ጁቪተር ላይ ዬባጁት ከፍተኛው የህግ ባለሥልጣን።
ጁቪተር ላይ ዬባጁት ከፍተኛው የህግ ባለሥልጣን።
"ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"
ምን አደረግሁህ የማከብርህ ጋዜጠኛ አቶ ሥሜንህ ባይፈርስ ማህፀኔ የተቀረደደበት መልስ ነው ያዳመጥኩት።
ለጥቂት ጊዜ እናቴን በስልክ አገኝ ነበር ከህወሃት ሽኝት በኋላ። አንድ ቀን እንዴት ያለ ደፋር፤ ጀግና ጋዜጠኛ ቢሆን ነው ሥምሽን ያነሳው፤ በዋልታ ቴሌቪዥን ሁለትጊዜ አነሳሽ። አንቺም ደፋር ዶር መራራ ጉዲናን ሞገትሽ። እና ይህን አዳመጥኩት። በአጠገቤ ብትኖሪ እሸልምሽ ነበር። ለእሱ ደግሞ እፀልይለታለሁ አለችኝ።
ሥሜን ስለ አነሳ ሳይሆን አብዮት ስላካሄደ ነው እሚደንቀኝ። ዬእኔን ሥም ማንሳት እንደ ወንጀለኛ ነው ዬሚያስቆጥረውና። ይህን በመርኽ ደረጃ በረቂቅ ሁኔታ የሞገተ ነው። ውስጡን አይቸበታለሁኝ። ጠረኑ ምን ንጥረ ነገር እንደሚያፈላልግ ተረድቻለሁኝ። ዛሬ ጥዋት ያገኜሁት ቃለ ምልልስ ይገርማል።
ሥማቸው አልተጠቀሰም - ተጠያቂው ማህበረ ኦቦ ይሆናሉ። ኃላፊነታቸው አልተጠቀሰም የሁሉም ቦታገዢ ማን ስለመሆኑ መከደን ስላለበት። እንዲህ በመናጆ የሃሳብ ፈሰሱን ውልብልቢት ይዤ ስጓዝ ያው የእሱበእሱ ቤተ -ላዕላይነቱ ስለመሆኑ ውይይቱ ፍንጭ ሰጠኝ።
"መግቢያው በዳኞች በአጠቃላይ ዬፍትህ አካሉ፤ ዬዳኞች የዲስፕሊን እና የአሰተዳደር ጉዳይ?"
ከመጨረሻው ስነሳ "ህገ መንግሥቱ ተጣሰ" የጋዜጠኛ ሥሜንህ የጭብጥ ዕድምታ ነው። አላግባብ ሠራተኞች ቦታ ያዙ?
"ሹመት ሳይሆን ምደባ" ነው ይላሉ ባለሥልጣኑ። ከዚህ ላይ ጋዜጠኛ ሥሜነህ ባይፈርስ ያልገባው ነገር ያለ መሰለኝ። "ሹመት" በመንግሥት የሚሰጥ ሲሆን "ምደባ" ግን በፓርቲ መመሪያ ዬሚሰጥ የኃላፊነት ደረጃ ነው። በሁለቱ መካከል ልዩነት አለ። ተመሳሳይነትም አለ።
ለሹመቱም፤ ለምደባም እጩ የሚያቀርበው አውራው ፓርቲ ነው። አፈፃፀም ላይ ይለያያል። ሹመት በተወካዮች ምክር ቤት፤ ወይንም ጉዳዩ በሚመለከተው አካል ኦፊሻሊ ፕሮፖዛሉ ቀርቦ ይፀድቃል። ምደባ ግን በቀጥታ ትዕዛዝ ይፈፀማል። ይህ የሚሆንበት ምክንያት በውስጡ የተለዬ ሚሽንም ሲኖር ነው። ማንኛውም አገሪቱ የምትተዳደርበት ህግ ለዚህ መሰል የፖለቲካ ውሳኔ አይሠራም።
እሥርም እንዲሁ ነው። የፖለቲካ ውሳኔ ዬሚታሠሩ አሉ። ህጉን ተከትሎ የሚታሠሩ አሉ። በሁለቱም የህግ አፈፃፀም ሽባ ነው። ምክንያቱም የሥልጣን ምንጩ ህዝብ፤ ህዝባዊ ህገ - መንግሥት ሳይሆን #ዴሞክራሲያዊ #ማዕከላዊነት ይሆናል። ተሸፍኖ ያለው ገመና ይህ ነው። የሥልጣኑ ምንጭ ከአውራው የፖለቲካ መሥመር ጋር በጽኑ ዬተቆረኜ ነው። በተለይ ሶሻሊስት ኦሬንትድ በሆኑ አገሮች። ኢህአዴግ ላዕላዕላዩም ታህታዩም የመዋቅሩ ሥርዓት የተገነባው በዚህ ነው። ከዛ ዬመውጣት አቅም የለም። ምክንያት ጉራጁ ስላለ።
ከኛ።ጁቪተር በታምር ወደ መሬት ብቅ ያሉት ባለስልጣን ተንሳፋፊ ሃሳባቸውን እንዲህ ያቀርቡታል።
ለዚህ ነው እኔ ጁቪተር የባጁት ያልኩት። ከ4500 በላይ የፋኖ እስረኛ በዚህ ሂደት ያለፈ ይሆን??? 700 አፋር በርኃ ላይ እንደ ዕቃ የተከዘኑትስ? እራሱ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ "ፍርድ ቤት ዬለንም ብለዋል። ዜሮ ነው ብለዋል።" ፍትህን አልጀመርነውም ብለዋል።
ይህን ገለፃ ዬ100 ቀን ጉዟቸውን አፋር ሰመራ ላይም ተናግረውት ነበር። በአራት ዓመቱ የሥልጣን ጉዟቸው ደገሙት እጅግ ተጠናክረው። ቢሮውን በማሳመር፤ አዲስ ሰወችን በማሸጋሸግ ሠርተዋል። መሠረታዊ የሆነ ለውጥ አልታዬም። ወገኖቼ 4 ዓመት አንድ የምርጫ ተርም ነው። እንደ ሌላ አገር ቢሆን ለቀጣዩ ምርጫ የማያበቃ። ለምን? አናቱ ካንሰር ስላለበት።
አላያችሁም በ45 ቀን እንግሊዝ ጠቅላይ ሚሯን ሲያሰናብት። ኢኮኖሚያዊ ያለመረጋጋት ቢሆንም። የህግ ዬበላይነት፤ የመፈፀም እና የማስፈፀም አቅም አልቦሽ ከሆነ አቅም ያለው ከፍተኛው ጉባኤ መክሮ ይወስናል። ዶር አብይ የ4 የኩሬ ውኃ ልባቸውን ሞልተው ሲናገሩ ምን እርምጃ ወሰድክ ተብለው አልተጠዬቁም። ዛሬም።
ጋዜጠኛው ……
ሌላ ስለሚሰወሩት፤ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር ያለውን ሁነት አጣቅሶ በስሱ ገለጠ ጋዜጠኛ ሥሜነህ።
ቀጠሉ ለዚህ ቃለ ምልልስ ከጁቪተር ወደ መሬት ትራንዚት ያደረጉት ተረበኛ ……
"ጣልቃ የሚገባብን የመንግሥት አካል የለም ብለዋል አስቀድመው። ዬእኛ ዳኞች ትዕዛዝ ሳይከበር ቀርቶ ቶለሬት ያደረጉበት ሁኔታ አለ ብይዬ #አላስብም። "
እሳቸው እስኪያስቡ ፍትህ ቀራንዮ ይከትም። ስንት ትዳር? ስንት ቤተሰብ? ዬወጣቶች ዬዕድሜ ብክነት፤ ዬሥነ ልቦና ቅጣት ከቁጥር አይገባም። ለምን? እሳቸው እስኪያስቡ።
መሃል አዲስ አበባ በጭንብል ለባሾች ታግተው፤ ለሚደበደቡ፤ ለሚሠወሩ፤ ነፃነታቸው በሚነፈጉ፤ በቁም እሥር ለሚገኙ ሁሉ እሳቸው "እስኪያስቡ" ጣልቃ ገብነት አይደለም። የሳቸው ቢሮ ነፃ ሆኖ እዬሰራ ነው።
እንደ ወጣ ዬቀረው፤ በቤቱ የታረደው፤ ሃብት ንብረቱ የወደመበት ህጋዊ ነው። የእነሱ የህግ ሥርዓት ዬተቋቋመው፤ ያስተካከለው፤ ያረቀው አንዳችም ነገር አልታዬም። በሀረር፤ በድሬ፤ በዝዋይ፤ በአርሲ ነገሌ፤ በአጣዬ በሽዋ ሮቢት፤ በቡራዩ በአዲስ አበባ። ትናንት እንኳን ለድሎተኛ ተጨማሪ ቤተ መንግሥት ሲባል አቤቱታ ያቀረቡ 18 ወገኖቻችን ወደ አልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን ህብር ዘግቧል።
ቅንጡው ዬህግ ባለሙያው ………ፖሊሶች በፍርድ ቤት የተለቀቀውን ደግመው ዬሚያስሩት ሌላ ጥርጣሬ ስለሚያድርባቸውም ነው ይላሉ። ይህ ለሳቸው የጫጉላ ሽርሽር ነው። እንግልት አይደለም።
"በይግባኝ ሂደት ውስጥ ነፃ ሆኖ ዬመታዬት፤ መብቱን ይህ ሰው አጥቶ ለ10 ቀን እና ለምናምን እዬተንገላታ ነው"
"10 ቀን¡¡¡¡¿¿¿¿እኔ ሥሜነህ 10 ቀን ???!!!!" ወይ ቅልጣን??? ወይ ዘመናይነት????
"እሺ ሌላ በ48 ሰዓት ውስጥ ሲቀርቡ ያሻቸውን አድርገው፤ በአሻቸው መንገድ ተጠርጣሪ ነው ብለው ያሰሯቸውን አካላት፤ ፍርድ ቤት ዬትም አሰንብቶ ሲያመጣ ፖሊስ ተጠያቂ ስታደርጉ አትታዩም? "
"ይህን የእኛ ዳኞች #ቶለሬት አያደርጉም አፌን ሞልቼ እናገራለሁኝ።።" ቆርበት ዬሆነ ጉድ። ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ፤ ጋዜጠኛ ታዲዮስ ታንቱስ? በህይወት እያሉ ግፍ የተፈፀመባቸው ወገኖች። ታፈኑ፤ ተሰወሩ፤ ወህኒ ተወረወሩ። ለመሆኑ ታሜ የት ይሆን ያለው?
አዲስ አበባ ላይ ህገ ወጡ እስር ቤት እና ማጎሪያ ጣቢያው፤ማሰቃያ የግል አፐርታማው ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፤ ፀሐፊ በላይ በቀለ ምስክር ናቸው። ወለሉ ላይ በደም የተበከለ ሁኔታ እንደነበርም ገልፀዋል። ሁለቱም የጥበብ ቤተኞች።
ለዛውም በሥም፤ በአድራሻ የማያታወቁ ዜጎች ጉዳይ የሚያነሳው የለም። ከሥር የምለጥፋቸው እስረኞች የጉዳያቸው ፍሰት በዚህ የክህደት ውሎ ለናሙና እማቀርባቸው ዕውነቶች ናቸው። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
#ሰብሰብ ብለው የሚታዩት ቢጫ ለባሾች ኦነግ አዲስ አበባ ሲገባ መስከረም 5/2011 ከታሠሩት 1300 እስረኞች ውስጥ ተለዬተው እስር ቤት የቀሩት ናቸው። ሁለተኞቹ የአርቲስት ሃጫሉን ሞት ተከትሎ የታሠሩ ናቸው። ችግሩ ህዝብን የእኔ ለማይል ሥርዓት ራህቡም፤
ጥማቱም፤ እንግልቱም ጭንቀቱ አይሰማውም። እሱ ገነት ውስጥ ነውና።
የተከበሩ እርስወ ጁቪተር ላይ በነበሩ ጊዜ የተፈጠሙ የሰባዕዊነት ጥሰቶች ለመረጃ ያህል። የጋዜጠኛ ታምራት ነገራን ዘልዬዋለሁ። ሰላሙን ማወክ ስላልፈለግኩኝ።
"ሞት አያምም።" (ከእሸት ባለቅኔ ከገጣሚ በላይ በቀለ ዋያ።) 25.07.2022
አስገራሚው የፖሊስ ቃል አቀባዩ ምላሽ! "በሐሰት አማራ ተጨፍጭፋል ብሏል
ገጣሚ በላይ በቀለን ያገተው ማን ነው? | ቀጥታ ከቤተሰቦቹ አንደበት!
"አባታችን በድንጋጤ ታሞ ተኝቷል" - የጎበዜ ሲሳይ ታናሽ ወንድም | ጎበዜ ሲሳይ | Gobeze Sisay | The voice of Amhara | Ethiopia
"የጋዜጠኛው እስር ከእኛ እውቅና ውጭ ነው" | አነጋጋሪው የባለስልጣናቱ ምላሽ! የአማራ ድምጽ | ጎበዜ ሲሳይ | Gobeze Sisay
የአማራ ድምጽ | ከጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ጋር የተደረገ የክፍል 1 ቆይታ | ግንቦት 4፣ 2014 ዓ.ም | Ethiopia Amhara | Gobeze Sisay
ጋዜጠኛ ታዲዮስ ታንቱ የገቡበት አልታወቀም›/ኦነግ የልዩ ኃይል አባላት ላይ ጥቃት ፈጸመ/ የግንቦት 11 ዜናዎች
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
29/10/2022
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ