ብቸኛው በኖህ መርከብ ቅርፅ የተሰራ ቤተክርስቲያን የሚገኘው ኢትዮጵያ ብቻ ነው

 

ከአቶ ጋሻው አባተ ያገኜሁት ነው። 

 
የዛሬ ዓራት ዓመት ፌስቡክ ስጀምር ፕሮፋይሌ ነበር። ዕትብቴ ዬተቀበረበት። ፊደል የቆጠርኩበት፣ ያደግኩበት።
ማህሌቱ፣ ዝማሬው፣ እጣኑ ጠጅ እሳር እሪያኑ፣ ጉሬዛው፣ እንቁላል ግንቡ፣ ቅጽር ግቢው፣ የወይራ ፍሬ ለቀማው፣ የአባ በጠኃ ቅኔ ቤት፣ የአባ ጌራ እና አባ ኃይለማርያም ፈገግታ፣ የመላከ ብርኃናቱ ቤተሰቦቼ የአብርኃሙ ቤት ……የተድያን መስተንግዶ ………
ይህን በነፍሱ እስከነ ግጥሙ እኔ ሠርቼዋለሁኝ።
👉👉👉ይህንን ያውቁ ኑሯል?👇
"በዓለም ላይ ብቸኛው በኖህ መርከብ ቅርፅ የተሰራ ቤተክርስቲያን የሚገኘው ኢትዮጵያ ብቻ ነው በእጃቹህ ያለውን ወርቅ ተዋወቁት።ይህ የምትመለከቱት ቤተክርስቲያን በ16ኛው ክ.ዘ የነገሠው የአፄ ፋሲል የልጅ ልጅ አለም ሰገድ(አድያም ሰገድ) ኢያሱ በኖህ መርከብ አምሳያ ጎንደር ከተማ ላይ ያሰራው ቤተክስቲያን ነው ስሙም ደብረ ብርሃን ሥላሴ ነው ይህ ዓለም የሰገደለት ንጉሥ ክህነትን እና ንግሥናን ሁለቱን ስልጣን በማጣመር ኢትዮጵያን ገዝቷል ቤተመቅደስ ገብቶ ካህን ሁኖ ይቀድሳል ቤተመንግስት ደሞ ንጉሥ ሁኖ ሀገር ይመራል አንዲያውም ይሄ ንጉሥ አክሱም ጽዮን ማርያም በመሄድ ታቦተ ጽዮንን ተሸክሞ ንግሥና እንዳከበረ ይነገርለታል።ልብ በሉ በመፅሐፍ ቅዱስ በጣም ገናና ከሆኑት የእስራኤል ነጉሦች መካከል ንጉሥ ዳዊትና ጠቢቡ ሰለሞንን እንኳ የኢትዮጵያውን ንጉሥ ቋረኛው እያሱን ያክል ስልጣን አልነበራቸውም ለምን ዳዊትና ልጁ ሰለሞን የክህነት ስልጣን አልነበራቸውም ነበር የክህነቱን ቦታ የሚያገለግሉ የሌዊ ነገዶች ብቻ ናቸው የኢትዮጵያ ነገሥታት ግን ከንጉሥነት አልፎ ካህንም ነበሩ ለዛ ነው የውጭ ሀገር ታሪክ ጽሐፊዎች የኢትዮጵያን ነገሥታት ሲጠሯቸው "prester john" ነው ሚሏቸው ትርጉሙም "ቄሱ ንጉስ"ማለት ነው ።ነገር ግን በ18ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ኢትዮጵያ የተዳከመችበት ዘመን ነበረና ከግብፅና ሱዳን የመጡ አክራሪ ደርቡሾች በቀላሉ ጎንደርን በወረሩ ግዜ 43ቱን ጥንታዊ ቤተክርስቲያንን አቃጥለው ወደ 44ተኛው ወደዚሁ ስላሤ ቤተክርስቲያን ሲመጡ ከየት እንደመጣ የማይታወቅ ነጭ ንብ ድርቡሾችን እየነደፈ አባረራቸው ቤተክርስቲያኑም ለወሬ ነጋሪት ለታሪክ ምስክርነት ብቻውን ሳይቃጠል ቀረ።
"ወዴት ሂዶ ኖሯል ሰሞነኛ ቄሱ
ታቦት ተሸከመ ዘዉዱን ጥሎ ኢያሱ ።
የተሸሸገዉን የአባቱን ቅስና
ገለጠዉ ኢያሱ ታቦት አነሳና ።
አየነዉ ኢያሱን ደብረ ብርሃን ቁሞ
ልክ እንደ ኪሩቤል ሶስቱን ተሸክሞ ።
ስላሤን ቢሸከም ኢያሱ ገነነ
ለአራቱ ኪሩቤል አምስተኛ ሆነነ ።"
ለተጨማሪ ጤና መረጃ የቴሌግራም ቻላኔን ይቀላቀሉ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።