#ወሮ አዜብ መስፍን እና ትናንት። ዬአማራን ተጋድሎ ለመጥለፍ ሲንደፋደፋ የተጣፈ ነው። ዛሬም የጠላፊ ናዳ ወጀብ ቢንጠውም።

#ወሮ አዜብ መስፍን እና ትናንት።


 
ዬአማራን ተጋድሎ ለመጥለፍ ሲንደፋደፋ የተጣፈ ነው።
ዛሬም የጠላፊ ናዳ ወጀብ ቢንጠውም።
ዬአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ መንፈሱ እንዲህ ጥበቃ ይደረግለት ነበር። እዚህ እምሠራው ቁራጭ ነገር ነው። በጣሳ። ቀደም ባለው ጊዜ ግን በዚህ መልክ ነበር እምሰራው። ዘለግ ያለ ሙግት፣ በጥንግ ድርብ ብርታት።
እንዴት አደርን? ደህና ነን? ዛሬ ሌሊት ነበር ዬገባሁት። ዬቤታችን መቀዬጥን ለማጽዳት። መቼም ዬዘንድሮ ጥር ያልቀማን ዬለም። ለዛ ነው ዝምታን መርጬ ዬምላትን ብዬ ሾለክ እምለው። ትናንት እና ዛሬ ዬብራና ዬጥዳት ቀን ነበር። ይቀጥላልም።
ቤታችን ናፍቋቸው ተሰልፈው ዬሚጠብቁ ቅኖች አሉ። ለእነሱ እድል ይሰጣል። ባለፈው ወር አንድ ወንድማችን መግባት ፈልጎ ፌስቡክ አስቸግሮት በስንት ጣጣ ወደ ቤታችን መጣልን። እንኳን ደህና መጣህልን ወንድማችን ልለው ፈቀድኩኝ።
ከአራት ዓመት በፊት ሙግቴ ይህን ይመስል ነበር። በረጅሙ ነበር እማስከነዳው። ዛሬ አንድ እርዕሰ ጉዳይ ፈልጌ ጉግል ስገባ ከች አደረግልኝ አጤ ጉግልሻ። ረጅም አትኩሮት ከህሊናዊነት ጋር ላለቸው ዬሚሆን ነው።
እንዳለ ሼር ለማድረግ ፈቀድኩኝ። ግን ካልሆነ ማስታወቂያ ጋር ሆነብኝ። ነጥዬ ለማቅረብ ስል አልቻልኩም። በዚህ መልክ ተቻለ።
መልካም ቀን። ደህና ዋሉልኝ። ቸሮቼ።
• ጉራጅ – ውራጅ – ከሥርጉተ ሥላሴ
January 18, 2017, 10:56 am
ከሥርጉተ ሥላሴ 18.01.2017 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ።)
„በአባቷ፡ ዬምታላግጥን፡ ዬእናቷን፡ ትእዛዝ፡
ዬምትንቅን፡ ዓይን፡ የሸለቆ፡ ቁራዎች፡
ይጎጠጉጧታል፥ አሞራዎች ይበሏታል።
(መጽሐፈ ምሳሌ (ተግሣጽ) ምዕራፍ ፴ ቁጥር ፲፯)
• ጠብታ።
ለከት ክት ሆኖ አንከሊስ ሲያማትብ
ቹፌ ተደፋበት ክህደት – በሥጋ ግንብ።
ውቅራት አሳኛት ዬሙት መንፈሰኛ፣
ቅኔው ይላክላት ለውርዴ – ቤተኛ።
ዬሞተችው ትናንት፣ መች ሆነ ዛሬኛ፣
ስትፈጠር ነበር ዬሆነች ቀበኛ!
• እፍታ።
• ወሮ አዜብ መስፍን።
ወይ ትግሬዋ¡ ወ/ሮ አዜብ መስፍን። አማራንትን፣ ጎንደሬነትን በስተርጅና? ወቼ ጉድ አሉ። ማንነት እንዲህ ዬማስታወቂያ ሰሌዳ ሰለባ ነውን?
#እርስትን ለሥጋ ፈቃድ ዬሚሸጥ ሰብዕና መሬት አልፈጠረችም – ከወ/ሮ አዜብ በስተቀር፣ ለሥጋ ፈቃድ እትብት ሲቸበቸብ ታሪክ ያዬው በእሳቸው ዬክህደት ዬመንፈስ እግረ ሙቅ ነው። እንዴት አንዲት አንስት ዬህልውናዋን ማዕከል ለሥጋ ፈቃድ እንዳወጣ ትቸበችባለች?! ጉድ ሳይሰማ … አሉ።
ጉድ! ጉድ!! ጉድ በል ጎንደርስ አሁን ነው። #ዬጉድፍ – ጉድጓድ። ዬዕድፍ – ጉድጓድ። ዬጉራጅ – ጉድጓድ። ዬውራጅ – ጉድጓድ። ዬውርዴ – ጉድጓድ።
ዬት ዬሚታወቀው መተማ ይሆን ቤተ ክርስትያን ሊሰራለት ድርድር ዬሚደረገው? እንዲህ ዓይነት ፈጣጣነት፣ ዓይኑን በጥሬጨው ያሸ ቅቤ ጠባሽነት፣ ዓይን ያወጣ ዬቅጥፈት ድክረት ታይቶም ተሰምቶም – አይታወቅም። ዬጅልነት ዝልቦ። ሙት!
እንኳንስ ድፍን ጎንደር ዬሄሮዳይ ዬእናት ሥጋ እህት ዬሐገር ሃብት ዬሆኑት – ዬምግባር እሙኃይ ሰብለወንጌል ጎላም አላደረጉትም። አዎና! ውራጅን ማን ሲፈልግ?
እንዲህ ዓይነቱ ውስጥን በትውስት ትቢያ አልብሶ ድርቆሽ ሲከምር ለኖረ ሰላላ ዕሳቤ ቅቡልነት ሲያልፍም አይነካካውም – ጎንደር።
መቀጥቀጫው ፋስና ገጆሞ – ዶድሞ በበቃኝ ሲሰናበት – በሰላው ኮማንድ ፖስት አዲሱን ውቃው በአዲስ ኃይልና ጉልበት በዘመቻ – ባልተወለደ አንጀት – ባላባራ ዬደምና ዬዕንባ ጎርፍ ያ አሳርኛ አሁንም ይሄው – ይማስናል። በሄሮዳይ ገዳይ ማኒፌስቶ።
ዬት ዬሚታወቀው ጎንደር ይሆን ቤተ – ክርስትያን ሊሰራለት ዬታሰበው? በዘመነ ቀዳማይነት ዬቆቆር ታክል አትኩሮት ያልተቸረው መከረኛ አሁን ለመናጆነት ተፈለገ። አንዲት ቆርቆሮ ያልገዛች ነፍስ እንዴት መንፈሱን ለመዳፈር ቃጣች? ግርንቢጥ – እፋኝት።
„ዶሮን ሲደልሏት በመጫኛ ጣሏት“ አሉ። ጎንደር በባድማው ሰላሙን ቀምተው – ዬጦር ቀጠና በማድረግ – ሰላሙን አሳጡት እንጂ መቼ ዬቤተ – አምልኩ አድባር አነሶኛልና ገንቡልኝ ብሎ አመለከተና?
ይህ በግራ በቀኝ ለእርድ ዬቀረበው መከረኛ በባሩድ እዬቀጠቀጡ ቤተ – ክርስትያን ላሰራ ብሎ በደመነፍስ መነሳት እርቃነ ነፍስ መነሳት ዬዕብደት ምልክት መሆን አለበት። ግን ዬዕውነት ሴትዮዋ ዬጤናቸውን ነው? ለነገሩ ወያኔ ሃርነት ትግራይ አብኩቶ ሲሰራቸው ነበር ህመሙ አህዱ ያለው። ህመምተኛ።
ከነመፈጠሩ ዬተዘለለው – ትንፋሹ እስክትወጣ በጥጋበኞች ተዘቅዝቆ ሲቀጠቀጥ እኒህ አልኩ ባይ ለመሆኑ ዬት ነበሩ? ህሊና ቢስ። ዬትውልድ አሰር። ጭላጭ።
በዬዘመናቱ ዬሚጠቀጠቀው። እርስቱን ዬተቀማው፤ አባቶቹን ለባዶ ስድስት ስንቅ ዬቀለበው፤ ቂሊንጦ ላይ ከነ ካቴናው ዬነደደው፣ ዬተረሸነው፣ ብር ሸለቆ ላይ በበቀል ዬሚቀቀለው፤ በቁርሾ ዬሚወገጠው ዬት ዬሚታወቀው ጎንደር ይሆን ባንዳን አሽኮኮ ብሎ ከገዳዮቹ ጋር ለድርድር ዬሚቀርበው?
ዬት ነበሩ ወ/ሮ አዜብ 25 ዓመት ሙሉ ሲቀጠቀጥ፣ ሲመነጠር፣ በግፍ አንጡራ ሃብቱ ሲዘረፍ ፤ በግፍና በገፍ ወደ እስር ሲጋዝ፤ ለሞት ሲታጭ እኮ ዬት ነበሩ ዬሄሮድስ መለስ ዬሙት መንፈስ ቅምጥል? እፍረተ ቢስ – ነዳላ።
ጎንደር ነው በባንዳ – ለባንዳዊ ተልዕኮ ዬሚደራደረው? ወይ አለማወቅ! ግርም ዬሚለው ይሄው ነው። #ልብ እንዲገጠምለት ዬተፈጠረ ህዝብ አለመሆኑን ጠላትም ወዳጅም ይወቀው ብዬ ነበር – ስለ ጎንደር በተከታታይ በምዕራፋት ዬፃፍኩት።
ጎንደር ላይ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ሆነ፤ ዬተፋውን መልሶ ገርገጭ ዬማድረግ ተፈጥሮ አልተፈጠረለትም። ትግሬ ነኝ¡ ተብለናል እኮ። እዛው እንደፍጥርጥራቸው መሆን ሲችሉ አሁን መጥቶ ማስመሰል – መቦጫረቅ ነው። ዬብድር ዱቄት።
ትምክህት ባይሆንብኝ ጎንደሬነት እኮ ተለምኖ አይገኝም። ጎንደሬነት እኮ ኩራት ነው። ጎንደሬነት እኮ ዬአትንኩኝ ባይ ምልክትነት ነው። ጎንደሬነት ሊናቅ? ህእ።
ጎንደሬነትን እንዲህ ማተብ በጥሶ ሊደራደሩበት፤ ህም! እና ምን ሲሆኑ ምንስ ፈልገው ነው አሁን ለመተንፈሻ ቧንቧነት ቀልዱ ዲል ብሎ በእብድ ሃሙስ ዬተደገሰለት? እንዴት ተቀለደ! ዬቧልትም ዓይነት አለው። ካህዲ! ወሮ አዜብ መስፍን ብሎ አደራዳሪ። ዬዛሬ ጭብጤ መነሻ ይሄ ነው – ዬሀገሬ ዬልዕልት ኢትዮዽያ ልጆች …
„ሕወሓት በወ/ር አዜብ መስፍን በኩል በመተማና በሌሎችም የአማራ አካባቢዎች ሕዝቡን ለመከፋፈል ቤተ/ክርስቲያን አሰራለሁ የሚል ዘመቻ ጀመረ – የህብር ሬዲዮ ጥር 7 ቀን 2009 ፕሮግራም“
አለቀባት አሉ ድንበር አልባ መዞር – በዕሴት ማመንዘር
ዘር ትቶ እንክርዳድ በጥራር – ማንዘርዘር።
እኔስ ይብላኝላት ለውራጅ – እረኛ
ህሊና ቢስ ሆና ለቀረች – መናኛ!
መቼም ጎንደር መሬት እንዲህ ዓይነት እፋኝት ሲወልድ ዬመጀመሪያ – ዬመጨረሻም መሆን አለበት። መለመላ ለቆመ ዬሄሮድስ መለስ ማኒፌስቶ #መለበጫ ይሆን – አዲሱ ተውኔት ዬመተማ አፍ ያለው መቃብር ተብዬው? እያላገጡ መሆን አለባቸው ወ/ሮ ሄሮዳይ።
ዬት ዬሚያውቁትን ጎንደርን? ትግሬነቱ ዬተቃጠለ ካርቦን ሆነን? ትግራዯችም አልተቀበሏቸውም። በአንድ ወቅት ሀገር ቤት ከሚታተም መጽሄት ጋር በግንባር ወጥቼ ጀግናዬ እለው ዬነበረው፤ በኋላ ላይ እንደ ሰማሁት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ „ቤተ አቧራ“ ያለን ልጅ አብርሃም ደስታ "አዜብ መስፍን አጀንዳችን" አይደለችም ብሎን ነበር።
እኔም እርዕሱን አላስታውውም – ስለማተበ ቢሷ አንድ መጣጥፍ ጥፌ ነበር። አዎን! ለእኛ ለጎንደሬዎችም ቢሆን ሄሮዳይድ ካሃዲዋ ወ/ሮ አዜብ መስፍን አጀንዳችን አይደሉም።
በአማራ ሆነ በትግራዊነት፤ በጎንደሬነት ሆነ በትግሬነት ተንገዋላይ ዬውራጅ ማንነት ያዘለ – ዘነዘና ግጥማችን መቼውንም አይሆንም። ውርዴ!
ኢትዮዽያዊነቱንም ቢሆን ዬመጤ እንደራሴ ዬሆኑት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ቅጃቸው ከሄሮድስ መለስ ስለሆነ ከታላቁ ዬዜግንነት ማንነትም ጋር ጦር ዬተማዘዙ ዬዘመን አሰር ናቸው። ስለዚህ እንደዋለሉ ይንገዋለሉ … ለነገሩ ከዛ ሽንክ ሰብዕና ዬተቀዳ ምን ጥግ ሲኖረው? በሰማይም በምድርም – ገኃነብ።
ዬክህደት – እንቆቆ።
አትፈትል፣ አትሰፋ ዬነገር `ድረኛ
ዬሴራ፣ ዬሁከት ይሏታል – ሸረኛ።
መሆን ዬተሳናት እንደራስ ግብረኛ
ዬአለቅቷ – ደንበኛ።።
ዬወልቃይትና ዬጠገዴ በተለይም ቃብቲያ ዬኒህን ዬክህደት ቅርሻ ሲሰማ ምን ይል ይሆን? ዘሩ – ዬፈለሰው። በገደል ዬተጣለው።
***#በባዶ ስድስት ስምጥ ተውጦ – ዬቀረው። ዬአቮ ዘመን አክትሞ አባት አልባ ልጆች በእናታቸው እንዲጠሩ ዬተገደዱበት ዬጥቅርሻ ዘመን።
«የወልቃይት አማራ የተሰቃየባቸው የትህነግ 15 ድብቅ እስር ቤቶች!» (ፀሐፊ አቶ ቢኒያም መስፍን)
ሺዎች በርስታቸው መኖሪያ አጥተው ዬስደት ስቃይ የገረፋቸው፣ ኧረ ስንቱ? በመሬቱ ላይ ያለው ዬግፍ አነባበሮ ቅጣቱን እኮ ሰማይ ታምሩን አሳይቷል። ነጠላ ቀርነት እኮ ዬሰማዩ ቁጣ ፍርድ ነበር። ለልብ አልቧዋ – ውልፍት።
ልባሞቹ ዬትግራይና ዬኤርትራ ሴቶችማ በስል ገብተው ያሻቸውን ያስ – ደርጋሉ። ዬፖለቲካ ዘብጥያ ዕትብትን ማሳጨት ሳይሆን – ለተፈጠሩባት እትብት ሆነ ባዕት ገነትን በድርጊትም በምግባርም ያሳውጃሉ። በሞራላቸውም ከፍ ያለ ሥነ - ልቦናዊ አቅም ያሳያሉ።
ዛሬ እንኳን በተቃዋሚ ጎራ አናቷን ጨብጠው ዝንብ እሽ እንዳይባል፣ ማገር ሆነው ዬድርሻቸውን ይወጣሉ። ሚዲያ ውይይት ላይ እንኳን ማህሏን ለመንካት ታቱ ያለውን ሃሳብ ሲገስፁ ተመልክተናል።
ለሚስቶቻቸው ፍላጎት ሲሉ ሁሉ ነገር ዳር ለዳር ነው። ወ/ሮ አዜብ መስፍን ደግሞ ዬዘር ጥፋት (genocide)
አርበኛ¡ ደመ ነብስ።
ቀትረ – ቀላል ሲሏት ውሎአድሮ ሰንብቼ
ግድፈቱ ለስጋ መሆኑ-ነን ስቼ።
ቀለም ዬለሽ ሲሏት፣ ድንቡልቡልም ሲሏት፣
ጠፍጣፋ ናት ሲሏት ….
…. እንዲህ እንዲያ ሲሏት …
ባንድነት ተስማሙ – ምርቃት ያላያት።
ወ/ሮ አዜብ መስፍን ዬዓራት ዓይናማው አርበኛ ዬአባ ፍታውራሪ መለሰ ኃይሉን አደራ ዬበሉ ዬባንዳ ቀረመተኛ ናቸው። ዬክህደትም አለው ዓይነት። #ማንነት እኮ ጨርቅ አይደለም – ዬሚዋሱት ወይንም #ለሥጦታ ዬሚያቀርቡት።
ውራጅነት ዬሚሰኘው ማንነት ለማኝ ሩህ በምድር ዬለችም – ከወሮ አዜብ መስፍን በስተቀር። ማንነት እራሱን ለሆነ ፍጡር ዬሰው መሆኑ ዓዕማደ ሚስጢር ነው። ካሃዲዋ ወ/ሮ አዜብ ግን ውስጣቸውን ዬተጸዬፋ ዬዕዳሪ ቅርፊት ናቸው። እንዲህ ሆኖ ከመኖር ሞት በስንት ጣዕሙ።
ዬአፈር ማዳበሪያ መሆን በፆምም በጸሎትም – አይገኝም። ሰው መሳይ በሸንጎ። ዬተረሳው ጎንደር ዛሬ ተፈለገ።
ወይ ነዶ!
ክህደት ሃቅን በርግዶ።
አታውቀውም እሷ ትውስት ሆድአደር፤
ዬርስት ንጡርነት – መቼ አውቃው ግብር፤
ዱብ ዕዳ ሆነባት ዬቅጥፈት – እስረኛ፤
መተማን ተመኜች – ዬባንዳ እግረኛ።
እትብቷን ሸለመች ለገዳይ ባሩድ፤
ትውልዱን ጨረሰች ጉዲት – ጉዳጉድ።
25 ዓመት ሙሉ ዬት እንደ ወደቀ ያልተጠዬቀ ማንነት ዛሬ ደርሶ ዱብ ሲል – ተዓብ ነው። ወይ መዳህኒተ ዓለም አባቴ? – ምኑን ይሆን እያሰማን ያለው? ዬቅርጥምጣሚ፣ ዬግፋፎ – ትውኪያ ጎንደር እንዲሆን እራሱ መታሰቡ – ያጨሳል።
ዬሄሮድስ ሙሽራ – ዬማንን ጎፈሬ ሲያበጥሩ እንደኖሩ ልባቸው – ያውቀዋል። ወንዶቹማ ዬወጡባትን እትብት – አደላድለዋል። በባለቤትነት 25 ዓመት ሙሉ አዲሱን ትውልድ በተገኜው አጋጣሚ ሁሉ ቦታ – አስይዘዋል። በተከፈተችው ቀዳዳ ሁሉ ዬዕድል ቡፌ – ዓይነት – በዓይነት ዬልብ ለልብ አድርሰዋል።
ከቀደምቶቹ ዬትምህርት ሁኔታ በላቀ ሁኔታ ዬተፈጠሩባትን መሬት በሚገባ መሰረት አስይዘው – ገንብተዋል። ዬኢኮኖሚ፤ ዬማህበራዊ፤ ዬፖለቲካ፣ ዬወታደራዊ አውታሩን ለሥጋዎቻቸው – አድለዋል፡፡ በሁሉም ቦታ ሁሉንም ሆነውበታል። አጊጠውበታል።
እሜቴ¡ አዜብ መስፍን ከ25 ዓመት በኋላ ነቃሁ ብለው ለመለበጃነት መንደፋደፍ ትርፋ ውርዴያዊ – ውርዴት ብቻ ነው። ማተበ ቢስ!
ውልፍት! እነዛ ስጋዎት መልካሙንም – ደጉንም ዬተጋሩት ዬወልቃይት ጠገዴ ዬማንነት ጥያቄ አቅራቢዎች እነ አቶ አታላይ ዛፌ ያን ያህል በርዕሰ መዲናዋ በሰው በላዎች ውረዱ – ተሰቀሉ – ተቆንጠጡ ሲባሉ ከቶ ዬክህደት ድውለቷ ዬት ነበሩ?
እስኪ ድፍረቱ ካላ #ብርሃኗን ንግስት ይርጋን ያስፈቱ? ኮሜቲውን በሙሉ ያስለቅቁ? #ጎንደርን በቀደመው #ወሰንና ደንበሩ እንዲቀጥል ያስወስኑ?
እስኪ ጥጋበኛውን ዬትግራዩን አፄ ዬአቶ #አባይ ወልዱን ዬተንጠራራ ጥጋብ – ያስተንፍሱ? ለዚህ ሁሉ ትርምስ ዬወጣውን ዬነፍስ ግብር ካሳ እንከፍሉ ያድርጉ።
ይቅርታም ጎንደርን እንዲጠይቁ ያድርጉ። እስቲ ዬተጋዳላዊቷ በተግባር ይፈተን። #አውላላ። ወንድነት ማለት ይሄ ነው። ልፍስፍስ – ቦዝ። ትርትር ….
እቴ ሆይ¡ እርግሚት ዬጉልት እራት
ቁሊቱን አሙቂው ለደም ግብርነት¡
ውልቅ ብሎ ነፍሷ – በልሳን ወለምታ
ታዛውን ተመኜች፣ አቤት ዬእኔ ጌታ!
ወ/ሮ አዜብ መስፍን ለቀዳማይ እመቤትነት ላበቃ አብሮ – ለታገለው ለኮነሬል ደመቀ ዘውዴ መሆን እንኳን አልቻሉም? ፍዝ። በዚህ ዬጎልማሳ ዘመኑ ጥሮታ መውጣቱ – ሳይጎረብጥ፤ አርፎ ከተቀመጠበት እንዲህ ዬፍዳ ተሸካሚ ሲሆን – ተው እንኮን ዬለም። ለነገሩ ቅናት ይመስለኛል። ዬአሁኑ ዬለበጣ መንደፋደፍ። ዝርክርክ።
ዬኮነሬል ደመቀ ዘውዴ ዬጀግንነቱ፣ ዬአትንኩኝ ባይነቱ፣ ዬመይሳው ደም ትንታግነቱ በዓለም አቀፍ ዕውቅና ከህዝብ ፍቅር ጋር መስከኑ ውስጣቸውን እረፍት ነስቶ – ነሰተው – ዬሴራ ባንዲትን።
ዬህሊና ትቅማጡ ይሆናል ይህ በእንቅልፍ እንኳን ዬማይታሰብ ህልመኝነትን – ዬተገረደፈው። ዬህዝብ ፍቅር አይሸመት ነገር። እንደ ጠበንጃ አይመረት ነገር።
ዬህዝብ ፍቅር ሲታደሉት ብቻ ለቅኖች፣ ለንዑዳን ዬሚሰጥ ልዩ ዬልብ ሥጦታ ነው። ታዲያ ለካህዲ ዬት ይሸመት? እርግፍጋፊ። እርጉም። ለነገሩ ዕንባ በገንዘብ ገዝታችሁ እኮ ነበር እነ ቅል ቋንቁራ። ሁሉንም አጋፋችሁ ደግሞ ዕንባን ሸቀጥ – አደረጋችሁት። ዳጦች!
• ቁርጥማት።
ተሟጧል – ቧልተኛ
ዬማታውቀው ሀገር ዬናፍቆት – ግረኛ።
መይሳው ሲያገሳ መቅደላ ላይ – ሆኖ፤
አደራው አረገ – በአኃቲዮሽ ገኖ!
ዬማረተ ፍላጎት አዝለው ዬተነሱት ወ/ሮ አዜብ መስፍን በእንቅልፋቸው ሲተሙ እንቅፋቱ ከች ብሎ ዬወለሌ ገበታ ከመሆን በፊት መሰብሰቡ – ይበጃል ብለን እንመክራለን። እንደ ጌሾ ቀሎ ከመመለስ።
እሾህ ሰብዕና፤ ዬጭካኔ አጋፋሪ፤ ዬዘረፋ ቁንጮ ጋር ጎንደር ክፍልም ዬለውም። ጎንደር አብሶ ለማተ ቢሶች፣ ለሆድ-አደሮች፣ ለመልቲዎች፣ ለአስመሳዮች ጎንደር በመንፈሱ ዬእግር መቆሚያ ብጣቂ ማሳ ዬለውም።
ለማንም ጎንደር – ለምንም ጎንደር – ልቡን ዬሚሸልመው አንድ ጊዜ ብቻ ነው - ለዛውም በዕውነት አጥቢያነት። … ገና ያመነው መሽሎክን ሲያልመው ጎንደር ከመቃብርህ ላልቆም —- ይለዋል። ግን ጎንደሬነት ሚስጢሩ „ሙያ በልብነት“ ነው። ወርቅ ቀልጦ ከፈሰሰ – አይታፈሰም።
በጣም በድፍረት ልናገረው ዬምፈልገው ምራቁን ዬዋጠው አምክንዯ፥ ጎንደር ዕምነቱን ለሰጠበት እድምታ በማንኛውም ዬግኑኝነት እርካብ ላይ ይህ ብቃቱ ተመስጥሮ ይገኛል። በቃ! ፍቅርም ግልጽነትም አንድ ጊዜ ነው – በጎንደሮች ቤት።
#ውስጡን ከከፋው #መድፋም ሆነ #ታቦቱ አይመልሰውም።
እንኳንስ ከልቡ ከጆሮው – አያስጠጋውም። ንጹህ ፍቅሩ ሆነ ታማኝነቱ በዳዩን እንዲቀጣው #በልብ #ሽፍትነት – ይታደምበታል። ቅኔው ይሄ ነው ዬጎንደር።
„እነዚህ ጎንደሬዎች“ እዬተባለ አብሶ በክፋ ዓይን ዬምንታዬውም ዘመን ተዘመን ለዚህ ነው። ሌላው እንዲሁም አንዱ ጎንደሬ በመንፈሱ ዬተቀበለው ነገር – ለእኔ ምንም ሊሆን – ይችላል። ለሌላውም እንዲሁ።
በጅምላ መትመም እእ … ለጎንደሬ ልጅ መሪው ዬውስጥ ውሳኔው ብቻ ነው። አብሶ ሁሉን ታዳሚ በሚያደርግ ይህን መሰል ዬህልውና ጉዳይማ አኃቲነቱ ከብረት ቁርጥራጭ ዬተሰራ ነው።
ለዛውም መላ ዬአማራ ህዝብ ሆነ ቅኖችና ደጎች ኢትዮዽውያን ታደመውበት፤ እርግጥ ቀድሞ ቃል ያሰረበት ጉዳይ ከኖረ፤ ደራሹ በፋክት ጭብጥ ያበራ ቢሆን እንኳን – ሙሉ ልቡን ለመስጠት ይቸገራል። ጊዜ ይሻል – ከአዲሱ ገጠመኝ ጋር ይርጋ እስኪል ድረስ …
አሁን ኤክስ ቀዳማይ እመቤት ባድማ እንደ አንጡራ ጠላት ሲያስጨፈጭፋት መኖሩ ብቻ ሳይሆን „ያንተ አይደለሁም“ መባሉ በምንም ዘመን አይደለም እሳቸው ልጆቻቸውን አያስጠጋም – ዬጎንደር መንፈስ።
#ጎንደር ከቆረጠ ውሳኔው መራራ ነው። እጅግ ከፍቶታል ጎንደር። ስጽፈው እራሱ እያለቀስኩ ነው። በግራ ቀኝ መገፋቱ እሬት ነው። እኔ ልከፋለት።
በግል ህይወታችን ሆነ በፖለቲካ ህይወታችን ይሄው ነው – ውስጣችን። ግን አሁንም ዬለውጥ ፈላጊዎችም ግድፈት – በግድፈት ሲሆኑ አያለሁ። አበክሬ ጽፌው ነበር ይሄንን ጉዳይ። ጥቃት ለጎንደር እራቱ – አይደለም።
አሁን ለእትዬ¡ አዜብ ይህንን ዬጻፍኩት ልካቸውን እንዲያውቁት እንጂ – ጎንደር እንደ ከብት በመላሾ – በአሞሌ ሸብረክም፤ በጅም ይላል ብዬ አይደለም። በፍጹም! እሳቸው አያውቁትም። እኔ ግን ዬባዕቴን ውስጡን አሳምሬ አውቀዋለሁ።
ለምሳሌ … በእኔ መንፈስ ውስጥ እንዳሻው ለመጨፈር ዬተፈቀደለት ዬለም። ዙሪያው በእንቁላል ዉሃ ግንብ ዬታጠረ ነው። ጎንደርዬም – እንደዛው።
በተለይ በባድማው ተወልዶ ማደግ ዬረቀቁ ሰብዕናዎች ባለቤት መሆን ያስችላል። እንደ ዬሰው ልጅነታችን ማጥፋት ቢኖርም ዬማንደራደርባቸው ጉዳዮች በርከትከት ያሉ ናቸው። አሁን ሰርግ ላይ ማዕዱ ሙሽራ ሲገባ ነው ዬሚቀርበው ቢባል – ጥሪውን አክብሮ ዬተገኘው ምልዐት አዳራሹን ለቆ – ይወጣል። ክብርን ሸጦ ለሆድ ማደር … እእ ….
መሽቷለኝ በሏተኝ – ለዝንትዓለም ሌባ፣
ጀንበር አዘቅዝቃ – በቅልውጥ አዝመራ።
ጎንደርን መተለም ማተብን – አጥብቆ
አጅሬ ውሎው-ን ያውቀዋል – ጠንቅቆ።
ዬባንዳ ህልመኛ ላትሆነው – አቻ፤
ካለማተብ አዳር ያላቻ – ጋብቻ!
• ሪህ።
መቅኖቸው ያለቀው ዬሙት መላክተኛ ወ/ሮ አዜብ መስፍን ማለቃቸውን በቁማቸው እያሉ ቢያውቁት ጥሩ ነው። ጎንደር ለልግጫ ጊዜ ዬለውም። ጎንደር ቃል በልቶ ለማደር – አልተፈጠረም።
ጥገቱን „ቃል ዬዕምነት ዕዳ ነው“ ዬንጉሦችን ንጉስ ዬመሪውን ዬመይሳውን ወተቱን ጠጥቶ ነው ያደገው። ከዚህች ውልፍት ዬለም። ሲወድም ሲጠላም ጠፈፍ ነው – ጎንደር።
ሲወድም እስከ ንፍጥ ልጋጉ፤ ሲጠላም እንዲሁ ከነዲሪቶውና ከነቡቶቶው አሽቀንጥሮ መጣል። ላይመለስበት፣ ላይከልሰው፣ ላይሰልሰው።
ሞት ዬታወጀበት መሆኑ ጎንደር ይጠፋዋልን „ሂዱና ግደሉ“ ዓዋጁ ስለማን ስለመሆኑ – ይገባዋል። በሱዳን ወታደር እኮ ነው ዬአንባ ጊዮርጊስ #ህፃናት ዬተጨፈጨፉት። ዬዚህ ሁሉ ማዕት ፍዳ እኮ ዋነኛዋ ተዋናይ ሲዖሏ እሜቴ ልጥፍጥፍ ናቸው። ውልቅ።
ቅርሚያ ለቅርሚያ ስትዘግን፣
ተበላች ነፍሷ በክህደት ብል።
ጎንደርን ዬመከራ ቁና ተሰፋሪ ሆነ። ጎንደር ፍልስ እንዲል – ታደመበት። ጎንደር ክው ብሎ እንዲደርቅ ተበዬነበት። በሁለቱ ሽንኮች #በወ/ሮ አዜብ መስፍንና በአቶ #በረከት ስምዖን። ጎንደር ዬሞት መንደር። ዬዋይታ ቋት። ዬዕንባ ቀዬ።
አዎን #ጎጃምም አልቀረለት። ስለምን? ማተቡን – ስለጠበቀ። ለውሉ ስለአደረ – ልጆቹን ገበረበት። ደምን መጋራት በዬትም ዘመን ያልታዬ ዬህልውና፤ ዬፍቅር፤ ዬፍጹም ታማኝነት ዬመንፈስ ውል፣ ዬህሊና ሃብል፤ ዬእኛነት ብልጹግ ብጡል ስጦታ!
#ዬቃል ኪዳን መንደር ጎጃም! እራስን ብረት መዝጊያ በመሆን ከመገበር ወዲያ ምን ወደር – አቻ ያለው ሥነ – ምግባር አለና። #በላይዋ ምንጊዜም ህያው ነህ።
አለህን ዬእኛ ጌታ!
ዬድፍረት ዋልታ፤
ዬጥቃት መከታ፤ ዬዘመን ጉልላት!
• አንስታዊነት።
ዬሆነ ሆኖ እናትነት ተፈጥሯዊ ጸጋው ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ሲደርስ በአረም መዋጡ – እርግማን ሆኖበታል። አንዲት አንስት እንዴት ለሰብዕዊ ዬሰው ልጆች መብት – አትታገልም?
አንስት እንዴት ለንጹህ ጸጋዋ ባላንጣ ትሆናለች?
ሴት እንዴት ለህፃናት ሰቆቃ – አትስብም?
ሴት እንዴት ለህዝብ ፍቅራዊነት ስለምን ቅርብ አትሆንም? ሴት ዬኃላፊነት ቦታውን አግኝታ እንዴት ለችግር መፍትሄ አመንጪ አትሆንም?
እንዴት ሴት ልጅ ዬርህራሄ ናሙና አትሆንም?
እንዴት ሴት ደግ አትሆንም? ሴት እንዴት ለእስረኞች አትጨነቅም?
ሴት እንዴት ከሚያለቅሱ፤ ሆድ ከባሳቸው፤ ከተገፋ ወገኖች ጥግ አትሆንም?
ሴት እንዴት ለድሆች ወገንተኛ መሆን ይሳናታል? ከቶ ለሰብአዊነት ደንበር አለውን?
ደግነት ሆነ መላጣ
በአረመኔነት – ገልባጣ።
ፍቅር መርዶ ላይ አዬሁት ….
በቅጥፈት ተርቲም ጥፋት
ዬደመር ቁርስ፥ ምሳ፥ `ራት –
እነኝህ „ቀዳማይ እመቤት¡“ ዬሚባሉት ሰው ቢሆኑ፣ እንደ ሰው ቢያስቡ፣ ኢትዮዽያ መሬት ላይ ዬጠብታ ዬንጹኃን ደም ፍሰት፤ ዬጭንቅ ኮሽታ ባልተደመጠ ነበር።
ዬትዳር አጋራቸውን ከርክመው፤ ሞርደው ዬሰው ልጅ ተፈጥሯዊ መልካም ሥነ – ምግባሮችን ባስታጠቋቸው ነበር። ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጫካ አውሬነት ወደ ሰውዊ ህሊና በገሯቸው – ነበር።
*** ሚስትነት ማለት እኮ ጥልቃዊ እናታዊነት ማለት ነበር። *** ሚስትነት ድንቅ ዬፍቅር ተቋምነት ማለት ነበር።
*** ሚስትነት ማለት ድርጇዊ መሪነት ማለት ነበር።
ቢያውቁበትማ።
ዬምናዬው ግን ትናንት ዛሬም ለአረመኔነት – አጋፋሬነት – እነ ቀዳማዊ እመቤት¡ ሴትነታቸውን እራሱ ፈቅፍቀውታል። ጋግጠውታልም …
#ልዕልቴ ጣይቱ ተነሽና ዬአጋርነትን ዬብቃት ልዕልና አስተምሪልን – እባክሽን – እመቤቴ?
#ምንትዬ ንግስቴ ሚስትነትን አመሳጥሪላቸው እባክሽን – እመቤቴ?
ዬዲያቢሎሱ ዬወያኔው ጠቅላይ ሚኒስተር ዬአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ዬትዳር አጋር ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ ይሄው እያዬነ ነው በኃላፊነታቸው ላይ እዬለሸለሹበት እንትኑን … ለመልካም ነገር፣ ለሰብዕዊ መብቶች እረገጣ፣ ለህፃናት እለቅሶ ቦታ – ዬላቸውም። ዬፖለቲካ እስረኞችን ሄደው – አይጠይቁም። ጠይቀው ቢታሰሩ ወይንም ቢገሰጹ ሰማዕትነት በነበረ።
በቀን ከ600 በላይ ንጹኃን እዬተጨፈጨፋ – ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ20,000 በላይ ወጣት እዬታሰረ – ዬቱ ላይ ይሆን ይህ „እግዚብሄር አዳኜ ነው“ ዬሚባለው ዬተቀመጠው? ዬቃሉ እኮ ድርጊት ነው መዳረሻው።
ከቶ ክርስትና ለርህርህና መንፈስ መሸመቻ ካልሆነ ከምኑ ላይ ይሆን ዬዕምነቱ ተገዢነት ሆነ ዬህይወት መሪነቱ? ግራ እኮ ነው።
ምድሪቱ ዬደም መሬት፣ ዬዕንባ መሬት ስትሆን በባዕድነት ስሜት እያዩት ነው ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬም – ቢሆኑ። ማህጸንን ደም ዬሚያስለቅሰው ይህ ከሰባዕዊ ተፈጥሮ ወጥቶ ዬጭካኔ ተባባሪ መሆን ነው።
ግን እነኝህ ዬዕውነት ሴቶች ናቸውን? ሁለቱም ይፈተሹ – ይመረመሩ። … ኡኡኡኡ ዬሥነ – ልቦና ሃኪም ያለህህህህህህህህህ?! ….
• መደምደሚያ።
ክህደትና ባንዳነት፣ ዝርፊያና ዬማንነት ቅልውጥና ለሚያባዝናቸው ጊንጧ ወ/ሮ አዜብ መስፍን ደባቸውን በሰፈሩት ቁና ዬሚያገኙበት ቀን – ይናፍቀኛል።
እትጌ ተዋበች ሆኑ እትጌ ምንትዋብ ዘመናቸውን በተግባር ወርቅነት እንዳላጻፋት ዬዛሬዎቹ ዬፈርዖን ዬትዳር አጋሮች ቀዳማይነታቸው ሀገር ለመግደል፤ ትውልድን ለመመንጠር፤ ነገን ለማሳረር፣ ዛሬን ለማስለቀስ ቀን ከሌት ዬሚተጉ ዬትዳር አጋሮቻቸው ዬምክር ባልደረባ ሆነው ተገኙ።
ወ/ሮ አዜብማ ዬሴት ሌባ፤ በእውነት ይደክማል ዬእሳቸው ዬእንሽላሊት ተፈጥሮ – ሲታሰብ። ዬሴት ዘር አጥፊ – ዬሴት ጨካኝ! ዬሴት አረመኔ! ዬሴት ሰው አራጅ! ዬሴት ሌባ! ዬሴት ቀንደኛ – ዘራፊ! ዬሴት ገፋፊ! ዬሴት ከፋፋይ! ዬሴት አድመኛ! ዬሴት ውሸታም ! ዬሴት ሳጥናኤል! ማፈሪያ! አልጫ።
ዬሴት ቀንደኛ ወንጀለኛ፣ ዬሴት ዬማንነት ቀማኛ መሆን ትውልድ ምን ቋንቋ ሊገልጸው ይችል ይሆን? ቅራሪ ጭላጭ ….
እግዚአብሄር ዬተመሰገነ ይሁን! ወ/ሮ አዜብ መስፍን አይናቸውን ያላሳዬኝ – ሆነ ደጅ ያላስጠናኝ አምላክ። ስለምን? ያን ጊዜ ያው ዬወያኔ ወደ ጎንደር መገስገስ ሁሉ ሰው ጭንቅ ላይ ነበር።
ምክንያቱም ዬእናቴ ድንበር አልቦሽ ደግነት፣ ከዛች ሰኞ ማክሰኞ፤ ቅልሞሽ አሞከሞ እጫወትባት በነበረው ቀዬ ላይ ለግለግ ብዬ ዬወጣሁ ቀንበጥ ፖለቲከኛ ስለነበርኩ፤ በምርቃት ደረጃም ቢሆን ዲታ ነበርኩ።
ስለዚህም አድባሯ በጭንቅ – ታመሰች። ስለሆነም ወያኔ ወደ ጎንደር እዬቀረበ ሲመጣ – ዬወ/ሮ አዜብ መስፍን ዬእናታቸው እህት ቤት ድረስ መጥተው ከቤታቸው ሊሸሽጉኝ ተማጽነው – ነበር።
ወ/ሮ አዜብ እንደሚመጡ ሰምቼ ነበር። መቼም ብርክት ናቸው አክስቶቻቸው። ሁለቱም ዬእናታቸው እህቶች መልካሞች ናቸው። ከእናቴ በላይ ነበር ዬተጨነቁት።
እናላችሁ ያው ዬሥርጉተ ነገር ሆኖ ሳይሳካላቸው ጫካ ገባሁ። እንዴት ተብሎ ሥርጉተና ወያኔ? #መቼውንም ዬማይታሰብ ነው።
እርግጥ ስወጣ ብቻዬን በቁስቋም በር ስለነበር አደጋው ሰፊ ነበር። እርግጥ ኮልቴና ታጣፊ ክላሽኔ አብረውኝ ነበሩ። ድፍረቴን ሳስበው ይገርመኛል ዛሬ ላይ። አዬ! ወጣትነት።
በማህል በአርማጭሆ በኩል ከኮማንድ ፖስቱ ጋር ዬወጣች አንዲት ዬፖሊስ ባልደረባ ሞተች ሲባል በተመስጦ አዘነ – ጎንደር። እሷ ነው ዬሞተችው ተባለ። ያው በሴት ዬኃላፊነት ደረጃ ፊት – ለፊት ነበርኩኝ።
በወጣትነቴ በፍጹም ሁኔታ ዬማይታሰቡ ሁለገብ ጥንካሬዎች – ነበሩኝ። ዬዛሬውን አያድርገውና አለቆቼም ይሳሱልኝ ነበር። ከሁሉ ዬረዳኝ ግን ቁጥብነቴ፤ ከወጣትነቴ ጋር መተላለፌ ነበር። ሁሉ ነገር ከዕድሜዬ በላይ ነበር።
ዬሆነ ሆኖ እነኛ ብርቅዬ ወገኖቼ እንደ እናቴ ገመድ ታጠቁ። አለቀሱ። መቼም ዬእኔ እናት በእኔ ያላዬችው ዬመከራ ዓይነት – ዬለም። እህቶቼም።
ዬሚገርመው ነገር ውጭ ሀገር መውጣቷ ከፖለቲካዊ ዕሳቤ ጋር ያፋታተል ዬሚል ፅኑ ዕምነት ነበራቸው። ከሁልጊዜ ጭንቅ ባድናቸው – ዬምር እመኛለሁ። ግን ዬቋያ ህይወት ዬፖለቲካ አዚም ሊለቀኝ አልቻለም።
ዬዬትኛውም ዬፖለቲካ ድርጅት ማኒፌስቶ ተገዥ አለመሆኔ – ምንአልባት በማያባራ ጭንቅ ለማሰቃዬው መንፈሳቸው ይሻል እንደሆን – አላውቅም። በእናቴም ሆነ በአባቴ ወገን ዬፖለቲካ ህይወት ቤተኛ እኔ ብቸኛ ነኝ። እነሱ ለፈጣሪ ማደር ዬተጋድሎ ዓውራ ነው ባዮች ናቸው።
ያን ጊዜ አድርሽኝም ሆነ ዬመስቀል ውሎ ዬእኔ ስለት ብቻ ነበር – አይኗን አሳዬን። ዛሬም ይሄው ነው ዓይኗን አሳዬን። ዬሆነ ሆኖ ዛሬ ላይ ሳስበው ዬወጣትነቴ ቁርጥ ውሳኔ ከኮማንድ ፖስቱ ተነጥዬ በቁስቋም በር መውጣቴ ለመልካም ነበር ልበለው ይሆን?
ዛሬም በዚህ በስደት ሀገር እንደ ባይታዋር በባለ ጊዜዎች – ዬለውጥ ፈላጊ ቤተኞች ስታይ – ሲገላምጡኝ፣ ሲያሳድዱኝ -ብቅ እንዳልል ሲጫኑኝ – ነገስ ሥልጣኑ ሲያዝ ድጋሚ ለካቴና ይሆን እምታገለው – እላለሁ? አብሶ #ዬእናቴ ነገር ያሳስበኛል። ነገም ስንቅ ለማቀበል – ስላጩላት።
መኖሩ ከተገኜ … ሥም ዬለሹ ገመና ብዙ ነው – ዬእኛ ነገር። ለመሆኑ እናንተዬ … #ተፈላጊው ነፃነት መልኩ ሆነ ቁመናው ምን ይመስል ይሆን? በመጣና – በተያዬን። አይደል? ሥደት ላይ ዬአፍ መውጫ ቋንቋው አቤቱ ነፃነት freedom ነው። መሬት ላይ ግን ኃይለ መብት በመጠራቅቅ – ዬተሰቀዘ። — በድርቅ ዬተመታ …
• ጨረስኩ – ለዛሬ።
ዬጹሁፌ ታዳሚዎች ሆይ! ባለፈው እቀጥለዋለሁ ባልኩት ጉዳይ ላይ – እመለሳለሁ። ያው ዬሌላኛው ሳጥናኤላዊ ሴራ ላይ ነው – ትኩረቱ። መቃብሮች ሁሉ መፈታተሽ – ስላለባቸው። ነገ እንዲቀና።
ሳተናው ወንድምዓለም እግዚአብሄር – ይስጥልኝ። አንተ ለግፋዐን አንስት ጸሐፍት ባትኖርልን ኖሮ ዬት ላይ ይተነፈስ ነበር? ይጨርስልህ ብለናል እኔና ውዷ ብዕሬ። ተባረክብም ይታከልልህ። መሸቢያ ጊዜ።
ኢትዮዽያዊነት ፈተናን አሸንፎ ዬተፈጠረ ሚስጢር!

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።