እዮራዊ ጥሪ ለትግራይ ሊቃናት እና ሊሂቃን። ሰማይም ተናገረ።
ዕውነት ነው ኢትዮጵያ ዬእግዚአብሔር የአላህ አገር ናት። የዕንቁ ምልክት ከቀስት እንድን ዘንድ። በዬጊዜው በዬሰዓቱ። በዬዘመኑ በዬክስተቱ። በዬተደሞው በዬዕድምታው። ምልክት መሪ ጮራ ይላካል። ቢደመጥ። ተመስገን።
#ዕፍታ።
በመቀሌ እና በአዲግራት አካባቢ የመሪት መንቀጥቀጥ ተደመጠ ልክ እንደ 2010 የመጋቢቱ የእዮር ጥሪ ቀረበ።
#እኔ።
ምዕራፍ 7 በብዙ አመክንዮዊ ጉዳዮች ላይ በተዕቅቦ ነው ያለሁት። እምጽፈው የህዝብ ጉዳት፣ የህዝብ የጉዳት ልክ፣ የህዝብ መንፈስ ከጉዳት ማገገም፣ በተፈጥሯዊ መልካም ነገሮች እና እኛ የግል ፍልስፍናዬ ብቻ ነው። ለዚህ ነው ተያዘ ተለቀ፣ ድርድር ንግግር፣ ድል ሽንፈት ቅርቤ ያልሆኑት።
ምክንያት ላም እረኛ ምን አለ ጮርቃውም፣ ዕድሜ ጠገቡም፣ አውራውም፣ አባ ወራውም ፖለቲከኛ፣ ተቋማት "ላም እረኛ ምን አለ" ቀልቡን ሊመራው ባለመፍቀዱ።
ከትነት፣ ከብነት፣ ከውጥን፣ በለጋ ከመቅረት፣ በተስፋ ሹፌር አልባነት መባዘን፣ አፍሶ በመልቀም፣ ለቅሞ በማፍሰስ ዬሜትር እርቀት ዬማይታዬው።
የተሰበሰበ አቅም ቀርቶ የሚሰበስብ ሃሳብ የለም። በወረት በወረቱ አቅም ሲባክን ትውልድ ሲታጨድ ሥልጣኔ ወደ ኋላ 30 ዓመት ሲኳትን፣ ዝልቅ ጽናት ሲፈትን ውኃ ቅዳ ውኃ መልስ።
#የሰማይ አናባቢ መልዕክት በምልሰት።
የሚያስታውስ ከተገኜ …… ደጉ ሳተናው ላይ ከሳይንቲስቶች ያፈነገጠ ዕይታዬን አጋርቼ ነበር። መጋቢት 17/2010 ለመጋቢት 18/2010 እዮር ለተጋሩ ሊቃናት መልዕክት ላከ።
የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ። ያን ጊዜ ሌት ተቀን ስብሰባ፣ መግለጫ ላይ ነበር ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ።
እናም ሰማይ መልዕክት ላከ። እኔ እባካችሁ አዳምጡት ብዬ ተማፀንኩት። በአጤ ሚኒልክ ዘመንም መሰሉ ተፈጽሞ ቀደምት ተጋራውያን ሊቀ ሊቃውንት አዳምጠው ከንጉሦች ንጉሥ ከአጤ ሚኒሊክ ጋር እንደ ተደራደሩ በአስተዋዮ እቴጋ።ጌ ጣይቱ የፖለቲካ ዊዝደም እና ያን ታሪክን ዋቢ አድርጌ ጣፍኩኝ።
ህወሃታውያን ከተፈጠሩበት የትግራይ መንፈሳዊ ፀጋ ውጪ ሆነው ማተብን እንደ ጣውንት ስለሚያዩት ሊያደምጡት አልፈቀዱም ነበር። ይኽው ከዚህ ተደረሰ። ብዙ ሚዛናዊ የፖለቲካ ሂደቶች ማዬት ይቻል ነበር።
"እግዚአብሔር በአንድም በሌላም
ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም።"
"አዲግራት እና መቀሌ አቅራቢያ የመሬት መንቀጥቀጥ ተሰማ። ትናንት ሌሊቱን መጠኑ 1.4 ማግኒቲዩድ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ በስሜን ኢትዮጵያ መሰማቱ ተዘግቧል። ሌሊት 7 ሰዓት ላይ ዬመሬት መንቀጥቀጡ ዬተሰማ ሲሆን መንቀጥቀጡ አነስተኛ መጠን ዬነበረው ሲሆን ንዝረቱ ዬ10 ኪሎሜትር ጥልቀት እንዳለው፣ ቮልካኖ ዲስከበር ዬተሰኜ ዬመሬት መንቀጥቀጦችን አስመልክቶ የሚዘግብ ድህረ ገጹ ላይ አሳውቋል።"
ዘገባው የፈታ ደይሊ ነው።
ያን ጊዜም ኢትዮጵያ ምጥ ላይ እያለች ሌሊት መቀሌ አቅራቢያ በ2010 መጋቢት ላይ፣ ዛሬም ህዳር 2014 መቀሌ እና አዳርቃይ አካባቢ ህወሃት ቀጠናዬ በሚላቸው ዬቀሩት መወላጃ ባዕት።
ያንጊዜም ቀዝቃዛ ጦርነት፣ ዛሬ ህዝባዊ ጦርነት። ዳኛው ግን ይልካል ያን ብሩክ መንፈሳዊ የተመረጠ ቦታ ለማዳን።
#ህውኃታውያን፣ የተጋሩ ሊቃናት።
አድምጡት። አታቃሉት። አንድ ቀን እንደ ተራዘመ ታውቋል። የአሜሪካ ፕላን ነበረው ማለት ይመስለኛል። ሁሉን ላለማጣት እኩል ዬአሸናፊነት ስንቅ እና ትጥቅ።
የስኬቱ ቃርሚያ ተምሳሌነቱ በአወንታዊም ይሁን በአሉታዊ በግሎባሉ የዓለም ዓቀፍ ዕድምታ ጉልበታም ነውና። አሻማ ካለች ኢትዮጵያ ብዙ የኃያላን መንፈስ ይነኩታሉ። ብዙም ያልታሰቡ የመንፈስ አቅሞች ጥላ ከለላ አግኝተው ያቆጠቁጣሉ። እና ጥንቃቄው በጥልቀት የሚታይ ይሆናል።
አስታውሱ የዛሬ 10/12 ዓመት በአሜሪካን አገር በአንድ ጣሊያናዊ ሰቲት፣ ኤርትራን፣ ሱዳንን ያማከለ ጥናት እንደ ነበር ዶር መስከረም ደቺሳ ገልጠዋል። እሳቸውም በወቅቱ ታዳሚ ነበሩ። ግን እንደ ዋዛ ያዩት ጉዳይ ነበር። ሰቲትን እንደ ቁራጭ መሬት የሚያዩት ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ አክቲቢስቶች ይገርሙኛል።
ሰቲት የአፍሪካ ቀንድ ህሊና ነው። ለመካከለኛው ምስራቅ አፍሪካም ዓይነታ እስትራቴጂክ ቦታ ነው። ቀደምቶች ጎንደርን የአገር ዬነቃ አንጎል ሲያደርጉ በትንቢትም በዊዝደም ልቅና እና ልዕልና ነበር።
እንደ አዘቦት ልብስ አቃለህ ዬምታዬው አይደለም ነገረ ሰቲት ሁመራን። በዬጊዜው አቃለው ለሚዩ በልኩ አስረድቻለሁ። አራቱን ነጭ ወርቃት ትቼ ማለት ነው። እሱ ሲዋህድ ቫወል ነው።
#በዚህ በአሁኑ የፖለቲካ የኃይል አሰላለፍ።
የዓለም ሁለት ካንፕነት በጎርባቾብ ፕሮስተሪካ ቢበወዝም መንፈሱ ግን አለ። ራሺያ፣ ኪዩባ፣ ቻይና፣ ስሜን ኮርያ ላይ አለ። አሁን በዩክሬን እና በራሽያ፣ በታይዋን እና በቻይና፣ በምዕራባውያን እና በአውሮፓ ህብረት፣ በአውሮፓ አገሮች፣ ያለው የፖለቲካ ፍልሚያ ዬዛ መንፈስ ቅኝት ነው።
ኢትዮጵያ ማዕከሉን መርጣ በገለልተኛ አቋሟ መጥናት ያተርፋታል። ደሃ አገሮች መራኮቻቸው ስለሆኑ። ኢትዮጵያ ድህነቷ የኢኮኖሚ እንጂ መንፈሷ የአህጉር ያህል ዬፈረጠመ ፈርኃ እግዚአብሔር እና ፈርኃ አላህ ያለው ነው።
ዬሳተው ሁሉ ቅርፊት ይሆናል። ከዛች አገር የሚነሳ ማናቸውም ሁነት አቅሙ ተፈጥሯዊ ነው። ፀጋችን አለማወቃችን፣ የተፈጥሯችን ህግ በመተላለፋችን ነው ድካማችን የበረከተው።
ዬሆነ ሆኖ ፈጣሪ በቃችሁ እያለ ነው። የተጋሩ ሊቃናት ይህን ያን ወስኑ ሥልጣኑ የለኝም። የሰማያ ሰማያትን ሚስጢር መተርጎም፣ ማመሳጠር ቢቀር ግን አንብቡት።
ዓለም በዬጊዜው በግሎባል ችግር ትዋጣለች። የኢኮኖሚ ንጠቱም በርትቷል። ድንገተኛ አደጋ፣ ወረርሽኝ፣ ቀልብ ሳቢ ዬተፈጥሮ አደጋም ይፈጠራል።
በሰው መዳፍ ውስጥ የሌሉ ክስተቶች ይፈጠራሉ። እና ምንም አድማጭ ዬማይኖርበት ዘመን ይመጣል። አሁን ያለው ቅልጣን ያልቃል። ሂደት ነዋ። ትሰለቻላችሁ፣ በሌላ አፋጣኝ ሁነት ትዋጣላችሁ።
የሹም ዶሮነት ዬሰማይ ምሰሶ፣ የምድር ካስማ አይደለም። ይህን ዬመሰለ ዕድል መቼውንም አታገኙትም። ሳይዝግ ቅደሙት። ዬመቀሌ እናቶች፣ ህፃናት፣ ምጥ ላይ ያሉ እናቶች፣ በሰሞናቱ በእዮር የሚጠሩ ደንጋጦች ሁሉም ያስጨንቃል። ፖለቲካ ለሰው ከሆነ ሰው ይትረፍ። ከጭንቅ ይገላገል። ድምጽ ለድምጽ ይገናኝ።
ዘመን ከዘመን ስሜን በጦርነት???? አለመሰልጠን።
ታውቃላችሁ እንዴት እንደሞገትኳችሁ። ሥልጣን በፈቃዳችሁ ስትለቁ አትንኳቸው ብዬ ዘብ ነበርኩኝ። ያን ሁሉ ጊዜ እስከ አፋር እና አማራን በመጠነ ሰፊ እስካጠቃችሁ ድረስ በዝምታ ነበርኩኝ።
ብራናዬ ስለ ህወሃት አያስተናግድም ነበር። በምዕራፍ አንድ ጦርነት እናንተው ጀምራችሁ ጉዳቱን በትጋት እዘግብ ነበር። ኃላፊነት እና ተጠያቂነት የወቅቱ ያለውን ቤተ መንግሥታዊ ባለ ሥልጣን ብቻ ነበር የሞገትኩት። ግን አባከናችሁት። ሁሉንም በተናችሁት። በዛ። እጁግ በዛ። ይበቃል።
ያን ጊዜ ዬፃፍኩትን አስኳሉን ብቻ ለማጠናከሪያ አቅርቤዋለሁኝ። ሙሉውን ለማንበብ ለምትፈልጉ ብሎጌ ላይ አለ። ከሥጋ ለባሽ ይልቅ የፈጣሪ ፈቃድ ይደመጥ ነው ቁም ነገሩ። ያን ጊዜ ያ ተደምጦ ቢሆን ኖሮ ከልብ ይህ ሁሉ ድቀት ተንበርክኮ ባልታፈሰ ነበር። ቢያንስ የትናንት ሌሊቱ ይደመጥ።
በ2010 እኢአ ይህን ጽፌ ነበር። በመቀሌ አቅራቢያ ስለተከሰተው የምድር መንቀጥቀጥ።
#ይድረስ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌሰቶ አራማጆች በሙሉ። ለመሪዎችም እንዲሁ ይድረስልኝ ብያለሁኝ።
አዲስ አበባ ይሁን
መቀሌ፤ መቀሌ ይሁን አዲስ አበባ።
ከሥርጉተ ሥላሴ (Sergute©Sselassie)
25.03.2018 (ከጭምቷ - ሲዊዘርላንድ)
· የእዮር ደውል ድምጸት ተደማጭነት በዳግማዊ ዐጤ ሚኒልክ ዘመነ መንግሥት፤
2/ እንደ ታሪክ ጠሐፊዎች ገለጻና ዕድምታ … በሌላ በኩል በዳግማዊ ዐጤ ሚኒሊክ ዘመን የዐጤ ዮሖንስ የጽናት፤ የማተብ ምልክትን በደሙ ያሰከበሩት የነፃነት አባት ልጅ አልጋው ለእኔ ይገባኛል ብለው በዳግማዊ ዐጤ ሚኒሊክ ላይ አመጡ። ሽማግሌ ሲላክም አሻም ብለው፤ ጉግስ ለመግጠም ወሰኑ። ነገር ግን ልክ እንደ ዛሬው ትግራይ ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ። ፈጠሪ እንደ ዛሬው ምልክት ሰጠ እዮር ደማቅ ድወል በጉልህ ደወለ። አባቶቻችን / እናቶቻችን ብልህነታቸው የሰማይ ነበር። ዕምነታቸውም ጽኑ እና የማያወላዳ ነበር። ስለሆነም የሰማዩን የቴሌቪዥን ዜና አዳመጡ፤ ምድራዊውን ሳይሆን። እናም ፈቃዱን ፈጸሙ። ሐገርም ህዝብም አረፈ። ክብር ለቀደሙት አስተዋይ አባቶቻችን / እናቶቻችን።
• ታሪኩ እንዲህ ይላል …
„ራስ መንገሻ ዮሖንስ ሁለት ጊዜ እጅ ለመንሳት ወደ አዲስ አባባ ተጉዘው ነበር። ሁለቱም ጉዟቸው በንጉሡና በእቴጌይቱ የተደረገላቸው አቀባባል፤ መስተንግዶም ግሩም ነበር። በተለይ እቴጌ ጣይቱ የለግሷቸው ልዩ ቀበሬታ እና እንክብካቤ ተገቢውን ቦታ እና ትርጉም ሊያገኝ አልቻለም። በሚዚያ 1899 ራስ መንገሻ ራሳቸውን እንደ ተበደሉና እንደ ተገፋ በመቁጠር ማፈንገጣቸውን እና የትግራይ ንጉሥ ተብለው ባለመንገሣቸው ቅሬታ ተላብሰው ለማመጽ ከተከታዮቻቸው ጋር ሲመክሩ እንደነበር የሰሙት እቴጌ ጣይቱ በግላቸው ይሄን የተማህጽኖ ደብዳቤ ፃፉ።“
„ይድረስ ለወዳጄ! ለልጄ! ራስ መንገሻ የላኳቸው ሰዎች መቼም ለጃንሆይ ወደ ሽዋ መቼም አልመለስም ማለትህን ሲናገሩ ሰምቼ አጥብቆ ገረመኝ! ደነቀኝ! እኛ የአንተን ቤት አንሥራለን ብለን ስንደክም የእኛን ቤት አፈርሳለሁ ብለህ አሰብክ?! ይህንን ነገር እግዚአብሄር ይወደዋልን?! ይህን ክፉ ሃሳብህን ብትተወውስ የሰይጣናትን ክንፋቸውን ስበረው ከዚህ ቀደም ወንድማማቾች ራስ አሉላ፤ ራስ ሐጎስ እርስ በርሳቸው ሲተላለቁ ምን ያህል እንዳዘን ታስታውሳለህን?! በዚህ አሳዛኝ ክስተት የሚደሰቱ የኢትዮጵያ ጠላቶች ብቻ ናቸው። ልጄ ወዳጄ! እኔ እናትህ በዚህ በአደረከው ነገር በጣም አዘንኩኝ። አጥብቄ አለቀስኩኝ። እኔስ ቁሜም ተቀምጬም ባስበው አንተን የሚያስቀይም ነገር የተፈጸመብህ የቱ ጋር እንደሆነ ለማወቅ አልቻልኩም።“
„Ethiopia | ክፍል 2: እቴጌ ጣይቱ ብጡል ብርሃን ዘኢትዮጵያ | Etegue Taitu በመኮንን ወ/አረጋይ Sheger FM,Sinkisar“
• ከዚህም በተጨማሪ እቴጌይቱ …
„መምህር ዜና እና መምህር ፈቃደን፤ መምህር አካለ ወልድን፤ የሐይቁ መምህርን አባ አምደ ሥላሴን፤ የግሸኑን ግራ ጌታ ውበትን፤ አባ ወ/ ገብርኤልን መስቀል እስይዘው ወደ ትግራይ በመላክ ነገሩ በሰላም እንዲያልቅ መማጸናቸውን ቀጠሉ።““
ዳግማዊ ዐጤ ሚኒሊክም በበኩላቸውም „የትግራይን አድባራት በሙሉ ይዛችሁ እኔ በድዬህ ከሆነ ማረኝ! ይቅር በለኝ! ብላችሁ መስቀሉን ተሸክማችሁ ውደቁና አስታርቁን ብለው መነኮሳትን ሽማግሌዎችን ላኩ።“
„ይህ ሁሉ ጥረት ባለመሳከቱ በራስ መኮነን የተማራ ጦር ወደ ትግራይ ዘልቆ መቆጣጠር ጀመረ። ራስ መንገሻ ራስ ስብሃት „በደገሃሙስ“ ምሽግ እያሉ ግትር አቋማቸውን ለመቀዬር ያስገደደ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ተከሰተ።“
የሚኒሊክ ዜና መዋዕለ ጸሐፊ እንደሚሉት „ የመሬት መንቀጥቀጡ እግዚአብሄር በያዝኩት አቋም ያለመደሰቱን፤ እንዲሁም ለእሳቸውም አብረዋቸው ካሉት የሰይጣን ሃሳብን ከሚያራምዱት ወገኖች እንዲነጠሉ ምልክት ያሰዬ ነው ብለው እንዲያሰቡ አደረጋቸው።
ከዚህ ክስተት በኋዋላ ራሳቸው ራስ መንገሻ ዮሖንስ ለራስ መኮነን እና ለራስ ሚኬኤል ነገሩን በሽምግልና ጥረት እንዲያልቅ ተማጸኗቸው። ራስ መኮነን ከእቴጌ ጣይቱ ጋር ሆነው ሁለቱም ድንጋይ ተሸክመው በእንብርክካቸው ከንጉሡ ዳግማዊ ዐጤ ሚኒልክ እግር ስር በመውደቅ ለራስ መንገሻ የሖንስ ምህረት ያደርጉላቸው ዘንድ ተማጸኑ ፈቃድም አገኙ።“ አዬችሁ እነ ቤተ - ተጋሩ ራስ መንገሻ የሖንስ የልባቸውን ጥልቅነት እና ሰፊነት የቻይነት አቅም እና ተስጥኦ - ምስባክ እኮ ነው። አናባቢም ተነባቢም።
ዛሬም እዬታመሱ በ4 ኪሎ ያሉት መሪዎቻችሁ ትክክል አለመሆናቸውን ነው ለማጠዬቅ ነው „ታሪክ ራሱን ይደግማል“ እዮር አዲስ ልክ እንደ ሚዘያው 1899 በተቀራረቢ ወራት የመሬት መታወክ መቀሌ አቅርቢያ የተደመጠው። በፊትም ንግሥና ይገባኛል ዛሬም ጠቅልለን እንያዝ ነው። 27 ዓመት አልበቃነም ነው። ፈጣሪ አምላክ ግን በቃ! ብሏል።
· ማጣቀሻ ለህሊና ዳኝነት።
እቴጌ ጣይቱ ለራስ መንገሻ ዮሖንስ በጻፉት መልዕክት ላይ እንዲህ የሚል አለበት
„እኛ የአንተን ቤት አንሥራለን ብለን ስንደክም የእኛን ቤት አፈርሳለሁ ብለህ አሰብክ። ይህንን ነገር እግዚአብሄር ይወደዋልን?!“ ይህን ዛሬ የወያኔ ሃርነት ትግራይ በድፍረት እና በማን አብኝነት ፈጽሞታል። በኮ/ ደመቀ ዘውዱ ትህትናዊ ሃሳብ ላይ የወሰደው የእብሪት እርምጃ ይሄውን ነበር። የትግራይን ቤት ሥራ በቅንነት ደሙን ወጣትነቱን ለገበረ፤ ለተገበረ፤ ዛሬ ማዕት ወረደ በመላ የአማራ ህዝብ ላይ። በመላ ኢትዮጵያ ላይም … አቧራዊ ፍርድ በሞት ቀለም። ማድመጥ፤ ማዬት፤ ማስተዋል ከህሊና ጋር ያላቸው ውል ያልተፈተሹ ስለመሆኑ የጠራ ግብረ ምላሽ የሚሰጡ ብዙ እጅግ በርካታ አምክንዮችን ማንሳት ይቻላል።
· መታበይ ፍርዱን ከሰማይ ነው የሚያገኘው።
ዛሬ ዕምነትም፤ ጽናትም፤ ሐገራዊነትም፤ ሃይማኖትም የጎደለው የወያኔ ሃርነት ትግራይ በትዕቢት ያን የተፈጠረበትን የትግራይ መሬት በክፉ ምግባሩ እያስነሳ ነው። ነገም ፍዳውን መለካት አይቻልም። እትዬ ትግራይ ግራጫም ጠፍቶባታል።
ባለግራጫዎችማ ቀደም ብለው ተመንጥረዋል። የባዶ ስድስት ሰላባ ሆነዋል። የሰማዩ ዜና የሚነግርን የዚህ ሁሉ ግፍ ድምር በቅጽበት ሁሉንም ነገር እንዳልነበር ማድርግ እንደሚቻለው ነው። „በቃህ!“ ነው የሚለው የእዮር አደባባይ ወያኔ ሃርነት ትግራይን። „ትርምሱን አቁም!“ ነው የሚለው የሠራዊት ጌታ እግዚአብሄር። „ህዝቤን ልቀቅ!“ እያለ ነው አዶናይ መቻሉ ጫፍ አድርሶ። „የህዝቤን ሰለሙን አትወክ!“ በማለት ሠራዊተ መላዕከትን በረድፍ አሰልፎ እዬጠበቀ ነው።
„ህዝቤን አትጨርስ የከፈትከውን ባሩድ ዝጋ!“ እያለው ነው አማኑኤል ለወያኔ ሃርነት ትግራይ እና ሰይጣናዊ መካሪዎቹን ሁሉ እያስጠነቀቀ ነው። „መታበይህን አስታግስ!“ ብሏል የእዮር አዳባባይ። „ የመንፈስ ሃብት አንድስም እንኳን እርሾ የለህም ቁጣዬን የ እኔን የፍርድ መቅሰፍ ሊያስቆም፤ ሊገድብ የሚችል አንዳችም ሃይል የለህም“ እያለ ነው የሰማዩ ዳኛ። „ቁጣዬ ሲነድ እንኳንስ ሰው ሰራሽ ወንበርህን እኔ የሰጠሁኽን ሰውነትን ለመሸከም ይሳንሃል፤ የ27 ዓመት የቁንጣን ጊዜህ ሲጠናቀቅ የቅጽበት ናት“ እያለው ነው ለወያኔ ሃርነት ትግራይ የሠራዊት ጌታ ልዑል እግዚአብሄር ከእዮር አደባባይ ሆኖ። ጆሮ ያለው ያድምጥ፤ ልብ ያለው ያስተውል ነው የዛሬው የብራና ቀለም ተደሞ።
· ቁጣ የሰማይ።
ይፋጃል። ቋያው አያሰቀርብም። የነዲዱ ወላፈን አያስጠጋም። እሳቱ ከተለመደው የገሃዱ ዓለም ፍብረካ ውጪ ነው። ፈጣሪ ሲቆጣ ነበልባሉ ከሰውኛ በላይ ነው። ሳይንስ ምንትሶ ቅብጥርሶ ሱናሜውን ማስቆም አይችሉም። ይህንም ዋልድባ ሲደፈር በመቅድሙ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ቁንጮ እስከ ጭንቅላቱ ነበር የተሰናበቱት።
ያ በሰውኛ ብቻ ተተርጉሞ ነው የታለፈው። ነገር ግን ታምሩ፤ ገድሉ የሰማይ ነበር። ዛሬ በካቴና ላይ ታስረው የፈጣሪን የቀራንዮ፤ የጎለጎታ ሰቆቃ በመቀበል ላይ ያሉ የዋልድባ አብርንታት አባቶች ስለምክንያት ነው ያን ያህል ፍዳ የሚከፍሉት። እንኳንም ታሠሩ።
የተከበሩ ፕ/ አስራት ወ/ደዬስ ሲታሠሩ እንኳንም ታሠሩ ብዬ አዕምሮ ጋዜጣ ላይ ጽፌ ጋሼ አብርሃም ጉዝጉዜ „ስለምን ብሎ“ ጠይቆኝ ነበር። ሐብት የሰው ነው። የሰው ሐብት ደግሞ የፈጣሪ ነው ብዬው ነበር። ትውልድ የማይተካቸው አባት ፕ/ አስራት ወልደዬስ በጤናው ዘርፍ እጃቸው አዳኝ ነበር። ሲዳስሱ ብቻ ፈውስ ነበረው።
ከዚህ በላይ በሰዋዊነት ለተገለለ እና ጥግ ላጣ የአማራ ማህበርሰብ የፈጸሙት ገድል ደግሞ የቅድስና ብትህትና ነበር። ለዛ ብትን አፈር ላጣ ከርታት ሰፊ ማህበረሰብ አለሁህ፤ እኔን ልገብርልህ ብለው ራሳቸውን ገበሩ። ያ የበለጠውን ክብር እና ሞገስ በፈጣሪ ዘንድ አስገኘላቸው። ሚሊዮኖች አባታችን አሏቸው። ዛሬም ጊዜ ጥሩ ነው ዳግሚያ ትንሳኤውን እያዬን ነው።
የዋልድባ አብርነታት ገደም ድርሳነ ታሪክ እንደሚነግርን ራሱ አማኑኤል የገደመው ነው። የባህተውያን እስርም እንደ ሥጋ ሳይሆን እንደ መንፈስ ፈጣሪ በጥበቡ በሰውኛው ሲዖል ውስጥ ሆነው አንዷ ቅንጣት ዕንባቸው አዮርን እንዲያስከፍት የተፈቀደላቸው ናቸው። ሰማዕት ናቸው።
እነሱ እኮ ገዳምም ቢኖሩ ፈተና ካልኖረው ገዳሙን አይፈቅዱትም። ምነው ፈተና አዘገዬህ ብለው ሁለት ሦስት ሱባኤ ይገባሉ። ልክ ቅዱስ አባት አበርሃም „እንግዳ እንዴት ነሳህኝ“ እንደሚለው ማለት ነው።
የዋልድባ መነኰሳት ፈጣሪ ዕንባቸውን ቆጥሯል። ገድለኛ ምልክትም ልኳል። ይህ ምልክት ለሁሉም ነው ለእክሌ ተከሌ አይልም። ኩራታችን፤ ክብራችን ሥማችን ወይንም ማንፌስቷችን፤ ዝናችን፤ ወይንም ጠበንጃችን ነው እኛን የፈጠረን፤ የቀረጸን አድርገን የምናስበው። ግን የፈጣሪ ሃይል ከሁሉም በላይ ነው። ሞት ራሱ የተረሳ ነው።
… በፈጣሪ የክት እና የዘወትር፤ መዳብ እና ነሃሳ የመደብ ምደባም የለውም። በገሃዱ ዓለም እና በመንፈሳዊ ዓለም መንፈስ መሃከል ትልቅ ገደል አለ። ገደሉን መሻገር የሚችሉት መንፈሱን ያከበሩ፤ የተቀበሉ፤ አለህ ብለው ያመኑት ብቻ ናቸው። ድምጹን የሚሰሙት። የተፈቀደላቸው ብቻ ናቸው።
ትውልድ መዳን የሚችለው የመጀመሪያው „ሰውን የፈጠረው ፈጣሪ ነው“ ብሎ አምኖ መቀበል ሲቻል ብቻ ነው። የፈጠረውን ፍጥሩን እንደ ጉልት ገብያ በሸቀጥ መድቦና በሜትር ሽንሽኖ፤ እንደ ጣቃ በቦንዳ መትሮ ሰብዕናውን ማግለል ወይንም ማቅረብ ወይንም መፈቅፈቅ ጠቡ ከአንድዬ ጋር ብቻ ነው …።
ፈጣሪ አምላክ ሰውን ሲፈጥረው እንዲያመስግነው ነው። አመስጋኙን የሚጻረር፤ የሚያጠፋ ደፋር እስከ ልጅ ልጁ ቅጣቱን ይልክበታል … ለዚህ ነው ቀደም ባሉ ጹሑፎች ወይኔ ሃርነት ትግራይም እና እትዬ ትግራይም ድንጋይ ተሸክመው የኢትጵያን ህዝብ የፈጠረውን አምላክ ይቅርታ ይጠይቁ እያልኩኝ ስቸከችክ የከርምኩት።
አሁን ከመሻል ወደ ባሰ ረግረግ ላይ ነው። የመጨረሻው የምልክት ደወል ተደውሏል። ከእዮር … ቀሪውን ደግሞ ከኛ የሚለጥቁት ትውልድ የሚያዩት ይሆናል።
· #የ4 እግር ውርክብክብ።
ቀኑ በፈጣሪ የታቀደ ነው። ቀኑ በፈጣሪ የተቀባ ነው። ቀኑ በፈጣሪ ለድህነትም ወይንም ለጥፋትም የተጋድሎ ምልክት ነው። ትግራይ መቀሌ አቅራቢያ ታዬ የተባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ይህ ምልክት ዛሬ ያለውን የ4ኪሎ ቤተ መንግሥት ውርክብ ጸጥ ረጭ አድርጎ በአንድ ቃል፤ በሙሉ ድምጽ፤ ያለመከፋፈል መፍትሄው አናት ላይ እንዲኮን ፈጣሪ እራሱ መወሰኑን ያበሥራል።
ቅብዕ የፈጣሪ ነው …. ቅብዕ የተሰጠው አለ። አመጣጡም ሁኔታውም ሂደቱም መሠረቱም አዲስነቱም ልብ ተብሎ ሲመረመር፤ ተወራራሽ ነገሮች ሲጠኑ ፈጣሪ በእሱ አድሮ ምን ሊሠራ እንደሚችል አማኑኤልን በርከክ ብሎ መጠዬቅ ነው። መልሱ እዛ ላይ ይገኛል።
ይህ ከተረገጠ ግን ወዬ ነው። ኢትዮጵያን የጠበንጃ ሃይል አይደለም የሚገዛት፤ ፈርሃ እግዚአብሄር ብቻ ነው። ስንቋም ትጥቋም ፈርሃ እግዚብሄር ነው - ለሐገረ ኢትዮጵያ። የሚያስተዳድርትም ፈርሃ እግዚአብሄር ብቻ ነው።
ራሱ ቤተ መንግሥቱ እኮ ረክሷል ይሄ ያልባለቀች ዕንቡጥን አስገድዶ የደፈሩ ምኖች ነው ያሉበት? በዬደረሱበት ከሥጋ ፈቃድ ጋር ግብ የሚገጥሙ፤ ገዳዮች የበረከቱበት። ደም- ደም ይሸታል ዓውዱ።
ዘማዊነት እንደ ሰዶም እና ገሞራው ዘመን ነግሦል እኮ። በዘረፋ ነፍስ ሁሉ በሌብነት ጨቅይቷል። በሃጢያት በተነፋ ባሎናዊ ነፍሳት ተውጧል - ቤተ ምክር ቤቱ ቁንጮዎች። ጠረኑ በሰው ደም እና እንግልት እጅግ ይከረፋል። ይጎፈንናል። ታዳጊ ወጣት የደፈረ ለጠቅላይነት ይቀፋል - ለመስማትም።
ይህን አሸኮኮ አድርጎ መውደቅ መነሳት ከጸያፍነትም በላይ ነው። ምን ገዳዩም አፈናቃዩም ሴረኛውም ገመናውን ተሸክሞ በረድፍ ተኮልኩሎ ሲመክር ሲታመስና ሲተራመስ ውሎ ማደሩ እዬተደመጠ ነው? እፍረት እኮ ክብር አይደለም - አይደል? ሎቱ ስብሃት። መጥኒ ለአንቺ ለእትዬ ትግራይ … ቅል ቋንቁራው ይጠቅመኛል ብሎ ለሚያጋብሰው ድውይ መንፈስ …
· ጥሞና!
የፈጣሪን ጥበብ ተዳፍሮ የሚገኘው የረከሰውና የበከተው የቤተ መንግሥት ጠረን መታጠብ አለበት - በጥሞና። በአዲስ ቡቃያ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ አዳኝ ሃሳብ በአዲስ ልዕለ ንዑድ መንፈስ መጽዳት አለበት የገናናው ኢትዮጵያዊነት መወሰኛ ምክር ቤት።
ለዛውም እያንዳንዷ ቅንጣት እርምጃ በርከክ ብሎ በጸሎት፤ በሱባኤ፤ በስግደት፤ በድዋ መትጋትን ይጠይቃል - በጥሞና እና በተመስጦ። ሐዋርያት እኮ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ሲሰጣቸው በጸሎት ነው የተጉት።
ለክብሩ ያደረጉለት አቀባላል በአርምሞ ነው። ስለሆነም ዘመናይነት ካባውን መሬት፤ ትቢያ ላይ መነጠፍ አለበት - ራስን ዝቅ አድርጎ። ቅብጠቱ፤ ቅልጣኑ፤ ለዛሬ አይሆንም። ደወሉ ከባድ ነው ‚የመሬት መንቀጥቀጥ‘ ባልታሰበ ቀንና ሰዓት ግን በወሳኝ የነፍስ ጉዳይ ከች አለ።
ድምጹ የእዮር ነው። ቅንጥ እንዲቆም ነው እዮር መልዕክቱን በማስጠንቀቂያ የላከው። ምልክቱን እንዲያሳይ በተፈለገበት ቀንና ሰዓት ነው ውሳኔው እንሆ የተላከው።
ይህን ልብ ያላችሁ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ማህበርተኞች፤ ሌሎችም አጃቢዎች ከልባችሁ በጥሞና ሆናችሁ፤ በተሰበረ ልቦና መመርመር የእናንተው ተግባር ይሆናል - ትእዛዝ ከቶውንም አይደለም።
እንዘምን የሚሉ ለውጥ ፈላጊዎችም ለውጥን መፍራቱ የፈጣሪን ደወል መጋፋት እንዳይሆንባቸው ከሚያመልኩት ዕምነት ጋር በውል በጥሞና መቀራረብ፤ መነጋገር የሚያስፈልጋቸው ይመስለኛል አሁንም ትእዛዝ ከቶውን አይደለም። ጊዜ ሳያጠፉ ቢሆን ይመረጣል - በትህትና። በአልባሌ ቀን አይደለም ይህ የመቀሌው የመሬት መነቃነቅ፤ ህውክት የተከሰተው።
በትክለኛው ነጥብ ቀን ላይ ነው። የእዮር ድምጽ ርግጠኛ ድምጽ ነው። ተረገጡን ልካችን እስከ ምን እንደ ሆነ ነግሮናል። „ልብ ያለው ሸብ።“
„እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የኀዘን የልቅሶና የጩኸት ድምጽ በራማ ተሰማ ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች ፤ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ድምጽሽን ከለቅሶ ዐይኖችሽንም ከእንባ ከልክየይ ፤ ለሥራሽ ፤ ዋጋ ይሆናልና ፥ ይላል፡፡ እግዚአብሔር ፤ ከጠላትም ምድር ይመለሳሉ። ለፍጻሜሽም ተስፋ አለ ፥ ይላል እግዚአብሔር ፥ ልጆችሽም ወደ ሀገራቸዎ ይመለሳሉ። »
• የፈታ ደይሊ የዛሬው የመሬት መንቀጥቀጥ ዜና ሊንክ። https://www.youtube.com/watch?v=3rE3lavnsXk
Ethiopia - "ድርድሩ በነጌታቸው ተማጽኖ ተራዘመ፣ ተደራዳሪዎች የፈጸሙት ቃለ መሃላ፣ ህወሃትን የሚከፋፍለው የመንግስት ጥያቄ፣ በትግራይ የመሬት መንቀጥቀጥ"
የዛን ጊዜ ምንጬ ልክ ይህ ነበር። ሎድ ሲበዛ ብዙው ይሰረዛል። ተሰርዞ ሊሆን ይችላል።
„Ethiopoa ሰበር ዜና አስደንጋጭ በመቀሌ የደረሰ
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
31/10/2022
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ