ ተፈጥሮ ነጩ ዓለም ጉድ ጉድ እያለ ነው።
"…ታላቋ እንግሊዝ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ በሙሉ Totally ይሉታል እነሱ ቶታሊ የሃገሯን 1ኛ ደረጃ ሥልጣን ጠቅላይነቱን የህንድ ዝርያ ላለው ሪሺ ሱናክ ሰጥታው የነጩን ዓለም አስደምማዋለች። በእንግሊዝ ነጩም፣ ጥቁሩም እርግጥ ነው ሠርቶ ይበላል። ለጠቅላይነት ግን የማይታሰብ ነው። ንግሥት ኤልሳቤጥ ይሄን ሳያዩ እንኳንም አረፉ የሚሉም አሉ። ትውልደ ህንዳዊው አዲሱ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትር ይሳካለት አይሳካለት፣ በቢሮው ይቆይ አይቆይ ጊዜ የሚፈታው ሆኖ ለጊዜው አሁን የሚታወቅ ነገር ባይኖርም ነገር ግን በሠለጠነው ዓለም ዓይናችን እያየ ጆሮአችንም እየሰማ ይሄ ተፈጽሟል።
"…ነፍጠኛ ከክልላችን ይውጣ…!! ወራሪ፣ ሰፋሪ በማለት በገዛ ሃገሩ ዜጋውን አርደው የሚበሉትን የእኛዎቹን ደናቁርት መሃይሞችን ባሰብኩ ጊዜ ግን እሳቀቃለሁ። ዐማራ ያገባችሁ ተፋቱ፣ አማርኛ ለሚናገር አትሽጡ የሚሉትን ቆንጅዬ የተስተማሩ ወደል መሃይሞችን ባሰብኩ ጊዜም እሳቀቃለሁ። ከጋምቤላ እና ከዐማራ ክልል በቀር በኦሮሚያ ኦሮሞ ነኝ ከሚል፣ በትግሬም ትግሬ ነኝ ከሚል በቀር በሶማሌም፣ በአፋርም፣ በሌሎችም መምረጥ እንጂ መመረጥ የማይቻልበት ሃገር እንዳለችኝ ሳስብ አሁንም እሰቀቃለሁ። አብዛኛው የኦሮሞም ሆነ የትግሬ ቦለጢቀኛ ግን የሚያስቀው ነገር ሚስቶቻቸው የዐማራ ሴቶች ናቸው። የዐማራ ሴት ተፋልጦ ያገባል፣ ይወልዳል። ቀን ቀን ማይክራፎን በያዘ ቁጥር የሚስቱን ዘመዶች ዐማራን ሲሳደብ፣ ሲያስገድል፣ ሲያፈናቅል ይውላል። ማታ ድክም ብሎት ቤቱ ሲገባ ከዐማራ ሴት በተወለዱት ልጆቹ ተከቦ፣ የዐማራ ሚስቱን እቅፍ አድርጎ ለሽ ይላል። ነግቱ ማይክ ይዞ ነፍጠኛ፣ ወራሪ፣ ሰፋሪ እስኪል ማለት ነው።
"…ኦቦ በቀለ ገርባ ሰምተሃል…!!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ