ጋዜጠኛ ጎበዜ ጎበዙ እራህብ የወባ ወረርሽኝ፣ ሌላም ከእንሰሳት ወደ ሰው የሚሻገር አባ ሰንጋ በሽታ መከሰቱን ገልፆ ነበር።

 

ጋዜጠኛ ጎበዜ ጎበዙ እራህብ የወባ ወረርሽኝ፣ ሌላም ከእንሰሳት ወደ ሰው የሚሻገር አባ ሰንጋ በሽታ መከሰቱን ገልፆ ነበር።




 
አሁን የዓለም የጤና ድርጅት የወባ ወረርሽኝ መጠናከሩን በአማራ ክልል እና በትግራይ ገልፆል።
በምን ምክንያት ስለመሆኑ በሚገባኝ ልክ በዚህ መግለጫው ለመጀመሪያ ጊዜ WHO "አማራ ክልል" የሚል አካቷል።
ይህንን ያሳወቁት WHO የድርጅቱ የኢትዮጵያ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ኢኃም አብዱላሂ ስለመሆናቸው ተገልጧል። ዘገባው የህብር ራዲዮ ነው።
ስለ ወባ ወረርሽኝ ካነሳሁ ዘንድ ህወሃት ድርጅቱን የወባ ማጥፊያውን ቢሮ በአማራ ክልል ዘግቶት ነበር። የወባ ወረርሽኝ ተቋም ዬነበረው ትግራይ ብቻ ነበር።
ስሜን ጎንደር በወባ ወረርሽኝ ከሚጠቁት አንዱ ነበር። ዬእኔ ቤተሰቦች በሙሉ ነበረባቸው። ያው ሰቲት ሁመራ ይኖሩ ስለነበር። የበሞቴ ልዕልቴ እናቴ ነበረባት፣ የአብርኃሙ ቤት አባባም ነበረባቸው።
አስታውሳለሁ በልጅነት ደብረሰላም ትምህርት ቤት አንባጅኔ ከነበረው የወባ ማጥፊያ ድርጅት በጥዋት ሄደው ምርመራ ቤተሰቦቼ ሲያደርጉ።
ነገርግን አንባጅኔ ዬነበረውን የወባ ማጥፊያ ድርጅቱን ዘግቶ፣ ብልኮ ያለውን በደሙ ዋጋ ያገኜውን የጎንደር ህዝብ ጄነሬተር ህወሃት ሥልጣን ሲይዝ ነቅሎ ወሰደው። በኋላ ስሰማ ጅማም፣ ወሎም መሰሉን የጠራራ ጠሐይ ዘረፋ መፈፀሙን አዳመጥኩኝ።
መብራትም ጤና ህዝብን ነፍጎ 27 ዓመት አገር መራ። አሁን የሚኒሊክ ቤተ - መንግሥትን ኩንትራቴ ለ100 ዓመት ነው ብሎ በይገባኛል ጦርነት ላይ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድም ከ50 -60 ዓመት ብለውናል። ትውልድ የሚያንፁበት በገዳ ርዕዮት ማለት ነው።
ወደ ቀደመው ጭብጤ ስመለስ ኃላፊው አያይዘው የገለፁት የትራንስፖርት አገልግሎት በመቋረጡ በትግራይ ችግሩ ተባብሷል ይላል።
ሽሬ፣ አክሱም፣ አድዋ አውሮፕላን ማረፊያወች አሉ። ከዶር አብይ መንግሥት ጋር ተነጋግሮ ችግሩን መፍታት ይገባል።
ህመሙንም፣ ረኃቡንም ለፖለቲካ ትርፍና ኪሳራ ማድረጉ ቢቆም ጥሩ ይመስለኛል። ስለ ሰው ልጅ ስቃይ ግድ ዬሚል ከሆነ በተገኜው ዕድል ተጠቅሞ ለህዝብ መድረስ ይገባል።
ጤና ይቅደም። ፖለቲካዊ ትርፍ ይከተል።

 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
30/10/2022
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።